ከመጻሕፍት ዓለም - Book shelf 📗📚📖


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


"ስለመጻሕፍት ከመጻሕፍት መንደር እንዘምራለን!"

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ዝክረ ስበሀት

ከቅብጠታት አንድ ቀን ፣አቶ አልአዛር ሲያቀብጣቸው ውሻቸውን " ሁለት መለኪያ አረቄ የተቀላቀለበት ክትፎ አኮሞኮሙት ፡፡
… ‹‹እናንተ የሰው ልጆች ኮተታችሁ ሲበዛ !›› አላቸው
‹‹አረቄዋ ከመቼው ስራዋን ሰራች !›› እያሉ ውስጥ ውስጡን ‹‹እንዴት እባክህ?!›› ሲሉት
‹‹የልብሳችሁ ብዛት ! ሙታንታ-ከናቴራ-ሸሚዝ-ሹራብ-ኮት-ካፖርት-ባርኔጣ-ካልሲ-ጫማ-ቀበቶ-ጡት መያዣ! አንሶላ-ብርድልብስ-አልጋልብስ-ፎጣ! ኧረ ወድያ !ኮተታም ዘር!››
‹‹ ኧረ ባክህ እናንተስ?››
‹‹እኛማ ፀጉራችን በቃን ፡፡ ፀጉራችን ፣በቃይ ከውስጣችን !››
‹‹እሺ!!!››
‹‹ማበጠሪያ፣ፀጉር መያዣ፣ፀጉር መጠቅለያ፣የፀጉር ቅባት፣ የ…››
‹‹በቃህ አታንዛዛብኝ!››
‹‹ደሞ የቤታችሁ ጣጣስ ? ማድቤት -ምግብ ቤት-እንግዳ ቤት-ሽንትቤት-እቃቤት-ወንበር-ጠረቤዛ-ሶፋ-ምንጣፍ-አልጋ-ቁምሳጥን-አግድም ሳጥን! ሌላ ኮተት ዝባዝንኪ ግሳንግስ !››
‹‹ሸይጣን ይንገስብህና! እናንተሳ ባክህን ?››
‹‹እኛማ ምድር ወለላችን ሰማይ ጣሪያችን ፡፡ በቃ ፡፡››
‹‹ወይ ጉድ !››
‹‹ሳህን -ማንኪያ -ሹካ-ኩባያ-ብርጭቆ-ጠርሙስ››
‹‹በቃህ ! በቃንግዲህ!››
‹‹ድስት-ጋን-ገንቦ››
‹‹ኧረ ባክህ ይበቃል››
‹‹የግሳንግሱ የኮተቱ ብዛት ! ሰፌድ-መሶብ-አገልግል››
‹‹በቃ!››ብለው ጮሁበት
‹‹ኮተታም ዘር! ቅራቅንቦ!››
‹‹ቅራቅንቦ?››
‹‹ቅራቅንቦ-ሞፈር-ቀንበር-ኮርቻ-ወስፈንጥር-ወስፌ››
‹‹እሰይ የኛ አዋቂ››
‹‹ግሳንግስ ቅራቅንቦ ! ጋሪ-ቢስኪሌት-ዶቅዶቄ-መኪና-ባቡር-መርከብ-ኤሮፕላን-በሮኬት ጨረቃ ላይ መውጣት››
‹‹ዝም በል አልኩህ! ሰካራም የውሻ ልጅ!››
‹‹ጠላ-ጠጅ-አረቄ-ወይን-››ሲል አቶ አልአዛር ጆሮአቸውን ደፈኑ
‹‹አለዝያ ያላሰብኩትን ሌላ ኮተት ያረዳኛል ››ብለው እያሰቡ ፡፡ ትንሽ ቆየት ብለው እጃቸውን ከጆሮአቸው ሲየወርዱ
‹‹ክርስትና-እስልምና-ፍጥምጥም-ሠርግ-ተዝካር-ሰደቃ…››
‹‹ኧረ ስለማርያም ተወኝ !›› አሉት
‹‹ማርያም-ሚካኤል-አቦ-ራጉኤል-ጅብሪል…›
‹‹ዝም በልኮ ነው የምልህ! የውሻ ልጅ››
‹‹አለቻ ስድብኤል!››
ስቀው ሲጨርሱ ቀጠለ‹‹ገበሬ-ነጋዴ-ቄስ-ጠበቃ-ዳኛ-አናጢ››
‹‹ኧረ በህግ አምላክ ተወኝ!››
‹‹ደሞ የህጋቹ ብዛት ! ወንጀለኛ መቅጫ-ፍትኃ ብሄር-የባህር ንግድ-የስነስርአት-አቤት ግሳንግስ ኮተት !››
‹‹ልብ አርግ፣ዋ!››
‹‹ደግሞ የክሳችሁ አይነት ፣ሰካራም-ተሳዳቢ-አጭበርባሪ-ነብሰገዳይ-እጅ እላፊ-አፍ እላፊ…››
‹‹አሁንስ በቃ !›› አሉና ተነስተው አንስተዉት በሩን ከፍተው ውጭ አስቀምጠዉት ተመልሰው በሩን ዘጉት ፡፡
‹‹ሰካራም የውሻ ልጅ ! ›› እያሉ ግማሽ እየሳቁ ፣ለራሳቸው ሲመርቁላቸው አንድ መለኪያ አረቄ ቀዱ፡፡

ምንጭ፡ አምስት ስድስት ሰባት ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ

Joni Tsegaye






ነፃ–ምርጫ | Freewill

«...Let those who call themselves philosophers bear the risk to their mental health that comes from thinking too much about free will.»₁

[— እሳቤ ዘ ነፃ ምርጫ... ]

አንዳንድ ነገሮች ከቁጥጥራችን ውጭ ናቸው— ከኑባሬያችን በስተፊት የተፈጠሩ ነገሮች፤ መወለዳችን፤ በዘረ-መል የተለገስነው ሁሉ።
ሌሎች ደግሞ በቁጥጥራችን ስር ይመስላሉ — ይሄን ፅሁፍ ማንበብ ወይም መተው፤ አንባቢው ምርጫ አለው!
እንደነገሩ ከላይ ከላይ ከታሰበ ⎡ሊብሪተሪያኒስት⎤ ነን— ነፃ ምርጫ ያለንና ሁሉ ቀድሞ ያልተወሰነ፤ ቀድሞ ከተወሰነ ደግሞ መወሰኑ ከነፃ ምርጫችን ጋር ላይጣጣም የተረገመ ይመስላል። መወሰኑ ነፃ-ምርጫችንን ስጋት ላይ የሚጥል ቢመስል፥ መምሰል ብቻ እንጅ፤ ቅድመ—ውሳኔ ድርጊቶቻችንን በዘፈቀደ ከመመራትና የጭፍን የእድል ውጤት ከመሆን ይጠብቃቸዋል። አእምሯችን ከተቀኘበት ትንሽ ወጣ ስንል ⎡ኮምባቴብሊስት⎤ ወይ ⎡'ስኬፕቲክስ⎤ ነን— ነፃ-ምርጫችንና ቅድመ-ውሳኔው የሚጣጣሙ፤ ወይ ደግሞ ቀድሞ ተወሰነም ቀረም ነፃ-ምርጫ የለንም እንደማለት! ሁሉም ነገሮች ቀድመው ከተወሰኑ ቶማስ ሊጎቲ እንደሚለው ከአሻንጉሊት ላንበልጥ፤ የዘረመልና የአካባቢያችን ባሪያ ልንሆን። ቅድመ-ውሳኔ ስሁት ቢሆን ድርጊቶቻችን ሁሉ ጭፍን እንቅስቃሴ እንጅ ድርጊት አይሆኑም— ድርጊት ከተራ ⎡ሪፍሌክስ⎤ የሚነጠለው የድርጊቱን አላማና ግብ መኖርን መሰረት አድረገን ነው። አላማ ያለው ድርጊት በፈፃሚው ቅድሚያ መፈለጉ፤ ቅድመ ውሳኔን እውነት አድርጎ የ⎡ሊበሪትሪያንን⎤ «ነፃ-ምርጫ አለን!» መፎክር ⎡ኢሉዥን⎤ ብቻ ያደርገዋል።

[— ነፃነት ለድርጊት ፤ ነፃነት ለውሳኔ... ]

[Will] ይላሉ — ወሳኔ የመስጠት ብቃት ነው። የድርጊት ነፃነት የዚሁ ውሳኔ የመስጠት ነፃነት ውጤት ነው። ሁለቱን ነጣጥሎ ማሰብ ከባድ ነው — አንዱን መቁጥጥር ስር ማድረጉ ሌለኛውንም እንደመቆጣጠር ይወሰዳል። [Will] ልቦናዊ ነውና ለሱ ያለንን ነፃ ምርጫ (Freedom of will) ድርጊቱ ላይ ያለንን ነፃ ምርጫ (Freedom of action) ብንገልፅበት— ድርጊቱን ልቦናዊ ፤ ውሳኔያችንን ደግሞ ድርጊት (Action proper) ማድረግ ነው። ስጋዊ የሆነውን ድርጊት ልቦናዊ ለሆነው [Will] ማሰገድ! ከዚ ውንጀላ ለማምለጥ ማለትም ቶማስ ፒንክ እንደሚለው' ⎡«ቮሊሽናስት»⎤ ላለመባል ድርጊቱ ኢ-ቀጥተኛ በሆነ መንገድ ከውሳኔው የተቀዳ ብቻ ሳይሆን በፈፃሚው በቀጥታና ያዊታዊ በሆነ መንገድ የሚተገበር ነው' የሚል መከራከሪያ ይቀርባል።—

«voluntary action ( Action other than 'action of will) is more than just an effect of an earlier action that was performed entirely inside my head. It is also a further and direct involvement on my part in agency, something over which I am exercising direct control as I do it»₂

[— ሰብዕ «አመዛዛኝ እንሰሳ» ስለመሆኑና፤ በመሆኑ ስለደረሰበት የነፃ-ምርጫ አፈና... ]

«ይሄን» ለመስራት ጠንካራ ምክንያት ካለህ «ያን» ለመስራት ነፃ ምርጫ የለህም። ድርጊቱ ጠንካራ ምክንያት በመኖርህ ቀድሞ ተወስኗልና! ቅድመ-ውሳኔ እውነት ከሆነ ⎡Incompatibilism⎦ ይሻራል— እርሱ የድርጊቶቻችንን ቀድሞ አለመወሰን መሰረት ያደርጋልና። በአንድ ጊዜ ምክንያታዊና ነፃ ምርጫ ያለው አካል መሆን ደግሞ ለፈጣሪ የተተወ ምሉዕነት ነው። ችግሩ ሲወስክ ተመልከት! ምክንያታዊነት የሚነግሰው ድርጊቶች—|Action proper| ላይ ባለን ነፃ-ምርጫ ላይ ብቻ አይደለም። በኛ ቁጥጥር ውስጥ ባልሆኑት እምነትና ፍላጎቶቻችንም ውስጥ ነው!—እነሱ |Theoretical reason| ሊሉት እኛ «ምናባዊ ምክንየታ» ልንለው ይሄን ፅሁፍ ቁጭ ብየ ደሴ ላይ ስፅፍ አዲስ አበባ ላይ ሽ ሰወች እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ አመንኩ! በተቃራኒው እንዳምን ግን ነፃ ምርጫ የለኝም— በምክንያታዊነቴ ተገድቦል!— [በምናባዊው ምክንያታዊነት]። ነፃ-ምርጫህን በስንዝር ስትቀርበው ወደ ኢ—ምክንያታዊነት በክንድ ትቀርባለህ። ምናልባት ግን ኢ-ምክንያታዊ መሆንም የነፃ ምርጫችንን ማሳያ ይሆን? አላውቅም!

