ኢትዮ ኘላስ + Ethio Plus


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ባሻገር ያሉ መረጃዎች እና ሃሳብ የሚቀርብበት ቻናል ነው።
አለምአቀፋዊ እይታ እና ግንዛቤን በመረጃ እናሳድግ!
#Diplomacy #International #Politics #Science #Culture #Sport #Art

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ፈረንሳይ ለዩክሬን የስለላ መረጃዎችን ማጋራት መቀጠሏ ተገለፀ
-----------

የፈረንሳይ መከላከያ ሚኒስትር ሴባስቲየን ለኮርኑ ሀገራቸው ለዩክሬን የስለላ መረጃ እያጋራች መሆኗን ዛሬ ሐሙስ ተናገሩ፡፡

ርምጃው ዩናይትድ ስቴትስ ከዩክሬን ጋራ የምታደርገውን የመረጃ ልውውጥ አቋርጫለሁ ማለቷን ተከትሎ የተሰማ ነው።

ርምጃው የተወሰደው የአውሮፓ ኅብረት መሪዎች በብራሰልስ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ በተገኙበት የመከላከያ ወጪያቸውን በማሳደግ እና ዩክሬን ከሩሲያ ጋራ በምታደርገው ጦርነት ድጋፍ ለመስጠት ቃል ስለ መግባት ውይይት ባደረጉበት በዛሬው ዕለት መሆኑ ነው፡፡

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከውይይቱ በፊት የአውሮፓ ኅብረት አባላት “ወደፊት ወሳኝ ርምጃዎችን እንደሚወስዱ” ተናግረዋል፡፡

በአዲሱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን ስለምትሰጠው ድጋፍ በወሰደው የአቋም ለውጥ ስጋት ያላቸው መሆኑንም ማክሮን ገልጸዋ፡፡

"የአውሮፓ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በዋሽንግተን ወይም በሞስኮ መወሰን የለበትም" ብለዋል ማክሮን፡፡


" ተፀፅቻሁ " አሉ ቭላድሚር ዜለንስኪ
-----

ኘሬዝደንት ዜለንስኪ ባለፈው አርብ በኋይትሃውስ ከትራምኘ እና ምክትላቸው ጋር በዘለፋ እና ቁጣ የታጀው ውይይት በዚያ መልኩ መካሄዱ ፀፀት ውስጥ ከቶኛል ብለዋል።

ኘሬዝደንቱ " ከአሜሪካ ጋር ያለንን አጋርነት ለማስጠበቅ አሁንም ዝግጁ ነኝ። የነጩ ቤተመንግስት ውይይት ፀፀት የፈጠረብኝ ቢሆንም ፥ አሁን ነገሮችን ወደ ትክክለኛ መስመር የምንመልስበት ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

ዜለንስኪ ይህን መልዕከት በኤክስ ገፃቸው ያስተላለፉት ዛሬ የአሜሪካ መንግስት በይፋ ለዩክሬን ሲሰጥ የነበረውን ወታደራዊ ድጋፋ እንዳቋረጠ ማስታወቁን ተከትሎ ነው።

ፈጣኑ የአሜሪካ ውሳኔ የሚጠበቅ ሲሆን ይዞት የሚመጣው ጣጣ የበዛ መሆኑን የሚያውቁት ዘለንስኪ ለሰላም ስምምነት ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

ባለፈው ሳምንት ውድቅ ያደረጉትን የማዕድን ስምምነት ለመፈፀምም ዝግጁ እንደሆኑ ዛሬ ምሽት አስታውቀዋል።

ዜለንስኪ የአቋም ለውጥ ማድረጋቸውን ተከትሎ የአሜሪካ መንግስት ምላሽ ምን ሊሆን እንደሚችል እየተጠበቀ ነው።


እንግሊዝ የያዘችው መንገድ የት ድረስ ያስጉዛታል ?
--------
የትራምኘ መንግስት በዩክሬን ጉዳይ የአቋም ለውጥ ማድረጉን ተክተሎ ነገሮችን ለማለዘብ ያልተሳካ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ይታወቃል።

በተለይ እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ሌሎች የአውሮፓ ሃገራትን አካተው ከዩክሬን ጎን መሰለፋቸውን እንደሚቀጥሉ ፣ ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ ባለፉት ሁለት ቀናት ሲገልፁ ተሰምተዋል።

በተለይ እንግሊዝ ከትራምኘ ጋር የተቃረነ አቋሟን እንደቀደሙት ጊዜያት ለማስታረቅ ስትሞክር ሳይሆን የታየችው ፥ ሌሎች የአቋሟ ተጋሪ የአውሮፓ ሃገራትን አስከትላ በተፃራሪነት መቀጠልን ነው።

አርብ ከኋይትሃውስ አቀርቅረው የተመለሱትን ቭላድሜር ዜሌንስኪን በክብር የተቀበለችው እንግሊዝ እሁድ እለት በለንደን የአውሮፓ ሃገራት የተሳተፉበት ቀጣይ ሂደት ላይ የሚመክር ጉባኤን አካሂዳለች።

ዛሬ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታንመር አማካኝነት ዩክሬንን በቀጣይ ለመደገፍ እና የሩሲያን ቀጣይ ወረራ ለመከላከል ያስችላል ያለችውን ባለአራት ነጥብ ዕቅድ ይፋ አድርጋለች።

