ለምን? ብሎ ኑሮ 6!!
:
ወይንዬ ከዮሲ ጋር አብረን መሆን ከጀመርን አራት ውር ሆነን በዚህ አራት ወር ውስጥ ቢያንስ በሳምንት ሁለት ሶስት ቀን እንገናኛለን ብዙ ነገር እናውራለን እሱ ከኔ ጋር በማሳለፉ ደስተኛ ይመስላል እኔ ግን ይሆነ ነገር አእምሮዬን ይበላዋል።
ምን ሆንሽ ደሞ? አለች ወይንሸት… ወይኔ እንደምታውቂው ውሸት አሎድም መዋሸትም የሚዋሽ ሰው መየትም አሎድም በተለይ ግኑኙት ውሸት ሲኖረው እግሩ ነው የሚቆረጠው ምንም ያህል ፍቅር ቢኖርሽ ውሸት ከተቀላቀለበት የፍቅር ህይዎትሽ እግሩ ይቆረጣል ሽባ ይሆናል ይሆነ ሰአት ላይ ይቆማል መሄድ ያቅተዋል…
እኔ ዮሲ እየዋሸሁት ይመስለኛል አምስት አመት ሳስበው መቆየቴን አለመናገሬ አእምሮዬን እየበላው ነው እሱ ያወቀኝ ከአራት ወር በፊት ቢሆንም እኔ የማውቀው ግን ከአምስት አመት በፊት ነው ይሄን አለመናገሬ እያመመኝ ነው ልነግረው እፈልጋለው ሁሉንም ነገር ልንግረው እፈልገለው… አለች ማርታ አልጋዋ ላይ ተጋላ…
አንቺ ያምሻል እንዴ? ምን ብለሽ ልትነግሪው? እኔ የሰላም ጓደኛ ነኝ ያቺ ሰላም በፍቅሯ ያበድክላት ሰላም ያቺ ስትወዳት አልውድህም ብላህ ከሃገር ጥላህ የጠፋችው የፍቅር ህይዎትህ ላይ ጠባሳ ጥላ ፈረንጅ ሃገር የገባችው ሰላም ስለንተ ቀን ከሌት ስትነገረኝ ሳላውቅህ የፍቅርህ ጣዖት በአእምሮዬ ሰፈራ የአፍቃሪነት ልብህ የትግስት ልክህ አይቼ ሳላውቅህ ሳላይህ በስዕል ብቻ ያፈቀርኩህ ልጅ ነኝ እኔ ማርታ ማለት ልትዪው ነው?…
አዎ ምን ችግር አለው እነግረዋለው… አንቺ ልጅ ያምሻል እንዴ ዛሬ ነው እንዴ መኖር የጀመርሽው ሁሉም እውነት እውነት ስለሆነ ብቻ አይነገርም አንዳድ እውነት ሰሚውን ይገላል አንዳድ እውነት ተናጋሪውን ይገላል በተቃራኒው አንዳድ አውነት ለሰሚው አንዳዱ ደሞ ለተናገሪው ይጠቅማል… ሁለቱንም ተናጋሪውንም ሰሚውንም የሚጠቅም እውነት ግን ብዙ የለም የምትናገሪውን ነገር እውቂው… እና ምን እያልሽ ነው ወይን አትንገሪው ነው?…
አላልኩም ንገሪው ግን የምትነግሪውን ምረጪ ሁሉንም አትናገሪ… እኮ ምኑን ነገሬው ምኑን ልተወው?… በቃ ረጅም ጊዜ ታውቂው እንደነበረ የምታውቂውም ሰላም በምትባል ልጅ እንደሆነ ንገሪው ነገር ግን የሰላምን ተረክ እየሰማሁ ሳላውቅህ አፍቅሬህ ነበር ብለሽ እንዳትነግሪው ድፍን እውነት ድፍን ነው አይገለጥም የተከፈተ የተገለጠ እውነት ግን መፈናፈኛ ነው የሚያሳጣሽ ነግሬሻለው… አለች ወይንሸት።
ማርታና ወይንሸት አልጋቸው ላይ ጎን ለጎን ተኝተዋል… ማርታ የወይንሸትን ምክር መቀበል አልፈለገችም ነገር ግን ሌላ ሃሳብ አጣች ነገሩን ሁሉ አፍረጥርጬ ነገሬው ባጣውስ ብላ ፈራች።
ሁለቱም ኮርኒሱ ላይ እንደፈጠጡ ብዙ ቆዩ… ማርታ ስልኳን አንስታ ለዮሴፍ ቴክስት ላከችላት “ዮሲ ነገ እራት ልጋብዝህ?" የሚል መልክት ላከች።
