Healthify Ethiopia


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


Welcome to Healthify Ethiopia!
At Healthify Ethiopia, we believe that access to quality health information is the foundation of a healthier society. It aims to empower all Ethiopians with reliable, evidence-based health knowledge, delivered a click away.

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


የእነዚህ በርካታ የቡና ጥቅሞች ተካፋይ ለመሆን ምን ላድርግ?


✍️ ቡና በመጠኑ መጠጣት አስፈላጊ ነው። የቡና ጤና ትሩፋቶችን ለማግኘት ከልክ ያለፈ ቡና መጋት አይፈልግም። በቀን ከሶስት ስኒ ያልበለጠ በቂ ነው።

✍️ ጸረ ተባይ የበዛበት ከሚሆን ይልቅ ኦርጋኒክ የተፈጥሮ ቡናን ይምረጡ።

✍️ በጣም አምሽተው ቡና ከመጠጣት ይልቅ በመክሰስ ሰአት በፊት ቢሆን እንቅልፍ እንዳይረብሽ ይረዳል።

✍️ ቡናን ማብዛት የልብ ምት ሊያዛባ ይችላል። የእንቅልፍ መዛባትና ተያያዥ ጭንቀት ሊያስከትል ይችላል።

✍️ በተጨማሪም የቡና ጥቅሞችን ለማጣጣም ቡና ሲጠጡ ማጣፈጫ (ስኳር፣ ክሬም፣ ጨው ወይም ሌላ ጤናን ሊጎዳ የሚችል) አይጨምሩ።

👉 ያስታውሱ ቡና ለጤናማ አኗኗር አንዱ አካል ያድረጉት። ሙሉ ጤናን ለመጠበቅ እና ደስተኛ ህይወት ለመምራት የተስተካከለ አመጋገብ፣ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ በቂ እንቅልፍ መተኛት፣ ጭንቀት አለማብዛት እና ከሱስ የጸዳ አኗኗር ዘይቤ ወሳኝ ነው።

#CoffeeLovers #HealthBenefitsOfCoffee #CoffeeAndWellness #DrinkCoffeeLiveLonger #HealthyLifestyle #CoffeeScience #BrainHealth #HeartHealth #CoffeeForLongevity

YouTube: https://www.youtube.com/@healthifyethiopia

@HealthifyEthiopia


ቡና ለጤና

ያለ ቡና መዋል ለብዙዎች የማይቻል ነው። ቀኔ የሚጀምረው የጧት ቡናየን ስቀምስ ነው የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም።

መልካም ዜና! ቡና በመጠኑ ሲጠጣ ከማነቃቃት ባሻገር በርካታ የጤና ጥቅሞች ይሰጣል። በመልካም መኣዛና ጥኡም ጣእም ከመደሰት በላይ ቡና ጤናን ይጠብቃል።

1️⃣ ቡና እድሜን ያረዝማል (Longevity)

እንደ ጆን ሆፕኪንስ ተቋም መረጃ መሰረት ቡናን የሚያጣጥሙ ሰዎች በልብ ህመም፣ ስትሮክ፣ ስኳር ህመም፣ ኩላሊት ህመም ወዘተ ያሉ ገዳይ በሽታዎችን ስለሚቀንስ ጤናማ ረጅም እድሜ ለመኖር ይረዳል። ስለሆነም ቡና ከመጠጥነት በላይ የሆነ እድሜ የሚያረዝም የህይወት መድህን ነው ማለት ይቻላል።

2️⃣ የዘረመል (ዲ ኤን ኤ) ጤናን ይጠብቃል

ቡና ተፈጥሯዊ የዲኤን ኤ ጠባሳ እና ብልሽት ሊቀንስ ይችላል የሚሉ ጥናቶች አሉ።

3️⃣ ለጉበት ጤና ይረዳል

ቡና ጉበት ላይ የአደጋ እንዳይደርስ ይከላከላል።

4️⃣ የካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል

በተለይም የአንጀት ካንሰር የመያዝ እድልን ይቀንሳል።

5️⃣ የደም ስኳር መጠን እንዳይጨምር ይረዳል

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቡና በትንሹም ቢሆን የደም ስኳር መጠን እንዳያሻቅብ ይረዳል። ቡና የሚጠጡ ሰዎች የተሻለ የግሉኮስ ሜታቦሊዝም ስላላቸው በስኳር የመያዝ እድልን ይቀንሳል።

6️⃣ ለልብ ጤና ይጠቅማል

በቀን ከአንድ አስከ ሶስት ስኒ ቡና መጠጣት ለልብ ጤንነት ይጠቅማል የሚሉ ማስረጃዎች አሉ። በልብ ድካም የመያዝ እድልን ይቀንሳል።

7️⃣ የአእምሮ/አንጎል ጤናን ይጠብቃል (Neuroprotective Effects)

በቀን ከአንድ አስከ ሶስት ስኒ ቡና መጠጣት የመርሳት በሽታ (አልዛይመር) ስጋትን ይቀንሳል። በተጨማሪም ከእድሜ ጋር የሚመጣ የእጅ መንቀጥቀጥ (Parkinson's disease) ለመቀነስ ይረዳል። ሰውነት ፓራላይዝ የሚያደርገው የአንጎል መታዎክ (Stroke) በእጅጉ ይቀንሳል።

#CoffeeLovers #HealthBenefitsOfCoffee #CoffeeAndWellness #DrinkCoffeeLiveLonger #HealthyLifestyle #CoffeeScience #BrainHealth #HeartHealth #CoffeeForLongevity

YouTube: https://www.youtube.com/@healthifyethiopia

@HealthifyEthiopia


የስኳር ህመም ሳይታወቅ የሚዘገየው ለምንድን ነው?

በአለማችን የስኳር ህመም ተጠቂዎች ከግማሽ ቢሊዮን በላይ አሻቅቧል።
በየአምስት ሴኮንዱ አንድ ሰው በስኳር ህመም ምክንያት ይሞታል።
በየሰላሳ ሴኮንዱ አንድ ሰው በስኳር ምክንያት እግሩ ይቆረጣል።
አጠቃላይ በምድራችን ላይ ለጤና ከሚመደበው በጀት ከ10 በመቶ በላይ ለስኳር ህክምና ብቻ ይውላል።

የበለጠ የሚያሳስበው ደግሞ በቀጣይ አመታት ስርጭቱ ከፍተኛ ጭማሪ ያሳያል ተብሎ ይገመታል። ምንም የመቀነስ አዝማሚያ ጭራሽ እያሳየ አይደለም።

ሌላው ገራሚ ነገር ደግሞ ስኳር ካለባቸው ግለሰቦች ግማሹ ስኳር እንዳለባቸው አያውቁም። ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ላይ ይህ ስኳር እንዳለባቸው የማያውቁት ሰዎች ቁጥር ወደ 70 በመቶ ይጠጋል።

ለመሆኑ የስኳር ህመም ሳይታወቅ የሚዘገየው ለምንድን ነው?

