✏️እርሳስነት
🔴እርሳስነት ለኑረት ስምረት የተመቸ ተምሳሌት ይመስላል፣ ለመስተጋብር ውበት የተስማማ ምልክት፣ ለመማር የተዘጋጀ ሰው በዙሪያው እልፍ መምህራን አሉለት።
“When the student is ready the master will appear” እንዲሉ…
🟡ተወዳጁ ደራሲ ፓውሎ ኩዌልሆ “Like the Flowing River” በተሰኘው መጽሐፉ ላይ የልጅ ልጃቸውን ታሪክ በሚጽፉ አያት አማካይነት ስለ እርሳስ ልዩ መገለጫዎች ይነግረናል፣ አንድ ሕፃን ሴት አያቱ የሚጽፉት ታሪክ የእርሱ ስለመሆኑ እንዲነግሩት ሲጠይቅ ከሚጽፉት ታሪክ በላይ በሚጽፉበት እርሳስ የተመሰጡት አያት “አዎን ልጄ ታሪኩ ስላንተ ነው… ግና ከምጽፈው ታሪክ ይልቅ የምጽፍበት እርሳስ የተለዩ ነገሮች አሉትና ስታድግ እንደዚህ እርሳስ እንደምትሆን ምኞቴ ነው” ይሉታል።
በአያቱ ንግግር የተገረመው ሕፃን እርሳሱን ትኩር ብሎ ይመለከትና ከሌሎች እርሳሶች የተለየ ነገር እንዳላየበት ለአያቱ መልሶ ይነግራቸዋል።
“አዎን ልክ ነህ” አሉት አያት፣ “የምታይበት መንገድ የምታየውን ነገር ዋጋ ይወስነዋል፣ በደንብ ተመልከት፣ እርሳስ ያሉትን ልዩ ጠባያት መገንዘብ የቻለ ሰው ከፍጥረተ-ዓለሙ ጋር ስሙር እንዲሆን የሚረዱትን አምስት ጥበባት ይማራል…” ሲሉ መለሱለት።
🔴እኒህን አምስት የኑረት መላዎች ከሌሎች አሰላሳዮች ጥልቅ ምልከታ ጋር ማዛነቅ ሻትኩ፣ ልክ እንደዚህ…
1️⃣‘First quality: you are capable of great things, but you must never forget that there is a hand guiding your steps. We call that hand God, and He always guides us according to His will.’
🔷“ታላላቅ ተግባራት የመፈጸም ሰዋዊ አቅም ቢኖርህም በመንገድህ ሁሉ የሚመራህ እጅ እንዳለ ግን መዘንጋት የለብህም፣ እርሱም መለኮት ነው። ሁልጊዜም እንደፈቃዱ ይመራሃል”
♦️ዓለም በስልጣኔ ብትረቅ፣ በቁስ ዕድገት ብታሸበርቅ፣ የሰው ልጅ ትንግርት በሚያስብሉ ተግባራት ቢራቀቅ ያለ መለኮታዊ ድጋፍ የትም ሊደርስ አይችልም። እያንዳንዲቷ እርምጃው መለኮታዊ እገዛ ያሻታል፣ ከራስ አቅም ጣሪያ በላይ ገደብ አልባ ጣሪያ መኖሩን አለመርሳት ደግ ነገር ነው። እብሪትና ማንአለብኝነት ከሚያመጡት አዙሪት ለመውጣትም ሆነ ከኑረት እልፍ ጉድጓድ ለመሻገር ሁነኛው መድኅን መለኮት ነው።
“I’ve forgotten all my learning’s but from knowing you I’ve become a scholar. I’ve lost all my strength, but from your power I am able.” ~ Rumi
2️⃣“በየቆምታዬ ታዛ መቅረጫ ተጠቅሜ እቀርጸዋለሁ፣ ይህ ተግባሬ እርሳሱ በመጠኑ እንዲጨቆን ቢያደርግም ስለቱ ለስራ ምቹ ያደርገዋል። አንተም ብትሆን በኑረት ውስጥ የተሻልክ ትሆን ዘንድ ጥቂት እንግልቶችን እና ጫናዎችን ማለፍ ይኖርብሃል”
🔶ብዙውን ጊዜ የገባንበትን ፈተና ጥልቀት እንጂ ከፈተናው በመውጣት ሂደት የሰነቅነውን ጥበብ አናስተውልም… በዚህም ምክንያት በርካታ የኑረት ክህሎቶች በማስተዋል እጦት ይቀጭጫሉ፣ የብዙ ስኬቶቻችን አሃዱ ግና የሕመማችን ማግስት ነው።
“The wound is the place where the Light enters you.” ― Rumi
3️⃣“እርሳስ ምንጊዜም ቢሆን የሰራነውን ስህተት በላጲስ አጥፍተን የማረም ዕድል ይሰጠናል ፣ ስህተትን ለማስተካከል መድፈር መጥፎ ነገር አይደለም። ይልቁን በቀናው መንገድ ጉዞአችንን እንድንቀጥል የሚረዳን አቅም እንጂ”
