🔥🔥"የሚያየኝን ፊት ለፊት አየሁት "(የራሺያ ወጣት
ኮሚኒስት) 😱🔥
ክፍል :12
✍......በነዚህ ጨካኞች ሰወች ትእዛዝ እሳት አቀጣጥለህ ካነደድከው በኋላ እራስህ ግባ ብሎ ሲያዙ የሚሰማችሁን ስሜት ልትመዝኑ ትችላላችሁ። ወይም አማኝ እናት ክርስቶስን አልክድም በማለቷ ምክንያት ህፃን ልጇን ፊት ለፊቷ እያየች ቢያርዱባት ወላጆች ምን ይሰማችኋል? በሷ ቦታ ሆናችሁ ለአንድ ጊዜ አስቡ።እንግዲያውስ ቅዱሳን ስለ እምነታቸው ሲሉ የተቀበሉትን አሰቃቂ መከራ እንደሚገባ ልገልፅላችሁ አልችልም።ኮሚኒስቶች መጥፎነታቸው ሰወችን ማሰቃየት ወይም መግደላቸው ብቻ አይደለም። በሀሰተኛ ወሬ የሰውን ህሊና ማቆሸሻቸው እንጂ።አላማቸው ክርስቲያኑን ወደ ክህደት መምራት ሲሆን በትምህርት ቤት ህፃናት እና ወጣቶችን እግዚአብሔርን እንዲጠሉ ያስተምሯቸዋል።
እኔ በእስር ቤት ያሳለፍኩት አስራ ሶስት አመታት ወደ ኋላ ተመልሼ ሳስበው በጣም ያረኩኛል ፤ያስደስቱኛል፣በደስታዬ ካገኘሁት ሰላምና እረፍት ይልቅ በመከራ ጊዜ ያገኘሁት #ኢየሱሴን በስቃዬ ስቃዩን ፣በግርፋቴ ግርፋቱን ፣በደም መፍሰስ የመስቀል ደሙን ይበልጥ እንዳስበው አድርጎኛል።ግርፋት ከሌለ ከባድ ስራ ካላጋጠመን በቀር በቀላል ቁፋሮ ጊዜ ድካማችንን ሳናስብ የለ ማቋረጥ እንፀልያለን።#ጌታን ለስምንት ጊዜ ፊት ለፊት ነጭ ውብ ልብስ ለብሶ ባማረና በተዋበ መልኩ ተገልጦልኝ ያየሁ በመከራዬና በእስር ሰዐቴ ላይ ነበር።ከዚህ ሁሉ በላይ አንድ ቀን በደረሰብን ከባድ ቶርች ለሶስት እና ለአራት ቀን እራሳችንን ስተን አጠገባችን ያሉት ከአሁን አሁን ሞቱ ብለው ሲጠብቁ ሳሉ ጌታ #ኢየሱስ እንደ ሰው ተገልጦ አሁን ካላችሁ እና ከገጠማችሁ ይልቅ ትወዱኛላችሁን?ሲል ጠየቀን። ሁላችንም የሞተው ሰውነታችን ሒወት ዘርቶ ያን ሁሉ ሰአታት የተገረፈ ሳይሆን ልምጭት ያረፈበት ሳይመስል ተፈውሰን ሀይል ተሞልተን የተየሳንበት ቀን አይረሳንም።ብዙውን ጊዜ ከሰው አእምሮ ና ህሊና ማስተዋል በላይ በሆነ አሰቃቂ ግርፋት ና ልፋት መፈጠራችንን እስክንጠላ ከስቃይ ለማረፍ ብለን ጌታን ለመካድ እስክንገዳገድ ያደርጉናል። ፊታችን በደም ተለውሶ ስንደናበር ኢየሱስን ክዳችሁ በሌኒን እመኑ ይሉናል፣ያን ጊዜ ጌታ በልዩ #ውቀቱ ይገለጥልናል፤የመስቀል ፍቅሩ ፣ስቅላቱ ድቅን ሲልብን እንበረታለን።በዙርያችን ከነብያት እና ከሀዋርያቶች ያላነሰ መከራ የደረሰባቸው ወገኖች አሉ። ይሁን እንጂ ኮሚኒስቶችን የሚጠላ ልብ ግን የለንም። በደላቸው ምንም የከፋ ቢሆንም ይህ የቀራኒዮ ስቃይ ኮሚኒስቶችን ያቅፋል፤እነሱ የሚያደርሱብን ስቃይ ባይገባቸውም እኛ ግን የመስቀሉ ፍቅር የገባን ሰዎች እነርሱን ያለልክ እንወዳቸዋለን። ካሰቃዩን በኋላ ጌታ ይባርካቹ ስንላቸው አእምሮአቸው ይመታል።ኮሚኒስቶችን ሊለውጣተው የሚችለው የፍቅር ሀይል ብቻ ነው።ጥላቻ የሰውን አይን ያሳውራል።ሌላው አንዲት ሀገር እንድትለወጥ ከፈለግን ለመሪዎች መፀለይ አለብን።መሪ ሲለወጥ ለጌታ ነገር ልቡ ሲከፈት እነርሱን ወደ ጌታ ለማምጣት ህዝቡ አስቸጋሪ አይሆንም።ለዚህ ነው ጌታ የእባቡን እራስ እንድንቀጠቅጠው ያዘዘን።