ቢስቲማ እና ተውሂድ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


አላማችን:
በተውሂድ የታነፀ ህብረተሰብ መፍጠር ነው።

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


‏حكم صيام تارك الصلاة بالكلية:
‏تارك الصلاة صومه ليس بصحيح ولا مقبول منه؛لأن تارك الصلاة كافر مرتد وعلى هذا فإذا صام الإنسان وهو لايصلي فصومه مردود غير مقبول،ولا نافع له عند الله يوم القيامة، ونحن نقول له: صل ثم صم،أما أن تصوم ولاتصلي فصومك مردود عليك لأن الكافر لاتقبل منه العبادة.
‏وقد سُئل رحمه الله ما حكم من يصوم ويصلي إذا جاء رمضان، فإذا انسلخ رمضان انسلخ من الصلاة؟
‏١-الذي يتبين لي من الأدلة أن ترك الصلاة لا يكون كفرا إلا إذا تركها الإنسان تركا مطلقا،
‏٢-وأما من يصلي ويخلي فيصلي بعض الأحيان ويترك بعض الأحيان، فالذي يظهر لي من الأدلة أنه لا يكفر بذلك.
‏ولكن هذا الرجل الذي لا يصلي إلا في رمضان ويصوم في رمضان أنا في شك من إيمانه، لأنه لو كان مؤمنا حقا لكان يصلي في رمضان وفي غيره، أما كونه لا يعرف ربه إلا في رمضان فأنا أشك في إيمانه، لكنني لا أحكم بكفره، بل أتوقف فيه وأمره إلى الله عز وجل.
#ابن_عثيمين
مجموع الفتاوى(١٩-٨٧) و (٢٠-٨٦).
https://t.me/Bistima1


🌸 ሀሰን አል በስሪ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላል:-

🌸 ሶብር ማለት ከጀነት ድልቦች አንዱ ነዉ።

🌸 ጌታዬ ሆይ በሶብር ላይ አግዘኝ ከአንተ ዉጪ በዚህ ትልቅ የጀነት ድልብ በሆነ ነገር የሚያግዘኝ የሚረዳኝ የለምና አግዘኝ እርዳኝ።

🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
https://t.me/Bistima1


💚አል-ኢማሙ ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦

💚“ለሙስሊሞች በአጠቃላይ የምስጠው ምክር ታላቅ የሆነውን የረመዳን ወራቸውን የላቀውን አላህን በመፍራትና ከሁሉም ወንጀሎቻቸው እውነተኛ ንስሃ በማድረግ እንዲቀበሉት ነው።”

💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
https://t.me/Bistima1


*ነገ ማክሰኞ…* ‼
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ፝፞

እንዳያመልጠዎ!__ በ ወረባቦና በ አቅራቢያዋ ላላቹህ በሙሉ ነገ ማክሰኞ ማለትም ሚያዚያ 15 በ ቢስቲማ ትልቁ መስጊድ ትልቅ የ ዳዕዋ ፕሮግራም አለ በ ፕሮግራሙ ላይ ትላልቅ ዳዒዎችና፣መሻኢኾች ከ ሌላ ሀገራት በመምጣት ምክራቸውን ለመለገስ ፍቃደኛ ሆነዋል!!! ከ እርሰዎ የሚጠበቀው በጥዋት ከች ብሎ የ ዳዕዋው ተካፋይ መሆን ብቻ ነው!!!

✅ፕሮግራሙ ጥዋት ነው የሚጀምረው…
https://t.me/Bistima1


🌱እነኚህ ናቸው... ደስተኞች

√ ደስተኞች እነዚህ ናቸው ፦ እራሳቸው በአኼራቸው ጉዳይ ቢዚ ያደረጉ...

ሁሌም ጉጉታቸው ልባችንን እና አይባችንን (ነውራችንን) እንዴት አድርገን እናስተካክል ... የሚሉ...