የስኳር ህመም በተለይም ዓይነት 2 ለብዙ ዓመታት ሳይታወቅ ሊቆይ የሚችል በሽታ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት በአመዛኙ ምልክት አልባ ስለሆነ ነው። ዝምተኛው ገዳይ (silent killer) የሚባለው ለዚያ ነው። አንደሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ሁሉ ግልጽ መገለጫ ምልክቶች የሉትም።

አብዛኛዎቹ ስኳር ያለባቸው ሰዎች ምንም አይነት የህመም ስሜት ሳይሰማቸው ለብዙ አመታት ሊቆዩ ይችላሉ። ነገር ግን ስኳሩ ሰውነታቸዉን እየጎዳው እንደሆነ ማስተዋል ይገባል።

ስለዚህ ስኳር ህመምን ገና ሳይብስ ለማዎቅ ዋነኛው መፍትሄ በየጊዜው የስኳር ምርመራ በማድረግ ነው። ለዚህ ነው መደበኛ ምርመራ በጣም አስፈላጊ የሚሆነው። በተለይም ተጋላጭነት ያለባቸው ሰዎች ቢያንስ በአመት አንዴ ስኳራቸውን መታዬት ያስፈልጋቸዋል።

በተለይ የስኳር መጠኑ በጣም ከፍ ሲል የሚታዩ ምልክቶች ለመጠቀስ ያህል የማያቋርጥና የማይረካ የዉሃ ጥም፣ ቶሎቶሎና አብዝቶ መሽናትና ሃይለኛ የድካም ስሜት ይገኙበታል።

ብዙውን ጊዜ የሚታዩት ምልክቶች ተጓዳኝ የጤና እክሎች አመላካች ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህም የእይታ መደብዘዝ፣ የቁስል ቶሎ አለመዳንና ማመርቀዝ፣ የእግር መደንዘዝና መቆጥቆጥ፣ ስንፈተ ወሲብ ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ።

ያስታውሱ፤ የስኳር ህመም ምንም አይነት የህመም ምልክት ላያሳይ ይችላል። ስለሆነም መደበኛ የስኳር ምርመራ በማድረግ ጤንነትዎን ይጠብቁ።

Telegram: https://t.me/HealthifyEthiopia

YouTube: https://www.youtube.com/@healthifyethiopia


አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ካለማድረግ (sedentary time) የሚመጣውን የጤና መዘዝ ለመቀነስ ምን እናድርግ?

1️⃣ ለረጅም ሰዓት አለመቀመጥ በተለይም ከአንድ ሰዓት በላይ ካለእንቅስቃሴ አለማሳለፍ

ዘመናዊ ህይወታችን በቴክኖሎጅ ቀላል እየሆነ ስለመጣ ብዙዎቻችንን ስንቅስቃሴ አልባ የአኗኗር ዘይቤ እንድንከተል ተገደናል። ካለእንቅስቃሴ ብዙ መቀመጥ ከበርካታ የጤና ችግሮች መንስኤ እንደሆነ ይታመናል። ለረጅም ሰአታት መቀመጥ ለበርካታ በሽታዎች የመጋለጥ እድልን በእጅጉ ይጨምራል። ስለዚህ ለረጅም ሰዓት አለመቀመጥ በተለይም ከአንድ ሰዓት በላይ ካለእንቅስቃሴ አለማሳለፍ ይመከራል።

2️⃣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መክሰስ (exercise snack) ማዘውተር

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ 'መክሰስ' ሲባል በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለትንሽ ደቂቃም ቢሆን አጭር የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራትን ነው። በተቻላችሁ ጊዜ በቤት ውስጥ ወይም በስራ ቦታ የመንቀሳቀስ እድሎችን መፍጠር እንደማለት ነው። በተለይም ስራ በዝቶብን ለስፖርት ጊዜ ስናጣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መክሰስ ‘መብላት' ባለንበት ቦታ ለትንሽ ደቂቃ ብናፍታታ አስገራሚ የጤና ጥቅሞችን ያስገኛል። ለምሳሌ ቢሮኣችን ጸሃፊያችንን ወረቀት አምጭልኝ ብለን ከማዘዝ እራሳችን ተንቀሳቅሰን ኮፒ ማድረግ፣ ደረጃ ወጣ ወረድ ማለት ሊሆን ይችላል። ወደ ምሳ ለመሄድ መኪና ከምንይዝ በእጋራችን የስፖርት ስናክ ማድረግ ማለት ነው። ስልክ ስናወራም እየተንቀሳቀስን ቢሆን ይረዳል። ከወዳጅ ጋር ስንቀጣጠር አንድ ቦታ ቁጭ ከማለት ወዳሉበት በእግር መሄድም ሊሆን ይችላል። አውቶቡስ ከተሳፈሩ ቀደም ብሎ ከፌርማታ ይውረዱ እና ቀሪውን መንገድ ይራመዱ።

3️⃣ በየቀኑ ከአስር ሺህ እርምጃ የማያንስ በእግር መጓዝ

በቀን ከ10,000 እርምጃዎች በላይ መንቀሳቀስ ጤናማ ለመሆን ይረዳል። በስልካችን ወይም የእጅ ሰዓታችን የእንቅስቃሴ መከታተያ በመጫን በየቀኑ ምን ያህል እርምጃ እንደተጓዝን በማየት በየጊዜው ለማሻሻል መትጋት ጠቃሚ ነው።

4️⃣ በየቀኑ ከ30 ደቂቃ የማያንስ እስኪያልብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በተለይም መካከለኛና ከዚያ በላይ ኃይለኛ የኤሮቢክ እንቅስቃሴ እና ጡንቻን የሚያጠናክሩ ልምምዶችን መስራት ይመክራል።

✍️ የበለጠ በሰራን ቁጥር የላቀ የጤና ጥቅም እናገኛለን

Telegram: https://t.me/HealthifyEthiopia

YouTube: https://www.youtube.com/@healthifyethiopia




🎉 Celebrating 5 Years of Healthify Ethiopia on Telegram! 🎉

Dear Family,

Wow—5 years!

It’s been an incredible journey of sharing reliable health information, empowering our community, and growing together.

