ታህሳስ 07 ቀን 2017 ዓ.ም
ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተላለፈ መመሪያ
__
ከሕዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ግዜ ከአምቡላንሶች በስተቀር መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ሆነው እንዲቆዩ እንዲሁም ከጤና ተቋማት ውጭ ማህበራዊ አገልግሎት ተቋማት እንዲዘጉ መመሪያ መሰጠቱ ይታወቃል።
ዛሬን ጨምሮ ላለፉት 8 ቀናት የተሰጠው ትእዛዝ ያለ መሸራረፍ ተተግብሯል። በእነዚህ ግዜያት ውስጥ በሲቪሊያን ላይ ሊደርስ የሚችል ጉዳትን መቀነስ ከመቻሉም በበርካታ አካባቢወች አስደናቂ ኦፕሬሽኖችን በማከናወን የቡድን እና የነፍስ ወከፍ መሳሪያወችን እንዲሁም ተሽከርካሪወችን ከጠላት ማርከናል። የጠላትን ወታደራዊ እቅዶችም ማዛባት ተችሏል።
ይሁን እንጅ የተላለፈው መመሪያ ተፈፃሚነት ከዚህ በላይ መቀጠሉ በህዝብ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚያደርሰውን ጫና በማገናዘብ #ከነገ #ማክሰኞ #ታህሳስ 08 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ እና የተቋማት ክልከላ እና ገደቡ የተነሳ መሆኑን እናስታውቃለን::
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአማራ ፋኖ በጎጃም!
ታሕሳስ 07/04/2017 ዓ.ም