🌠 ረመዳንና ቁርኣንን በማስተንተን
አብዝቶ ማንንበብ!💐 ይህ ረመዳን የቁርኣን ወር ነው!
👉 አማኝ ለሆነ ሰው ይህን "ቁርኣን" በማንበብ ላይ ሊያበዛ ይገባል ! በሁሉም (ፊደላት) ምንዳ ያለው ሲሆን እስከ አስር (እጥፍ) ይደረግለታል።
👉 ይህንንም ሲያረግ ልክ አላህ እንዳለው ከማስተንተንና ከማገናዘብ ጋር ነው።
( كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ )
« (ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡»
አል-ሷድ 29
( إِنَّ هَٰذَا الْقُرْآنَ يَهْدِي لِلَّتِي هِيَ أَقْوَمُ وَيُبَشِّرُ الْمُؤْمِنِينَ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ الصَّالِحَاتِ أَنَّ لَهُمْ أَجْرًا كَبِيرًا )
( ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ ኾነችው መንገድ ይመራል፡፡ እነዚያንም በጎ የሚሠሩትን ምእመናን ለእነሱ ታላቅ ምንዳ ያላቸው መኾኑን ያበስራል፡፡)
አል-ኢስራህ 9
( وَهَٰذَا كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ مُبَارَكٌ فَاتَّبِعُوهُ وَاتَّقُوا لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ )
( ይህም ያወረድነው የኾነ የተባረከ መጽሐፍ ነው፡፡ ተከተሉትም፡፡ ይታዘንላችሁም ዘንድ (ከክህደት) ተጠንቀቁ፡፡)
( አል-አንዓም 155)
💐 (እንግዲህ) ይህ ሁሉ የሚሆነው በቁርኣን በማስተንተንና አብዝቶ በማንበብ ነው !!!
(ታላቁ ኢማም ኢብን ባዝ)
🔗
t.me/Al_Furqan_Islamic_Studio✍️ ትርጉም በኢስማኤል ወርቁ
🔗
t.me/Al_furqan_fetwa_chanal