የጋዜጠኛ ስሜነህ ባይፈርስ ‹‹የግዞት ሰንሰለት›› መጽሐፍ
**********
ጋዜጠኛ ስሜነህ ባይፈርስ፤ ‹‹የግዞት ሰንሰለት›› በተሰኘው መጽሐፉ፣ ታሪክ ከቁብ በማይቆጥረው የሁሴን ሀጂ አልዬ የፖለቲካ ህይወት በቅሎ አፈናጥጦ፤ አንባቢን በምርጫ 97 ዓውድ አስገብቶ፤ ብዙዎቻችን ጨርሶ በማናውቃት አንዲት የገጠር ወረዳ (ኮኪር ገደባኖ ጉታዘር) እያመላለሰ፤ ለ27 ዓመታት ከእኛ ጋራ ሲኖሩ ሳናውቃቸው፤ ታሪክ በመጋረጃው ከሸፈናቸው ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራቶች›› ጋር ያስተዋውቀናል፡፡
‹‹ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት›› በተባለ ድርጅታዊ መርህ የተበተበ ጥብቅ ፖለቲካዊ መዋቅር ከጫፍ ጫፍ የዘረጉት አብዮታዊ ዴሞክራቶች፤ ሀገሪቱን እንዴት ያስተዳደሩ እንደ ነበር ሊያሳየን የሚሞክረው ደራሲው ስሜነህ ባይፈርስ፤ በ‹‹ግዞት ሰንሰለት›› የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን ሴራ የራሱን ግምገማና እውነት ያለ ምንም መሳቀቅ እየገለጸና ሰውኛ የሆኑ አስረጂ ክስተቶችን እየጠቀሰ፤ እንደ ልብ-ወለድ ድርሰት ሳይሰለች የሚነበብ ድንቅ መጽሐፍ አበርክቶልናል፡፡
የኢህአዴግ የፖለቲካ ርዕዮት ተቋዳሽ እና ዋና ተዋናይ የነበረው ስሜነህ፤ ጥልቅ የፖለቲካ ርዕዮታቸውን በውል ሳንረዳ፤ ዛሬ ድረስ ብዙዎቻችን በጥላቻ ዓይን የምንመለከታቸውን የድርጅቱን ከፍተኛ አመራሮች እውነተኛ ስብዕና በግልጽ ባሰፈረበት ‹‹የግዞት ሰንሰለት›› የተሰኘ መጽሐፉ፤ በቁጥር ቀላል የማይባል የኢትዮጵያ ሕዝብ በጭፍን ጥላቻ እየዳከረ፤ ስለ ድርጅቱ መዋቅር እና ስለ ርዕዮቱ ምንነት ሳያውቅ ስርዓቱ ለ27 ዓመታት እንዲቆይ ማድረጉን በበርካታ አስረጂዎች አስደግፎ ያብራራልናል፡፡
‹‹የግዞት ሰንሰለት››፤ ስሜነህ ጋዜጠኛ ሆኖ በሰራባቸው ‹‹ፋና›› እና ‹‹ዋልታ›› በተባሉ ሚዲያዎች ያስተዋላቸውን ‹‹የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት›› የረዘሙ የግዞት ሰንሰለቶች ሀሳብን በነጻ ከመግለጽ መብት ጋር አያይዞ ሂስ ይሰነዝራል፡፡
በተለይ በዋልታ ‹‹የነጻ-ሐሳብ›› ፕሮግራም አዘጋጅ ሆኖ በሰራባቸው ዓመታት፤ የግዞት ሰንሰለቱ አላለውስ እያለው፤ ከነአካቴው ሳይተላለፉ የቀሩ አስገራሚ ቃለ-መጠይቆችን እና በአሳፋሪ ሁኔታ እየተቆረጡ የወጡ ለተመልካቾች የተሰወሩ አንዳንድ ነገሮችን አደባባይ ያወጣበትን ይህን መጽሐፍ የሚያነብብ ተደራሲ፤ ከቀረጻ በፊት እና በኋላ ያሉትን የሚዲያ የግዞት ሰንሰለቶች በመመልከት፤ በንዴት፣ በግርምት እና በእፍረት ስሜቶች ይታሰር ይሆናል።
ከቴዎድሮስ ተ/አረጋይ የፌስቡክ ገጽ የተወሰደ!!!