🙏ይቅርታ ጠይቆም ተሳድቦም ይሆናል ?!
ትራንስፖርት ላይ ነበረኩ ከመገናኛ ወደ ሜክሲኮ የሚሄድ ባስ ላይ ወደ ፒያሳ የሚሄድ ትራንስፖርት በመጠበቅ በጣም የተሰላቸች አንዲት እህት
እዚህ ከምቆም ብላ ወደ ሜክሲኮ በሚሄደው ሄጄ ከዚያ ወደ ምፈልገው ቦታ ብሄድ ይሻላል ብላ ወደ ሜክሲኮ የሚሄደውን ባስ ተሳፈረች።
በዚህ ቅጽበት ባሱ ለመንቀሳቀስ በመዘጋጀት ላይ እያለ ወደ ፒያሳ የሚሄደው ባስ መጣ ይህቺው እዚህ ከመቆም ብላ አቆራርጣ የተሳፈረችው እህት ወደ ሰፈሯ የሚሄደውን ባስ እንደመጣ በመመልከቷ
አሽከርካሪ ሹፌሩን በስህተት ነው የገባሁት አቁምልኝ ብሉት ብላ ተማጸነች ተሳፋሪዎችም ተሳስታ ነው ብለው በማሰብ ከወጣት እስከ አዛውንቱ እባክህ አቁምላት ተሳስታ ነው እያሉ ይለምኑላት ጀመሩ ባሱም ተንቀሳቅሶ ስለነበረ መቆም ባለመቻሉ ትንሽ ወረድ ብሎ የትልልቅ ሰዎችን ልመና በመመልከት መቆም የሌለበት ቦታ ላይ ለማቆም እየተዘጋጀ እያለ በጣም ይቅርታ አቁምልኝ ተሳስቼ ነው ብላ ተማጽኖዋን አሰማች ሹፌሩም እሱን ሊያስቀጣ የሚችል ቦታ ላይ አቁሞ እንድትወርድ አደረገ ።
ልክ እንደ ወረደች ግን ምቀኛ ስትል ተናገረች ይህን ነገር የተመለከቱ ሹፌሩን ለምነው ያስወረዷት ትልቅ ሰው
ይቅርታ ጠይቀውም ተሳድበውም ይሆናል ?
ሲሉ ራሳቸውን ጠየቁ እውነታቸውን ነው።
እስቲ ይህን ወደ ራሳችን ህይወት እናምጣው እና በህይወታችን እግዚአብሔርን በህይወቴ ተሳስቼአለሁ ኃጢአት ሰርቼአለሁ በድዬአለሁ ብለን ለምነን የእግዚአብሔርን ጊዜ ባለመጠበቅ ምላሽ እስከ ሚሰጠን ህይወታችንን እስኪያቃናልን መጠበቅ ተስኖን አረኸ በቃኝ ማረኝ በማለት በመደጋገም ጠይቀን ጊዜው ደርሶ ኃጢአታችንን ይቅር ብሎ ትክክለኛ ኑሮ ለመጀመር ስንል እኔ አሁን ነው እንዴ የጠየኩህ ምነው ዘገየህ ብለን ልመናችንን ሁሉ ከንቱ የምናደርገው ስንቶቻችን ነን??
እግዚአብሔር በህይወታችን የሚሰራበትን ሂደት የሚያውቀው እግዚአብሔር ራሱ ነው በትእግስት ጠብቀን ሥራውን ሲሰራ ደሞ የምናማርር ከሆነ ሁልጊዜም ቢሆን የምስጋናን ህይወት አንለምደውም ስለዚህ ከሰዎች ስህተት እንማር
ብልህ ከሰው ይማራል
ሞኝ ከራሱ ይማራል ይላሉና አባቶቻችን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ጸሐፊ ፦ ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ
አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚
➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻
@Orthodox_spiritual_question
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