ነፍሳቸውን ነጌ የውመል ቂያማ አለህ ሳይተሳሰባቸው በፊት የሚተሳሰቧት ናቸው።

ተቃራኒው ግልፅ ነው።
🌸እኛስ ከየትኛዎቹ ነን? ያአለህ ልባችንን አስተካክልልን🌸

https://telegram.me/Bistima1


♡الإرشاد الى صحيح الإعتقـ♡:
°•♡✍🏻ሂስድ ( ቅናት ) (ምቀኝነት)

ሂስድ ➬ በሰው ልጅና በጂኒዎች ላይ ብቻ የሚገኝ በሽታ ነው ።
===

ሂስድ ➬ የአላህን ወሳኔ በመቃወም የሌሎችን እድገትና ስኬት ማየት ካለመፈለግ ከልብ ውስጥ የሚመነጭ ጥላቻ ወለድ በሽታ ነው ።
===

ሂሰድ ➬ በባህሪው በፍጥነት እየተሰፋፋ የሚሄድ አደገኛና አቃጣይ በሽታ ነው ።
===

ሂስድ ➬ ያለበት ሰው የሚፈለገውን ነገር ሁሉ አላህ ቢሰጠውም አይደሰትም ። የእሱ ደስታው የሌሎችን ማጣትና ውድቀት ሲመለከት ብቻ ነው።
===

ሂስድ ➬ ውጤቱ የበሽተኛውን መልካም ስራዎችን ማቃጠል ( ማበላሸት ) ነው ።
#መፍትሄው ሁሌም በኑሮ ፣ በጤና ....ከእኛ በታች ያሉትን በመየትና አላህ በሰጠን በመደሰት ብሎም አላህን በማመስገን ብቻ ነው


ምቀኝነት ልክ እሳት እንጨትን እንደምትበላው መልካም ሥራን ትበላለች!!

ነብዩ ሙሀመድ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም❤️
➹ ቅን እናስብ መልካምነት ለራስ ነውና➹

https://telegram.me/Bistima1


‏معالي الشيخ د. صالح الفوزان حفظه الله :

نحن لا نترك بيان الحق وإن كان كثير من الناس لا يقبلونه

[دعوة التوحيد وسهام المغرضين ص19]
ታላቁ አሊም ፈውዛን አል ፈውዛን አላህ እድሜያቸውን ያርዝመውና እንድህ ይላሉ፡–
እኛ ሀቅን መግለፅን አንተውም አብዘሀኛው ሰው ባይቀበለውም፡፡

የትልቅ ሠው ምክር እንድህ ነው፡፡
https://telegram.me/Bistima1


ታላቁ ታቢዕይ ሀሰን አልበስሪ ጓደኛቸው ሞቶ ከቀበሩት በኋላ ቀብሩ አፋፍ ላይ ቆሙ፤ ከዚያም ከጎናቸው ወደ ቆመ አንድ ሰው ዞሩና እንዲህ አሉት፡* “ይህ ሟች ወደ ዱንያ ቢመለስ ምን የሚያደርግ ይመስልሃል?” ብለው ጠየቁ ሰውየው፡- “ኢስቲግፋር ያደርግ ነበር፤ ይሰግድም ነበር፤ መልካም ነገሮችንም ሁሉ ይጨምር ነበር” አላቸው
ሀሰን አልበስሪም፡- “ለእሱ አምልጦታል፤ ለአንተም እንዳያመልጥህ” አሉ

https://telegram.me/Bistima1


•°♡ የሰው ልጆች በዱንያ ላይ
ከተሽቀዳደሙህ ተውላቸው
๏ ነገር ግን በአኺራ ላይ ከተሽቀዳደሙህ
ቀዳሚያቸው አንተ ሁን ።
⇘ አላህ ዱንያን ለሚወደውም ሆነ
ለማይወደውም ይሰጣል ግን አኺራን
ለሚወደው ብቻ ነው የሚሰጠው
https://telegram.me/Bistima1


°•♡✍ •°♡ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ 【ረሂመሁላህ】እንድህ ብለዋል፦
« ቀጥተኛውን ጎዳና ለማገኘት ከቁርአን እና ሱና ውጭ ፍለጋ ያካሄደ
ከአላህ መራቅን እንጅ ሌላ ነገርን አይጨምርም።»
【መጁሙዕ አልፈታዋ 5/120】
https://telegram.me/Bistima1


°•♡✍ ልብን ከአላህ ቃል የበለጠ የሚያሳምራት ነገር የለም!
ቁርዓንን ማስተንተን የመጀመሪያው ልብን የማሳመሪያ
መንገድ ነው!!!
°https://telegram.me/Bistima1


°•♡✍ •°♡ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ 【ረሂመሁላህ】እንድህ ብለዋል፦
« ቀጥተኛውን ጎዳና ለማገኘት ከቁርአን እና ሱና ውጭ ፍለጋ ያካሄደ
ከአላህ መራቅን እንጅ ሌላ ነገርን አይጨምርም።»
【መጁሙዕ አልፈታዋ 5/120】
https://telegram.me/Bistima1


#የሽርክ መጨረሻው በጀሐነም ውስጥ መዘውተር ስለሆነ ጨለማ ነው!!