አራት ነጥቦችን የያዘው የእንግሊዝ ምክረ ሃሰብ የሚከተለው ነው፦

1. ለዩክሬን የሚደረግ ወታደራዊ ድጋፍ መቀጠል

2. ዩክሬንን ያካተተ የሰላም ንግግር እንዲጀመር ማድረግ

3. የሩሲያ ወረራ ለመመከት የሚያስችል የመከላከያ አቅም ዩክሬን እንድተገነባ መደገፍ

4. ዩክሬንን የሚደግፉ ፈቃደኛ ሃገራት ጥምረት መመስረት እና ሰራዊት ወደ ዩክሬን መላክ የሚሉ ናቸው።

በዩክሬን ጉዳይ የጠ/ሚር ስታንመር መንግስት የያዘውን አቋም ለሃገሪቱ ምክር ቤት ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን አብላጫ ድጋፍ አግኝቷል።

እንግሊዝ አሜሪካ አልሄድበትም ባለችው መንገድ " ምን ያህል ልትጓዝ ትችላለች ?" የሚለው የወቅቱ ጥያቄ ነው።


ዜለንስኪ ከቡጤ መዳኑ ተአምር ነው -ማርያ ዛካሮቫ
---------

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ማርያ ዛካሮቫ የዋሽንግተኑ ክስተት እንዳበቀ ይህን መልዕክት አሰፈረች።

በዜለንስኪ ውርደት አንጀቷ የራሰው ማርያ 👇

" ትራምኘ እና ጄድ ቫንስ በዚህ ከሃዲ ላይ (ዜለንስኪን ማለቷ ነው) ቡጢ ከማሳረፍ የታቀቡት ራሱ በተአምር ነው " ስትል ፅፋለች።

ዜለንስኪ ከትራምኘ ጋር ባደረገው ንግግር ላይ እኳን ብዙ ውሸቶችን ተናግሯል ያለችው ዛካሮቫ ፥ ለዚህም ቁጣ እና የቃል ዘለፋ ብቻ ሳይሆን ቡጢም ይገባው ነበር ብላለች።

ክሬምሊን በኋይት ሃውስ ተግባር እንደዛሬው ጮቤ የረገጠበት ዕለት በታሪክ ቢፈለግ ከቶም አይገኝም።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የትራምኘ እና ዜለንስኪን ቪድዮ እንካችሁ

ዛሬ የአለም መነጋገሪያ የሆነው ዶናልድ ትራምኘ ከምክትላቸው ጋር በመሆን የዩክሬኑን ኘሬዝደንት ቭላድሚር ዘለንስኪን ፊት ለፊት የዘለፉበት ንግግር ፥


ይመልከቱት ☝️


አንድ መሪ በሌላ መሪ እስከ ዶቃው ማሰሪያ ሲነገረው ዛሬ አየሁ
-------
-----

በታሪክ አንድ መሪ የሌላ ሃገርን መሪ ቀሃገሩ ጦርቶ በሚድያ ፊት ለዚያውም በቀጥታ ስርጭት ለአለም እየተላለፈ እንዲህ ሲዘልፍ ፣ ሲቆጣ ፣ ሲገፅስ ታይቶ አይታወቅም።

ትራምኘ ዘለንስኪን ዛሬ እንደ መሪ ሳይሆን እንደ ሰፈር ጎረምሳ በስድብ እና ሃይለቃል ፍፁም ዲኘሎማሲን በጣሰ አግባብ ሲዘልፉ ታዩ።

ትራምኘ ከምክትላቸው ጄድ ቫንስ ጋር እየተቀባበሉ በአለም ህዝብ ፊት ዘለንስኪን ቃል ሳይመርጡ ወርፈው አባረውታል።

እንዲህ ያለ የሁለት መሪዎች ንግግር በይፋ ለህዝብ ቀርቦ አያውቅም ሲሉ ሚድያዎች እየዘገቡ ነው።

ዜለንስኪ ዋሽንግተን የተገኘው አሜሪካ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ለምታደርገው ጦርነት ለሰጠኋት ገንዘብ መካሻ ማዕድኖቿን በመስጠት ትክፈለኝ በሚል በያዘችው አቋም ለመደራደር ነበር ።

ድርድሩ ሳይካሄድ በሚድያ ፊት የተዘለፈው ዘለንስኪ የመጣበትን ጉዳይ ሳይፈፅም ወደ ሃገሩ ተመልሷል።

እስከ ዶቃው ማሰሪያ በሚያስብል ደረጃ ቁጣና ዘለፋን ትራምኘ ከምክትላቸው ጋር እየተቀባበሉ አዝንበውበታል።

ስሜቱን መቆጣጠር የተሳነው ዜለንስኪ የሁለቱን ሰዎች ዘለፋ ለማቋረጥ ቢሞክርም " በኦቫሉ ቢሮ መጥተህ አስተዳደራችን ልትተች ተሞክረለህ እንዴ ፥ ይህ ክብረነክነት ነው " ብለው አስጎንብሰውታል።

በነበረው የጦፈ ንግግር ትራምኘ ዜለንስኪን በንቀት እና ቁጣ እንዲህ አሉት፥

👉" የምትሰራው ስራ ለአሜሪካ ያለህን ዝቅ ያለ አክብሮት የሚያሳይ ነው "

👉"በምናቀርብልህ መደራደሪያ ወይ ትስማማለህ ወይ ብቻህን ትቀራለህ "

👉" ክብር የሌለህ ሰው ነህ "