Your support, engagement, and trust have made this platform what it is today!

Thank you for being part of this mission, for every message, every share, and every moment you’ve spent spreading health awareness.

Here’s to many more years of healthifying Ethiopia together!

Stay informed, and stay healthy! 💙

#HealthifyEthiopia #5YearsStrong #ThankYou


የማህፀን መውጣት ችግር
--------------------------------------------
የማህፀን መውጣት ችግር ማለት የውስጠኛው የማህፀን ክፍል ቦታውን በመልቀቅ ወደ ውጭ መውጣት ማለት ሲሆን፣ ይህ ችግር በአብዛኛው የውስጠኛውን የማህፀን ክፍል በቦታው የሚይዙት ጡንቻዎች በተለያዩ ምክንያቶች መደበኛ ስራቸውን መስራት ሳይችሉ ሲቀሩ የሚከሰት የህመም አይነት ነው፡፡

ዋና ዎና መንስሄዎች

እርግዝናና ወሊድን ተከትሎ የሚከሰትና
ከማረጥ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ናቸው
በተጨማሪም፡- ወደ ሆድ አካባቢ ግፊትን የሚጨምሩ ነገሮች ለምሳሌ፡- የረዥም ጊዜ ሳል፣ የሆድ ድርቀት እንዲሁም ከባድ ነገሮችን አዘወትሮ ማንሳት የመሳሰሉት ናቸው
የማህጸን መውጣት ችግር ያለባቸው የሚያሳይዋቸው ምልክቶች
አብዛኛው ታማሚዎች ምንም አይነት የህመም ስሜት ምልክት የላቸውም ምልክቱ መታየት ሲጀምር፡-ዋነኛው ምልክት የውስጠኛው ልጅ የሚይዘው ማህፀን ወደ ውጪ ሲወጣና ታማሚዋ በብልቷ በኩል የወጣ ስጋ መሰል ነገር ስታይ ነው ::

በተጨማሪ የሚታዩ ምልክቶች ፡-

የሽንት ምንም ሳይታወቅ መፍሰስ
ወደ ዳሌ አጥንት አካባቢ ከባድነት ወይም ሙሉነት ስሜት መኖር
ከማህፀን አካባቢ ያበጠ ነገር መኖር
የወገብ ህመም
የዳሌ አጥንት አካባቤ የግፊት ስሜት መኖር

የማህጸን መውጣት ህክምና

በመድሀኒት የሚደረግ ህክምና ፡- ማህጸን አንድ ጊዜ ከወጣ በራሱ የመመለስ እድል የለውም፡፡ በመድሀኒት የምናደርገው ህክምና የቀዶ ጥገና ህክምና ለማድረግ ምቹ ባልሆነበት ጊዜ ጊዚያዊ መፍትሄ ለመሰጠት ነው፡፡በቀዶ ጥገና የሚደረግ ህክምና ለማህፀን መውጣት ችግር መፍትሄ ነው

የማህጸን መውጣት ችግር መከላከያ ዘዴዎች

በእርግዝና ወቅት፡- የዳሌ አጥንት እንቅስቃሴ ማድረግ
በወሊድ ወቅት፡- የማህጸን በር ሙሉ ለሙሉ እስከሚከፍት አለመግፈት
ከወሊድ በኃላ ማህጸንን ወደ ታች ከሚገፋ ነገሮች እንደ ከባድ ነገሮችን ማንሳት፣ የሆድ ድርቀት እንዲሁም የዳሌ አጥንት እንቅስቃሴ ማድረግ
ከማረጥ ጋር ተያይዞ ለሚመጣ የማህጸን መውጠት ችግር የሆርሞን መተካት ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ

የማህጸን መውጣት ችግር ባይታከም የሚያስከትላቸው ጉዳቶች
የወጣው ማህጸን መቁሰል የማህጸን በር መላላጥ ፣የሽንት መታፍን/ ሽንት እንደልብ አለመውጣት፣የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እና የማህጸን መውጣት መባባስ ናቸው::

@HealthifyEthiopia


🌟 ወሳኝ የጤና መረጃን እና ዜናዎች ለማግኘት የሚረዳ የቴሌግራም ቻናል 🌟

በዚህ ተለዋዋጭ አለም ውስጥ ሳይንሳዊ እና ወቅታዊ የጤና መረጃ ማግኘት ጤናን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው።
Healthify Ethiopia

በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ላይ አዳዲስ መረጃዎችን የሚሰጥ ጠቃሚ የቴሌግራም ቻናል ነው።

✍️ የስኳር፣ ውፍረት፣ ኮሌስትሮል እና ሌሎችም የሆርሞን ጤና

✍️ የጥርስ እና አፍ ጤና አጠባበቅ

✍️ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ዙሪያ ሰፊ መረጃ

✍️ በተለመዱ የቀዶ ጥገና ህክምናዎች እና ከኦፕሬሽን የማገገም ሂደት

✍️ የወንዶችና ሴቶች ስነ ተዋልዶ ጤና

✍️ አዳዲስ የጤና ዜና

✍️ በተለያዩ የጤና ጉዳዮች የጥያቄ እና መልስ መድረክ


የጤና መረጃዎችን በቀላሉ እንዲቆረጠም አድረገው የሚያቀርቡ ትጉህ ባለሙያዎች የሚሰሩበት ቻናል ነው።

የጤና ግንዛቤን ለማዳበር እና ጤና-ነክ መረጃዎች እንዲደርሳቸው ሌሎችን ብትጋብዙ ያተርፉበታል።

Telegram: https://t.me/HealthifyEthiopia

YouTube: https://www.youtube.com/@healthifyethiopia


የትራምፕ የጤና ፖሊሲ እርምጃዎች ምንድን ናቸው?