#የተውሒድ መጨረሻው ጀነት ውስጥ ለዘላለም መዘውተር ስለሆነ ብርሀን ነው !!

#ወንድሜ #ብርሀንን #ከጨለማ ለመለየት ከሚረዱህ ዋና ዋና ነገሮች መካከል አንዱ ሸሪዓውይ እውቅት ስለሆነ የሸሪዓ እውቀትን ከመቅሰም አትቦዝን !!

#ካለወቅክ(መሀይም ከሆንክ) ያስተካከልክ እየመሰለህ ታበላሻለህ
#ሱና የተገበርክ እየመሰለህ ቢዳአ ውስጥ ትዋኛለህ

እችንዱኒያ ከመልቀቅህ በፊት
ከሽርክ ወደ ተውሒድ
ከቢደዓ ወደ ሱና
ከጅህልና ወደ ዒልም ተመለስ
https://telegram.me/Bistima1


ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ እንስጥ።
🌻┈┈••◉❖◉●••┈🌻

👌 የሃቅ ባለቤቶች ሃቅን ይፋ ከማድረግ ቢቆጠቡ ... ተሳሳቾች በስህተታቸው ይዘወትሩ ነበር። ሌላው ተራው ሰው ደሞ እነሱን ከነስህተታቸው ሞዴል አድርጎ ይከተላቸው ነበር። ለዚህም ነው ሃቅን ከመናገር የታቀቡት ወንጀለኛ የሆኑት።
(كَانُوا لَا يَتَنَاهَوْنَ عَنْ مُنْكَرٍ فَعَلُوهُ).

📕 ابن باز، مجموع فتاواه ٣/ ٧٢
https://telegram.me/Bistima1


ﻋﻦ ﺍﺑﻦ ﻣﺴﻌﻮﺩ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﺃﻥ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﺻﻠﻰ
ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻗﺎﻝ : ‏( ﻣﻦ ﻣﺎﺕ ﻭﻫﻮ ﻳﺪﻋﻮ ﻣﻨﺪﻭﻥ ﺍﻟﻠﻪ
ﻧﺪﺍً ﺩﺧﻞ ﺍﻟﻨﺎﺭ ‏) ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ
ዓብድላህ ኢብኑ መስዑድ በአስተላለፉት
ሐዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ይላሉ
“ከአላህ ውጭ ሌላን አካል ለአላህ አጋር
አድርጎ መለመንን ሳይተው (ተውበት
ሳያደርግ) የሞተ ሰው እሳት ገባ፡፡” ቡኻሪ
ዘግበውታል
ﻓﻔﻲ ﺍﻟﺤﺪﻳﺚ ﺍﻟﺼﺤﻴﺢ ﻗﺎﻝ ﺍﻟﻨﺒﻲ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ
ﻭﺳﻠﻢ ﻻﺑﻦ ﻋﺒﺎﺱ ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻬﻤﺎ : ‏( ... ﺇﺫﺍ ﺳﺄﻟﺖ
ﻓﺎﺳﺄﻝ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺇﺫﺍ ﺍﺳﺘﻌﻨﺖ ﻓﺎﺳﺘﻌﻦ ﺑﺎﻟﻠﻪ ‏) ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﺘﺮﻣﺬﻱ
ﻭﻗﺎﻝ ﺣﺪﻳﺚ ﺣﺴﻦ ﺻﺤﻴﺢ
በሌላ ሐዲስም የአላህ መልዕክተኛ
እንዲህ ብለዋል “መለመንን ስትፈልግ
አላህን ብቻ ለምን፣ እርዳታንም ብትፈልግ
በአላህ ብቻ ተረዳ” ቲርሚዚይ ዘግበውታል

https://telegram.me/Bistima1


ለማስታወስ ያህል...