👉" አንተ ሶስተኛውን የአለም ጦርነት ለመቀስቀስ የቆመርክ ሰው ነህ "

👉" ፑቲንን አስቀያሚ ነገር እንድናገርልህ እና አየህ ፑቲን እኛ ተግባብተናል ማለት ነው የአንተ ፍላጎት ፥ ይህ ፈፅም አይሆንም "
👉" በተቃራኒ ያለውን ልንገርህ እኔ ፑቲንን እወደዋለሁ ፥ እኛ እንዋደዳለን "

👉" አሁን ምንም አይነት የመደራደሪያ ካርድ የለህም "

👉" ያለ እኛ ምንም አይነት አቅም የለህም "
👉 " የውጊያ አቅም የለህም ሰራዊትህ ሁሉ ተበትኗል "

👉 " ልታመሰግነኝ ይገባህ ነበር ፥አንዴም ግን ስታመሰግን አልተሰማህም "

የመናገር እድል ያጣው ዜለንስኪ እጅግ ለአንድ መሪ በማይገባ መልኩ በንዴት ተሞልቶ ከነጩ ቤት ወጥቷል።

ጉብኝቱም ስምምነቱም ሳይፈፀም ቆይታውን በአጭር ቋጭቶ ወደ ሃገሩ ተመልሷል።

ትራምኘ ከውይይቱ በኋላ ዘለንስኪ መንግስታቸው ያቀረበውን የድርድር ሃሳብ ባለመቀበሉ ስምምነት ሊፈፀም አልቻለም ብለዋል።

" ለሰላም ዝግጁ ሲሆን ተመልሶ ይመጣል " ብለዋል።

የዩክሬን ህዝብ ምን ብሎ ይሆን ግን ?

ተፃፈ በሰይፈዲን በአማን ለ #ኢትዮ_ኘላስ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ዜለንስኪ የተጠየቀውን ሊሰጥ ዋሽግንተን ደርሷል

ድራማው ቀጥሏል። ከቀናት ቀፊት ትራምኘ " አምባገነን ...ብዙም ያልተሳካለት ኮሜድያን " ብለው በአደባባይ የሸነቆጡት ቭላድሚር ዘለንስኪ አሜሪካ አምጣ ያለችውን ለመስጠት ኋይት ሃውስ ደርሷል።

ከ300 ቢሊየን ዶላር በላይ የአሜሪካንን ገንዘብ በጦርነት ስም ወስዶ መና አስቀርቷል ሲሉ ትራምኘ ዘለንስኪን ሲወቅሱ ሰንብተዋል።

ገንዘባችን ተብልቶ አይቀርም በሚል ዩክሬን ያላትን የማዕድን ሃብት ትስጠን የሚል ቀልድ መሳይ ሃሳብ ጣል አድርገው ፥ ይኸው ቃላቸው ሊፈፀም እሺ እንነጋገር ብሎ ደጃቸው ላይ ተገኝቷል።

ከትራምኘ ወደ ስልጣን መምጣት ወዲህ ይሆናል ተብሎ የማይገመቱ ታሪኮች በዩክሬን ሩሲያ ጉዳይ ላይ እየተፃፉ ነው።

ዓለም ከትናንት በስቲያ ሰኞ በርካታ አስደማሚ ክንውኖችን አስተናግዳለች፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የፀጥታው ምክር ቤት በዩክሬን ጉዳይ ሩሲያን እንደ ፀብ አጫሪ ቆጥሮ ለማውገዝ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ከሩሲያ ጎን በመሆን የተቃውሞ ድምፅ በመስጠት አሜሪካ አስደማሚና ሆኖ የማያውቅ አዲስ የኃይል አሠላለፍ ታሪክ ሠርታለች፡፡

በዕለቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የፈረንሣዩን አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮንን በነጩ ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋግረዋል።

ዩክሬን የኪሳራ ናዳ እየወረደባት ነው።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ነጩ ቤት ደርሰዋል
---------

ከደቂቃዎች በፊት የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታንመር ወደ ዋሽንግተን በማቅናት በነጩ ቤት ከዶናልድ ትራምኘ ጋር ተገናኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አትላንቲክን የተሻገሩበት ዋና ምክኒያት በሩሲያ ዩክሬን ቀጣይ ጉዳይ ላይ ከአሜሪካ ጋር ለመምከር ነው።

ትራምኘ ለፈአገራቸው በዩክሬን ጉዳይ ስትከተል የነበረውን አካሄድ መቀየራቸውን እንዲሁም ታደርግ የነበረውን ድጋፍ ማቋረጧን ተከትሎ ድንጋጤ ውስጥ ከገቡ አገራት አንዷ የሆነችው እንግሊዝ ቀጣይ መንገዷን ለመወሰን ከትራምኘ ጋር መነጋገርን መርጣለች።

ከዩክሬን ጎን በመሰለፍ ጦርነቱን በገንዘብ ፣ በመሳሪያ እና በሌሎች መልኮች ሲደግፉ የነበሩ ዋንኞቹ የአውሮፓ ሃገራት በአሜሪካ የፓሊሲ ለውጥ ምክኒያት ግራ መጋባት ውስጥ ገብተዋል።


ሱዳን አውሮፕላን ተከስክሶ 46 ሰዎች ሞቱ
-----------

የሱዳን አንቶኖቭ ወታደራዊ የማጓጓዣ አውሮፕላን ከዋና ከተማዪቱ ካርቱም ወጣ ባለ የመኖሪያ ሥፍራ አካባቢ ተከስክሶ 46 ሰዎች ሞቱ ። ከሟቾቹ መካከል የመላ ካርቱም የቀድሞ ጦር አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ባህር ይገኙበታል ተብሏል ።

