(የተሰዋ - ይዌድስዋ)
ኤልያስ ሽታኹን
- - - - - -
ሰውነቱ ወልቋል።
ተንበረከከ አጥንቱ ከወለሉ ሲጋጭ ይሰማል።
የሚናገረው ነገር ጠፋበት።
ልጅነቱ ትዝ አለው። በጣም ጎበዝ ተናጋሪ ነበር። ዛሬ አፉን የፈታበት ቋንቋው ጠፋው።
ፀጉሩን እየጠቀለለ
"ብሬን ስጨርስ መጣሁ" አላት
ዝም አለችው።
"ደስታዬን ስጨርስ መጣሁ" አላት
ዝም።
"መልኬ ሲረገፍ መጣሁ
ጉልበቴን ስጨርስ መጣሁ
ጤናዬን ስጨርስ መጣሁ"
ብሎ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ!
ዝም አለችው።
ከውስጡ አንድ ድምጽ ሰማ
"እድሜህን ሳትጨርስ መምጣትህ ነው ደስታዬ" አለችው።
ጭራሽ ከፋው።
ዝም ብላ አየችው።
ዝም ብሎ አያት።
ሳቀ።
የልጅነቱ የአብነት ተማሪ እያለ የነበረው ስም ትዝ አለው። "ቄሴ"
እየሳቀ አለቀሰ።
የማይቆረጠው ፀጉሩ ትከሻውን ነክቶታል።
በፊት ተዓምረ ማርያም ሲነበብ ነበር ጃንጥላ የሚይዝበት እጁ አሁን
በሲጋራ የሚይዝበት ጠቁሯል።
ሱሪውን ዝቅ አርጎት ሊወልቅ ደርሷል።
ለሎቲ የተበሳው ጆሮው ተደፍኗል።
ቅዱስ ዳዊት ከጠላቶቼ የተነሳ አረጀሁ እንዳለ
ገና በወጣትነቱ አርጅቷል።
ፊቱ ላይ አጥንት አለ።
ራሱን አየው።
አፈረበት በራሱ።
ጥግ ላይ የተቀመጡት ሽማግሌ ጋ አይኑ ተጋጨ። በግንባራቸው ጠሩት።...
"ጉዴ ነው" አለ በውስጡ።
"አቤት አባቴ... እንኳን መጣህላት"
"ለማን"
"ለማርያም"
"ሰምተውኝ ነበር ማለት ነው አለ" ለራሱ
"ምን ዋጋ አለው ብለው ነው...አሁንማ ከረፈደ"
"እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ፍቅሩ ለምን እንደማይቀንስ ታውቃለህ ?"
ዝም አላቸው።
"በፀጋ ስለሚያየን።
በዛሬ ማንነታችን ሳይሆን በፈጠረን ፀጋ ነው የሚያየን። በልጀነት ንጽህናችን በበፊቱ ቀናነታችን በትንንሹ አግልግሎታችን ነው የሚያየው። አይኑ እስከዛሬ ከፀጋችን ተነስቶ አያውቅም።"
ልቡንም ጆሮውንም ሰጣቸው።
"በኛ ተስፋ የማይቆርጠው የልጅነት ፀጋችንን ስለሚያውቅ ነው። ሌብነትህን ሳይሆን ልጅ ሆነህ የዘመርከውን ዘማዊነትህን ሳይሆን ድሮ ፀበል የቀዳኸውን ገዳይነትህን ሳይሆን ቤተመቅደስ መጥረግህን ነው የሚያየው። እግዚአብሔር ሰውን የሚያየው በፀጋው ነው።"
"እኔ ምን አለኝና ታዲያ ?"
ካንተ በላይ ያውቅሀል።
በፀጋህ ነው የሚያይህ ባሁኑ ኃጢያትህ አይደለም። እናት ልጇ ቢታሰር አትክደውም ልጅነቱን አስታውሳ ታዝናለች። ድሮኮ ተምሮ እንደዚህ ይሆንልኛል ብዬ ነበር የማስበው ብላ ልጅነቱን ነው የምታስታውስለት። አየህ እግዚአብሔር ልጅነታችን ጋ ነው አይኑም ልቡም።
ዕንባው ወረደ።
"ልጠይቅህ" አሉት
"ገብርኤል ማርያምን ከሰላምታ በፊት ምንድነው ያላት"
ይዌድስዋ ትዝ አለው።
"ፀጋን የሞላብሽ ሰላምታ ይገባሻል"
"ጎበዝ
ማርያምም ፀጋን የሞላባት መንፈስ ቅዱስ ያደረባት ናት። ሁሉንም የምታየው በፀጋ ነው። እንኳን አንተን ለሚቃወሟት ሳይቀር ሩህሩህ ናት። ለምን በልጅነት ፀጋቸው ነው የምታውቃቸው። ክፋት አታውቅም ቂም አታውቅም ለምን ፀጋን የሞላባት ናት።"
ጉልበታቸው ስር ወደቀ።
እጣን እጣን ሸተተው።
(ተፈጸመ)