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስልጣን እንደተቆናጠጡ ከፈረሟቸው ፕሬዝዳንታዊ ትእዛዛት መካከል ጤናን የሚመለከቱ ስር ነቀል ፖሊሲዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ ሆነዋል። አሜሪካን ከአለም ጤና ድርጅት (WHO) ከማስወጣት እስከ ቁልፍ የጤና ኤጀንሲዎች እስከ መዝጋት ድረስ ሰፊ ክርክር አስነስተዋል።

1️⃣ ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) መውጣት፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት ለመውጣት ሂደቱን የጀመሩት ድርጅቱ የዓለም ጤና ጉዳዮችን በተመለከተ ያለውን ቸልተኝነት በመንቀፍ ነው። ትራምፕ የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመግታት አፋጣኝ እና ግልጽ ስራ ባለመስራቱ ለቫይረሱ መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል ብሎ ያምናል። የቻይና ፖለቲካዊ ጣልጋ ገብነት አለበትም ሲሉ ከሰዋል።

ይህ እርምጃ የአለም አቀፋዊ የበሽታ ልየታ፣ ክትትል እና ምላሽ አሰጣጥ ስርዓቶችን ያዳክማል በሚል ስጋት ፈጥሯል።

2️⃣ የአሜሪካ የጤና ተቋማትን ኮሚኒኬሽን መዝጋት፡

የአሜሪካ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል እና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣንን ጨምሮ ሁሉም የፌደራል ጤና ኤጀንሲዎች የውጭ ግንኙነቶችን እንዲያቆሙ ትእዛዝ ተላልፏል። ይህ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ መመሪያ ሲሆን አዲስ የበሽታ ወረርሽኝ ሲነሳ ወቅታዊ መረጃዎችን ለተቀረው አለም መንግስታትና ህዝብ ለማሰራጨት መዘግየት ይፈጥራል የሚል ስጋትን ጭሯል።

3️⃣ የዲኢአይ (Diversity, Equity, and Inclusion, DEI) መታገድ

ይህ ፕሮግራም በአሜሪካ ተቋማት ውስጥ አካታችነት፣ እኩልነት እና ፍትሃዊነትን ለማስፈን የወጣ ፕሮግራም ሲሆን ትራምፕ እንዲቆም ፈርሟል። ይህ እርምጃ በተቋማት ስራ ውስጥ ፍትሃዊ አካታችነት እና እኩልነት ለማስፈን የሚደረግውን ጥረት ወደኋላ ሊመልስ ይችላል ሲሉ ብዙዎች ተችተዋል።

4️⃣ የሮበርት ኬኔዲ የጤና ሚኒስቴር ሆኖ መሾም፡

ይህ ሰው በክትባት እና አንዳንድ የጤና አሰጣጥ ስርአቶች ላይ አወዛጋቢ አቋም እንዳለው ስለሚታዎቅ ስራዉን እንዴት ይመራው ይሆን የሚል የሰላ ክርክር አስነስቷል።

ለታዳጊ ሃገራት ጤና ምን ተጽእኖ ያመጣል?

እነዚህ እርምጃዎች የአሜሪካ መንግስት በጤና ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እያሳየ መሆኑን አመላካች ናቸው። ይህ ፖሊሲ በአሜሪካ ድጋፍ የሚሰሩ በርካታ የጤና ዘርፎችን፣ ህክምናዎችና እና ዓለም አቀፍ የጤና ትብብር ስራዎች ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል ሲሉ የጤና ባለሙያዎች እና ተሟጋቾች ስጋታቸውን አንጸባርቀዋል።

ለብዙ ታዳጊ ሃገራት የጤና ወጪ ከፍተኛውን ድጋፍ የምታደርገው አሜሪካ ናት። ስለሆነም የዚህ ድጋፍ መቀነስ አስፈላጊ የጤና ፕሮግራሞች የገንዘብ እጥረት ያጋጥማቸዋል። ለምሳሌ
👉 የክትባት ዘመቻዎች፣
👉 ኤችአይቪ/ኤድስ፣
👉 ቲቢ እና
👉 ወባን መከላከል
የመሳሰሉት ፕሮግራሞች በአሜሪካ ድጋፍ ላይ ጥገኛ ናቸው። የአሜሪካ ገንዘብ ድጎማ ከቀነሰ እነዚህ ወሳኝ የጤና አገልግሎቶች አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ።

እነዚህ ፖሊሲዎች በኢትዮጵያ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ምን አንድምታ ይኖራቸዋል ብለው ያስባሉ? ሃሳብዎትን ያጋሩን!

ቴሌግራም @HealthifyEthiopia
YouTube https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia


ፕሬዝዳንት ትራምፕ - ዩናይትድ ስቴትስን ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የመውጣት ሂደት የሚያስጀምረውን የሥራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ (Executive Order) ፈረሙ።

አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ከሚያደርጉ አገሮች ግንባር ቀደሟ እንደሆነች ይታወቃል።

ከዚህ ቀደም ፕሬዝዳንቱ "ድርጅቱ ቻይናን ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተጠያቂ ማድረግ ሳይችል ቀርቷል" ካሉ በሗላ አክለውም ቻይን ለመቅጣት የሚወስዷቸውን እርምጃዎች ይፋ ሲያደርጉ “ቻይና የዓለም ጤና ድርጅትን ሙሉ በመሉ ትቆጣጠረዋለች” ማለታቸው ይታወሳል።

ቴሌግራም @HealthifyEthiopia
YouTube https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia


የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ለህጻናት የስክሪን ጊዜ ገደብ መመሪያ

ከልክ በላይ የስክሪን ጊዜ በልጆች አካላዊ እንቅስቃሴያቸው፣ በማህበራዊ ግንኙነታቸው እና ጤናማ የእንቅልፍ ስርዓታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያመጣል። የአእምሮ እደገትም ያዘገያል። የአይንና እይታቸው እድገት ላይም ተጽእኖ አለው። አሁን አሁን በርካታ ልጆች የእይታ መነጽር እምዲጠቀሙ ያስገደደው አንዱ ምክንያት ከልክ ያለፈ በልጅነት ኤሌክትሮኒክስ ስክሪን ላይ ማፍጠጥ እንደሆነ የሚጠቁሙ ጥናቶች እየተሰሙ ነው። ስለሆነም በተልቻለ መጠን ልጆች ስክሪን ላይ የሚያሳልፉትን ጊዜ መገደብ ይገባል።

ለልጆችና ታዳጊዎች የስክሪን ጊዜ ገደብ መመሪያ ምን ያህል ነው?

ከሁለት አመት በታች ያሉ ህጻናት ምንም አይነት ኤሌክትሮኒችስ ስክሪን ፈጽሞ ማየት የለባቸውም።

ከሶስት እስከ አስራ ስምንት አመታ ያሉ ልጆች ደግሞ የስክሪን ጊዜያቸው ከሁለት ሰዓት መብለጥ የለበትም።

የልጆቻችንን የስክሪን ጊዜ ለመቀነስ ምን እናድርግ?