🔷በፊቶቻችን የተንኮታኮቱ ጅምሮች፣ የጨነገፉ ሕልሞች፣ ያልተሳኩ ሙከራዎች በርካታ ናቸው። የጅምር እንከን ለዳግም ጅማሬ እንቅፋት ሆኖባቸው ከመንገድ የቀሩ ጓደኝነቶች፣ ትዳሮችና መሰባሰቦች እልፍ ናቸው። ጥፋትን በይቅርታ ማንፃት የተሳናቸው ግትርነቶች፣ ትዕቢትን በአትሕቶ ርዕስ ማጠብ ያቃታቸው አምባገነንነቶች፣ ጭካኔን በአጥፍቻለሁ ዝቅታ ማረቅ የማይሹ ድርቅናዎች የየዕለት ገጠመኞቻችን ናቸው። ይህ ሁሉ ታዲያ መሳሳትን ለመቀበል ድፍረት ከማጣት የሚመጣ እንከን ነው። አልያም ‘ካፈርኩ አይመልሰኝ’ ከሚል አኞነት…
“A man should never be ashamed to own that he has been in the wrong, which is but saying in other words that he is wiser today than he was yesterday.” ― Alexander Pope
“O, happy the soul that saw its own faults.” ~ Rumi
4️⃣ “የእርሳስ ወሳኙ ክፍል ከውጭ የሚታየው እንጨት አይደለም፣ ከውስጥ ያለው መፃፊያ እንጂ፣ ስለሆነም ትኩረት ማድረግ ያለብህ በውስጣዊው ሁነትህ ላይ ነው”
♦️ወጭቱን በአፍአ ጽድት አድርገው የሚይዙ ውስጣቸው ግን በኖራ እንደተለሰነ መቃብር የሚገለሙ በርካታ የአዘቦት ተመሳስሎዎችን እናውቃለን፣ አለማወቁን በቃል ብልጠት የሚሸሽግ ከንቱ… ባዶነቱን በከፈን ድምቀት የሚከልል ሰነፍ ፣ መልከ-ጥፉ ልቡን በስም የሚደግፍ ነውረኛ፣ የነፍሱን እርቃን በመንፈሳዊነት ካባ የሚከፍን አስመሳይ… ቁጥሩ ብዙ ነው።
Beauty is not who you are on the outside, it is the wisdom and time you gave away to save another struggling soul like you.” ― Shannon L. Alder
5️⃣ “እርሳስ ሁልጊዜም አሻራውን ትቶ ያልፋል። አንተም ብትሆን በኑረት የምትሰራው ማንኛውም ነገር ምልክቱን እንደሚተው ልብ ልትል ይገባል። ስለዚህም ድርጊትህን ሁሉ በአስተውሎት ከውን። ለደቀመዛሙርቱ የሚሰጠውን የሚያውቅ መምህር ከራሱ የሚሻሉትን ያፈራል። ፍርሃቱን ከራስ አኑሮ ድፍረቱን የሚጋራ ሰው ለሌሎች ተስፋ ያተርፋል፣ ለዛሬው የሚጠነቀቅ ነገውን አሁን ይሰራል። በብርሃን ላይ የተመሰጠ የጽልመት አምካኝ መላ ያፈልቃል።
ምንህን እየሰጠህ ነው?… “What kind of footsteps will you leave for those who follow you?” ― Kathy Bee …
🔑ፍቅርን ነው ጥላቻ፣ ሰላምን ነው ጸብን፣ አንድነትን ነው መለያየትን፣ ስታልፍ የምናስብህ ለሰላማችን በጣልከው መሰረት ነው ወይስ ለግጭታችን በሰራኸው ሴራ? ለአብሮነታችን በገነባኸው ታዛ ነው ወይስ ለመቋሰላችን ባኖርከው ሰይፍ?
ለሚያነቡህ ምን እየፃፍክ ነው? ለሚሰሙህ ምን እየተናገርክ ነው? ወላጅ ላሉህ ምን ትተሃል? ከቶ አሻራህ ምን ይመስላል? ቅርስህሳ ምን ሸክፏል? ከኑረትህ ምን ተርፎናል?
በአያቱ ተግባር የሚያፍር ዘመነኛ – በተራው ልጁ እንዳያፍርበት ያለው ብቸኛ አማራጭ ልቡናውን ከቂም አንጽቶ የእርሱን ውብ ነገ ዛሬ ላይ መስራት ነው። ይህ ግን ከኢጎ የመላቀቅን ድፍረት ይሻል!!
“Take nothing but memories, leave nothing but footprints!” ― Chief Seattle
✏️በደምስ ሰይፉ
እርሳስነት – ምርጥ ብልሃት
ውብ አሁን❤️
💎ሃሳብ ፣ ንባብ፣ ኑረት፣ ሕይወት፣ፍቅር እና ምናብ! ድልድይ👇
@BridgeThoughts @BridgeThoughts✍
@EthioHumanitybot