🔻 I ክለባችን ሊቨርፑል በዘንድሮ ዉድድር አመት በአጠቃላይ 36 ጨዋታዎችን ተጫዉቷል ፣ ከባለፈዉ የዉድድር አመት በአንድ ጨዋታ ብዛት የሚበልጥ ነዉ።
ይህም ሆኖ ግን አንድ አነስተኛ ጉዳት ነዉ ያለብን ፣ የተጨዋቾችን ጤንነት የሚጠብቀዉም አዲሱ የሜዲካል ስታፋ ሀላፊ የሆነዉ ሩበን ፒተርስ ነዉ።
ሩበን ፒተርስ ከአርነ ስሎት ጋር በፌይኑርድ ቤት አብሮት የሰራ ሲሆን ስሎት ነዉ ይህ ሰዉ እንዲመጣ የወሰነዉ።
ሩበን ፒተርስ በፌይኑርድ ቤት የሚሰራዉ ስራ ማይክሮባዮም የተባሉ ረቂቅ ተዋህሲያኖችን [Microorganism] ማጭበርበር ወይንም ማታለል ነዉ። በሌላ በኩል ስራዉ የአንጀት ጤንነት እንዴት ብቃትን ማሻሻል እንደሚችል ማወቅ ነዉ። ሌላዉ ስራ በDNA EPIGENETIC ሲሆን የተጫዋቾችን ዘር ግንዳቸዉ ባህሪ ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር የሚሰራ ስራ ነዉ። የተጫዋቾችን ብቃት ለመከታተልም የእንቅልፍ ጊዜያቸዉን የሚከታተል ቆራጥ ሜዲካል ስታፍ አባል ነዉ።
The Man Behind The Health❤️
@Ethioliverpool143@Ethioliverpool143