በአፋር ክልል የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በጤና ዙሪያ የሚያስከተትለውን ተፅዕኖ ለማጥናት እና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንዲያስችል ወደ ክልሉ የባለሙያዎች ቡድን ተላኳል
____
ጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን የመሬት መንቀጥቀጡ በጤና ላይ የሚያስከትለውን ተፅዕኖና መደረግ ያለበትን ጥንቃቄ ለመለየትና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንዲያስችል ጥናት ለማድረግ የተለያየ የሙያ ስብጥር ያላቸው የባለሙያዎች ቡድን ወደ ቦታው ልኳል።
በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት ከጤና ጋር በተገናኘ በቀጣይ ምን ሊከሰት እንደሚችል ፣ ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግና መወሰድ ባለባቸው እርምጃዎች ዙሪያ ጥናት ለማድረግ ከተለያዩ የጤና ሙያ ዘርፎች የተውጣጣ ቡድን በቦታው የደረሰ ሲሆን ከክልሉ ጤና ቢሮ እና ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱት ጋር በመሆን አስፈላጊዉን ፈጣን ምላሽ በመስጠት በቅንጅት እየተሰራ ነዉ።
ህብረተሰቡ መደናገጥና አላግባብ መረበሽን በማስወገድ ትክክለኛ መረጃ ከሚመለከተዉ አካል መከታተልና መተግበር ይኖርበታል።
https://www.facebook.com/share/p/19osb51okY/