👉🏽 ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው በተክሊል ማግባት ይችላልን?
በወጣትነት ወራት ስለ አባል ዘር ሥራና ውጤት ለማወቅ ካለ ጉጉትና ለተቃራኒ ፆታ የሚኖር ዝንባሌ ከመጨመሩ የተነሣ ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች የመራብያ አካላቸውን በመነካካት ጾታዊ ስሜት እንዲሰማቸውና የስሜት እርካታ እንዲያገኙ ሆን ተብሎ የሚፈጸም ተግባር ሴጋ ወይም ማስተርቤሽን በመባል ይታወቃል።
የዚህ ጽሁፍ አላማ ስለ ግለ ወሲብ በዝርዝር ማብራራት ሳይሆን ማስተርቤሽን የተባለውን የዝሙት ኃጢአት የፈጸመ ሰው ተክሊል መፈጸም ይችላል ወይስ አይችልም የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ነው ተወዳጆች ሆይ እያወራን ያለነው ከወንድ ጋር በአካል ዝሙት ፈጽማ የማታውቅ ነገር ግን የዝሙትን ጣዕም ለማጣጣም ራሷን በራሷ ለማርካት ማስተርቤሽን ስለፈጸመች ሴት ወይም የዝሙትን ጣዕም ለማጣጣም ራሱን በራሱ ለማርካት ማስተርቤሽን ስለፈጸመ ወንድ ነው።
እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ከተቃራኒ ጾታ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ሳያደርጉ ለእንደዚህ አይነት የዝሙት ተግባር በመጋለጣቸው ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ ከወንዱ ጋር በምንጣፍ አንድ አልሆንኩም ነገር ግን ማስተርቤሽን ፈጽሜለሁኝ ድንግል ልባል እችላለሁ?
እና ለድንግላን የሚፈጸመውን ሥርዓተ ተክሊልስ ለእኔ ሊፈጸምልኝ ይችላልን?
የሚለው ዋነኛ ጥያቄ ነው።
ማስተርቤሽን ሲፈጽም የኖረም ሰው ኃጢአቱን አምኖ ሲመለስ ድንግል ልባል የድንግልና ሥርዓትም ሊፈጸምልኝ አይገባም በሚል በተሰበረ መንፈስ ነው እንጂ በይገባኛል የሚል የትዕቢት ሐሳበ በልቡ የያዘ መንፈሳዊ ኪሳራ ውስጥ መሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነው።
የሚል ጥያቄ በአእምሯቸው የሚፈጠረው ፍቅር እግዚአብሔር ሲጎድልብንና ራስ ወዳድ ስንሆን ነው።
ምክንያቱም ማስተርቤሽን ቪድዮ ሴክስ ፎን ሴክስ የመሰለ ብዙ ኅቡረ ዝሙት እየፈጸምን ያሳስበን በደልነቱ ሳይሆን ተክሊል መፈጸም አለመፈጸም መሆኑ ነው።
እንዲህ አይነት አስተሳሰብ "የቤተ ፈት" አስተሳሰብ ይባላል።
ቤተ ፈት የምትባለው ባል አግብታ እየኖረች ከጊዜ በኋላ ባሏን ፈታ የኮበለለች ሴት ናት።
ከሄደችም ችግር ሲያጋጥማት የሚታያት ባሏን መበደሏ ሳይሆን ከባሏ ጋር በምትኖርበት ጊዜ የነበራት ምቾት እና ክብር ነው።
አባታችን አዳምን ግን የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም ማለትም ኃጢአት ሰርቶ ከገነት በተባረሩ ጊዜ ፈጣሪዬን አስቀየምኩት ስለ በደሉ ያለቅስ ነበር።
እንደዚህ ሁሉ ሰው በልዩ ልዩ የዝሙት ኃጢአት በተሰነካከለ ጊዜ "ድንግል ነኝን?"
"ተክሊል ይገባኛል?" እያለ ያወጣውና ያገኘውን እያሰበ ከመተከዝ" አንተን ብቻ በድልሁ በፊትህም ክፋትን አደረኩ መዝ 51፥4
ተወዳጆች ሆይ ከድፍረት የሚገኝ ምንም አይነት መንፈሳዊ በረከት የለም። ድፍረት መንፈሳዊ ኪሳራን ለዚህ ነው ቅዱስ ዳዊት እንደዚህ ያለው "የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባርያህን ጠብቀኝ ያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ" መዝሙር 19፥13
ምን አልባት አንዳንድ ካህናት ስለዚህ አይነት ኃጢአት ግንዛቤ ሳይኖራቸው ቀርቶ ተክሊል ፈጽሚ ተክሊል ፈጽም ቢሉን እንኳን ራሳችንን ዝቅ አድርገን አይገባኝም😔 ልንል ያስፈልጋል።
•➢ ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄
🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾
➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