📚 عن أبي قتادة رضي الله عنه قال:

🍁 قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:

🍃 ((إذا دخل أحدكم المسجد،

فلا يجلس حتى يصلي ركعتين)).
አንዳችሁ መስጂድ ከገባ ሁለት ረከኣ (ተይተል መስጂድ) ሳይሰግድ ቁጭ አይበል።
🌹 متفق عليه. 🌹

ዛሬ ልክ ጁመኣ ስትሄዱ የመጀመሪያ ተግባራችሁ ሊሆን የሚገባው ሁለት ረከኣ መስገድ መሆን አለበት...

https://telegram.me/Bistima1


•°♡✍ #ተውሂድ_መማር_ለምን?

✔ #ተውሂድ ከዲን መሰረታዊ ከሆኑ ነገሮች በሙሉ ቅድሚያ ሊቸረው የቻለው አያሌ ጠቀሜታዎች ስላሉት ነው።

✔ #ተውሂድ በዱንያም ሆነ በአኼራ ለሚከሰቱ ጭንቀቶችና ቅጣቶች መከላከያና መጠበቂያ ነው።

✔ #በልቦናው ውስጥ ቅንጣት ታክል እንኳ ተውሂድ ኖሮት ወንጀሎችን ፈፅሞ የአላህ እዝነት ሳያገኘው ቀርቶ እሳት ቢገባ ግለሰቡ እሳት ውስጥ ዘውታሪ አይሆንም። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ልቦናው በተውሂድ የተሞላ ከሆነ በዱንያ ከጥመት የራቀ ይሆናል በአኼራ ደግሞ ሙሉ ደህንነትን ያገኛል። እሳት ከነጭራሹ አይገባም።

✔ #ተውሂድ የአላህን ውዴታና ምንዳውን ለማግኘት ብቸኛው ሰበብ ነው።

✔ #ተውሂድን የያዘ ግለሰብ ብዙ አስከፊ ነገሮች ቢገጥሙትም እንኳ ከአላህ ውሳኔ መሆኑን በማመን በህይወቱ በጣም ደስተኛና የተረጋጋ ይሆናል።

✔ #ተውሂድን የያዘ ግለሰብ ለፍጡር ተገዥ ባሪያ አይሆንም የሚፈራው የሚከጅለው ደጅ የሚጠናው ጌታውን አንድ አላህን ብቻ ይሆናል ይህ ነው የክብርና የልቅና መገለጫተውሂድን የያዘ ግለሰብ አላህ መጥፎ ከሚባል ነገር በሙሉ ሊጠብቀውና ጀነትን ሊያስገባው እንዲሁም በዚች አለም እርሱን በማውሳት የመንፈስ እርካታን ሊያጎናልፋቸው ቃል ገብቷል።
✍°• https://telegram.me/Bistima1


•°♡✍ #ጠንካራ_ሁን

ዘመናት ይፈትኑሀል ምን አልባት ትሰደዳለህ፣ ከሀገርህ
ትርቃለህ፣ የእናትህን እንጀራ ዳግም ትናፍቃለህ ግን.
#ብርቱ_ሁን
ምድር ላይ እራስህን ብቸኛ ሆነህ ታገኘዋለክ ያለ ወዳጅ፣ ያለ ጓደኛ፣ ያለ ወንድም የምድርን ፈተና ብቻህን ትጋደላለህ ግን ,,
#ጠንካራ_ሁን፡፡
https://telegram.me/Bistima1


➡ ጀነትና ጀሀነም

ቁርአን ስለ ሰማያዊ ሁነቶች የሰው ልጅ በሚገባው ቋንቋ እንዲህ እያለ ያስረዳል ።

« ከስሮቻቸው ወንዞች ይፈሱባቸዋል »

« በርሷም ( በጀነትም) የገቡት በወርቅና ሉል ጌጦች ያጌጣሉ ። ልብሶቻቸውም ሃር ናቸው »

የወይንና የማር ወንዞች በስሮቻቸው ይፈሳሉ ። በርሷም ዓይኖቻቸው በቅርፊቱ ያለ ሉል የመሰሉ ዓይን ያላቸው ሁሌም ወጣት የሆኑ ልጃገረዶች አሉ ። »

