አንዳንድ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ የተሳሳቱ ነገሮች እንደሚያዩ እና ያም እንደሚያሳዝናቸው ይነግሩኛል። እኔም ለእነዚህ ሰዎች ይህን እላቸዋለሁ...
ዝምብን አግኝታችሁ “እዚህ አካባቢ አበባ አይተሻል?” ብትሏት፡- “ስለ አበቦቹ እንኳን የማውቀው ነገር የለም። ባይሆን እዚያ ጋር የምታየው ክምር ላይ የፈለግኸውን ቁሻሻ ልታገኝ ትችላለህ” ብላ ልትመልስልህ እና ንጹሕ ያልሆኑ ብዙ የቆሻሻ ዓይነቶችን ልትዘረዝርልህ ትችላለች።
ንብን አግኝተህ ደግሞ “እዚህ አካባቢ የተጣሉ ቆሻሾች አይተሽ ይሆን?” ብለህ ብትጠይቃት፣ “ቆሻሻ ነገሮች? ኸረ እኔ ምንም አላየሁም። ይህ ቦታ እኮ ልዩ ልዩ መዓዛ ባላቸው አበቦች የተሞላ ነው” ስትል ልትመልስልህ እና በአትክልቱ ስፍራ ያሉትን አበቦች አንድ በአንድ ልታስቆጥርህ ትችላለች።
አየህ! ዝምብ የቆሸሹ ነገሮች የት ሊገኙ እንደሚችሉ ብቻ ስታውቅ፣ ንብ ግን ውብ የሆኑ አበቦች መኖሪያ ወዴት እንደሆነ ታውቃለች።
አሁን ላይ እንደ ተረዳሁት ከሆነ አንዳንድ ሰዎች ንብን ሲመስሉ ሌሎች ደግሞ ዝንብን ይመስላሉ። ዝንብን የሚመስሉት በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ክፉን ነገር ብቻ እያሻተቱ የሚፈልጉ እና ሐሳባቸውም በዚያ የሚዋጥባቸው ናቸው። እነዚህ ሰዎች የትም ቦታ ቢሆን ጥሩ ነገር አይታያቸውም።
ንቧን የሚመስሉት ግን በሚያዩዋቸው ነገሮች ሁሉ ውስጥ ጥሩን ነገር ያስተውላሉ።
ምንጭ፡ St. Paisios of Mt. Athos, "Good and Evil Thoughts”