ሕብረት ባንክ ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ
ሕብረት ባንክ ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም በባንኩ ዋና መ/ቤት ተፈራርሟል።
በስምምነት የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሕብረት ባንክ ተ/ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ጽጌረዳ ተስፋዬ ሕብረት ባንክ ሁሉን አቀፍና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የተሻለ አገልግሎት ለደንበኞቹ እየሰጠ የሚገኝ ባንክ መሆኑን ገልፀው ባንኩ በ2ዐ3ዐ ስትራቴጂክ ዕቅዱ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በአጋርነት ለመስራት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እየሰራ እንደሚገኝና የዛሬው ስምምነትም የዚሁ ዕቅድ አካል እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሐፊ የሆኑት ቀሲስ ታጋይ ታደለ በበኩላቸው ተቋማቸው ትልልቅ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ እየሰራ መሆኑንና በዋናነት ሃገራዊ ሰላም ላይ ትኩረት በማድረግ በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ ፈጥሮ ሰላማዊ ሀገር ለመገንባት እየሰራ እንደሚገኝና ሕብረት ባንክም በየክልሎች በሚገኙ ቅርንጫፎቹ አማካኝነት ይህንን ቅዱስ ዓላማ በመደገፍ አሻራውን እንደሚያኖር ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
በፊርማ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የሕብረት ባንክ የሥራ አመራር አባላት፣ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮችና ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!!