Репост из: ከደራሲያን እልፍኝ
❤ለመልካም ቀናችን!!
#አንድ ሠው ሶቅራጠስ ወዳረፈበት እልፍኝ ሄዶ እንዲህ አለው፡፡
‹‹ሶቅራጠስ ወዳጄ፣ እገሌ ስለተባለው ወዳጅህ ዛሬ የሠማሁት ነገር ምንም ደስ አይልም›› አለው፡፡
ሶቅራጦስ መከዳው ላይ እንደተደገፈ መልስ ሳይሰጠው ዝም አለ፡፡
ሠውዬውም እንደገና ‹‹ይገርማል ከእርሱ አይጠበቅም፤ በጣም ገርሞኛል›› ሲል ተናገረ፡፡
ሶቅራጦስ፣ ይህ ሠው በቀላሉ እንደማይፋታው ስለተረዳ አንድ መደራደሪያ አቀረበለት፡፡
‹‹ስለ ወዳጄ ልትነግረኝ የፈለከውን እንድሠማህ ከፈለግህ ሶስት ጥያቄዎች አሉኝ፤ እነርሱን በቅድሚያ ልትመልስልኝ ይገባል! ይህ ሲሆን ብቻ ነው የምሰማህ›› አለው፡፡
ሠውዬው ለወሬው ቢቸኩልም አማራጭ ስላልነበረው በሶቅራጠስ ሀሳብ ተስማማ፡፡
‹‹የመጀመሪያው ጥያቄዬ የእውነት ጥያቄ ነው" አለ ሶቅራጠስ።
"ስለወዳጄ የሠማኸው መቶ በመቶ እውነት ነው ወይ?›› ሲል ጠየቀ፡፡
ሠውዬውም፡- ‹‹መቶ በመቶ እንኳን እርግጠኛ መሆን አልችልም›› ሲል እያመነታ መለሰለት፡፡
‹‹በጣም ጥሩ! ልትነግረኝ የፈለግከው እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው ማለት ነው፡፡ እሺ ሁለተኛው ጥያቄዬ የመልካምነት ነው፡፡ የምትነግረኝ መልካም ነገር ነው ወይ?›› ሲል ሶቅራጠስ አቀረበ ጥያቄውን፡፡
ሠውዬውም፡- ‹‹እርሱማ መልካም አይደለም›› አለ ቱግ ብሎ፡፡
የሶቅራጠስ ጥያቄዎች ለማውራት የቋመጠለትን ወሬ እንዳያወራ እንቅፋት መስለው ታዩት።
ሶቅራጦስም ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠና መልካም ያልሆነ ነገር ልትነግረኝ ፈልገሃል፡፡ እሺ ሶስተኛውና የመጨረሻው ጥያቄዬን ልጠይቅህ?›› አለው፡፡
ሠውዬውም ጥያቄውን ለመስማት ፈጥኖ ‹‹እሺ›› አለ፡፡
ሶቅራጦስ ጠየቀ፤ ‹‹የምትነግረኝ ነገር ለእኔ የሚጠቅመኝ ነገር አለው ወይ?››
‹‹የለም! የለም! መጥቀም እንኳን አይጠቅምህም። ብቻ ብትሰማኝ...›› ብሎ ሰውዬው መቅለስለስ ጀመረ።
ይሄን ጊዜ ሶቅራጦስ ‹‹ታዲያ እንደምን አድርጌ እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ መልካም ያልሆነ እና ለእኔ ምንም ጥቅም የሌለው ነገር ልንገርህ ስትለኝ እንዴት እሰማሃለሁ። ዞር በል ካጠገቤ አልሰማህም!!›› አለው ይባላል፡፡
ስንቶቻችን ነን ሰው የሚነግረን ነገር እውነት፣ መልካምና ጠቃሚ መሆኑን አጣርተን የምንሰማው?
ስንቶቻችን ነን ለሰው ቁምነገር ብለን ልንናገር ስንል ከሶስቱ አንዱን ማሟላቱን የምናረጋገጠው?
አሁን እኮ ሰው ዝም ብሎ የተነገረውን ስለሚሰማ በቀላሉ እንደ እንስሳ የሚነዳ ሆኗል፡፡ በየሶሻል ሚዲያው ላይ ፖስት የሚደረጉት ብዙዎቹ መረጃዎች እውነት ያልሆኑ፣ መልካምነት የሌላቸው እና ለእኛ ምንም ጥቅም የማይሰጡ ናቸው፡፡ በተቃራኒው የውሸት መረጃዎች ሆነው ስንቱን ያጭበረበሩ፣ ሰይጣናዊ ርምጃ ለመውሰድ የሚገፋፉ ሆነው ሳለ ያለማቅማማት እንሰማቸዋለን፡፡
አሁን አሁን እውነት ከሚናገሩት ሰዎች በላይ በመርዝ የተለወሰ ውሸት የሚናገሩ ሰዎች የተሻለ ብዙ ተከታይ አላቸው፡፡ መልካም መልካሙን ከሚሰብኩ ሰዎች ይልቅ የጥፋት ሰባኪዎች ብዙ ደጋፊ አላቸው፡፡ የጀገኑት ፍለጠው/ቁረጠው ባዮች ናቸው፡፡
እነሱን ማስቆም አይቻል ይሆናል፤ ነገር ግን እነሱን አለመስማት/አለመከተል ቀላል ነው፡፡ እነዚህን የሶቅራጠስ 3ቱ ጥያቄዎችን እንደ ወንፊት ተጠቅመን ማጣራት ብቻ በቂ ነው፡፡
‹ፅሁፉን› እውነት፣ መልካም እና ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት #Like #Share አድርጉት፡፡
✍ መሳፍንት ተፈራ
##LIKE👍👍እና
ለምትወዱት 20 ሰው ሼር አርጉት‼📗📒📕📗📒📕
📚
┄┉┉✽»🎶••✿••🎶»✽┉┉┄ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆንን እናመሰግናለን 🙏
ለሃሳብ እንዲሁም ለማንኛውም አስተያየት
@kederasiyanBot ላይ ያስፍሩልን
ቻናሉን ለመቀላቀል
Join us 👇👇👇
https://t.me/kederasiyan.