ህጻናት ለአጠቃላይ እድገታቸው መሳለጥ መጫወት፣ ማንበብ እና ከቤተሰብ ጋር ማህበራዊ መስተጋብር መፍጠር እንጅ ስልክ፣ ቴለቪዥን እንዲሁም ቪዲዮ ላይ እንዲያሳልፉ መፍቀድ የለብንም።

የልጆችን ስክሪን ጊዜ ገደብ (screen time curfew) በማበጀት ልጆችን መቆጣጠር ያስፈልጋል።

ነገር ግን ልጆችን በመከልከል መቆጣጠር ከባድ ነው። በዋናነት የሚማሩት ወላጆችን በማየት ስለሆነ ወላጆች ህጻናት ባሉበት ስልክ ባለመነካካት፣ ቴሌቪዥን በማጥፋት ለልጆቻቸው አርዓያ መሆን ይኖርባቸዋል።

Youtube: https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia

@HealthifyEthiopia


የእባብ መነደፍ አደጋ ( Snake Bite )

✅በአገራችን ካሉት እባብ አይነቶች ውስጥ መርዛማ የሆኑት ጥቂቶች ናቸው፡፡

✅ የብዙዎቹ ንድፊያ ለህይወት አያሰጋም::

ስለዚህ ከተነደፈ በጣም መርበትበት ወይም አላስፈላጊ መረበሽ ውስጥ መግባት አያስፈልግም፡፡ ነገር ግን መርዛማ አለመሆኑ እስኪጣራ ጊዜ ስለሚፈጅ አስፈላጊውን የመጀመሪያ እርዳታ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

በእባብ የተነደፈ ሰው ምን አይነት ምልክቶችን ያሳይል ?

ከንድፊያ በኋላ የእባቡ ጥርስ ያረፈባቸው ቁስሎች ይኖራሉ፣ አካባቢው ሊያብጥ ይችላል፡፡ የቆዳ ቀለምም በዚያ አካባቢ ሊለወጥ ይችላል፡፡ እንደ እባቡ አይነት ሌሎች ምልክቶች ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ አይን ብዥ ማለት፣ ማላብ፣ መተንፈስ ችግር፣ የአፍ መኮላተፍ ፣ መዝለፍለፍ እና የአካል መንቀጥቀጥ ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡

✅ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ምን እናድርግ ?

የተነደፈውን ሰው ከእባቡ ማራቅ።

የተነደእውን ሰው ማረጋጋት ፣ እንዲንጋለሉ ማድረግ፡፡

የባለሙያ እርዳታ ወዲያውኑ እንዲገኝ ማድረግ፡፡

መርዝን በአፍዎ ለመምጠጥ ሙከራ አያድርጉ፡፡ አይጠቅምም፡፡

የተነደፈውን የሰውነት ክፍል አለመነቃነቅ (መርዙን ስርጭት ለመቀነስ)፡፡

በረዶ ወይም ቀዝቃዛ ነገር ቁስሉ ላይ አያድርጉ፡፡ አይጠቅምም ሊጐዳ ይችላል፡፡

የመርዙን ስርጭት ለመቀነስ ከቁስሉ በላይ (በቁሰሉና በልብ መሃከል) በፋሻ በጣም ሳይጠብቅ ይሰሩት፡፡ (በጣም ከጠበቀ የበለጠ አደጋ ይደርሳል)::

ወደ ሐኪም ቤት መውሰድ ካለብዎ የተነደፈውን አካል እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ::ይህም የእባቡ መርዝ ወደ ሰውነታችን በጡንቻዎች እንቅስቃሴ በሊንፋትክ ( lymphatic system ) እንዳይሰራጭ ይጠቅመናል።

እባቡን ከርቀት ፎቶ ማንሳት ( የእባቡን አይነት ለመለየት) ::


በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም (gestational diabetes, GDM) የህክምና ግቦች ምንድን ናቸው?

በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የስኳር ህመም እንዳለቦት ከታወቀ — አትደንግጡ። የስኳር ቁጥጥርን በአስተማማኝ ግብ ውስጥ ካስተካከሉ እናት ጤና፤ ልጅም ደህና መሆን ይቻላል።

ለጤናማ እርግዝና ስለስኳር ህክምናው ግቦች ጠንቅቆ ማወቅና መረዳት ይፈልጋል። ውጤታማ ህክምና የስኳር ቁጥጥር እቅድ ማውጣት እና ግልጽ የሕክምና ግቦችን በማዘጋጀት ይጀምራል።

የደም ስኳር መጠንን ጤናማ በሆነ ክልል ውስጥ መቆጠጠርን ያካትታል። በአለም አቀፋዊ የሕክምና መመሪያዎች የሚደገፉት የስኳር ግቦች እንዲህ ናቸው፡-

1️⃣ የባዶ ሆድ የስኳር መጠን፡ ከ70 እስከ 95 mg/dL

2️⃣ ከምግብ ከአንድ ሰዓት በኋላ የስኳር መጠን፡ ከ140 mg/dL በታች

3️⃣ ከምግብ ከሁለት ሰአት በኋላ የስኳር መጠን፡ ከ120 mg/dL በታች

እነዚህን ግቦች ማሳካት ለእናትም ሆነ ጽንስ ጤና ወሳኝ ነው። የጽንስ መፋፋትና ክብደት ከፍ ማለት (macrosomia)፣ ከምጥ ጋር የተያያዙ ችግሮች፣ የጽንስ መታፈን፣ ህጻኑ እንደተወለደ መተንፈስ መቸገር፣ ወዘተ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመቀነስ ስኳርን እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ማስተካከል ይገባል።

እነዚህ ግቦች ለእያንዳንዷ እናት በሚመች መልኩ በትንሹ ሊለያዩ ይችላሉ። የእያንዳንዷን እናት ጤና፣ የአኗኗር ዘይቤ፣ የአመጋገብ ምርጫዎች እና ለመድሃኒት ያላትን ምላሽ ከግምት ያስገባ መሆን ይገባዋል። ይህን ከጤና ባለሙያው ጋር በመመካከር ማስተካከል ይችላሉ።

ስለ ጂዲኤም ጥያቄዎች አሉዎት? አስተያየትዎትን ይጻፉልን።

ቴሌግራም @HealthifyEthiopia
YouTube https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia


ለታይሮይድዎ ጤናማ አመጋገብ

የእርስዎ ታይሮይድ በልዩ ፍቅር የሚመርጠው ምግብ እንዳለው ያውቃሉ? ያለዚህ የምግብ አይነት ታይሮይድ በትክክል ላይሰራ ይችላል።

በዚህ ጽሁፍ ለታይሮይድ አስፈላጊ ስለሆነው አዮዲን እንነጋገራለን!