ከሞቱት ሰላማዊ ሰዎች በተጨማሪ ሁለት ወታደራዊ መኮንኖችም ይገኙበታል ተብሏል፥ 10 ሰዎችም ቆስለዋል ።

የዓይን ምስክሮች በወቅቱ ከባድ ፍንዳታ መስማታቸውንና በአካባቢው የነበሩ ቤቶች ላይም ጉዳት ሲደርስ ማየታቸውን ተናግረዋል። አንድ ወታደራዊ ምንጭ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት፦ የአደጋው መንስኤ የቴክኒክ ችግር ሳይሆን አይቀርም ።

የአውሮፕላን አደጋው ትናንት ሌሊት የደረሰው ኦምዱርማን ከተማ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ ወታደራዊ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር፤ ዋዲ ሴይድ አቅራቢያ መሆኑን የአካባቢው መንግሥት ዐሳውቋል ።

አደጋው ከመድረሱ አንድ ቀን አስቀድሞ የሱዳንን ጦር የሚወጋው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ኢልዩሽን የተባለ ሩስያ ሠራሽ አውሮፕላን በደቡብ ዳርፉር ዋና ከተማ ኒያላ ውስጥ ተኩሶ መጣሉን ተናግሮ ነበር ። ቡድኑ እንዳለው አውሮፕላኑ በውስጡ ከነበሩት ሠራተኞች ጋር ወድሟል ።

የሱዳን ጦር ሠራዊት ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ጋር ጦርነት ውስጥ ከገባ ሁለት ዓመታትን ሊያስቆጥር ነው ።


የፌደራል ቤቶች በሶማሌ ተራ እየገነባ የሚገኘው ቅይጥ ፎቅ ግንባታ 95 በመቶ መድረሱ ተገለፀ
------------

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አመራሮች የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ
በሶማሌ ተራ እየገነባ በሚገኘው የከፍተኛ ፎቅ ቅይጥ ግንባታ ፕሮጀክት የመስክ ጉብኝት አድርገዋል።

የመስክ ጉብኝቱን ተከትሎም የኮርፓሬሽኑ የ2017 የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ላይ ውይይት ተካሂዷል።

ኮርፖሬሽኑ ያለፉት 6 ወራት ገቢ ከእቅድ በላይ 117 በመቶ እንደሆነ ተገልጿል። ለማካሄድ ከታቀደው የቤቶች ጥገና 99.3 በመቶ መከናወኑ ታውቋል።

የሶማሌ ተራ ፕሮጀክት አፈፃፀም 99.5 በመቶ መድረሱ በጉብኝቱ ላይ ተገልጿል።

አፈጻጸሙን የበለጠ ለማሳደግ ኮርፖሬሽኑ በኪራይ ውል ስምምነቶች እና በኮንትራት አስተዳደር ላይ በማተኮር ንብረት የማስተዳደር አቅሙን መገንባት ትኩረት እንደሚሰጠው ተጠቅሷል።

በተጨማሪም፣ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የአዋጭነት ጥናቶች ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ስራዎች ሌላኛው ይሆናል።

ለቤቶች ልማት የተለያዩ የፋይናንስ ምንጮችን ማሰስ የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት እምነት፣ የመንግስት የግል ሽርክና እና የጋራ ቬንቸርን ጨምሮ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ናቸው ተብሏል።


ግብፅ ለናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት "ግድቡን አትጎብኙ" የሚል ደብዳቤ ፅፋ እንደነበር ተገለፀ
---------

የናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት የዓባይ ግድብን የጎበኙት የግብፅን "አትጎብኙ" ደብዳቤ ውድቅ አድርገው መሆኑ ተነግሯል።

በዓባይ ግድብ ላይ የናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት ሚኒስትሮች የተካሄደው ጉብኝት በኢትዮጵያ ተቃራኒ የቆመውን አካል ያሽመደመደ ነው ሲል የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሀገራቱ ሚኒስትሮች ወደ ናይል ቀን ስብሰባ ሲመጡ እግረ መንገዳቸውን የዓባይ ግድብንም እንዲጎበኙ ኢትዮጵያ አስቀድማ ደብዳቤ መላኳን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሀባታሙ ኢተፋ ተናግረዋል።

በአንጻሩ የግብፁ የውሃ ሚኒስትር ለሁሉም የተፋሰሱ ሀገራት ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ በኩል የተላለፈላቸውን የዓባይ ግድብን ጎበኙ ጥሪ መቀበል የለባችሁም ብሎ ነበር።

ይሁንና ሚኒስትሮቹ የግብፅን ጥሪ ባለመቀበል የዓባይ ግድብን ጎብኝተው ከሰማይ በታች፤ ከምድር በላይ አለኝ የሚሉትን ጥያቄዎቻቸውን ሁሉ ጠይቀው ምላሽ ማግኘት ችለዋል ነው ያሉት ሚኒስትሩ።

እኛ በደብዳቤ ለታጀበው የግብፅ የ"አትጎብኙ" መልዕክት የመልስ ምት አልሰጠንበትም ያሉት ሚኒስትሩ፣ ጉዳዩ የተለመደ የግብፅ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ አካል እንደመሆኑ ንቀን አልፈነዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ግድቧን ለማስጎብኘት መጋበዝ መብቷ እንደሆነ ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድ በመጀመሪያም ቢሆን የዓባይ ግድብን እንዲጎበኝ የጋበዘችው ኢትዮጵያ እንጂ የናይል ቤዚን ኢንሼቲቭ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል።