[— ስለ ሆብስ ሁለንታ፣ ግድፈቱና፤ በተራ ፍላጎታችን ስለተቃኘው ነፃነታችን... ]

«አነባለሁ» ብሎ መወሰን —ለማንበብ ጠንካራ በሆነ ፍላጎት መካበብ ነው። ፍላጎት ሲጠነክር ወደ ውሳኔ ይቀየራል። እናማ [Will] አለ ሆብስ « ከተራ ፍላጎት አይለይም»። ይሄ ተራ ፍላጎት ደግሞ በሁሉም እንሰሳቶች ዘንድ ስላለ ተለይቶ ለሰብእ የተሰጠ አይደለም። [Will] ወደ ተራ ፍላጎት ከወረደ ከቁጥጥራችን ውጭ ሆኗል የሚለውን ያስይዛል— የሁለተኛው ከዚሁ ነውና። ስለዚህ በሆብስ ሁለንታ ውስጥ ያሉ ፍጡራን እነሱ «Action of will» ያሉት እኛ «ልባዊ-ድርጊት» ያልነው የላቸውም። ታድያ የሁሉ ፍጡር ነፃ ምርጫ ከዚሁ ከቁጥጥሩ ውጭ ከሆነው፤ ቀድሞ ከተወሰነለት ተራ ፍላጎቱ የተመዘዘ ከሆነ ነፃነቱ ምኑ ላይ ይሆን? «የሰው ልጅ ነፃነት የሚያርፈው በተራ-ፍላጎቱና— እሱን በመፈፀሙ መካከል ባለው ነፃነቱ (መሰነካል ባለመኖሩ) ነው! ነፃ-ምርጫ ያልተደናቀፈ ተራ ፍላጎት ነው።» [Hobbesian Freedom]–ን ከቅድመ ውሳኔ ይልቅ ካቴና ይገድበዋል!!

« A free man, is he, that ... is not hindred to doe what he has a will to ... from the use of the word Free-will, no Liberty can be inferred of the will, desire or inclination, but the Liberty of the man; which consisteth in this, that he finds no stop, in doing what he has the will, desire, or inclination to doe.»³

የሆብስ ሃሳብኮ ጥሩ ነበር «የሰው ልጆ 'ነፃነት' አለው የሚባለው የፈለገውን ሁሉ መስራት ሲችል ነው» ነፃነቱን የሚያጣው ደግሞ «በፍላጎቱና— ፍላጎቱን በመፈፀሙ መካከል እንቅፋት ሲገባበት ብቻ ነው።» ግን የሰው ልጅ ነፃ ምርጫ ለማጣቱ ምክንያቱ ራሱ ፍላጎቱ ሆኖ ሲገኝ—[ Hobbesian Freedom] ይብረከረካል። ለምሳሌ፥ የእፅ ተጠቃሚወችን ውሰድ — የአለመጠቀም ነፃ ምርጫቸው በዕፅ ፍላጎታቸው ተገድቧል።

[—ፀሃፊው በነፃ ምርጫው እዚጋ የተወው! ምናልባት የሚቀጥለው ...
(© Ā৳ì৳⎝ª৳ì৳—)
______
₁–Henrik Walter, Neurophilosophy of Free Will, Pp. 4
₂— Thomas Pink, Free will: short introduction, Pp. 38
³–Thomas Hobbes, Leviathan, Chapter– 21, Pp. 145




‹‹ፍቅርና ወሲብ›› በObjectivism ፍልስፍና
=============================
© Yonas Tadesse Berhe
==================
በObjectivism ‹‹ፍቅር ያዘኝ›› ማለት ‹‹እኔ የራሴ እሴቶች አሉኝ፤ value system አለኝ፤ የምወደውና የማከብረው አለኝ›› ማለት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ያሉት አእምሯችን ውስጥ ነው፡፡ የሰው ልጅ የሁለት ነገሮች ውህደት ነው ― የነፍስና የአካል፡፡ አየን ራንድ ‹‹ነፍስ›› የምትለው ‹‹የንቃተ ህሊና (Consciousness) የሆኑትን ነገሮች›› ነው፡፡
""""
የሰው ልጅ የራሱ የሆኑ እሴቶች (values) ላይ አንድ ፍላጎት አለው፡፡ ይሄውም፣ ልክ መስታወት አካላዊ ገፅታችንን እንደሚያሳየን ሁሉ፣ የያዝናቸው ረቂቅ እሴቶችም (abstract values) አካል ነስተው ማየት እንፈልጋለን፡፡ ‹‹አካል መንሳት›› ማለት ከረቂቅነት ወደሚታይ አካላዊ ነገር እንዲቀየሩ መፈለግ ማለት ነው፡፡ ይሄም የሚገለፀው በሌላ ሰው ላይ ነው፡፡ በመሆኑም፣ ‹‹የያዝናቸው ረቂቅ እሴቶች አካል ነስተው ማየት እንፈልጋለን›› ሲባል ‹‹የእኛ እሴቶች በሌላ ሰው ውስጥ ማየት እንፈልጋለን›› ማለት ነው፡፡ ይሄም ማለት፣ ሌላ ሰው የኔን ዓይነት እሴቶች ተላብሶ ሳይ፣ የኔን ነፍስ እሱ ላይ አየዋለሁ፤ እናም በፍቅሩ እወድቃለሁ ማለት ነው፡፡ ይሄ ፍቅር ግን የግድ ፆታዊ ብቻ ሳይሆን ልባዊ ጓደኝነትንም ይጨምራል፡፡
"""""
እናም ያፈቀርኩት ሰው ‹‹የኔ የእሴቶች መስታወት›› ነው፤ በእሱ ውስጥ የእኔን እሴቶች አይበታለሁ፤ መስታወት ይሆነኛል፡፡ ነፍሴ እሱ ላይ መገለፅ ስትጀምር ማድነቅ እጀምራለሁ፡፡ የኔን ዓይነት ‹‹value system›› ሌላ ሰው ሲያደርገው ወይም ስታደርገው ስናይ ማድነቅ እንጀምራለን፡፡ ነገሩ የሚጀምረው በአድናቆት ነው፡፡ አየን ራንድ፣ ‹‹የዚህ አድናቆት የመጨረሻው ደረጃ ‹‹ፍቅር›› ይባላል›› (the highest form admiration is Love) ትላለች፡፡
""""
በObjectivism ፍልስፍና፣ ሰው የሚያፈቅረው በሌላ ሰው ውስጥ የሚገኘውን የራሱን እሴቶች ነው፡፡ ‹‹ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ ይቀዳል›› የሚባለው ዓይነት መሆኑ ነው፡፡ ባል የራሱን values በሚስቱ ውስጥ ያገኛል፤ ሚስቲቱም እንዲሁ፡፡ ይሄ ነገር objectivist ስለሆንክ ምናምን አይደለም፤ ሁሉም የሰው ልጅ experience የሚያደርገው ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ሂትለር አያፈቅርም ማለት አይደለም፡፡ እሱም የራሱ values አሉት፡፡ ይሄም ማለት፣ ሂትለርም የራሱ ዓይነት values ያላትን ሴት ያፈቅራል ማለት ነው፡፡
"""""
በObjectivism ፍልስፍና፣ ፍቅር ስሌት ወይም calculation አይደለም፡፡ ‹‹አፍቃሪ እንድትሆን ወይም ሴቷ እንድታፈቅርህ እንዲህ አድርግ፣ እንዲህ ሁን…›› የሚባል ነገር የለም፡፡ በሰራኸው የነፍስህ ቅርጽ እንደዛ ዓይነት ቅርጽ ያለው ሌላ ሰው ነፍስ ታያለች፡፡ ፍቅር ስሌት አለመሆኑን ለማሳየት አየን ራንድ እንዲህ ትላለች ‹‹አንድ ወንድ አንዲትን ሴት በቀላሉ ዘለላ ፀጉሯን ወደ ኋላ ስትመልሰው አይቶ ነፍሷን ሊለየው ይችላል፡፡ ነፍስ ነፍስን ልታስተውል ትችላለች፡፡
"""""
በሌሎች ውስጥ ያለ የራስን እሴቶች በማድነቅ የሚጀመረው ይሄ ክስተት ወደ ፍቅር ያድግና በስተመጨረሻ በወሲብ Celebrate ይደረጋል፡፡ ‹‹Sex is the Celebration of this Love›› ትላለች አየን ራንድ፡፡ ትክክለኛው ወሲብ ይሄ ነው ትርጉሙ፡፡ አየን ራንድ እንዲህ ትላለች፣
‹‹ከአድናቆት ወደ ፍቅር ያደገውን ግንኙነት Celebrate ለማድረግ ፖስት ካርድ ልሰጥህ እችላለሁ፤ እሱ ግን አያረካኝም፡፡ የአንገት ሐብል ልገዛልህ እችላለሁ፤ እሱም አያረካኝም፡፡ የሚያረካውና የመጨረሻው ውዱ ስጦታዬ ርቃን የሆነውን አካሌን እሰጥሃለሁ፡፡ I am happy to give you this naked body in celebration of that administration and love.››




ለመሆኑ የአዳም ልጨኛ ስራው የቱ ነው?

በሙዚቃና በፊልም ምሳሌ ልጥቀስ፦ የማይክል ጃክሰን ሙዚቃዎች ከነቪዲዮ ክሊፓቸው ሁሉም ምርጥ ናቸው—አንዱን ከአንዱ ማበላለጥ አይቻልም፦ thriller, beat it, dangerous, black or white, earth song, you rock my world, bad ወዘተ

የክሪስቶፈር ኖላን ፊልሞችም ሁሉም እኩል ተወዳጆች ናቸው—Memento, The Prestige, Insomnia, Interstellar, Inception, Dunkirk, Oppenheimer. በእርግጥ TENET የተሰኘ ፊልሙ ምንም ነው ያልገባኝ።🤣🤣

የአዳም ረታ ብርቱ አንባቢዎች ዘንድ አራት የተለያዩ ስራዎቹን እንደየ አንባቢው ዝንባሌ የደራሲው ታላቁ ስራ ተደርገው ይቆጠራሉ። እነሱም

ግራጫ ቃጭሎች
ይወስዳል መንገድ፣ ያመጣል መንገድ
መረቅ እና
የስንብት ቀለማት ናቸው።

እኔ መረቅንና የስንብት ቀለማትን ስላላነበብኳቸው፣ ለእኔ የአዳም ማስተርፒስ ግራጫ ቃጭሎች ነው። በነገራችችን ላይ ይሄ ድምጽ መደብሰቢያ poll አይደለም። የትኛው ልብወለድ በድምጽ ብልጫ አሸናፊ መሆኑን ማወቅ ጥቅም የለውም። ጥቅም ያለው ከነዚህ አራት መጻሕፍት/ከአስሩም ሊሆን ይችላል አንዱን የመረጣችሁበት ምክንያት ነው።

እኔ ልጀምር



በመጀመሪያ ግራጫ ቃጭሎችን የሚመስል ልብወለድ ከአሁን በፊት አልተጻፈም ወደፊትም አይጻፍም። አዳም የራሱ የሆነ ወጥ/ኦሪጅናል ስልት አለው።

❷❷

አዳም ጋር ሌላው ሁሌም የምደነቅነት ኳሊቲው፣ ማንም ንቆ የሚተዋቸውን ጥቃቅን ጉዳዮች በሰነጽሁፍ መነጽር አጉልቶ፣ በስነጽሁፍ ለዛ አስውቦ የሚያቀርብበት ጥበቡ ነው።

Small things matter.
Actually, they are the only size that matters.
ትለናለች አሩንዳቲ ሮይ።

ይህንን መንገድ መከተል የጀመረው ደግሞ በግራጫ ቃጭሎች ነው። በዚህ ልብወለድ አዳም ለአማርኛ ስነጽሁፍ ትልቅ ልጅ ነው ከምናቡ አፍልቆ ያዋለደው።

❸❸❸

ቋንቋ ለደራሲ መሳሪያው ነው ካልን አዳም የቋንቋ ኒውክሌር የታጠቀ ደራሲ ነው።

በነዚህ ምክንያቶች ግራጫ ቃጭሎች ልጨኛ የአዳም ልብወለዴ ነው። እስኪ የእናንተንም ንገሩነ፦ የመጽሀፍ ዝርዝር ሳይሆን ከምርጫችሁ ጀርባ ያለውን ስነጽሁፋዊ ምክንያት። እንደዚህ ስንወያይ ነው እርስሸእርስ የምንማማረው!!