ታይሮይድ በጣም የሚወደው ምግብ አዮዲን ነው። አዮዲን ለታይሮይድ አስፈላጊ ነው። ያለ አዮዲን ወሳኝ ሆርሞኖችን ማምረት አይችልም።
ነገር ግን ሰውነታችን በራሱ የሚፈልገውን አዮዲን ሊያመርት አይችልም - የግድ ከምግብ ማግኘት አለበት።

በአዮዲን የበለፀጉ ምግቦች ምን ምን ናቸው?
1️⃣የባህር ምግቦች ዋነኛ የአዮዲን ምንጭ ነው።

2️⃣ በቂ አዮዲን ያለው አካባቢ የሚመረቱ አትክልቶች፣

3️⃣የወተት ተዋጽኦዎችን እና

4️⃣ በአዮዲን የበለጸገ ጨው ነው። በተለይ በግፊት ህመም፣ ልብ ህመም ወይም ኩላሊት ህመም ምክንያት ጨው የተከለከሉ ከሆነ ሌሎች የአዮዲን አማራጭ ምንጮችን መጠቀም ሊኖርብዎ ይችላል።

5️⃣ ለነፍሰ ጡር እና ለሚያጠቡ እናቶች ደግሞ ከምግብ ተጨማሪ የአዮዲን ሰፕሊመንት መወሰድ ይመከራል።

https://youtu.be/-1qYBN_DBac?si=M1Ctn0xYtx1diiA7
@HealthifyEthiopia


ሰው ሰራሽ ጥርስ አፍ ያሸትል???

ሰው ሰራሽ ወይም አርቴፊሻል ጥርስ የአፍ ሽታ ያመጣ ይሆን???

-መልሱ ሰው ሰራሽ ጥርስ በራሱ የአፍ ሽታ አያመጣም ነው...ታዲያ ይሄ ጥያቄ ለምን ተነሳ?

-የሰው ልጅ የተፈጥሮ ጥርስ ህይወት አለው። በውስጡ ደም ይዘዋወራል። ስርአተ ነርቭ አለው። የህመም ስሜት፣ የንዝረት ስሜት እንዲኖረው ያደርገዋል። የተፈጥሮ ጥርስ በዙሪያው ብዙ ህይወት ያላቸው አካላት አሉ የደም ዝውውር፣ ትንንሽ የምራቅ እቅጢዎች...እነዚህ ሁሉ ጥርሳችንን ከጉዳት እና መጥፎ ከሆኑ ጀርሞች ይከላከሉለታል። በዚህም የተነሳ የዛን ያክል ልናስተውለው የምንችለውን ያክል የአፍ ውስጥ ለውጥ ላይኖር ይችላል ማለት ነው።

-በሌላ በኩል ሰው ሰራሽ ጥርስ ህይወት አልባ እና ግኡዝ ነገር እንደመሆኑ ጤንነቱ እና ንጽህናው የሚወሰነው በኛ ድክመት እና ብርታት ብቻ ነው። በዚህም ምክንያት የሰው ሰራሽ ጥርስ በቀላሉ የምግብ የመሰብሰብ ባህሪ ስላለው ቶሎ እንድናስተውለው ያደርገናል። 

-እኛ በጣም ጠንቃቆች እና ለአፋችን ንጽህና ትኩራት የምንሰጥ ከሆነ ያለምንም መታከት፣ ያለምንም መዘናጋት ወጥ በሆነ መልኩ በትገቢ እውቀት ቅሪቶችንአፋችንን እና ጥርሳችንን የምናጸዳው ከሆነ ፤ እኛ ለማጽዳት የተቸገርነውን ለሀኪም አማክረን ወጥ በሆነ ሁኔታ በ6ወር ወይም በአመት የምናጸዳ ከሆነ በየቀኑ በመስታወት እያየን የአፍ ንጽህናችንን ደረጃ የምንገመግም ከሆነ...ከላይ የተነሳውን ጥያቄ በራሳችን መመለስ እንችላለን።
https://youtube.com/@healthifyethiopia?si=KoaubEAd_8nX7Dqk

...ቸር ነገር ያሳየን ያሰማን...


ስለታይሮይድ/እንቅርት ሆርሞን መብዛት (hyperthyroidism) ህክምና ማወቅ ያለብን አራት ነገሮች?

ሃይፐርታይሮይዲዝም የሚከሰተው ታይሮይድዎ ከመጠን በላይ ሆርሞን ሲያመነጭ ነው።

የታይሮይድ ሆርሞን መብዛት ሁሉን ነገር ያፈጥናል - የልብ ምትዎ፣ የሜታቦሊዝምዎ መጠን፣ ጭንቀትዎም ጭምር ይንራል! እንቅልፍ ይነሳል፣ ጸባይ ያልተለምደ ብስጩ ያደርጋል።

ምግብ በደንብ እየበሉ ክብደት ግን መቀነስ ሊያስተውሉ ይችላሉ። አጥንት ያሳሳል። ጸጉር ያረግፋል።

የታይሮይድ ሆርሞን መብዛትን ለማስተካከል በርካታ የህክምና አማራጮች አሉት።

የታይሮይድ ሆርሞን መብዛት ህክምና ሲሰጥ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች እንደሚከተለው መሆን ይኖርበታል

1️⃣ የሆርሞን ደረጃውን ማወቅ

2️⃣ የህመሙን መነሻ ምክንያት ማወቅ

3️⃣ ዘላቂ የህክምና መፍትሄውን በውይይት መወሰን ያስፈልጋል።

4️⃣ መድሃኒት ከተጀመረም ለውጡን መታየትና መድሃኒት ማስተካከል ወይም ሌላ አማራጭ መፈለግ ይመከራል።

https://www.youtube.com/shorts/zo7IUyOdw-E

@HealthifyEthiopia


የእንቅርት መድሃኒት (thyroxine) ትክክለኛ አወሳሰድ እንዴት መሆን አለበት?

የታይሮይድ መድሀኒትዎን እየወሰዱ ግን ምንም ጥሩ ስሜት አይሰማዎትም? እንግዲያውስ የታይሮክሲን መድሃኒት በትክክል እየወሰዱ ላይሆን ይችላል!