በመሆኑም የግብፁ የውሃ ሚኒስትር የአትጎብኙ መልዕክታቸውን ሲያስተላልፉ አንድም ሀገር እንዳልተቀበላቸው ተናግረዋል። ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል።

ግብፅም በኢትዮጵያ ሜዳ ለመጫወት ፈልጋ በራሷ ላይ ግብ አስቆጥራለች ሲሉ ገልጸውታል።

አስገራሚው ነገር እንዳትሔዱ ብለው ያሏቸው ሚኒስትሮች ወደ ዓባይ ግድብ የሔዱት እንዲያውም በከፍተኛ ተነሳሽነት ጉብኝቱን እንደጎበኙም አስረድተዋል።

የታንዛኒያው የውሃ ሚኒስትር በሀገራቸው ምርጫ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ባጋጠማቸው አስቸኳይ ጉዳይ ካለመሄዳቸው በስተቀር ሁሉም የዓባይ ግድብን በሚኒስትር ደረጃ ጎብኝተዋል።

ሚኒስትሮቹ ዓባይ ግድብ ከደረሱ በኋላ የነበራቸው አግራሞት በግልጽ የሚታይ ነበር ያሉት ሚኒስትሩ፤ ቀደም ሲል ሲነዛ የነበረው ፕሮፓጋንዳ እና መሬት ላይ ያዩት እውነታ ልዩነቱ አስደንቋቸዋል ብለዋል።
ያንን የሚያክል ግድብ ኢትዮጵያ መገንባት መቻሏ እንደ ተዓምር የሚታይ ነው የሚል አስተያየትም መስጠታቸውንም ገልጸዋል።

እንደ ሚኒስትሩ ማብራሪያ፤ ጎብኚዎቹ አንደኛ የግድቡ መጠን ከጠበቁት በላይ ሆኖባቸዋል። ስፋቱና የውሃ መጠኑ አስደምሟቸዋል።

ከምንም በላይ የሥራው ጥራት ትንግርት ሆኖባቸዋል። ትልቁ ስኬት ያሉት ደግሞ ኢትዮጵያ የዓባይ ግድብን ለመገንባት ስትል ያለፈችው ፈተና የሚያስደነቅ ስለመሆኑም የጉብኝቱ ሚኒስትሮች አስተያየታቸውን አካፍለዋል።

ምክንያቱም ጎብኚዎቹ ግድቡን ገና እንዳዩት ከመደነቃቸው ባለፈ፣ ግብፆች ሲያራግቡት የነበረው ፕሮፓጋንዳ ሐሰት መሆኑን ተገንዝበዋል ሲሉም አብራርተዋል።


ኤለን መስክ በአሜሪካ መንግሰት ሰራተኞች ላይ የፈጠረው ግራ መጋባት
-------


ቢሊየነሩ ኤለን መስክ የሁለት መቶ አመት ዲሞክራሲያቸውን ገደል ከቶታል።

እንደ የአሜሪካ ፌዴራል የምርመራ ቢሮ(ኤፍቢአይ) እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም ፔንታጐን በመሳሰሉት እና በሌሎችም ትላልቅ የአሜሪካ መንግስት መስሪያ ቤቶች ቱጃሩ ኤለን መስክ ሳምንታዊ ስኬታችሁን ላኩልኝ በሚል ለጠየቀው ጥያቄ ሰራተኞቻቸው ምላሽ ከመስጠት እንዲቆጠቡ መስሪያ ቤቶቹ ሀላፊዎች ቢያዙም የኤለን መስክ አካሄድ እጅግ አደገኛ መሆኑ ተነግሯል።

Department of government efficiency በሚል በፕሬዝደንት ትራምፕ በቋቋመውና ኤለን መስክ እንዲመራው የተደረገው ወጪ መቆጠብ በሚል ጅማሮ በተለያየ መስሪያ ተቀጥረው ያሉ ሰራተኞች ሳምንታዊ ስኬታቸውን በዝርዝር እንዲልኩለት ጠይቋል። ምላሽ አትስጡ የሚል ትዕዛዝ ካስተላለፉት መካከል የፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ)፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ፔንታጎን የሚገኙ ቢሆንም መረጃ የሠጡ አንዳንድ መስሪያ ቤቶች እንዳሉ ተነግራል።

ሌሎች የመስሪያ ቤት ኃላፊዎች ከመስክ ለተላከው ኢሜይል ምላሽ እንዲሰጡ የመከሩ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ምላሽ ከመስጠታቸው በፊት ተጨማሪ መመሪያ እንዲጠብቁ ተነግሯቸዋል።

ኤለን መስክ ሰራተኞች እስከ ሰኞ እኩለ ሌሊት ድረስ ምላሽ ካልሰጡ እንደለቀቁ ይቆጠራል ሲል አስጠንቅቋል።

ኤለን መስክ ቅዳሜ ምሽት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የፌደራሉ ሰራተኞች ኢሜይል ከመላኩ በፊት "ባለፈው ሳምንት ያከናወኗችኋቸውን ተግባራት እንዲገልጹ የሚጠይቅ ኢሜይል ይደርሳችል" የሚል መልዕክት በኤክስ ገጹ አስፍሮ ነበር።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መስክ በላከው ኢሜይል የሰጡት ምላሽ የለም።