ደግሞም ከእኛ ከአንባቢዎቹ ባሻገር አዳም ረታ ራሱ ትልቁ ስራዬ ይሄ ነው ብሎ የሚጠቅሰው የትኛውን የልብወለድ መጽሐፉን ነው? ለምን? ምርጫውንና ምክንያቱን ሊነግረን ፈቃደኛ ከሆነ ይኸው እዚህ Adam Retaን ታግ አድርጌዋለሁ።

© Te Di




ኢሉዥን ነው» ሲል ከመሰረቱ ስህተት ነው እያለ ሳይሆን «የ'ነዚያ የጥንት፣ ተንካራና አስቸኳይ ፍላጎቶቻችን ስኬት ነው» እያለ ነው። የኢሉዥኑ የጥንካሬ ሚስጥር የሚያርፈው በምኞቶቻችን ጥንካሬ ላይ ነው!። እነዚህ ምኞቶቻችን የትኞቹ ናቸው? ሰብዕ ህመሙ፣ ጎርፉ፣ መብረቁ ሲያስጨንቀው በነሱ ላይ ቁጥጥርን በመሻት ከአእምሮው ፈስ ፈጣሪን አበጅቶ— ሊደልለው፤ ከሰጠው ሓያልነት ላይ የሆነ እጁን በእጅ አዙር ሊቀበለው ነው ፈጣሪውን የፈጠረው። ይሄ ነበር በሃዘኑ ላይ ቁጥጥርን አስችሎ ትንሽ ደስታን የሰጠው። የሞትስ ስቃይ ፤ «ከሞት ኋላ ሂወት» በሚለው ይቀል የለ!። ፍሮይድ ግን በሗለኛዋ ሂወት ስለማያምን የሞትን ስቃይ ፈርቶ ያችን ከዶክተሩና ጓደኛው Max schur ጋር ያሰሯትን ቃልኪዳን ትፈፀም ዘንድ አዘዘ። ሁለት ሴንቲግራም ሞርፊን በፍሮይድ የደም ስር ገባ— በሰላም ተኛ። Schur ከ 12 ሰዓታት ቡሃላ ያንኑ መጠን ያለው ሞርፊን ደገመው— ፍሮይድ ኮማ ውስጥ ገባ። September 23 ፤ 1939 ሞተ!

© አብዱልዐዚዝ
— የካቲት፡ 2017 ፡ ደሴ።
_____
ዋቤ መፅሃፍት፤
| Freud, Future of an illusion, 1927
| Freud, Totem and taboo, 1912
| Freud, Three essay on theory of sexuality, (1905?)
| Elliot Oring, The Jokes of Sigmund Freud, 2007


በጎሳው ዘንድ ይሄ Totem እንደ ጠባቂ መንፈስ፤ የጎሳው አባላት በሙሉ አንድ መነሻ ተደርጎ ነው የሚቆጠረው። ቶተሙ እንስሳ ከሆነ ያን እንስሳ መግደል አይቻልም! መብላትም እንደዛው። ቶተም ታቡ ነው (መግደል ክልክል ነው)። ይሄን የታቡ ህግጋት የሚጥስ እራሱ ታቡ ነው! መጥፎ ነገርን በጎሳው ላይ ያመጣል ተብሎ ይታመናል። ስለዚህ ከተፀናወተው ታቡ መፅዳት አለበት— ለዚህም አምልኮ ተደርጎ እጁን በመታጠብ ካረፈበት እኩይ ይፀዳል። ከዚህ ነበር ፍሮይድ አንድ ድምዳሜ ላይ የደረሰው፥ ታቡ (ልክ እንደ incest አይነቱ) በጣም የተጠላ ሁኖ ጠንካራ ማዕቀብ የተጣለበት፤ ባናውቀውም Unconsciously እሱን ለመፈፀም ጠንካራ ፍላጎት ስለነበረን ነው። ይሄ Ambivalence ወደ 'ሚባለው ሌላ የፍሮይድ እሳቤ ይወስደናል— ማለት አንድ ታቡን የማህበረሰቡ እገዳ ይዞን ወደ Unconscious mind ሪፕረስ አድርገነው እንጅ Inherently ጠንካራ የሆነ የማድረግ ፍላጎት አለን። ይሄም ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን እንድንፈልግ ያደርገናል— አንድ፥ unconscious mind ላይ ሪፕረስ አድርገን የያዝነውን ፍላጎት ማሳካት (ባናውቀዎም)። ሁለት፥ የማህበረሰቡን እገዳ ስላለብን ሪፕረስ አድርጎ መቆየት። ይሄን ተቃራኒ የሆነ ፍላጎት ነው ፍሮይድ «phenomenon of Ambivalence» ያለው። ቅድም እንዳነሳነው ይሄ ወደ «የልታወስ—አልታወስ» ጦርነት ውስጥ ያስገባንና የኒውሮሲስን ቁልቁለት ያስጀምረናል።
የጥንት ታቡወቻችን (የተከለከልነው) ከ Incest ና የቶተም እንሰሳን ከመግደል ስለነበረ— የጥንት ፍላጎቶቻችንም ማለትም Unconscious mind ላይ ተገደን የቀበርናቸው— Incest እና የቶተም እንስሳን የመግድል ፍላጎታችን ነበሩ። ድሮም ህግ የሚጣለው፤ የሰው ልጅ በይበልጥ የሚፈልጋቸው ነገሮች ላይ ነው!!

እስኪ የፍሮይድን ኦዲፐስ ኮምፕሌክስ ከዳርዊን Primal Horde Theory ጋር እናጣምረው፥ የጥንት ሰው ይኖር የነበረው በአንድ ወንድ መሪነት ጋንታ መስርቶ ነበር። ሁሉም ሴት አባላቶችን መሪው እንደሚስት ጠቅሎ ይይዛል— ልጆቹም የሱ ብቻ ናቸው። ይሄንን ንግስናውን ማስቀጠል የሚችለው ደግሞ አንድም፥ ወንድ አባላትን ከቡድኑ በማባረር፤ ሁለትም፥ በወሲብ ላይ ታቡ በመጣል። «ይሄ ደግሞ...» ይላል ዳርዊን «ከቡድኑ በተባረሩት ወንዶች ላይ ቅናትና Sexual frustration ን ፈጥሮ — ተባብረው አባታቸውን ገድለው እንዲበሉት አድርጓል (They were Cannibals, after all!)።» ነገር ግን አባትን ገድሎ ረፍት የለምና «እነዚህ ወንድማማቾች በሰሩት ስራ ተፀፀቱ! የአባታቸውን ቦታ ለማያዝም አልደፈሩ። ይልቁንም አንድ የወድማማቾች ጎሳ አቋቁመው Exogamy ን መተግበር ጀመሩ። ለአባታቸው መተኪያ፤ ማስታወሻ ቶተም እንስሳ ሰየሙ— (ቅድም ቶተም የጎሳው መነሻ ተደርጎ ይወሰዳል ስላችሁ የነበረው!)። በየአመቱ የሚያካሂዱት የቶተም ዝግጅትና መብልም ያችን የመጀመሪያዋን ጥፋት— የአባታቸውን ግድያ የሚያስታውሱባት ናት!» ( ዳርዊን «Original crime» ብሎ የሰየመው)። አሁን ሶስት ነገሮች ባ'ንድ ላይ እየመጡ ይመስላል— ኦዲፐስ ኮሞፕሌክስ፤ ሐይማኖት እና/ ወይም ቶተሚዝም። በሌላ አባባል በቶተሚዝም ውስጥ የሐይማኖት አጀማመርን አግኝተናል፤ በቶተሚስዝሞ ልብ ውስጥ ደግሞ በአባቱ ላይ የፈፀመውን ያን ወንጀሉን ያስታውስበት ዘንድ የሰውልጅን የፈጠረውን የጥንት ድግሱን ቀምሰናል!—( Totem meal )፤ አወ ሐይማኖት የኒወሮሲስ ማዕከሎችን ሁሉ ሰብስቦ ይዟል።
*በቶተሚዝም ስርዐት ውስጥ ሁለቱ ታላላቅ ታቡወች፥ 1— Incest፤ ማለትም የራስ ጎሳ አባልን ማግባት ፤ 2— የቶተም እንሰሳን መግደል (ለምን ከተባለ፤ አባትን ስለሚተካ)
*የኦዲፐስ ታላላቅ ጥፋቶቹ፥ 1— አባቱን መግደሉ ፤ 2— እናቱን ማግባቱ ( This is also an Incest! )
ፍሮይድ በ Totem and taboo መፅሃፉ ላይ እንዳለን የቶተሚክ ሃይማኖት የሚነሳው ከጥፋተኝነት ስሜት ነው። የገደለውን አባቱን በማሰብ፤ በመታዘዝ ነፍሱን ሊያስደሳለት! ከዛ ቡሃላ የመጡ ሁሉም ሃይማኖቶች ይሄን ጥያቄ ለመመለስ የሚሞክሩ ናቸው።

«...Totemic religion arose from the filial sense of guilt, in an attempt to ally that feeling and to appease the father by deferred obedience to him. All later religions are seen to be attempts at solving the same problem...» ( TAT, Page፡ 168)

ቀጣዩ ጥያቄ የሚሆነው ይሄ የቶተሚክ ሃይማኖት እንዴት በፈጣሪ ወደ ማመን ተሸጋገረ የሚል ነው፥ ከአባት ሞት ቡሃላ ከወድማማቾቹ መካከል አንዱም እንኳን የአባቱን ቦታ መሸፈን አልቻለም። ይሄ ድክመቱ አርኣያ አድርጎ ይዞት የነበረውን፤ የገደለውን አባቱን ተስፋ በመቁረጥ ውስጥም ቢሆኖ እንዲናፍቅ ያደርገዋል። ጊዜ ሲያልፍ፤ ወደ አባቱ ይዞት የነበረው ጥላቻ እየቀነሰ ሲመጣ፤ ናፍቆቱ እየጨመረ ይመጣል። ይሄን ናፍቆቱ መጀመሪያ ለሰወች ከፍ ያለ ቦታን በመስጠት ውስጥ ይገለጣል። ቀስ በቀስ ከሰውም ከፍ ያለ አርኣያን መፈለጉ— አምላክን እስከመፍጠር ያደርሰዋል። የአባት ናፍቆት የፈጣሪ ውልደትን ፈጠረ። ስለዚህ አማልክት/አምላክ/ፈጣሪ— የ'ዛ የአባትነት ኣርኣያ ትንሳኤ ነው። የገደለው አባቱ የኣምላክነት ዘውድ ተደፍቶበት ነው። ይሄን እሳቤ ከክርስትና በላይ የሰበከው አለ'ዴ? የለም! ያ የመጀመሪያው የአዳም ወንጀል ከእግዜሩ ተቃርነን የፈፀምነው፤ እጅግ ከመክፋቱ የተነሳ በልጁ ደም (ሞት?) በኩል እንጅ በሌላ እንደማይፀዳው!። ስጋ ወ ደሙንስ ተንበርክከህ የምትጎርሰው፤ ከቶተሙ ድግስ ምን ለየው!
ሁሉም ሃይማኖተኞች ኒውሮቲክ'ስ ናቸው። ያልተፈታ የኦዲፐስ ኮምፕሌክስ ሰለባወች! ይሄ ኮምፕሌክስና የወለደው የጥፋተኝነት ስሜት በሁሉም ሰወች ጋር መኖሩ— (እያንዳንዱ ህፃን ከተቃራኒ ፆታ ወላጅ ጋር ባለው የሊቢዲኒል ትስስር ምክንያት)። ይሄ ብቻ ሳይሆን የኮምፕሌክሱና የጥፋተኝነት ስሜቱ የሚወረስ መሆኑ— (የመጀመሪያወቹ የኮምብሌክሱ ተጠቂወች እነዚያ ዳርዊን Primal Horde ያላቸው አባላት ላይ እንደነበሩ አይተናል)። ፍሮይድ የኦዲፐስ ኮምብሌክስን አመጣጥ በሁለት መንገድ ይገልፀዋል— አንደኛ ኦዲፐስ ኮምብሌክስን በ phylogeny ከዝርያ አንፃር — ማለትም ከ ዳርዊን ቲወሪ አንፃር ተወራራሽ አድርጎ። ሁለትኛ ደግሞ በ ontogeny— ማለትም ከግለሰብ አንፃር ፤ ያ ሪፕረስ ባደረግነው ወሲባዊ ግፊት አንፃር። እነዚህ ሁለት ነገሮች ናቸው ኦዲፐስ ኮምፕሌክስን ከሰው ልጅ ላይ ለመፋቅ የማይቻል የሚያደርጉት። ኦዲፐስ ኮምፕሌክስ አንድም፥ በእድገትህ ሂደት ላይ የሚፈጠርብህ፤ ሁለትም፥ ከአባትህ የተቀመጠልህ ውርስህ ነው (It is your birthright!)።