#የጀነትን እውነተኛ ገፅታ ማወቅ ከሰው እውቀት በላይ ነው ። አሏህም በሰው ልጆች ቋንቋ እንዲገባን አድርጎ አስረድቶናል ። ስለሆነም ፤ ስለ ጀነት የተነገረን ነገር በዚህ ምድር ካሉት ከየትኛውም ጋር እንደማይመሳሰል መታወቅ አለበት ።

#ወንዙ ፣ ማሩ ፣ ወተቱ ፣ እና ቆነጃጅቱ ልጃገረዶች ወዘተ እዚህ ምድር ካሉት ጋር አንድ አይነት አይደሉም ። ለዚህም አባባላችን ከቁርአን መረጃ አለን ፦

فَلَا تَعْلَمُ نَفْسٌ مَّا أُخْفِيَ لَهُم مِّن قُرَّةِ أَعْيُنٍ جَزَاءً بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

ይሠሩትም በነበሩት ለመመንዳት ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፡፡
(አስ_ሰጅዳህ 17)

#ተወዳጁ ነቢያችን ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰላም ሲናገሩ አሏህ እንዲህ ይላል ፦ « ለቅን ባሮቼ ዓይኖች ያላዯትን ፣ ጆሮ ያልሰማትን ፣ ልቦች ላይ ውልብ የማትል (ጀነት) አዘጋጅቻለሁ ። »

ይህም አስቀድመን ጀነት በሰው ልጆች ልትታሰብ እንኳን እንደማትችል የተነጋገርነው ይደግፍልናል ።

በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፊ ትንታኔ የሰጡት የቁርአን ሙፈሲሮች ትንታኔዎቻቸውን በበቂ ማስረገጫ አላስደገፉም ። ስለመጪው ዓለም ስዕል ለመፍጠርና ከዚህ ዓለም ጋር ለማነፃፀር እምብዛም አልሞከሩም ። ጥረታቸው ልክ እንደ ስነ መለኮት ምሁራን ሁሉ የአሏህን ፍትሐዊነትና ባህሪያት ከሰው «ፍትሃዊነት» ጋር ማነፃፀር ነበር ።

በዚህም ምክንያት በንድፈ ሃሳብና በክርክሮች መረብ ተተብትበዋል ። ለነሱ በዚህ ጉዳይ ላይ የሰው ልጅ አዕምሮ ከድንበሩ አልፎ ማሰብ እንደማይችል ለማሳወቅ ከቁርአን አስተምህሮ ዝንፍ ያላሉትን ሰለፎች አቋም ቢይዙ ይሻላቸው ነበር ።

ከነዚህ ሰዎች ጉንጭ አልፋ ክርክሮች ውስጥ አንዱ ፣ ጀነት ውስጥ ያሉት ቆነጃጅትን ይመለከታል ። ጥያቄያቸው « ጀነት ውስጥ ካሉት ቆነጃጅት ጋር የሚኖረን ግንኙነት በዚህ ምድር ካሉት ጋር ያለ ዓይነት ነውን ?» የሚል ነው ።

የረሱት ግን በዚህ ምድር የትዳር ዓላማ ልጅ ማፍራትና ዘርን ማቆየት መሆኑን ነው ።በመጪው ዓለም ግን እነዚህ ዓላማዎች ስለሌሉ ጥያቄያቸው ትርጉም አልባ ይሆናል ። ቁርአን ውስጥ ያሉትን ነገሮች ሁሉ በጥልቅ አውቄ ካልተረዳሁ ከማለት ይልቅ ማመን ይበልጥ ምክንያታዊ ነው ።

ወደ #ጀነት …

ወደ #ጀነት መግባት በምኞትና በፍላጎት ብቻ የሚገኝ አይደለም ። በኢማንና በመታዘዝ እንጅ ። ቁርአን ስለዚህ ጉዳይ ሲገልፅ ፦

أَمْ حَسِبْتُمْ أَن تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ وَلَمَّا يَعْلَمِ اللَّهُ الَّذِينَ جَاهَدُوا مِنكُمْ وَيَعْلَمَ الصَّابِرِينَ