የታይሮይድ ሆርሞን ማነስ (Hypothyroidism) ብዙ ሰዎችን በተይም ሴቶችን የሚያጠቃ የሆርሞን መዛባት ችግር ነው። አንገታችን ላይ የሚገኘው ታይሮይድ ወይም እንቅርት የታይሮይድ ሆርሞኖችን በበቂ ሁኔታ ማማንጨት ሲቀንስ የሚከሰት በሽታ ነው።

የሃይፖታይሮዲዝም መንስኤዎች በርካታ ቢሆኑም ህክምናው ተመሳሳይ ነው። ዋና ህክምናው ያነሰውን ሆርሞን ታይሮክሲን በሚባል መድሃኒት መተካት ነው። ይህ የሆርሞን መድሃኒት ያነሱትን ሆርሞኖችን ይተካል።

የታይሮክሲን መድሃኒትዎን በየቀኑ በተመሳሳይ ጊዜ መውሰድ አስፈላጊ ነው። ታይሮክሲን መወሰድ ያለበት በባዶ ሆድ ብቻ ነው። በጣም ተመራጩ የታይሮክሲን መውሰጃ ሰዓት በጠዋት ከእንቅልፍዎ እንደተነሱ የመጀመሪያው የእለቱ ስራዎት ማድረግ ነው። ታይሮክሲን ከዋጡ በኋላ ቢያንስ ግማሽ ሰዓትና ከዚያ በላይ ምንም ምግብ መመገብም ሆነ ከውሃ ውጭ መጠጣት የለበትም። እኔ ጧት አይመቸኝም ቀን ወይም ማታ ነው የምፈልገው ካሉ ግን ታይሮክሲን መወሰድ ያለበት ከበሉ በኋላ ቢያንስ ለ4 ሰዓታት ራቅ ማለት አለበት ።

በተጨማሪም ሌሎች መድሃኒቶች ካሉዎት ሰዓታቸው ከታይሮክሲን ጋር መቀራረብ የለባቸውም ። በተለይም የጨጓራና የደም ማነስ መድሃኒቶች፣ ቫይታሚኖች እና ሌሎች የመሳሰሉ መድሃኒቶች ከታይሮክሲን ጋር ሲወሰዱ በትክክል እንዳይሰራ ሊያደርጉት ይችላሉ። ስለዚህ የእነዚህን መድሃኒቶች ከታይሮክሲን መውሰጃ ሰዓት ቢያንስ ለ4 ሰዓታት ለመለየት ይሞክሩ።

የታይሮክሲን መዳሃኒቱ መጠን በቂ መሆን አለመሆኑን ለመከታተል መደበኛ የታይሮይድ ሆርሞን ምርመራዎች ማድረግ ወሳኝ ነው። መድሃኒቱ እንደተጀመረ ወይም መጠኑ እንደተቀየረ በየ6-8 ሳምንቱ ምርመራ ማድረግ ይገባል። የታይሮይድ ሆርሞኑ በደንብ ተስተካክሎ ከተረጋጋ በኋላ ደግሞ በየ4-6 ወሩ ያለማቋረጥ መከታተል ይመከራል።

ያስታውሱ ታይሮክሲን ሲወስዱ ሁሌም በተመሳሳይ ሰዓት መዋጥ ይመረጣል።

ይህን መረጃ የእንቅርት መድሃኒት ለሚወስዱ ሼር ያድርጉ።

https://www.youtube.com/watch?v=LOpARDnAelk

@HealthifyEthiopia


ከጭማቂ ይልቅ ሳይጨመቅ ሙሉ ፍራፍሬዎችን መብላት

የፍራፍሬ ጭማቂ መጠጣት በጤና እና የደም ስኳር ላይ የሚያመጣው ተጽእኖ ሙሉ ፍሬውን ከመብላት በተቃራኒ ነው። የፍራፍሬ ጭማቂ መጠጣት ሙሉ ፍሬውን ከመብላት በበለጠ ፍጥነት በደም ውስጥ ያለው የግሉኮስ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል።

ጠቃሚ የፍራፍሬው ክፍል ተራግፈው ስለሚቀሩ ንጹህ የፍራፍሬ ጭማቂ የፍራፍሬውን ስኳርና ውሃ ብቻ የያዘ ነው። ጭማቂ ውስጥ የሚቀረው የፋይበር መጠን በጣም ትንሽ ነው። በተጨማሪም ጣዕምን ለማሻሻል ሲባል የፍራፍሬ ጭማቂ ውስጥ ስኳር የመጨመር እድላችን ሰፊ ነው። መጠኑም ቢሆን አንድ ብርጭቆ ጭማቂ ብዙ ፍራፍሬ ሊይዝ ይችላል። ጭማቂ ፈሳሽ ስለሆነ ከአንጀት በፍጥነት ሰርጎ ወደ ደም ይገባል።

ሙሉ ፍራፍሬ ፋይበር፣ ቫይታሚንና ማዕድኖችን ይዟል ይህም ለአጠቃላይ ጤና ጠቃሚ ነው። ፋይበሩ የፍራፍሬው ተፈጥሯዊ ስኳር ወደ ደም ውስጥ የሚገባበትን ፍጥነት እንዲቀንስ እና ረዘም ላለ ጊዜ የጥጋብ ስሜት እንዲኖር ያደርጋል። በተቃራኒው ጭማቂ ወይም የታሸገ ጁስ ከሆነ ግን አብዛኛው ፋይበር በጭማቂ ማዘጋጀት ሂደት ይወገድና ስኳር ብቻ ይቀራል። ጭማቂ ስንጠጣም ፍራፍሬ እንደማኘክ ጊዜ ስለማይወስድ ሳናስተውለው በአንድ ትንፋሽ ብዙ ስኳር ለመጠጣት ይዳርጋል።

ለዚህም ነው በጁስ (ፍሬሽ ጭማቂም ይሁን የታሸገ) መልክ ካለው ፍራፍሬ ይልቅ ሙሉ ፍራፍሬን መብላት የሚበጀው።

ምንም እንኳን የፍራፍሬ ጭማቂ ከመጠጣት ሙሉ ፍራፍሬን መብላት የተሻለ ቢሆንም የተወሰነ ጭማቂ መውሰድ ከፈለጉ በቀን ከአንድ ትንሽ ብርጭቆ (150 ሚሊ ሊትር) የማይበልጥ ሆኖ በውሃ በደንብ በማቅጥን መጠቀም ይችላሉ።

Telegram: https://t.me/HealthifyEthiopia

YouTube: https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia

@HealthifyEthiopia


ለስኳር ታካሚዎች የፍራፍሬ አመጋገብ መመሪያ

የስኳር ታካሚዎች ከሚያነሷቸው መጠይቆች መካከል ‘ፍራፍሬ መመገብ እችላለሁ ወይ?’ የሚለው የተለመደ ጥያቄ ነው። የስኳር ታካሚዎች ፍራፍሬዎችን እንዴት መመገብ እንደሚችሉ በርካታ እርስ በእርስ የሚጣረሱ መረጃዎች ስለሚሰሙ ግራ መጋባት ይፈጥራሉ። ይህን ፍራፍሬ ብላ፣ ያንን ፍሬ እንዳትነካ፣ ይህ የተፈቀደ ነው፣ ያኛው ግዝት ነው ወዘተ የሚሉ ውዥንብር የሚፈጥሩ ያልተረጋገጡ የአመጋገብ ምክሮች አሉ። አንዱ ሃኪም አዎ ያለውን ሌላኛው አይ ብሎ ሊያወዛግበን ይችላል።

ይህ ጽሁፍ የስኳር ታካሚዎች ፍራፍሬዎችን በማእዳቸው እንዴት ማካተት እንደሚችሉ ያስረዳል። እርስዎ እራስዎ የስኳር ታካሚ ከሆኑ ወይም የሚያውቁት ስኳር ያለበት ሰው ካለ ይህ መረጃ መነበብ አለበት።

ፍራፍሬዎችን በስኳር ህክምና አመጋገብ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ያስፈልጋል?