1927፡ ፍሮይድ በሰፊው የተነበበለት «The Future of an Illusion» የሚለው መፅሃፉ ወጣ፥ («የብዥታ እጣ— ፋንታ» እንደማለት ነው ወደኛው ቋንቋ ሲመጣ)። በዚ መፅሃፉ አስቀድሞ በ Illusion እና በ Delusion መካከል ያለውን ልዩነት ሲነግረን፥ Delusion ማለት ከጅምሩ ገና ስሁት የሆነ፣ ከህላዌ የተቃረነ ማለት ሲሆን lllusion ደግሞ ስህተት ላይሆን ይችላል ይልቁንስ የፍላጎቶቻችን ስኬት ነው— (it is «wish fulfillment» )። ፍሮይድ «ሃይማኖት


ፍሮይድ | ኦዲፐስ ኮምፕሌክስ| ሐይማኖት| ሪፐርሽን| ኦብሰሽናል ኒ'ውሮሲስ|
___________

(መውጫ፥ ከዚህ በታች የከተብኩላችሁ ፅሁፍ ምናልባትም ከኢትዮጵያውያን ባህልና እምነት ጋር በቀጥታ ይቃረን ይሆናልና፤ አንድም— ላንባቢው ሳይጀምሩ የመተውን ነፃነት ሲሰጥ ፤ ሁለትም— የፃፍኩት ሁሉ ያመንኩበት ነው ማለት እንዳልሆነ ከልባችሁ ይጣፍ። ፀያፍ ቃላቶች ሁሉ በፈረንጅ አፉ ተከርዘዋል!)
____
«ዳርዊን እንደ ዝርያ ከነበርንበት የክብር ማማ አወረደን፤ ሲግመንድ ፍሮይድ እንደ ግለሰብ አራቆተን!»

Elliot Oring, The Jokes of Sigmund Freud

ፍሮይድ ሐይማኖታዊ ተግባራትን አትኩሮ በመመልከት ይጀምራል፥ እነዚህ ድርጊቶች የኦብሰሽናል ኒ'ውሮሲስ ታማሚወች ከሚያሳዩት ምልክቶች ጋር እጅጉን ይመሳሰላል። ተደጋጋሚ የሆነ አንድን አምልኮ በመፈፀም ሰዓታትን ያሳልፋሉ። ከ'ነዚህ ህግጋቶች ማፈንገጡ ደግሞ ምዕምኑን በጥፋተኝነት ስሜት እንዲታጀብ ያደርጉታል። እነዚህ አምልኮወችን መፈፀሙ ለምዕምኑ አንድም፥ ከ Instinctual ግፊቶቹ መላቀቂያ፤ ሁለትም፥ ባለመፈፀሙ የሚደርሰበትን ቅጣት ለማስወገድ የተቀረፁ ናቸው። እነዚህ Instinctual ግፊቶች ምንድን ናቸው ስንል— ወደ ፍሮይድ የኒውሮሲስ እሳቤ ይመልሰናል። ኒውሮሲስ በሁለት መርሆች የተዋቀረ ነው— በሪፐርሽን እና በኦዲፐስ ኮምፕሌክስ።
ፍሮይድ፤ አንዳንድ ከኛ እውቅና ውጭ የሆኑ ፤ unconscious የሆኑ አእምሯዊ ሂደቶች— በሌላ ተጨባጭ በሆነ የአእምሮ እክል ሊገለፁ የማይችሉ በሽታወች መኖራቸውን የ Psychoanalysis መሰረት አድርጎ ይወስደዋል። ምሳሌ፥ ሂስቴሪያ ህመምተኞች— የእነዚያ ስቃይ የተሞላባቸው ወይም ደግሞ አሳፋሪ የሆኑ ታሪኮቻቸው ስብስብ ተቆልፈው ከነበሩበት Unconscious Mind መታወሳቸው ነው ምክንያቱ (ie. Organic የሆነ መሰረት የለወም።) እነዚህን አሳማሚ ትውስታወች እንደይተወሱ ፤ ማለትም ከተከማቹበት Unconscious mind ወደ እኛ እውቅና —Conscious Mind እንዳይመጡ የሚያደርግልንን የመርሳት ሂደትን ነው ሪፐርሽን ያለው ፍሮይድ። ይሄ ከሰወየው እውቅና ውጭ የሆነ «የልታወስ—አልታወስ» ጦርነት እና እነዚያ የድሮ ግን የተረሱ አሳማሚ ታሪኮች አይወገዱምና ቡሃላ እራሳቸውን በፎቢያ፣ በኦብሰሽን፣ በሂስቴሪያ፤ በአንዛይቲ መልክ ይገልጣሉ።

ቀጣዩ ጥያቄ የሚሆነው ሁሉም የ—Trauma አይነቶች ተመሳሳይ የሆነ መሰረት አላቸው ወይ የሚል ነው። በ 1905? (Not sure) — Three essay on theory of sexuality በሚል ርዕስ በታተመው መፅሃፉ ፥ «የሁሉም ኒውሮሲስ ዋና መነሻ የወሲባዊ—ግፊቶች (sexual instinct) ሪፐርሽን ነው» ሲል ደምድሟል። ይሄንን ግፊት ነበር «ሊቢዶ» ያለው። ፍሮይድ ይሄ የውሲባዊ-ግፊት ሪፐርሽን በሁላችንም ዘንድ እንደነበረ ጠቅሶ እሱም፥ በልጅና በወላጅ መካከል ያለው የወሲባዊ ግፊት ሪፐርሽን እንደሆነም ገልጿል። ይሄም ወንድ ልጅ ለተቃራኒ ፆታ ወላጁ (ለእናቱ) ያለው— Sexual instinct እና ለተመሳሳይ ፆታ (ለአባቱ) የሚያሳየው በቅናትና ፉክክር ላይ የለመሰረተ ጥላቻ— ነው። ይሄንን ነው ፍሮይድ «ኦዲፐስ ኮምፕሌክስ» ያለው።— (ኦዲፐስ በግሪክ አፈታሪክ ውስጥ እንደሚነገረው አባቱን በመግደል እናቱን ያገባ አንድ ካራክተር ነው)። በጥቅሉ በእያንዳንዱ ሪፕረስድ በተደረገ Trauma ውስጥ አንድ ወሲባዊ የሆነ ማንነት አለ። ያ ማንነት ኦዲፒናል ኢምፐልስ)— (የኦዲፐስ ግፊት!) እነዚህ ሁለት ግፊቶች ማለትም— ወደ ተቃራኒ ፆታ ወላጅ ያለ Sexual instinct እና ወደ ተመሳሳይ ፆታ ወላጆ የሚቃጣው ጥላቻ— ምንም እንኳ በሁሉም ህፃናት የእድገት ሂደት ላይ የሚፈጠር Normal የእድገት ክፍል ቢሆንም፥ ልክ እነዚያ የጥንት ዝርያወቻችን (እንደ ማነፃፀሪያ ራሱ ፍሮይድ የወሰደውን የኦስትራሊያወቹን አቦርጅናል ጎሳወች ተጠቀም!) እንደ ታቡ (Taboo) የወሰዱትን Incest ሪፕረስ የማድረግ ግዴታን «በዘር የወረስነው» ይመስል! (የላማርክን «በእንስሳት ላይ የሚፈጠር አዲስ ትሬይት ወደ ቀጣይ ትውልድ የሚዋረስ ነው» የሚለውን እሳቤ እየደገፍኩ አለመሆኑ ይታወቅ!) ይሄንንም የኦዲፐስ ግፊት— አቦርጅናሎች ለ Incest ት ያላቸውን ዝንባሌ ሪፕረስ እንዳደረጉት፤ ዘመናዊው ሰውም ኦዲፒናል ግፊቱን ሪፕረስ በማድረግ እንዳያስታውሰው አድርጎ ከ unconscious አእምሮው ውስጥ ቀብሮታል።(ይሄ Normal ነው) ነገር ግን ጥሰው በግዴታ ወደ መታወስ ከመጡ ማለትም ወደ Conscious mind ከገቡ የኒወሮሲስ መንስኤ ይሆናሉ።
አሁን ፍሮይድ እንዳለው፥ እውነትም ሐይማኖት ኒውሮሲስ ከሆነ የሱን ጥቁር አሻራ የኋሊት ስንከተለው የወሲባው—ግፊቶች ሪፐርሽን ላይ ሊያደርሰን ግድ ነው። የሐይማኖት አጀማመር (አነሳሱ) ከኦዲፐስ ኮምፕሌክስ አንፃር ይነደፋል።...
አንድ ወንድ ልጅ እድሜው ከሁለት እስከ ሶስት ዓመት በደረሰ ጊዜ ፍሮይድ «Phallic phase» ወዳ'ለው የእድገት ደረጃ ይሸጋገራል። በዚህ እድሜው ላይ Pleasure ን Drive የሚያደርገው፥ By manual stimulation of his sexual organs and he becomes his mother's lover ይላል ፍሮይድ! በጥቁሩ ሲተረጎም የእናቱ አፍቃሪ ይሆናል እንደማለት። ለአንባቢውም ለፀሃፊውም ቅድስና ስል ቀጥታ ፅሁፍን ባመጣው ይሻላል...
«He becomes his mother’s lover. He wishes to possess her physically in such ways as he has divined from his observations and intuitions about sexual life, and he tries to seduce her by showing her the male organ which he is proud to own...» ልጁ በአባቱ ላይ የሚያየው የአካል ጥንካሬ፤ በቤቱ ላይ ያለው የማዘዝ ስልጣንን ሲያይ ከቅናትም ባለፈ እንደ አርኣያ አድርጎ እንዲይዘው ያስገድደዋል። አሁን በመንገዱ ላይ ያለው የልጁ ተፎካካሪ አባቱ ነውና እንዲወገድለት ይፈልጋል (ኦዲፐስ አባቱን መግደሉን አስታውስ!)። ልጁ— አባቱ ሲኖር ያለው ድብርትና፤ ሳይኖር ያለው ደስታ በልጁ አእምሮ ውስጥ ሰርገው የሚቀሩ ትውስታወች ናቸው።