በእውነቱ አላህ ከናንተ እነዚያን የታገሉትን ሳያውቅ (ሳይለይ) ታጋሾቹንም ሳያውቅ ገነትን ልትገቡ አሰባችሁን ??
(አል_ዒምራን 142)

لَّيْسَ بِأَمَانِيِّكُمْ وَلَا أَمَانِيِّ أَهْلِ الْكِتَابِ ۗ مَن يَعْمَلْ سُوءًا يُجْزَ بِهِ وَلَا يَجِدْ لَهُ مِن دُونِ اللَّهِ وَلِيًّا وَلَا نَصِيرًا

(ነገሩ) በምኞታችሁና በመጽሐፉ ሰዎች ምኞት አይደለም፡፡ መጥፎን የሚሠራ ሰው በእርሱ ይቀጣል፡፡ ለእርሱም ከአላህ ሌላ ጠባቂንም ረዳትንም አያገኝም፡፡
(አል_ኒሳእ 123)

ስለዚህ ፥ በምድረ_ጀነት ተቀባይነት የሚያገኘው ሰው በመልካም የሚያዝ ። ስለአሏህ የሰራ ፤ ጊዜውን ፣ ሀብቱን ፣ ኃይሉን ሁሉ ለአሏህ ብሎ እውነትን ለማስፋፋት የተጠቀመ ነው ። ይህ ቢያቅተው እንኳ ፣ ነፍሱን ከሚያቆሽሿት ስራዎች ታግሶ ያልፋቸዋል ።

ደህንነት ( ነጃ መውጣት) የሚረጋገጠው ሂሳብ ከተጠናቀቀ ፥ ሲራጥም በሰላም ከታለፈ በኋላ ነው ።

وَسِيقَ الَّذِينَ اتَّقَوْا رَبَّهُمْ إِلَى الْجَنَّةِ زُمَرًا ۖ حَتَّىٰ إِذَا جَاءُوهَا وَفُتِحَتْ أَبْوَابُهَا وَقَالَ لَهُمْ خَزَنَتُهَا سَلَامٌ عَلَيْكُمْ طِبْتُمْ فَادْخُلُوهَا خَالِدِينَ

እነዚያም ጌታቸውን የፈሩት የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገነት ይንነዳሉ፡፡ በመጧትም ጊዜ ደጃፎችዋ የተከፈቱ ሲኾኑ ዘበኞችዋም ለእነርሱ «ሰላም በናንተ ላይ ይኹን፡፡ ተዋባችሁ፡፡ ዘውታሪዎች ኾናችሁ ግቧት» በሏቸው ጊዜ (ይገቧታል)፡፡

وَقَالُوا الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي صَدَقَنَا وَعْدَهُ وَأَوْرَثَنَا الْأَرْضَ نَتَبَوَّأُ مِنَ الْجَنَّةِ حَيْثُ نَشَاءُ ۖ فَنِعْمَ أَجْرُ الْعَامِلِينَ

«ምስጋና ለአላህ ለዚያ ተስፋ ቃሉን ለሞላልን፡፡ የገነትን ምድር በምንሻው ስፍራ የምንሰፍር ስንኾን ላወረሰን ይገባው» ይላሉም፡፡ የሠሪዎችም ምንዳ ምን ያምር!
(አዝ_ዙመር 73➖74)
https://telegram.me/Bistima1


•°♡✍ መጥፎ ነገር ሲያደርጉብህ
ከዛ በበለጠ መጥፎ ነገር ለመመለስ ሳይሆን
ጥሩ በሆነው መልስ ለመመለስ አስብ‥
⇘ ወንድማማችነት እንዲቀጥል
ስህተትን አጥፋት እንጂ ለስህተት ብለህ
ወንድማማችነትን አታጥፋ ።

(وَلَا تَسْتَوِي الْحَسَنَةُ وَلَا السَّيِّئَةُ ۚ ادْفَعْ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ)
" መልካሚቱና ክፉይቱም (ፀባይ) አይተካከሉም ፡፡ በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ፀባይ (መጥፎይቱን) ገፍትር ፡፡ "°•
https://telegram.me/Bistima1

Показано 20 последних публикаций.

40

подписчиков
Статистика канала