አሌሀንድሮ ጋርናቾ ቡድኑን ይቅርታ ይጠይቃል !
የማንችስተር ዩናይትዱ ተጨዋች አሌሀንድሮ ጋርናቾ በኢፕስዊች ታውን ጨዋታ ላሳየው ባህሪ ቡድኑን እራት በመጋበዝ ይቅርታ እንደሚጠይቅ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ገልጸዋል።
ጋርናቾ በጨዋታው ዶርጉ በቀይ መውጣቱን ተከትሎ በማዝራዊ ተቀይሮ የወጣ ሲሆን ቀጥታ ወደ መልበሻ ቤቱ ሲገባም ተስተውሎ ነበር።
" ትላንት ጠዋት ቢሮዬ መጥቶ ነበር " ያሉት አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ምንም ችግር የለም ቡድኑን እራት ይጋብዛል ብለዋል።
ጋርናቾ ስላደረገው ነገር ምርመራ ማድረጋቸውን ያስረዱት አሰልጣኙ ልብሱ ረጥቦ ስለነበር መልበሻ ቤት ቀይሮ ጨዋታውን ከዛው እንደተከታተለ አረጋግጫለሁ ብለዋል።
አሰልጣኙ አክለውም ማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትኩረት የሚደረግበት በመሆኑ ግንዛቤው እንዲኖረው አስረድቼዋለሁ ብለዋል።