ፍሮይድ Totem and Taboo በሚል ርዕስ ባሳተመው መፅሃፍ ይሄን የኦዲፐስ ግፊት የበለጠ አንትሮፖሎጂካል ስዕል ሰጥቶ አቅርቦታል። የኦስትራሊያ አቦርጅናል ጎሳወችን የወሲብ ህግጋቶቻቸው ከዘመናዊው ዓለም ሰው የበለጠ ጥብቅ ነው። እንደ incest አይነት ተግባሮችን ፈፅሞ ይከለክላሉ— Incest ታቡ ነው፤ (Incest የደም ዝምድና ባላቸው ሰወች መካከል የሚደረግ ጋብቻ ብቻ ሳይሆን በአንድ ጎሳ ውስጥ ያሉ ሰወችም ከተጋቡ— ምንም እንኳ የደም ዝሞድና ባይኖራቸውሞ— በአቦርጅናሎች ዘንድ ይሄ Taboo ነው! የተከለከለ ነው)። በአጭሩ— አቦርጅናሎች Exogamy ን ይተግብራሉ— ማግባት የሚችሉት ከጎሳቸው ውጭ ብቻ ነው። ይሄንና ሌሎች ህግጋቶችን የያዘ የእምነት ሲስተም— Totemism ይባላል። Totem ማለት አንድ የተቀደሰ የጎሳ መለያ ነው። እንስሳ ሊሆን ይችላል፤ እፅዋት ሊሆን ይችላል..! ብቻ




ደራሲዎቻችንና ማስተርፒሶቻቸው (የኔ ምርጫ)

ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ― ሌቱም አይነጋልኝ
በአሉ ግርማ ― ሐዲስ
ሐዲስ አለማየሁ ― ፍቅር እስከ መቃብር
ዳኛቸው ወርቁ ― አደፍርስ
አቤ ጉበኛ ― አንድ ለናቱ
ፀጋዬ ገብረመድህን ― እሳት ወይ አበባ
አዳም ረታ ― ግራጫ ቃጭሎች
አለማየሁ ገላጋይ ― ወሪሳ
ዘነበ ወላ ― ማስታወሻ
ብርሃኑ ዘርይሁን ― የታንጉት ሚስጥር
ደበበ ሰይፉ ― የብርሃን ፍቅር
ኃይለመለኮት መዋእል ― ጉንጉን

ሊያከራክሩ የሚችሉት

በአሉ ግርማ ― ኦሮማይ ወይስ ሀዲስ?
አዳም ረታ ― ግራጫ ቃጭሎች ወይስ የስንብት ቀለማት?
አቤ ጉበኛ ― አልወለድም ወይስ አንድ ለናቱ?

* ማስተርፒስ ― የአንድ ደራሲ፣ ሰአሊ፣ ቀራፂ ወይም ሙዚቀኛ አብይ ስራ፤ ጠቢቡ ከሌሎቹ ስራዎቹ በላይ የሚታወቅ ስራው

እስኪ እናንተም የምትወዷቸውን ደራሲዎችን እና ከሁሉም የሚበልጥባችሁን ማስተርፐስ የሆነ ስራ ንገሩን።

© Te Di




መሳሪያ በተጠመደባቸው ጠመንጃዎች መገደላቸው ታወቀ።

ይህንን በመሰለ ሁኔታ ኮሎኔል መንግስቱ ከጃቸው ያመለጠችውን ስልጣን ሙሉ በሙሉ በጃቸው አስገቡ። አገርጥለው እስከሄዱበት እስከ ፲፱፻፹፫ ዓ.ም ድረስም በጃቸው እንደጨበጧት ቆዩ!

▼ምንጭ:- እኛና አብዮቱ ፤ ሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ

Ethiopian hisory and tourism/የኢትዮጵያ ታሪክ እና ቱሪዝም


ከ 48 ዓመት በፊት ጥር 26 ቀን 1969 ዓ.ም የኢህአፓ ደጋፊዎች ተብለው የተፈረጀባቸው የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር የነበሩት ጀነራል ተፈሪ በንቲ እና ሌሎች 6 ግለሰቦች ላይ በደርግ ዘመቻና ጥበቃ ኃላፊ በሌ/ኮሎኔል ዳንኤል አስፋው አማካኝነት ድምፅ ማፈኚያ (Silencer) በተገጠመለት መሳሪያ ሽጉጥ የተገደሉበት ዕለት ነበር።

⩩ በወቅቱ በሰባቱ ግለሰቦች ላይ የተወሰደው እርምጃ በብሔራዊ ራዲዮና የተላለፈው እና በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ የወጣው ፅሁፍ

"....በመለዮ ለባሹ መሀከል መከፋፈል በመለዮ ለባሹና በሰፊው ሕዝብ መካ ልከ መቃቃርን እያስፋፉ በሔዱት በኢሕአፓና በኢዲዩ የውስጥ አርበኞች ላይ አብዮቱ ከመጠቃት ወደ አጥቂነት በመሸጋገር ዛሬ የማያዳግም አብዮታዊ ርምጃ ወስዶባቸዋል።

በዚህም መሠረት በጊዜያዊ ወታ ደራዊ አስተዳደር ደርግ ውስጥ ለኢ አፓና ለኢዲዩ በውስጥ አርበኝነት ብዮቱን ለመቀልበስ ተራማጅ የደርግ አባላትንና የሕዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ/ቤት ታጋዮችን ለማፈን ሲያሴሩ እጅ ከፍንጅ በተ ያዙት በሚከተሉት የውስጥ አርበበኞች ላይ በትናንቱ ዕለት አብዮታዊ ርምጃ ተወስዶባቸዋል። እነርሱም:-

፩. ብ/ጀነራል ተፈሪ በንቲ :- የደርግ ሊቀምንበር
፪. ሌ/ኮ አስራት ደስታ :- የማስታወቂያ ጉዳይ ም/ኃላፊ
፫. ሌ/ኮሎኔል ህሩይ ኃ/ስላሴ :- የህዝብ ደህንነትና መረጃ ዘርፍ ሃላፊ)
፬. ሻምበል ሞገስ ወ/ሚካኤል :- የውጭ ጉዳይና የህዝ ብ ማደራጃ ዘርፍ ሃላፊ)
፭. ሻምበል አለማየሁ ሃይሌ :- የደርጉ ዋና ፀሃፊ
፮. ፲ አለቃ ሃይሉ በላይ :- የውጭ ጉዳይና የህዝብ ማደራጃ ዘርፍ ምክትል ሃላፊ)
፯. ሻምበል ተፈራ ደነቀ:- የደርግ አባል

*****

መጀመርያ አካባቢ ደርግ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት ህዝብ የሚያውቃቸውን ጄነራሎች በአመራርነት ይሾም ነበር። በዚህም መሰረት ጄነራል ተፈሪ በንቲ የደርጉ ሁለተኛ ዋና ሊቀመንበር ነበሩ (ከጄነራል አማን አንዶም በመቀጠል)። ምንም እንኳን በጊዜው የደርጉ ሊቀመንበር ጄነራል ተፈሪ በንቲ ቢሆኑም፤ እውነተኛ የስልጣን ባለቤት የነበሩት ግን ምክትል ሊቀመንበሩ ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪም ነበሩ።

የደርጉ ሁለተኛ ሰው የነበሩት ሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ እንደሚተርኩልን ከሆነ በደርግ የመጀመርያ ጊዜያቶች አካባቢ የኢህአፓ አባሎች በደርግ ውስጥ ሰርገው ገብተው ነበረ። ኢህአፓ እነዚህን አባላ ት በመጠቀም፣ ከደርግ ስልጣን ለምንጠቅ ካካሄዷቸው በርካታ እንቅስቃሴዎች መካከል በደርጉ ሊቀመንበር በኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪያም ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራ አንዱ ነው። የግድያ ሙከራው ሳይሳካ በመቅረቱ ምንክያት ኢህአፓ ሌላ የስልጣን መጨበጫ መንገድ መፈለግ ነበረበት። ይህም መንገድ ደግሞ ደርግ ውስጥ ባሉት አባላት አማካኝነት ስልጣንን በሰላማዊ መንገድ መቀበል ነበር።

⩩ ከመስከረም ፲፱፻፷፱ ዓ.ም ጀምሮ በተካሄዱ ተከታታይስብሰባዎች አማካኝነት ኢህአፓ

አባሎቹን በመጠቀም የደርግን ስልጣን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ለመቆጣጠር ችሎ ነበር... በመሆኑም ስ ልጣን ለመጀመርያ ጊዜ ከኮሎኔል መንግስቱ እጅ ወጥታ በጄነራል ተፈሪ ፤ በሻምበል ሞገስና በመቶ አለቃ አለማየሁ እጅ ዉስጥ የገባች መስላ ነበር። ኮሎኔል መንግ ስቱ ስልጣን ከጃቸው በመውጣቱ ምክንያት እና ስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ ብዙ ጠላቶች አፍርተው ስለነበር ሁ ኔታዎችን በጊዜው ለሳቸው በሚመች መልኩ ካላስተካከሉ ለህልውናቸውም ጭምር አስጊ እንደሆነ አመኑ። በመሆኑም ኮሎኔል መንግስቱ ከእጃቸው የወጣችውን ስልጣን ለማስመለስ በጥር 26 ቀን 1969 ዓ.ም አንድ እርምጃ ወሰዱ።

⩩ ሻምበል ፍቅረስላሴ ወግደረስ ሁኔታውን በሚከተለው መልክ ገልፀውታል።

"... የቛሚ ኮሚቴ አባላት ግራና ቀኝ ቦታቸውን እንደያዙ ጄነራል ተፈሪ ኮሎኔል መንግስቱን አስከትለው በስተኋላ ባለው በር በኩል ገቡ፡፡ ሁላችንም ከመቀመጫችን ተነሳን፡፡ "እንደምን አደራቹ?" ብለው ሲቀመጡ እኛም ተቀመጥን።

በሊቀመንበርንት ስብሰባውን የሚመሩት ጄነራል ተፈሪ "የቛሚ ኮሚቴው በዛሬው ቀን የሚወያይበትን ጉዳይ አስ መልክቶ የመቶ አለቃ አለማየሁ የደርጉ ዋና ፀሃፊ ይገልፅልናል" ብለው ስብሰባው መጀመሩን ካበሰሩ በኋላ አለማየሁ ባጀንዳው ላይ ኣጭር ገለፃ ማድረግ ሲጀምር ስልክ ተደወለ። ስልኩ ኮሎኔል መንግስቱ አጠገብ ስለነበርወዲያው ቅጭል እንዳለ መነጋገሪያውን በማንሳት ሃሎ አሉ። ከሌላው ጫፍ ማን እንደደወለ አላወቅንም። በኋላ እንደታወቀው ሌ/ ኮሎኔል ዳንዔል ነበር የደወለው፡፡ ምን እንደተነጋገሩ አልተሰማንም። ኮሎኔል መንግስቱ ብቻ "እሺ እሺ" ብለው ስልኩን ዘጉት። "ይቅርታ ስልኩ የተደወለው ከጎንደር ነው፡፡ ጎንደር ውስጥ ችግር አለ። እናንተ ቀጥሉ'' ብለው ከጀርባቸው ባለው በር በኩል ውልቅ አሉ። በዚያን ጊዜ አለማየሁ እና ሞገስ ጥርጣሬ የገባቸው መ ሰሉ።

