አንዱን እምነት ከአንዱ ጋር እያነፃፀሩ የሀይማኖት ግጭትን የመፍጠር ሙከራ የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አወገዘ‼️
የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መጋቢት 2/2017 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚደረግ ሀይማኖትን ከሀይማኖት የሚያጋጭ ተግባር ወንጀል መሆኑን አመላክቷል።
መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሀፊ ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፤ ከሰሞኑ በኦርቶዶክስና እስልምና ሀይማኖቶች መካከል በማህበራዊ ሚዲያ የሚደረጉ አላስፈላጊ የቃላት ምልልሶችን ጉባኤው በእጅጉ እንደሚያወግዝ ተናግረዋል።
የእምነት ነፃነትና የማምለክ መብት ለሁሉም የተፈቀደ ቢሆንም፤ አንዱን እምነት ከአንዱ ጋር እያነፃፀሩ የሀይማኖት ግጭት መፍጠር የማይፈቀድ መሆኑን ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ተናግረዋል።
አሁን ላይ የተፈጠረውን ይህንን ልክ ያልሆነ ተግባር የፈጠሩ አካላትን የሚመለከተው አካል በመያዝ ለፍርድ እንዲያቀርብ ጉባኤው በመግለጫው ጠይቋል።
በመሆንም ጉባኤው በእምነቶች መካከል ግጭት የሚፈጥሩ አካላትን ለመቅጣት የሚያስችሉ የጉባኤው ህጎች እየተሻሻሉ መሆኑን በመግለፅ፤ የሁለቱ እምነት ተከታዮች ፆማቸውን ከፈጣሪ ምህረትን በመለመንና መልካም ተግባራትን በማከናወን እንዲያሳልፍ ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ጥሪ አቅርበዋል።(መግለጫው ተያይዟል)
(ከአ/አ መገናኛ ብዙሃን በከፊል የተወሰደ)
@Esat_tv1