ቢቢሲ በደረሰው የኢሜይል ግልባጭ ሰራተኞች ሚስጥራዊ መረጃዎችን ይፋ ሳያደርጉ ባለፈው ሳምንት ያከኗወኗቸውን ዋና ዋና ተግባራት በአምስት ነጥቦች እንዲዘረዝሩ ተጠይቀዋል።

የፌደራል መንግሥት የሰራተኞች አስተዳደር ቢሮ የኢሜይሉን ትክክለኛነት አረጋግጧል።የላከው ኢሜይል ሰራተኞች ምላሽ አንሰጥም ቢሉ ስራቸው ምን ይሆናል በሚለው ላይ ግልጽ ነገር ባይዝም መስክ "ምላሽ አለመስጠት ስራ እንደለቀቃችሁ ያስቆጥራል" በሚል ማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አስፍሯል።

አዲስ የተሾሙት የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ካሽ ፓቴል ሰራተኞቻቸው "ምላሽ ከመስጠት እንዲታቀቡ" በኢሜይል መልዕክታቸው አሳስበዋል።

"የኤፍቢአይ ሰራተኞች ከመንግሥት ሰራተኞች አስተዳደር ቢሮ መረጃዎችን የሚጠይቅ ኢሜይል ደርሷችሁ ይሆናል" ማለታቸውን ሲቢኤስ ያጋራው የፓቴል መልዕክት ያትታል።

"ኤፍቢአይ በዳይሬክተሩ በኩል ሁሉንም የግምገማ ሂደቶቻችንን ይቆጣጠራል። እናም የመስሪያ ቤታችን መመሪያ ተከትለን ግምገማ እናካሂዳለን ይላል።

የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትም ተመሳሳይ መልዕክት የላከ ሲሆን አመራሩ ምላሽ ይሰጣል ብሏል።

"ማንኛውም ሰራተኛ ተግባራቸውን በተመለከተ ከመስሪያ ቤቱ የትዕዛዝ ሰንሰለት ውጭ ሪፖርት የማድረግ ግዴታ የለበትም" ሲል የመስሪያ ቤቱ ጊዜያዊ ጸሐፉ ቲቦር ናጊ በላኩት መልዕክት አስፍረዋል።

ፔንታጎን በበኩሉ "አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት መስሪያ ቤቱ ምላሽ የሚሰጥ ይሆናል" ሲል ለሰራተኞቹ በላከው ኢሜይል አስፍሯል።

የሃገር ውስጥ ደህንነት መምሪያ እና የፌደራል ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ኤጀንሲ ለሰራተኞቻቸው ተመሳሰይ መመሪያ መስጠታቸውን ዘገባዎች ጠቁመዋል።


እስራኤል የፍልስጤም እስረኞችን የመልቀቁን ሂደት እንደምታዘገይ አስታወቀች
-----------

እስራኤል ቀጣዮቹ ታጋቾቿ መፈታታቸው እስከሚረጋገጥ እና በጋዛ በሚካሄደው የእስረኛ ልውውጥ ወቅት ይፈፀማል ያለችው አሸማቃቂ ሥነስርዓት እስከሚነሳ ድረስ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፍልስጤም እስረኞችን የመልቀቁን ሂደት ማዘግየቷን አስታውቃለች።

የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ፅህፈት ቤት ዛሬ እሁድ ያወጣው መግለጫ ይፋ የሆነው እስረኞችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ከኦፈር ማረሚያ ቤት እየወጡ ባሉበት ወቅት ሲሆን፣ መኪናዎቹ አዙረው ወደ እስርቤቱ ተመልሰዋል።

ስድስቱ የእስራኤል ታጋቾች ቅዳሜ እለት መለቀቃቸውን ተከትሎ ከእስር መፈታት የነበረባቸው 620 የፍልስጤም እስረኞች እስካሁን እንዳልተፈቱም ተገልጿል።

ይህ ድንገተኛ የእስራኤል መግለጫ፣ የተኩስ ማቆሙን ስምምነት እጣፈንታ ጥርጣሬ ላይ ጥሎታል።

የእስረኞቹ መፈታት መዘግየቱን የፍልስጤም አስተዳደር እስረኞች ጉዳይ ኮሚሽን ያስታወቀ ሲሆን ዌስት ባንክ ውስጥ የተቀረፀው የአሶሽዬትድ ፕሬስ ምስል፣ የእስረኛ ቤተሰቦች እጅግ በጣም በሚቀዘቅዘው አየር ውስጥ ሆነው ሲጠባበቁ እና በመጨረሻ ሲበተኑ ያሳያል።

ቅዳሜ እለት የተለቀቁት ስድስቱ ታጋቾች፣ በመጀመሪያው ዙር የተኩስ ስምምነት ይለቀቃሉ ተብለው ከተጠበቁት በህይወት ያሉ የመጨረሻዎቹ ታጋቾች ሲሆኑ፣ ይህ ዙር ከአንድ ሳምንት በኃላ ይጠናቀቃል።

ለሁለተኛው ዙር የተኩስ ስምምነት የሚደረገው ድርድር ገና አለመጀመሩም ተመልክቷል።


ነባሩ ፓስፓርት ጊዜው እስከሚያበቃ ያገለግላል
-------

የኢሜግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ኢ-ፓስፖርት ዛሬ ይፋ አድርጏል::