አለማየሁ ንግግሩን አቛርቶ በመስኮት ውጭ ውጭውን መመልከት ጀመረ፡፡ አይኖቹ አላርፍ አሉ። ግራና ቀኝ ይመ ለከታል። አጠገቡ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በጥርጣሬ ተመለከተ። ሻምበል ሞገስም በር በሩን ይመለከታል። ከአሁን አሁን አንድ ችግር ይከሰታል የሚል ፍርሃት ያደረበት ይመስላል። ሁሉም የኢህአፓ አባላት እና ደጋፊዎች ፈርተዋል። እንደፈሩት አልቀረም ኮሎኔል መንግስቱ ከወጡ ሁለት ደቂቃ እንኳን አልሞላም ከበስተጀርባ ባለው ኮሪደር የወታደሮች እርምጃ ሰማን። ወታደሮቹ ሲንቀሳቀሱ በፊት ለፊታችን ባሉት ምስኮቶች በኩል ተመለከትን። በዚህን ጊዜ ፍ ስሃ ደስታ "ተከበናል" አለ። ወዲያው ሁለቱም በሮች በሃይል ተበረገዱ። ሁላችንም ደነገጥን ፤ ቀልባችን ተገፈፈ። ድርቅ ብለን በተቀመጥንበት ቀረን።

በአስፈሪ ሁኔታ ጠመንጃቸውን ወድረው በርካታ ወታደሮች ወደ ውስጥ በመግባት ዙሪያችንን ከበቡን። አንድም ሰው አልተንቀሳቀሰም። ሻምበል ገብሩ ተሰማ የኦፐሬሽኑ ሃላፊ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ "ወንድሞቼ አትደንግጡ ምንም አትሆኑም! የሚፈለጉት ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው ስለዚህ ምንም ችግር ሳትፈጥሩ ጥትቃቹን እያስረከባቹ አንድ ባንድ እንድትወጡልን ብቻ ነው የምንፈልገው" አለ።

ወታደሮቹ ሰገቡ ጄነራል ተፈሪ ከመቀመጫቸው ተነስተው በጀርባቸው ባለው በር በኩል ለመውጣት ፊታቸውን ወደዚያ ሲያዞሩ ወታደሮቹ ጠመንጃ ደገኑባቸው፡፡ እንደገና በፊት ለፊታቸው ባለው በር በኩል ለመውጣት ሲሞክሩ ወታደሮቹ ጠመንጃ ወድረው ካዳራሹ ኣስወጧቸው፡፡ የቀረነው ታጋቾች ሻምበል ገብሩ በሰጠን ትዛዝ መሰረት ከ ተቀመጥንበት ተነስተን ቆምን። ከሌ/ ኮሎኔል ተስፋዬ ገ/ኪዳን በስተቀር ሁላችንም ሳናንገራግር ሸጉጣችንን እየመዘዝን አስረከብን።

... ማን ወዴት መሄድ እንዳለበት ለወታደሮቹ በተሰጠው መመርያ መሰረት ከፊሎቹ ወደ ግራ የቀሩት ደግሞ ወደ ቀኝ እንዲያመሩ ወታደሮቹ ተቆሟቸው፡፡ ወደ ግራ እንዲሄ ዱ የተደረጉት የነአለማየሁ ቡድን ሲሆን ወደ ቀኝ ደግሞ እንዲሄዱ የተደረጉት ደግሞ የኮሎኔል መንግስቱ ደጋፊዎ ች የተባሉና አቆማቸውን በግልፅ ያላሳዩ ናቸው፡፡ የነ አለማየሁ ቡድን አባላት ጠመንጃ ተወድሮባቸው ለማረፊያ ወደ ተመደበላቸው ቦታ ተወሰዱ። ይህ ቦታ ከኮሎኔል መንግስቱ ቢሮ ስር የሚገኝ የመኪና ጋራዥ ነው። ይህ ቦታ ቀድሞ የ ንጉሱ መኪና ማቆሚያ ቦታ ስለነበር መዝጊያ አለው፡፡ የዚህ ቡድን አባላት በሙሉ በዚህ ጋራዥ ውስጥ ተቆለፈባቸው። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ቀንደኛ የኢህአፓ ደጋፊዎችና የኮሎኔል መንግስቱ ባላጋራዎች ናቸው የተባሉት ሰባቱ የደርግ አባላት ብቻ በጋራዡ ውስጥ መገኘታቸው እንደተረጋገጠ ድምፅ የሚያፍን




፬) ለአምስት ደቂቃ ብቻ እንኳን ልብወለድ ማንበብ ውጥረት እና ጭንቀት ይቀንሳል። አእምሮ በተጨባጩ አለም የገጠመውን ችግር ረስቶ ለግዜውም ቢሆን በሌላ አለም ውስጥ ይመሰጣል። ከተመስጦው ሲነቃ አእምሮው ስለተረጋጋ በእውኑ አለም የገጠመውን ችግር በቀላሉ ይፈታል።

፭) ይሄኛውን ለማመን ቢከብድም ተመራማሪዎች ልብወለድ ማንበብ ህይወት ይቀጥላል ብለዋል።

በአጠቃላይ አንድ ደራሲ እንዳለው ልብወለድን ማንበብ በየግዜው አዳዲስ አለማትን መተዋወቅ ነው። በነዚህ አዳዲስ አለማት ውስጥ አንባቢው የራሱን የተወሳሰበ አለም ያያል። ምክንያቱም ልብወለዶች ሌላ ምንም ሳይሆኑ የራስን ነፍስ የሚያሳዩ መስታወት ናቸው። ምናልባት ጥሩ መስታወት ያልገጠማቸው ሰዎች ቆንጆ ልብወለድ አልገጠማቸውም ማለት ነው። ልብወለድ ጠቃሚ ነው ማለት ሁንሉም አይደለም። እንደውም በብዙ እርካሽ ልብወለዶች ተጥለቅልቀናል። ሁሉም ኢልብወለድ መፅሀፍት ጥሩ እንዳልሆኑ ሁሉ ልብወለድም እንዲሁ ነው። የምናነበውን መምረጥ አለብን። ጃኪ ኮሊንስ እና ጃኩሊን ሱዛን የቸከቸኩትን አንብቦ ልብወለድ አይጠቅምም ማለት አያስኬድም። እነዚህ እርካሽ ተብለው የሚቆጠሩ ልብወለዶች እንኳን ለለጋ ወጣቶች ከፍተኛ የመዝናናት ስሜት ተመራጭ ናቸው። ስለዚህ እንደ እድሜያችን የምናነበውን መምረጥ አለብን። የልብወለድ አለም ራሱ ሰፊ ነው። በብዙ የሚቆጠሩ ዘውጎች አሉት። የተለያየ ባክግራውንድ፣ ባህል፣ ስነልቡና የሚፃፉ ናቸው። የዲክንስንም፣ የአቼቤን፣ የስቴፈን ኪንግን፣ የጄ ኬ ሮውሊንግንም በአንድ ጨፍልቆ ማየት አይገባም። ሁሉም ለተለያየ አንባቢ ትርጉም ይሰጣል። በ20 አመት እና 40 አመት አንድ አይነት ልብወለድ አናነብም። ጉዞ ላይ ለመዝናናት የምንመርጠው ቀለል ያለ ልብወለድ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ከተለያየ አንፃር መርጠን ማንበብ አለብን።

📚📚📚

ብዙ ሰዎች ልብወለድን ተረት–ተረት እያሉ ሲያናንቁት ስሰማ ያስቀኛል። የእውቀት ዘርፎችን እንደ ሽንኩርት አንድ በአንድ እየላጣችሁ መሀሉ(core) ላይ ብትደርሱ የምታገኙት ስነ–ልቦናን (psychology) ነው።

የማይጠቅም እውቀት የለም። ታሪክ፣ሳይንስ፣ሂሳብ በአጠቃላይ የቁስ ሥልጣኔዎች ሁሉ የሰው ልጅ አእምሮ ስራ ውጤቶች ነው። የሰው ልጅ አእምሮ ስለፈጠራቸው ነገሮች ይህን ያህል ትኩረት ከሰጠን ስለ አእምሮ፣ስለ ሰው ልጅ ራሷ/ራሱ ምንኛ የበለጠ አንሰጥም። ስለ አእምሮ ስል ኒውሮሳይንስ እያልኩ አይደለም። ስለ ሰው ልጅ ስል ስለ ስጋው እያልኩ አይደለም― ስለ ስነልቦናችን ማለቴ እንጂ!

ምክንያቱም እኛ የስነ ልቦናዎቻችን ውጤት ነን―በግልም፣በቡድንም። "You are not what you think you are. What you think, you are!" እኛ እያንዳንዳችን የአስተሳሰባችን ድምር ውጤት ነን፤አለም የሁላችንም አስተሳሰብ ድምር ውጤት ነው። ስነ ልቦና ደግሞ የሰውን አስተሳሰብ የሚያጠና ሳይንስ ነው፤የሰውን ነፍስ የሚያጠና ዘርፍ ነው። ምክንያቱም psyche ነፍስ ማለት ነው። "We are not human beings with spiritual experience. We are spiritual beings with human experience."

እኛ ነፍስ ነን፤ስጋው ቅርፊት ነው። ስጋውን ቀርፋችሁ ብትጥሉት የምታገኙት ነፍስ ነው። ነፍስ አይቀረፍም። ስነ–ልቡና ይህንን ነፍስ ነው የሚያጠናው። ሌላው እውቀት ሁሉ በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣ ነው። ስነልቡና የእውቀት ሁሉ ቁንጮ ነው። የሰው ልጅ ስነልቦናን ከተረዳችሁ jackpot አሸነፋችሁ ማለት ነው።

ታዲያ ልብወለድ እዚህ ውስጥ ምን ጥልቅ አደረገው ሊባል ይችላል? ስነልቦናን በደረቁ ለመተንተን መሞከር አሰልቺ ሊሆን ይችላል። የተፈለገውን ሀሳብ በምሉእነት ለመግለፅ አቅም ያጥረዋል። ልብወለድ የሚመጣው እዚህ ጋር ነው። አያችሁ ልብወለድ የእውነተኛው አለም አነስተኛ ሞዴል ነው። ሁሉም ኢለመንቶች ሪፕረሰንት ይደረጋሉ። እውነተኛው አለም በአውሮፕላን ብንመስለው ልብወለድ ማንበብ የአውሮፕላን simulation ነው።

ልብወለድ ተራም ፣ ተረት ተረትም አይደለም። ምንአልባት ጥሩ ልብወለድ ካላገኛችሁ ጥሩ ሲሙሌተር አልገጠማችሁም ማለት ነው። ለስነልቦና ህይወት የሚሰጠው ልብወለድ ነው። የhuman conditionን ልንረዳ የምንችለው በስነፅሁፍ ነው―ከስነፅሁፍም በልብወለድ። ልብወለድን የሚያክል simulator እስከአሁን የለም። ታላቅ ስነፅሁፍ የልብወለድ እና የስነልቦና ጋብቻ ነው።

© Te Di


ልብወለዶች የፃፈውም ከቁማርተኝነቱ እና ከሚጥል በሽታው ጋር እየታገለ መሆኑን ስትረዳ ነው። አንድ ደራሲ መርጠህ ማንበብ ብቻ ካለብህ ዶስቶቭስኪን አንብብ። አንድ ልብወለድ ብቻ ማንበብ ካለብህ የካራማዞቭ ወንድማማቾችን አንብብ።

