© ከ Atiqa Ahmed Ali Facebook የተወሰድ
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!
"ኧረ ያንቺስ የጉድ ነው!"አለ በደፈናው አንዱ አፍቃሪ ለወደዳት ሴት፥ሁሌ እያስደነቀችው የሚላት ቢጠፋው!እኔ ደግም ነብዬን ነው ኧረ ያንቱስ የጉድ ነው!የምለው፤ሁልጊዜ ይገርሙኛል እያደር ይደንቁኛልና!
አቡ ጀህል በእስልምና እና ሙስሊሞች ላይ ጦርነት ያወጀ፣በአንድ አላህ ስላመኑ ብቻ ብዙዎችን ያሰቃዬ፣ረሱሉላህን ለመግደል ብዙ ሴራ ያቀነባበረ፣ብዙ ግፍ የሰራና እስከ መጨረሻውም የተዋጋቸው ሰው ነው።ልጁ ኢክሪማህ ከአባቱም ጋር ሆኖ ከአባቱ ህልፈት በኋላም ከሙስሊሞች ተቃራኒ ተሰልፎ ተዋግቷል።ታድያ ያ ሁሉ አለፈና ሙስሊሞች ድል ካደረጉና መካን ከከፈቱ በኋላ ረሱልን ሰ.ዓ.ወ ሊያገኝ ሄደ።ውዱ ነብዬም ኢክሪማህ መምጣቱንና እሳቸውንም ሊያገኝ እንደሚፈልግ ሲሰሙ ለባልደረቦቻቸው ግሳጼ ለመንገር ወደነርሱ አመሩ።
ጉዳዩ እንዲህ ነበር..
የኢክሪማህ አባት አቡ ጀህል ትክክለኛ ስሙ አምር ቢን ሂሻም የነበረ ሲሆን በደህናው ጊዜ ሁሉም"አቡል ሃኪም"ብለው ነበር የሚጠሩት የጥበበኞች አባት እያሉ!የህዝቡ መሪ ነበርና።ኋላ ላይ ግን በድንቁርናውና አማኞች ላይ እያሳዬ በነበረው ያልተገባ ባህርይ አቡ ጀህል አሉት የድንቁርና አባት!ወንድምዬ ምግባርህ ያለህን ነጥቆ መከበሪያ ስምህንም መታወቂያህንም ይቀይረዋል!ሸቂይ ሆኖ ሰዒድ መባል የለም አለዚያ አብሺቁም አሺቅ ነህ ጃሂሉም ዓሊም ነህ መባልን ወደደ እንዳሉት ነው የሚሆነው!
ታድያ ውዱ ነብይ ባልደረቦቻቸውን ሰብስበው ምን አሏቸው መሰለህ"ኢክሪማህ እየመጣ ነው፣እስልምናን ይቀበላል ብዬም አስባለሁ እርሱ ፊት ማንም ሰው አባቱን ‘አቡ ጀህል’ በሚለው ስያሜ እንዳይጠራ ስሜቱ ይጎዳልና! ምንም እንኳን ቢሰልምና አባቱ ስህተት ላይ እንደነበረ ቢያምንም፣ጥፋቱ ቢገባውም ያው ዞሮ ዞሮ አባቱ ነውና የእምነት ወንድምና እህቶቹ አባቱን በዛ ስም ሲጠሩ መስማቱ ያስከፋዋል ስለዚህ ማናችሁም ከዚህ ድርጊት ተቆጠቡ!" አሉ።ራሳቸውን በኢክሪማህ ቦታ አስቀምጠው ህመሙን ታመሙ፣ስሜቱን ተረድተው ጥበቃ ቆሙለት ጠላታቸው ለነበረ የጠላታቸው ልጅ!እንዴት አይነት ስልጡንነት፣እንዴት ያለ የስነ ልቦና አዋቂነት፣እንዴት ያል ይቅር ባይነት ነው?!
እንዴት ያለ ነብይ!ሰይዲ..!ኧረ ያንቱስ የጉድ ነው!በስማቸው እንለምነዋለን ፈረጃው እንዲቀርብ፣ሶለዋት እንላለን ያመመው ሁላ እንዲሽር፣ያሲንን እንደጋግማለን ኢንሱ ሁላ ጭንቁ እንዲለቀው፣ፋቲሃ እንላለን ዑዝሩ ሁላ እንዲነሳ፣ደግሞም ተባረክ ስንል በረካው እንዲመጣ ዛሬም እንሃድራለን አብሽሩማ!!
#ሶሉ_ዓለል_ሃቢብ
አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዱና ሙሀመድ!💚💚💚
{ @ETHIO_NESHIDA }