አዲሱ ኢ-ፓስፖርት የአንድን ግለሰብ ባዮሜትሪክ መረጃ ጨምሮ የጣት አሻራዎችን፣ የፊት ለይቶ ማወቂያ እና የኤሌክትሮኒክስ ቺፕስ ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎ ታዲያ አሁን አገልግሎት ላይ ያለው ነባሩ ፓስፖርት ምን ሊሆን ነው? የሚል ጥያቄ ያስነሳል::

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ይፋ እንዳደረገው ነባሩ ፓስፖርት የአገልግሎት ጊዜው እስከሚያበቃ ድረስ ስራ ላይ ይውላል::

ቀደም ሲል ፓስፖርት የነበራቸው የፓስፖርቱ የአገልግሎት ጊዜው እስኪያበቃ መጠቀም እንደሚችሉ ታውቋል::

አዲሱን ፓስፖርት መቀየር የሚፈልጉ ከሆነ ግን አሻራ ከሰጡ በኋላ በአስር ቀናት ውስጥ ፓስፖርቱ በእጃቸው እንደሚገባ ነው የተገለፀው፡፡

በሂደት ግን ነባሩ ፓስፖርት በአዲሱ የኢ-ፓስፖርት እንደሚተካ አገልግሎቱ ይፋ አድርጏል::

ከዚህ ቀደም ለ125 አመታት ኢትዮጵያ ትጠቀምበት የነበረውን የማንዋል ፓስፖርት ወደቴክኖሎጂ ለመቀየር በማሰብ ነው አዲሱ ፓስፖርት ይፋ የተደረገው::


ከአሜሪካ የተባበሩ ስደተኞች ወደ ኮስታሪካና ፓናማ እየተጓጓዙ ነው
---------

ከአሜሪካ የተባረሩትን ፍልሰተኞችን በጊዜያዊነት ለማስተናገድ ኮስታሪካና ሆንዱራስ ከፓናማ ጋራ ተቀላቀለዋል፡፡

በዐዲሱ የትረምፕ አስተዳደር የኢምግሬሽን ፖሊሲ ከሀገር የተባረሩና የተለያየ ሀገር ዜግነት ያላቸው 135 ስደተኞችን የጫነ አውሮፕላን ትላንት ሐሙስ ኮስታሪካ ዋና ከተማ አርፏል፡፡

65 ህፃናት ይገኙበታል የተባሉት እነዚህ ፍልሰተኞች ከኡዝቤክስታን፣ ከቻይና ከአፍጋኒስታን ከሩሲያ እና ከሌሎች ሀገሮች የመጡ ናቸው፡፡

ፍልሰተኞቹ ወደ የሀገራቸው ከመሸኘታቸው በፊት ኮስታሪካ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋራ በገባችው ስምምነት መሰረት በሀገሯ ታቆያለች፡፡

ኮስትሪካ፣ ፓናማ እና ሆንዱራስ ወደ ሌሎች ሀገሮች የሚላኩ ፍልሰተኞችን ለጊዜው ተቀብለው ለማቆየት ከዩናይትድ ስቴትስት ጋራ ስምምነት የተፈራረሙ ሀገሮች ናቸው፡፡


የታላላቆቹ የአውሮፓ ሃገራት ውርደት እና ክስረት
-----------

የአውሮፓ ሃገራትን እና የዩክሬን መንግስትን ወዲያ በሉ ብለው ኘሬዝደንት ትራምኘ ፥ መንግስታቸው በዩክሬን ጉዳይ ከሩሲያ ጋር በሪያድ ንግግር መጀመሩ ጨዋታውን ሁሉ ቀይሮታል።

በትራምኘ እርምጃ ተከዳን ያሉት የአውሮፓ ሃገራት ትላንት በፓሪስ ተሰብስበው የነበረ ይሁን እንጂ በሃሳብ ተከፋፍለው ፥ በአቋም ተለያይተው ያለ ውጤት ተበትነዋል።

ከዩክሬን ጎን ተሰልፈው ያለፉትን ሁለት አመታት ጦርነቱን በገንዘብ ፣ በመሳሪያ ፣ በሚድያ እና በዲኘሎማሲ ሲደግፉ የነበሩት ዋንኞቹ ሃገራት ፈረንሳይ ፣ ጀርመን እና እንግሊዝ የአሜሪካ መንግስት በጀመረው አዲስ ድርድር ፍፁም ልዩነት ያለው አቋም ይዘዋል።

ሁሉም ግራ ተጋብተው ተከዳን የሚል ድምፅ እያሰሙ ነው።

የአውሮፓ ህብረት መሪ የሆኑት ሶስቱ ሃገራት የጋራ በሚሉት ጉዳይ ላይ እንዲህ ያለ የተለያየ አቋም ይዘው አያውቁም እየተባለ ነው።

ፈረንሳይ የአውሮፓ ህብረት የሌለበት ድርደር በዩክሬን ጉዳይ መካሄድ የለበትም የሚል ሃሳብ ይዛ በመቅረብ ሃሳቡን ጀርመን እና እንግሊዝ እንዲደግፉ ጠይቃለች።

ከአሜሪካ መንገድ የማትወጣው እንግሊዝ ደግሞ ሪያድ ላይ ስምምነት የሚደረስ ከሆነ ሰላም አስከባሪ በዩክሬን አሰማራለሁ በማለት አቋሟን አሳውቃለች። በሌላ መልኩ ለትራምኘ መንግስት እርምጃዎች እውቅና ሰጥታለች።