አንድ ሌላ ታላቅ ደራሲ ልጨምር። ደራሲው ብዙ መፃህፍት ቢኖሩትም ያነበብኩት አንዱን ብቻ ነው። ታዲያ ይህ ልብወለድ እጅግ የተዋጣለት በመሆኑ ደጋግሜ አንብቤዋለሁ። መፅሀፉ ወደ አማርኛ እንኳን በሶስት የተለያዩ ደራሲዎች ተተርጉሟል—ችግረኞቹ፣ መከረኞቹ፣ ምንዱባን። በሬዲዮ ተደጋግሞ ተተርኳል። ወደ ብዙ አለም አቀፍ ቋንቋዎች ከተተረጎሙ ድንቅ የፈረንሳይ የስነፅሁፍ ሃብቶች አንዱ ነው። በመድረክ፣ በፊልም ተደጋግሞ ተሰርቷል። ደራሲው ቪክቶር ሂዩጎ ይባላል። የመፅሀፉ የፈረንሳይኛ ርእስ Les Miserables ይባላል። ርእሱ ራሱ ዝነኛ ከመሆኑ የተነሳ ወደ እንግሊዝኛ ሲተረጎም እንኳን እንዳለ ነውንጂ በእንግሊዝኛ ተመጣጣኙ The Miserables ተብሎ አይተካም። በእርግጥ እንግሊዝኛ እና ፈረንሳይኛ ተቀራራቢ በመሆናቸው ብዙም ልዩነት የለውም። ለማንኛውም ይህ ልብወለድ ሁሉም ቁምነገረኛ አንባቢ ሊያነባቸው፣ ሊደጋግማቸው፣ ሊከልሳቸው ከሚገቡ ጥቂት ውድ የአለም ስነፅሁፍ ሃብቶች ዋነኛው ነው። እንደውም አንድ አንባቢ ሲያዳንቅ መከረኞቹን የፃፈው ቪክቶር ሂዩጎ አይደለም። እራሱ እግዚአብሔር ከሰማይ ወርዶ የፃፈው የሁላችንም የምድር ጎስቋሎች ታሪክ ነው። እኔም በተምሳሌታዊ አገላለፁ እስማማለሁ። ገፀባህሪያቱ በምናብ የተፈጠሩ ሳይሆን አጥንትና ደም፣ ስጋና ነፍስ ያላቸው ተአማኒ በሁለት እግራቸው የሚራመዱ ሰዎች ናቸው። ዣንቫልዣ፣ ፋንቲን፣ ኮዜት፣ ዣቪየር ሁሉም የእውኑ አለም ሰዎች መሳይ ናቸው። በጣም ተአማኒ ከመሆናቸው የተነሳ ከነገፅታቸው፣ ከነባህሪያቸው ከተነበቡ ከብዙ አመት በኋላ እንኳን ወለል ብለው ይታወሳሉ፤ አይረሱም። የደራሲው ብእር ሃያል ነው። ልብወለዱ የአለምን አስቀያሚነት፣ ፍትህ አልባነት፣ የሰዎችን ጨካኝነት እና ሩህሩህነት፣ የፍቅርን መጥፋት ብቻ በአጠቃላይ በእውኑ የምናውቃትን አለም ለዛ ባለው ብእራቸው እንዳለ ቁጭ አድርገዋታል። ይሄም ሁሉም አንባቢ ደጋግሞ ሊያነባቸው ከሚገቡ ግሩም መፃህፍት መሀል አንዱ ነው።

የመጨረሻ ምርቃቴ ደግሞ Gone With the Wind ነው። በእርግጥ የዚህ ልብወለድ የፊልም ቨርዥኑ ጆርጅ ፍሎይድ በዘረኛ ፖሊስ ከተገደለ በኋላ በግፊት ከኔትፍሊክስ ስትሪሚንግ ሰርቪስ በዘረኝነት ተወንጅሎ እንዲወርድ ሆኗል። በእርግጥ ልብወለዱ እዚህም እዚያም ዘረኛ ጭብጦች አሉት። ነገር ግን ሁለት ነገሮችን ግልፅ ማድረግ እፈልጋለሁ። በመጀመሪያ የልብወለዱ አብይ ጭብጥ ዘረኝነት አይደለም። ልብወለዱ ስለ ጦርነት አስከፊነት እና ስለ ጠንካራው የሰው ልጅ መንፈስ ነው። የትኛውም አንባቢ ከራሱ ህይወት ጋር በቀላሉ አቆራኝቶት ሊዝናናበት፣ ሊማርበት ይችላል። ሁለተኛው ጉዳይ አሁንም ቢሆን እጅግ የተማሩ ዘረኛ ሰዎች በመሀከላችን አሉ። ዘረኝነት ክፉ በሽታ ነው። ለማጥፋትም ረዥም ግዜ ይፈልጋል። ይህንን መፅሀፍ ማንበብ ስላቆምን ብቻ ዘረኝነት ከመሀከላችን ተጠራርጎ አይጠፋም። እንደዚያም ሆኖ መፅሀፉ የተጋነነ ዘረኝነት አለው ብዬ አላስብም። ደራሲዋ በመፅሀፏ ያንፀባረቀችው የነበረውን ዘረኝነት ነው። እንዲያውም በመፅሀፉ ውስጥ ዘረኛ እሳቤው ባይካተት ጎደሎ ይሆን ነበር። ሰዎች ፍፁም አይደሉም፤ እንከን አላቸው። ያንን እንከናቸውን እየገደፍን የምንፅፍ ከሆነ ደራሲ ሳይሆን ፕላስቲክ ሰርጅን እየሆንን ነው። ተአማኒ ነገር ለመፃፍ ሰዎችን ከነእንከናቸው፣ ከነብጉራቸው መሳል አለብን። በእርግጥ ደራሲዋ ያንፀባረቀችው የገፀባህሪያቱን ዘረኝነት ብቻ ሳይሆን የራሷንም ጭምር ነው። ታዲያ ይሄኮ ብዙ አይገርምም። ለዘመናት ባሮችን እየፈነገሉ ሲሸጡ የነበሩት የተማሩ አውሮጳውያን እና አሜሪካውያን ዘረኛ ነበሩ። ቅኝ ግዛትን ያስፋፉትም እንደዚሁ። ስድሰት ሚሊየን አይሁዳውያንን በመርዝ ጋዝ የፈጁት እጅግ የተማሩ ጀርመናዊያን ነበሩ። አሁንም በምሁር ካባ የተሸፈነ ዘረኝነት አለ። የነጮቹ መፅሀፍ ውስጥ ብናገኘውም ያን ያህል ሊደንቀን አይገባም። አሁንም በማስመሰል ፈገግታ የተሸፈነ ዘረኝነት ሞልቷል። መፅሀፍ ውስጥ ስናገኘው እንክርዳዱን ከስንዴው ማጣራቱ የአንባቢ ፋንታ ነው። ወደ መፅሀፉ ስንመለስ የደራሲዋን የትረካ ብቃት አለማድነቅ አይቻልም። መፅሀፉ ብዙ ንግግር(dialogue) የለውም። ደራሲዋ የመረጠችው አብዛኛውን ታሪክ በትረካ መንገር ነው። የትረካ ችሎታዋ የተዋጣለት በመሆኑ አንባቢ ሳይሰለች ብዙ ገፆችን በአንዴ ፉት ሊያደርግ ይችላል። ይህ መፅሀፍ ለመፃፍ አስር አመት ፈጅቷል። እንዲሁ ለመተርጎም አስር አመት ፈጅቷል። አስገራሚ ግጥምጥሞሽ! ይሄን ያህል አመት ፈጅቶ ባይበስል ነው የሚገርመው። ገፀባህሪያቱ እዚህም የማይረሱ ናቸው—እስካርሌት ኦሃራ፣ ሬት በትለር፣ አሽሌ ዊክስ፣ ሜላኒ ሃሚልተን። ልብወለዱ እንዲህ ይላል። ሬት በትለር እስካርሌት ኦሃራን አፈቀረ፣ እስካርሌት አሽሌ ዊክስን ፈቀደች፣ አሽሌ ሜላኒ ሃሚልተንን አገባ። የአራት ሰዎች የፍቅር ህይወት ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ሆነ። ይሄ መግቢያ ብቻውን ልብወለዱን ለማንበብ አጓጊ ያደርገዋል። ልብወለዱ ግን ከእስካርሌት እና ሬት ፍቅር የላቀ ነው፤ ከተራ የፍቅር ሰንሰለት የጠለቀ ነው። ልብወለዱ ስለ መራራ የህይወት ገፅታ ነው። ልብወለዱ ስለማይበገረው የሰው ልጅ መንፈስ ነው።

የሰርቫንቴስን ዶን ኪኾቴ ልብወለድ በማንበብ ይህን ያህል ስቄ አላውቅም!ዶን ኪኾቴ ከመጠን በላይ የጦረኛ ልብወለድ መጽሀፍትን ያነበበ የልብወለዱ ዋና ገጸባህሪ ነው። ጎረቤቶቹ ዶን ኪኾቴ ብዙ በማንበቡ አእምሮው ተነክቷል ብለው ያስባሉ። እሱ ግን ማንንም ከቁብ ሳይቆጥር አሮጌ ጥሩሩን ለብሶ ፣ ፈረሱን ሮሲናንቴ ተፈናጦ አሽከሩን ሳንቾ ፓንዛን አስከትሎ ፣ እመቤት ዱልሲናን በልቡ ይዞ ያነበባቸው መጽሀፍት ላይ እንዳሉት የማይታመኑ ገድሎች ለመፈጸም ይወጣል።

ስፔን እነሆ ከ400 አመት በኋላ እንኳን “ዶን ኪኾቴ”ን የሚተካከል የስነጽሁፍ ስራ የላትም።

ዶን ኪኾቴ ሁላችንንም ነው። ለራሳችን ያለንን የተጋነነ አመለከት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የከንቱ ምኞታችንን ስፋትና ጥልቀት ለፍላጎታችን ምርኮኛና እስረኛ መሆናችን ሁሉ ይከስትልናል። ይሄ ሁሉ በተለያየ መልኩ ይገለጻል። የእያንዳንዱ ወንድ የፍላጎት ማረፊያ የምትሆንም አንዲት ሴት አትጠፋም።

ሁሉም አንባቢ እነዚህን አራት ታላላቅ ልብወለዶች ደጋግሞ እንዲያነብ እጋብዛለሁ።

📚📚📚

ልብወለድ ማንበብ ግዜ ማባከን ነው የሚሉ ሰዎች አጋጥመውኛል። ልብወለድ ህልመኛ የሚያደርግ፣ ለተጨባጩ አለም ህይወት ምንም የማይጠቅም፣ ደራሲው በዘፈቀደ የፃፈው ተረት ተረት ነው ይላሉ።

በሌላ በኩል ጥናት እንዲህ ይላል

፩) በየአመቱ ከሚሸጡ እና የሚነበቡ መፅሀፍት 80% ልብወለዶች ናቸው

፪) ልብወለድን ማንበብ የራስንም የሌሎችን አመለካከት ለመረዳት ቁልፍ ነው። በአጭሩ ልብወለድ ስለ ሰው ነው። አብዛኛዎቹ ኢልብወለድ መፅሀፍት(ሁሉም አይደለም) ከሰው ውጪ ስላለ ነገር ነው። ታድያ እራስን ሳያውቁ በቢሊዮን የሚቆጠር የብርሃን አመት ላይ ስለሚገኝ አለም ለመረዳት መሞከር ከንቱ አይደለም!