ራሱን ሲመታ ይሞታል እኛ ግን ሆዱን እና ጅራቱን እየረገጥን መልሶ እነኛኑ ነድፎ ይገለናልና።ሀይለኛውን ሳናስር ለመበዝበዝ ማሰብ ሞኝነት ነውና።ስለዚህ እኛ እንደደረስንበት መሪዎች በጌታ ቢየምኑ ህዝቡ ቀቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መሪውን የመከተል ግዴታ ወይም ፍላጎት ይኖረዋል።እኔ ምን አልባት ከነበረብኝ ስልጣንና ሀላፊነቴ የተነሳ ወደ ቀደመው ኑሮዬ ለመመለስ ከሁሉ ይልቅ የከፋ ስቃይ ተቀብያለው።የቀኝ ጡቴን በአሰቃቂ ሁኔታ አጥቻለሁ። የስጋ ጡቴን ለክርስቶስ ስል ባጣውም እውነተኛ ጡቴ ልቤ ግን በሰማይ አለ በጽዮን ይቆየኛል።እንደወንድሞቼ እና እህቶቼ ለውዴ #ለኢየሱስ በሰማዕትነት አልሞትኩም እንጂ ስቃይ እስኪ በቃኝ ጠግቤአለሁ።
ይሁን እንጂ የዘላለም ሕይወት ሳያገኙ ለሚጠፉት ኮሚኒስቶች ለደቂቃዎች እንኳ ጠልቻቸው አላውቅም ፤ይህ ደግሞ የሁላችንም ጠባይ ነበር። በሳይቬርያ እያለን አንዳንድ ሴቶችን ይወስዱና ስጋዊ ፍላጎታቸውን በተደጋጋሚ ከተጠቀሙባቸው በኋላ እንደ ርካሽ ዋጋ ይወረውሯቸዋል ፣ይህ ብቻ አይደለም፣ማርገዛቸውን ሲያውቁ ከኮሚኒስት ቢሮ የሚደርስባቸውን ቅጣት ስለሚያውቁ ኃጥያታቸውን ለመሸፈን ወስደው በጥይት ይገድሏቸዋል፤ ቢሆንም ልንወዳቸው እንጂ ልንጠላቸው አልተፈቀደልንም። ስለ አባታችን እና ወንድማችን ሪቻርድ ውምብራንድ ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ስለኛ ምን ትላለህ ብለው ኮሚኒስቶች ሲጠይቋቸው የሚፈሰው ደማቸውን እየጠራረጉ ፈገግ ብለው ለእናንተ ያለኝ ፍቅር በወጣትነት ዘመኔ ባለቤቴን ለማግባትና ለመውሰድ የነበረኝ ፍፁም ደስታ የተለየ ለሊት ያህል ነው ይሏቸው ነበር።ኮሚኒስቶች ይህ ነው በማንለው በመከራ ስቃይ ቀጥተውናል።በላያችን የተፈፀመው ግፍና ስቃይ የፈጠሩብንን ህመም እና ቁስል ለልጅ ልጅ ለዘለአለም ይቅር የሚያስብል ከልባችን ይሁን ከህሊናችን ሊጠፋ የሚችል አይደለም። ይሁን እንጂጰ""የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው "የተባለውን የፍቅሩንና የመስቀሉን ቃል ወዴት እንጣለው። ስለዚህ እነሱ ከአቅማችን በላይ በሆነ ሁኔታ ገርፈው ረግጠው ቀልደው አመናጭቀው በዚያ ወፍራምና ጠንካራ ጫማቸው ረግጠው እንደ እቃ ሲጫወቱብን ስቃይ የፈጠረው ጣር ጩኸት በሰለለው ጉሮሮአችን በቀረችልን ትንሿ ስትንፋሳችን አንደምንም አሰባስበን """እንወዳችኋለን💗💖💖ጌታ ይባርካችሁ """ስንለቸው ይደነግጣሉ። አንዳንዴም በመደነቅ ፈዘው ያዩናል🙁።ሌላ ጊዜ ደግሞ እንደዚህ የምትሉን ወዳችሁን ሳይሆን የናንተ ፓርቲ አባል እንድንሆን ነው ይሉናል።እነርሱ የፈለጉትን ይበሉ እንጂ እኛ ግን እንወዳቸዋለን። ይህ ነው በልባችን የሞላው ፤ ከዚህ በላይ ባያምኑን ግን እምነት እና ፍቅር ዳቦ ሆኖ አናጎርሳቸው፤ወይም ውሀ ወይም ቮድካ አይደል በብርጭቆ ቀድተን አናጠጣቸውም። እኛ ግን #የኢየሱስ ልብ አለን ጌታ ይመስገን።ይቀጥላል......
🔥🔥ይቀጥላል የቀሩትን ገፅ ለማግኘት join ይበሉ🔥🔥
🔥🔥 @AmharicBSH 🔥🔥
🔥👆join 👆👆👆👆🔥🔥
🗒ክፍል:13 እና የመጨረሻውን በቅርቡ ይጠብቁ 🖊