ዮሴፍ መለሰ “በደስታ ነዋ እንደውም ከአሁን ሰዐት ጀምሮ አልበላም አስቢበት" ይላል የዮሴፍ መልስ።
ማርታ ቴክስቱን አንብባ ሰቅ አለች።
በነጋታው ምሽት ማርታና ዮሴፍ በቀጠሮቸው ተገናኙ… ማርታ ዘውትር የምታዞትርበት ቤት እራት ጋበዘችው።
እራት እንደበሉ… እሺ ወይዘሪት ማርታ በኢኮኖሚ ና በሴት መሃል የስጋ ዝምድና አለ ይላል ጓደኛዬ አሊ እና ይቺ የእራት ግብዣ የሆነ ነገር አላት ወርውሪያት እስኪ…
አለ ዮሴፍ ማርታ ላይ አፍጥጦ… በኢኮኖሚስትና በአካውንታት መሃል ያለው ልዩነት የሁለት ከፈሮች ያህል ነው ሲባል የሰማሁ መሰለኝ እና በኔና በአንተ መሃል ያለው የአይዶሎጂ ልዩነት አፍ በመክደን ብቻ ይስተካከላል… አለች ማርታ ሳቅ እያመለጣት…
ማርቲ ሳቂው ሳቂው ሳቅሽን አታፍኚው እኔ ዝም ብዬ ሳስብሽ ጋሃነም የምትገቢው በሳቅሽ ይመስለኛል ልውጣ ሲሉ ስታፍኛቸው… አረ በስመአብ በል አንተ በጋበዝኩ… እሺ ማርቲ ገነት ልኬሻለው ታዲያ ግብዣው ከየት ነው የመጣው? … እንዴ ዝም ብዬ ልጋብእህ አልችልም እንዴ?…
ትችያለሽ ግን ከመሸ ጨለማን ተገን አድርጎ የሚመጣ የግብዣ ሃሳብ ብዙ ጥያቄ አለው ብዬ ነው… እሺ ይሁንልህ ከአንተ ጋር ማን ይከራከራል! ዮሲ የሆነ ነገር ልነግርህ ፈልጌ ነበር… ንግሪኝ ምነው?… እ እ እ… አረ ማርቲ መፈራራት ተጀመረ እንዴ?… አይ ፈርቼህ አይደለም ይሆነ ነገር እ ዮሲዬ እኔ አንተን የማውቅህ አሁን አይደለም ማለቴ ከአራት ወር በፊት አይደለም እኔ አንተን የማውቅህ ከአምስት አመት በፊት ነው…
ብላ አቀርቅራ ዝም አለች… አንዴት? አለ ዮሴፍ ግራ እንደመጋባት ብሎ… ሰላም የምትባል ልጅ ታውቃለህ?… ሰላም ሰላም?… ሰላም የአዋሳ ልጅ ባንክ የምትሰራ አሁን ካናዳ ነው ያለችው… ok ሰላም so what ሰላም?… አለ ዮሴፍ እንደመኮሳተር ብሎ… ማርታ ፊቱን ስታየው ደነገጠች ያወጣችውን አትመልሰው አታጥፈው ጨነቃት… ሰላም ጓደኛዬ ነበረች አብረን ነበር የምንኖረው ማለቴ ከአዋሳ ለስራ አብረን አዲስ አበባ መጥተን አብረን ተከራይተን እንኖር ነበር… አለች ማርታ እየተርበተበተች።
ዮሴፍ ፊቱ ተለዋወጠ ተቁነጠነጠ… እና? አለ።
እናማ የዛኔ ነበር የማውቅህ ሰላም ብዙ ነገር ስለአንተ ታውራልኝ ነበር… ይቅራታ ማርቲ ስለእሷ ማውራት አልፈልግም… ዮሴዬ ሰላምን ታፈቅራት እንደነበረ አውቃለው… ምን እኔ ነኝ እሷን የማፈቅራት? እንዴ ማርቲ ምን አይነት ወሬ ነው የምታወሪው እኔ እሷን?
ሃሃሃሃሃ ማርቲ እሷ ማለት የውድ ጓደኛዬን የደስታ ህይዎት ጋሃነም ያደረጋች ሴት ነች… ብሎ ተንቀጠቀጠ ቀይ ፊቱ ደም ሲመስል ታያት ማርታ የምትገባበት ጠፋት… አሪዎስ አሪዎስ ነች እኔ እሷን ላፈቅር?……
ይቀጥላል።
ሼር ለማንኛውም አስተያየት @EthioBini_bot
👇👇👇👇
@EthioBini