በስኳር ህመም እና በፍራፍሬ አመጋገብ ላይ በጣም ከተለመዱት ሳይንሳዊ ያልሆኑ መረጃዎች መካከል አንዱ ‘የተወሰኑ ፍራፍሬዎች ሙሉ በሙሉ የተከለከሉ ናቸው’ የሚል ይገኝበታል። ይህንን በሳይንሳዊ ጥናቶች ያልተረጋገጠ መረጃ ከእውነታ መለየት ይገባል። እንደ እውነቱ ከሆነ አብዛኛዎቹ ፍራፍሬዎች በስኳር ህመም አመጋገብ እቅድ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ።

የስኳር ህመም ላለባቸው ሰዎች ሙሉ በሙሉ የተገዘተ ምንም አይነት ፍራፍሬ የለም። ዋናው ቁምነገር የፍራፍሬ አጠቃቀም መመጠን እና በቶሎ ስኳር ከፍ የማያደርጉትን አይነቶች መምረጡ ላይ ነው። ፍራፍሬዎች ለጤና አስፈላጊ የሆኑ ቪታሚኖች፣ ማዕድናት እና ፋይበር ምንጭ ናቸው። በማስተዋል መጥነን ከተጠቀምንባቸው ለስኳር ታካሚዎች ተስማሚ የሆነ ምግብ አንድ አካል ሊሆኑ ይችላሉ።

ለስኳር ታካሚዎች የፍራፍሬ አመጋገብ መመሪያ ምን ይመስላል?

የስኳር ህመም አለብን ማለት ፍራፍሬዎችን ዞር ብለን ማየት የለብንም ማለት አይደለም። ነገር ግን የደም ስኳር መጠን በጣም ከፍ ሳይል እንዴት ፍራፍሬዎችን በጥበብ መመገብ እንዳለብን ማወቅ ይገባል።

ዝቅተኛ የስኳር መጠን ያላቸውን ፍራፍሬዎች መምረጥ

አብዛኛዎቹ ፍራፍሬዎች በውስጣቸው ተፈጥሯዊ ስኳር ቢኖራቸውም ከፍተኛ ፋይበር ይዘት ስላላቸው በተመገብን ከመቅጽበት የደም ስኳር መጠን በድንገት እንዳያሻቅብ ያደርጋል (low glycemic index)።

መጠናችንን መገደብ


ፍራፍሬ ስንመገብ ዋና ቁልፉ ልከኝነት ነው። ምንም
እንኳ ፍራፍሬዎች ለጤናችን ጠቃሚ ቢሆኑም ቢሆን አብዝተን ከበላን የስኳር መጠን ከፍ ያደርጋሉ። ስለሆነም ፍራፍሬዎችን በተመጣጣኝ መጠን መጠቀም አስፈላጊ ነው። ሁሌም ቢሆን የምንመገበውን ፍራፍሬ መጠን መመጠን (Portion control) ይገባል።


ሙሉ ጽሁፉን በዚህ ሊንክ ማንበብ ይቻላል።

Telegram: https://t.me/HealthifyEthiopia

YouTube: https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia

@HealthifyEthiopia


3️⃣ የእንቅልፍ ሚና

እንቅልፍ ብዙ ጊዜ የሚረሳ የጤና ዋልታ ነው።
የእንቅልፍ ማነስ (በቂ ያልሆነ ወይም የማያረካ) የሆርሞን መዛባት ያመጣል፤ የመላ ሜታቦሊዝምን ስርአት ሊያስተጓጉል ይችላል። እንቅልፍ ማጣት ከጥጋብ በላይ መብላት ስለሚገፋፋ ውፍረት ያመጣል። በቂ እንቅልፍ አለማግኘት የስኳር ህክምና ቁጥጥርን ያበላሻል።

ለጤናማ እንቅልፍ የሚከተሉትን ይተግብሩ፤

✍️ በቂ የእንቅልፍ ሰአት (quantity): በየቀኑ ከ6-8 ሰአታት ጥራት ያለው የማታ እንቅልፍ ይኑርዎት።

✍️ የእንቅልፍ ጥራት (quality): የሚያረካ እንቅልፍ እንዲኖረዎት በየቀኑ የማይቆራረጥ ተመሳሳይ የእንቅልፍ ሰአት ማበጀት። ለእንቅልፍ አመቺ መኝታ መፍጠር ለአብነትም እንቅልፍ የሚረብሽ ድምጽ፣ ብርሃን እና ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮችን በማስወገድ ለእንቅልፍ ምቹ የሆነ መኝታ ቤት ይኑዎት። ከመኝታ በፊት ከባድ ምግብ እና አነቃቂ ነገሮችን (ለምሳሌ ቡና) ያስወግዱ።

✍️ የመተኛ ሰአት (Sleep Chronotype)፡ የመተኛ እና መነሻ ጊዜ ጤና ላይ ተጽእኖ አለው። ተፈጥሯዊው የሰውነት የመተኛ ሰዓት በጊዜ ተኝቶ (ማታ ከ3 እስከ 4 ሰአት) በጠዋት መነሳት (ጠዋት ከ11 እስከ 12 ሰአት) ነው። ከዚህ በተቃራኒው የሆነ የእንቅልፍ ልማድ ያላቸው ሰዎች ወይም የማታ ሺፍት ስራ የሚሰሩ ጤናቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሊኖረው ይችላል።

በመረጃ የተደገፉና የተረጋገጡ ተግባራዊ የጤና ምክሮችን እንዲደርስዎት ይከታተሉን። ለሌሎችም እንዲያጋሩ በትህትና ተጋብዘዋል።

Telegram: https://t.me/HealthifyEthiopia

YouTube: https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia

@HealthifyEthiopia

Показано 20 последних публикаций.