ይህ የእንግሊዝ አቋም ጀርመን እና ፈረንሳይን ይበለጥ አስደንግጧል።

የጀርመን መራሄመንግስት ኦላፍ ሾልዝ የእንግሊዝ አቋም በጣሙን አስቆጥቷቸው የሃገራቱን ፍላጎት የገፋ እና ወቅቱን ያልጠበቀ ሃሳብ ሲሉ ነቅፈውታል።

የጉዳዩ ባለቤት ነን የሚሉት ሶስቱ ሃገራት እነርሱን ከጨዋታ ሜዳ ያገለለ ድርድር መጀመሩን በመቃወም የጋራ አቋም እንዲይዙ ቢታሰብም ሊሳካ አልቻለም።

የትራምኘ መንግስት ፈጣን እና ያልተጠበቀ አካሄድ ክፍፍላቸው እንዲሰፋ አድርጓል።

በፓሪስ ለምክክር ሲጠራሩ በዩክሬን የሰላም ሂደት ላይ ለመነጋገር መሆኑን ቢገልፁም " ያለፉት ሁለት አመታትን ጦርነቱን ሲደግፉ ቆይተው አሁን ከየት መጥተው ስለሰላም ለማውራት ደፈሩ " የሚሉ የስላቅ አስተያየቶች ከአሜሪካ እና ሩሲያ ሰዎች ተሰንዝሮባቸዋል።

ሶስቱ ሃገራት መቶ ቢሊየኖችን ያፈሰሱበት ጦርነት በውርደት እና ከባድ ክስረት ሊደመደም ዋዜማው ላይ እንደሆነ ተረድተዋል።


የታላላቆቹ አውሮፓ ሃገራት ውርደት እና ክስረት
-----------


የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ወታደሮች በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎችን መግደላቸው ተነገረ
----------

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በነጭ አባይ ግዛት በፈጸመው ጥቃት ጨቅላ ህፃናትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሲቪሎች መሞታቸውን የሱዳን ባለሥልጣናት እና የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ትላንት ማክሰኞ አስታወቁ።

የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ “ቡድኑ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ በሱዳን ጦር ‘አሰቃቂ ሽንፈት’ ከደረሰበት በኋላ በአል-ጊታይና አካባቢ በሚገኙ መንደሮች ውስጥ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ፈጽሟል።” ብሏል፡፡ የሱዳን ዶክተሮች ሠራተኛ ማኅበር የሟቾች ቁጥር 300 መኾኑን ሲያስታውቅ መግለጫው ቁጥሩ 433 አድርሶታል።

በሲቪሎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የሚከታተለው የአደጋ ጊዜ ጠበቆች የመብት ተሟጋች ቡድን ትላንት ማክሰኞ ማለዳ በሰጠው መግለጫ፣ “ባለፉት ሦስት ቀናት ውስጥ፣ ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ ከ200 በላይ ሰዎች በፈጥኖ ደራሽ ጥቃቶች መገደላቸውን” ጠቅሶ ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል ብሏል።


ኢትዮጵያና ሶማሊያ የመጀመሪያ ዙር የቴክኒክ ውይይት በአንካራ አካሄዱ
------------

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የመጀመሪያውን ዙር የቴክኒክ ውይይት በቱርክ አንካራ አካሂደዋል፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የተመራ የልዑካን ቡድን የመጀመሪያውን ዙር የቴክኒክ ውይይት ከሶማሊያ የልዑካን ቡድን ጋር በአንካራ አድርጓል፡፡

ውይይቱ በፈረንጆቹ ታህሳስ 11 ቀን 2024 በቱርክ አመቻችነት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተደረሰውን ስምምነት ለማስተግበር የሚያስችል መሆኑን በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል፡፡


የህዳሴ ግድብ አምስተኛው ተርባይ ኃይል ማመንጨት ጀመረ
-----------
የቅድመ ኃይል ማመንጨት ሙከራ ስራ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኖባቸው ወደ ዋና ስራቸው እንዲገቡ ዝግጁ ከሆኑ ተርባይኖች መካከል ተርባይን ቁጥር 6 የሙከራ ስራው ተጠናቆ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀምሯል።

አሁን ባለው ተጨባጭ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም እስከ 401.26 MW ኃይል እያመነጨ ይገኛል።

እያንዳንዱን የውኃ ጠብታ ወደ ኃይል በመቀየር 400 ምጋ ዋት ኃይል ከሚያመነጩት 11 ተርባይኖች መካከል አምስተኛው ተርባይን ቁጥር ስድስት ወደ ኃይል ማምረት ስራ ገብቷል፡፡

በተጨማሪ ተርባይን ቁጥር 5 ደግሞ የኮሚሽኒንግ ስራው የመጨረሻ ምዕራፍ ሙከራ ላይ ይገኛል፡፡

የግድቡ ስድስተኛው ተርባይን የሆነው ተርባይን ቁጥር 5 በቅርቡ ማለፍ ያለበትን የሙከራ ሂደቶቹን አጠናቆ ወደ ማመንጨት ስራ እንደሚገባም የማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቱ መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ቀደም የቅድመ ተርባይን ቁጥር 8 እና ተርባይን ቁጥር 7 ኃይል የማምረት ሂደት መግባታቸው ይታውቃል፡፡

Показано 20 последних публикаций.