፫) ልብወለድ በሚነበብበት ወቅት የአእምሮአችን ኤሌክትሮኬሚካል ስርአት ይቀየራል። ይህም በተጨባጩ አለም ለሚገጥመው ነገር ንቁ እና ቀልጣፋ ምላሽ ይሰጣል።


ልብወለድ የአዋቂዎች ተረት ተረት አይደለም።

ህፃናት ከንባብ ጋር የሚተዋወቁት በተረት መፃህፍት ነው። የተረት መፅሀፍት ታሪክ ነጋሪዎች ናቸው። ለጋ ወጣቶችም በብዛት የሚያነቡት ልብወለድ መፃህፍትን ነው—በተለይ genre fiction የምንላቸውን። ልብወለዶች በተለምዶ በሁለት ይከፈላሉ—genre fiction እና literary fiction ተብለው።

በአማርኛ እቅጩን የሚገልጽ ትርጉም የላቸውም። በቀላሉ ለመግለፅ ያህል ዠነር ፊክሽን ከገፀባህሪ ይልቅ ለሴራ ቦታ የሚሰጡ፣ ስነፅሁፋዊ ፋይዳቸው እምብዛም የሆነ፣ አስፈሪ፣ የፍቅር፣ የስለላ፣ ልብ አንጠልጣይ ወዘተ እየተባሉ የሚከፋፈሉ ናቸው። ሊተራሪ ፊክሽን ደግሞ ስነፅሁፋዊ እሴታቸው እጅግ የላቀ፣ የቋንቋ ውበታቸው የረቀቀ፣ ከሴራ ይልቅ ለገፀባህሪ አትኩሮት የሚሰጡ ናቸው። እውነተኛ ልብወለድ የሰው ልጅ ነፍስ ጥናት ነው። ከሰው ልጅ ነፍስ የበለጠ ርእስ ደግሞ የለም። ታዲያ በሳል አንባቢዎች ለምን የልብወለድ ንባብን ገሸሽ አድርገው በኢልብወለድ ንባብ ይጠመዳሉ? ለምንድነው ልብወለድ ያልበሰሉ ለጋ አንባቢዎች ምርጫ ሆኖ የቀረው?

ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ቀላል አይደለም። ቢሆንም ልብወለድን ልብ የወለደው፣ ተራ ቅዠት አድርጎ የመመልከት አባዜ አለ። በመጀመሪያ የትኛውም የልብወለድ ደራሲ መቶ በመቶ የፈጠራ ታሪክ ሊፅፍ አይችልም። የልብወለዱን ገፀባህርያት የሚስለው ከራሱ፣ በአካባቢው ካሉ ሰዎች፣ በአጠቃላይ በእውኑ አለም ከሚያውቃቸው ሰብጀክቶች ነው። ታሪኩንም ቢሆን በዙሪያው ከሚያየው፣ ከሚሰማው፣ ከሚከናወነው ተነስቶ ነው። ታላቅ ደራሲን ከሌሎቻችን የሚለየው የምናውቀውን አሮጌ ነገር እና ታሪክ በለዛ አጅቦ፣ በቋንቋ አስውቦ ስለሚያቀርብ ነው። እውነተኛ ባለ ተሰጥኦ ደራሲ የተለመደውን አዲስ፣ አዲሱን ደግሞ የተለመደ የማድረግ ረቂቅ ችሎታ ያለው ከያኒ ነው። ከዚህም ባሻገር አስተዋይ አይን፣ ረቂቅ ምናብ የታደለ ነው። የምናውቀውን እውነት አድሶ ሲነግረን አፋችንን በአድናቆት ከፍተን እንሰማዋለን።

ታሪክ ነገራ ከሁሉም የስነፅሁፍ አይነቶች ለሰው ልጅ መንፈስ ቅርብ ነው። አንባቢም ደረቅ እውነት በብዛት ማንበብ ይቸከዋል። የልብወለድ ንባብ አስደሳችና መልእክቱም ከአንባቢ መንፈስ ጋር ለረዥም ግዜ ተጣብቆ የሚቀር ነው። ችግሩ ያለው አሳማኝ፣ ተነባቢ፣ ከራሳችን ህይወት ጋር በቀላሉ ልናቆራኘው እና ልናዛምደው የምንችለው የልብወለድ ታሪክ መፅሀፍ ለመፃፍ ቀላል አይደለም። ታላቅ ችሎታ ይጠይቃል። እጅግ የተዋጣላቸው የልብወለድ ታሪክ ፀሀፊዎች ጥቂት ናቸው። ለአብነት ዶስቶቭስኪን፣ ሂዩጎን፣ ዲክንስን፣ ቶልስቶይን መጥቀስ ይቻላል። እነዚህ ደራሲዎች የሰውን ነፍስ ገላልጠው ራቁቱን የማየት የረቀቀ ብቃት አላቸው። ያዩትን በለዛ እና በተዋበ ቋንቋ የመግለፅ ተሰጥኦ አላቸው። የሚፈጥሯቸው ገፀባህርያት ከተአማኒነታቸው የተነሳ ከመፅሀፍ ገፅ አምልጠው በመካከላችን የሚኖሩ ያህል እንዲሰማን የሚያደርጉ ናቸው። የልብወለዶቻቸው ሴራ ሽንቁር የለውም። የተወለዱትም ከተራ ቅዠት ሳይሆን ከታላቅ መንፈስ ነው። ትጉህ አንባቢ እንደዚህ አይነት ጥበብ የጠገቡ ልብወለዶችን መርጦ ቢያነብ በቀላሉ ከልብወለዶች ጋር በፍቅር ይወድቃል።

ስታትስቲክስ እንደሚያሳየው በየአመቱ ከሚታተሙት ሁሉም መፃህፍት መካከል 80% ልብወለዶች ናቸው። ይሁን እንጂ ከነዚህ መሀል አብዛኛዎቹ ዠነር ፊክሽን ናቸው። ስነፅሁፋዊ ውበት የተላበሱ ቁምነገረኛ ሊትራሪ ልብወለዶች በቁጥር ጥቂት ናቸው። እነዚህ ልብወለዶች ለገበያ አያመቹም። ከፍተኛ የሽያጭ ሪከርድ አያስመዘግቡም። እሴታቸው ትልቅ ተፈላጊነታቸው ትንሽ ነው። ገበያው በእርካሽ ዠነር ፊክሽን ስለተጥለቀለቀ በሳል አንባቢዎች ፊታቸውን ወደ ኢልብወለድ አዙረዋል። ነገር ግን እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ከሰው ልጅ ነፍስ የበለጠ፣ የረቀቀ ርእስ የለም። የታላላቅ ልብወለዶች ዋነኛ ርእስም የሰው ልጅ ነፍስ፣ የሰው ልጅ ስነልቦና ነው። አዋቂ አንባቢዎች ይህንን ታላቅ ርእስ ገሸሽ አድርገው የኢልብወለድ ንባብ ላይ ተጠምደዋል። የታላቁን ፍጡር የሰው ልጅ ነፍስ ችላ ብለው የሰው ልጅ መገልገያ የሆኑ ተራ ቁሶች ላይ አተኩረዋል።

የሰው ልጅ በሳይንስ እጅግ ተራቅቆ አተምን ሰንጥቋል፤ በስነህይወት የሴልን ፍጥረት መርምሯል፣ የዲኤንኤን ሚስጥር ደርሶበታል፤ ወደ ጨረቃ ተጉዟል፤ ኒውክለር ቦምብ ሰርቷል። በጀኔቲክ ኢንጂነሪንግ፣ በሮኬት ሳይንስ፣ በናኖቴክኖሎጂ ተመንጥቋል። ይሁን እንጂ ከሁሉም የረቀቀ የእውቀት ክፍል ከነዚህ አንዱም አይደለም። ከሁሉም የጠለቀ፣ የረቀቀ፣ የገዘፈ ርእስ የሰው ልጅ ስነልቦና ነው። ስነልቦና የሰውን ነፍስ የሚያጠና ሳይንስ ነው(በግሪክ psyche ማለት ነፍስ ሲሆን psychology የነፍስ ጥናት ነው)

ሳይንስ እስከ አሁን ስለ ሰው ልጅ ስነልቦና የሚያውቀው እፍኝም አይሞላ። ቸር እንኳን እንሁንለት ቢባል የሳይንስ እውቀት ከ10% አያልፍም። ስነልቦና እጅግ የተወሳሰበ ሳይንስ ነው። በተጨማሪ ደረቅ የስነልቦና ኢልብወለድ መፃህፍት ይህንኑ እውነት በአግባቡ መግለፅ አይችሉም። ሊተራሪ ፊክሽን የሚመጡት እዚህ ጋር ነው። ከኢልብወለድ የስነልቦና መፃህፍት ይልቅ ሊተራሪ ፊክሽን የሰውን ልጅ ስነልቦና በመግለፅ የተዋጣላቸው ናቸው።

በምሳሌ ላስረዳ። ግባችን በውቅያኖስ ውስጥ መዋኘት ነው ብለን እንነሳ። ኢልብወለድ የስነልቦና መፃህፍት በዚህ ተምሳሌት ውስጥ የዋና መመሪያ(swimming manual) ናቸው። የፈለግነውን ያህል የዋና መመሪያ መፃህፍት ብናነብ ዋናተኛ መሆን አንችልም። ለመዋኘት ምን ማድረግ እንዳለብን እናውቃለን። ግን ድንገት ውሃ ውስጥ ተነስተን ብንገባ በተአምር ካልሆነ መዋኘት አንችልም። ሊተራሪ ፊክሽን የሚመጡት እዚህ ጋር ነው። ልብወለዶች ልክ እንደ ሲሙሌሽን ናቸው። ምናባዊ አለም አላቸው፤ ገፀባህርያት እና መቼት አላቸው፤ ታሪክ አላቸው። ራሳቸውን የቻሉ ሚጢጢ ህይወት ናቸው። እዚህ ውስጥ ገብቶ ዋና መለማመድ ይቻላል። እንደ ውቅያኖሱ ሰፊ እና ጥልቅ ባይሆኑም መዋኘት ለሚፈልግ በቂ ናቸው። ስነፅሁፋዊ ልብወለዶች 100% እውነተኛውን አለም ባይሆኑም በሰው ልጅ ነፍስ ዙሪያ ለመዋኘት በቂ ናቸው። የሰውን ልጅ ስነልቡና ለመረዳት ያስችላሉ። በዚህ ስሌት የዶስቶቭስኪ ልብወለዶች እያንዳንዳቸው 100 ደረቅ የስነልቡና መፃህፍትን ከማንበብ ይልቃሉ። የሰውን ነፍስ ራቁቷን ተገላልጣ ሲያሳያችሁ አጀብ ያስብላል። በነገራችን ላይ ታላቁ የስነልቦና ጠበብት እና የሳይኮአናሊሲስ ፈጣሪ ሲግመን ፍሪይድ የዶስቶቭስኪ ግርፍ ነው። ፍሩይድ ዶስቶቭስኪን አንብቦ ነው ስለ ነፍስ የተረዳው። ፅንሰሃሳቦቹንም ያፈለቀው ከዚያ ወዲህ ነው። ይህ ያልተለመደ ነገር ነው። በስነፅሁፍ፣ ስነልቦና እና ፍልስፍና አለም የተለመደው ፈላስፋው ወይም ሳይኮሎጂስቱ ቀድሞ ነው የሚወለደው። ከዚያ ደራሲው ፍልስፍናውን ያነብና ከማረከው ፍልስፍናውን በሚፅፈው ልብወለድ ውስጥ ያንፀባርቃል። በፍሩይድ እና በዶስቶቭስኪ ግን የሆነው የተገላቢጦሽ ነው። ቀድሞ ደራሲው ተወለደ። ሳይኮሎጂስቱ ልብወለዶቹን አነበበ። በልብወለዱ ሃሳብ ተነሳስቶ አነጋጋሪ ፅንሰሃሳቦቹን አረቀቀ። ታዲያ ዶስቶቭስኪን አታደንቀውም?! ወንጀልና ቅጣት፣ የካራማዞቭ ወንድማማቾች፣ የስርቻው ስር መጣጥፍ፣ ቁማርተኛው፣ ብርሃናማው ሌሊት፣ ድሃ ሰዎች፣ ዘ ኢዲየት፣ ዘ ፖሰስድ ሁሉም ድንቅ የዶስቶቭስኪ ልብወለዶች ናቸው። ደራሲውን ጨምረህ የምታደንቀው ደራሲው ከሞት ፍርድ ያመለጠ፣ ወደ ሳይቤሪያ ለአምስት አመት ተግዞ ከባድ የቅጣት ስራ የሰራ፣ እነዚያን ውብ

Показано 20 последних публикаций.