በአለማችን ላይ ያሉ አደገኛና አስፈሪ የሆኑ እስርቤቶች!
ሳን ፔድሮ እስርቤት
ስለ እስርቤት ስናስብ በውስጡ ታሳሪዎችንና ጠባቂ ፖሊሶችን ማሰባችን አይቀርም።
በሳን ፔድሮ ግን ፖሊሶች የሚጠብቁት እስረኞችን ሳይሆን እስርቤቱን ነው፤ ለዚያውም ከእስርቤቱ ግቢ ውጪ ሆነው ነው። እስርቤቱ የሚመራውም በራሳቸው በታሳሪዎቹ ነው።
ይሄ በደቡብ አሜሪካ በቦሊቪያ ዋና ከተማ እጅግ ግዙፍ የሆነው እስርቤት የተገነባው እ.ኤ.አ በ1895 ነው።
ታዲያ ይሄ እስርቤት በመጀመሪያ ሲገነባ 500 ታሳሪዎችን ለመያዝ ታስቦ ቢሆንም አሁን ላይ ግን 3000 እስረኞችን በውስጡ ይዟል። ታዲያ በሳን ፔድሮ ያሉ እስረኞች ህይወታቸውን የሚያቆዩት በእስርቤቱ ውስጥ በሚሰሯቸው ስራዎች ነው። ከነዚህም ስራዎች መሃል አንዱ የራሳቸውን ማደሪያ አዲስ ለሚገባ እስረኛ በማከራየት ገንዘብ ማግኘት ነው። በዚህም መንገድ አንዳንድ እስረኞች ከቤተሰባቸው ጋር በእስርቤቱ ውስጥ ለመኖር ስለሚፈልጉ የተጠየቁትን ገንዘብ በመክፈል የሚፈለጉትን የቤተሰብ አባል አስገብተው ይኖራሉ።
በሳን ፔድሮ እስርቤት ተራ ከተባሉ እስረኞች ጀመሮ እስከ አደገኛ የሆኑ ባለስልጣናትና ከበርቴዎች ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት አንዳንድ የእስርቤቱ ክፍሎች ግዙፍና አስፈሪ በሆኑ እስረኞች የሚጠበቁ ሲሆኑ በአንዳንድ ክፍሎችም
የራሳቸው ቴሌቪዥን አላቸው።
ታዲያ ይሄ በሀይል፣ በማስፈራሪያና ጭካኔ በተሞሉባቸው ስቃዮች የሚተዳደረው እስርቤት የሚመራው ከዛው ከታሳሪዎች መሃል በተመረጡ አስተዳዳሪዎችና ገዢዎች ነው።