Immigration And Citizenship Service (ICS Ethiopia)

Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ

This is the official channel of the FDRE Immigration and Citizenship Services

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций

አዳማ፣ መቐለ፣ ጅግጅጋ፣ ጅማ፣ ሀዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ ባህር ዳር፣ ደሴ፣ ሆሳዕና ያመለከታችሁ ደንበኞቻችን ስም ዝርዝር የለቀቅን ስለሆነ ስምዎን እና ያመለከቱበትን ቅርንጫፍ ወይም ስምዎን እና የትራኪንግ ቁጥርዎን በቴሌግራም ቦታችን @ICSPassportBot ወይም በድረ-ገፅ አማራጭ passport.ics.gov.et ላይ በማስገባት ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ጽ/ቤቶቹ በሚያወጡት ኘሮግራም መሰረት በመገኘት ፓስፖርታችሁን እንድትወሰወዱና ወደ ተቋማችን ስትመጡ ኦንላይን ያመለከታችሁበትን ፕሪንት አውት ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

——

Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/

አዲስ አበባ ያመለከታችሁ ደንበኞቻችን ስም ዝርዝር የለቀቅን ስለሆነ ስምዎን እና ያመለከቱበትን ቅርንጫፍ ወይም ስምዎን እና የትራኪንግ ቁጥርዎን በቴሌግራም ቦታችን @ICSPassportBot ወይም በድረ-ገፅ አማራጭ passport.ics.gov.et ላይ በማስገባት ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን በስም መነሻ ፊደል ቀናችሁ መሰረት በመገኘት ፓስፖርታችሁን እንድትወሰዱና ወደ ተቋማችን ስትመጡ ኦንላይን ያመለከታችሁበትን ፕሪንት አውት ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ለመመዘን በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት የመስክ ምልከታ ተደረገ፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የተቋሙን የ2ዐ17 በጀት አመት የ6 ወር የዕቅድ አፈፃፀም ያቀረቡ ሲሆን ከሰው ሀብት ልማትና ውጤታማነትን ከማሻሻል ፣ የአገልግሎት አሰጣጡን ምቹ ከማድረግ፣ የህግ ማዕቀፍ ከማሻሻል ፣ ብልሹ አሰራርን ከመከላከል፣ ነፃ የሰዎች እንቅስቃሴን ከማመቻቸትና ከማሻሻል አንፃር፣ የጉዞ ሰነዶች የዜግነትና የመኖሪያ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥን ከማሻሻል፣ የዲጅታል ቴክኖሎጅን በመጠቀም አገልግሎቱን ከማቀላጠፍ አኳያ፣ የውጭ ዜጐች ቁጥጥርና አገልግሎት ከማሻሻል አንፃር የተሰሩ ስራዎችን እና ወደፊት የዕቅድ አካል አድርጐ ከመስራት አኳያ ተቋሙ የሄደበትን ርቀት አብራርተዋል፡፡

አክለውም አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ቅ/ጽ/ቤት ለመክፈት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የተጠናቀቁ መሆኑን ገልፀው አሁን ላይ የሪፎርም አጀንዳዎችን በመቅረጽና ያሉትን ችግሮች ደግሞ በፍጥነት በመፍታት ከሰው ሀይል፣ ከበጀት፣ ከቴክኖሎጅ አኳያ እያሻሻልን መጠናል ብለዋል፡፡

በመስክ ምልከታ እና በቀረበው ሪፖርት ላይ ከቡድኑ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ጐሳ ደምሴ እና አቶ ቢቂላ መዝገቡ ለጥያቄዎች በቂ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም የቡድኑ አባላት ተቋሙ ከዚህ በፊት በርካታ ቅሬታዎች የሚነሱበት ተቋም የነበረ መሆኑን አስታውሰው አሁን ላይ በአጭር ጊዜ ችግሮችን ለመፍታት የተሄደበትን እርቀት አድንቀዋል፡፡ አክለውም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዬችን የቀሪ ወራት ዕቅድ ላይ በማካተት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ቀንአ ያደታ በበኩላቸው ከአለምአቀፍ ተቋማት ጋር ለመስራት፣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለማስፋት፣ ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር ፣ አገልግሎቱን የተቀላጠፈ ለማድረግ፣ ቴክኖሎጅን ለመጠቀም የተሰራው ስራ የሚያበረታታ መሆኑን ገልፀው ከአገልግሎት አሰጣጥ አኳያ የተጀመሩ የዲጅታል ስራዎች በፍጥነት ወደ ትግበራ እንዲገቡ አሳስበዋል፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
--
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia

ኢትዮጵያ ስደትና ከስደት ተመላሾች ጋር በተያያዘ እያከናወነች ያለችውን ጥረት እንግሊዝ እንደምትደግፍ አስታወቀች።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በም/አምባሳደር ሉክ ቡሎክ የተመራ ልዑክ፣ ክሪስ ዊሊያምስ ስደት ተመላሾች ዳይሬክተር፣ ጀኒ ጆንስ ፓለቲካል ኮንስለር ፣ ጆን ፌርክላው አለምአቀፍ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን ኢትዮጵያ ስደትና ከስደት ተመላሾች ጋር በተያያዘ እያከናወነች ያለችውን ተግባር በሚመለከትና በቀጣይ ከእንግሊዝ ጋር በዘርፉ ያለን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

አክለውም ተቋሙ በሪፎርም ሂደት
ላይ መሆኑን እና የሚሰጡ አገልግሎቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጅ ለማደራጀት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀው በቅርቡ ኢትዮጵያ ወደ ኢ ፓስፓርት መግባቷን ተናግረዋል፡

ሉክ ቡሎክ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ስደትና ከስደት ተመላሾችን በሚመለከት እያከናወነች ያለችውን ስራ እንደሚያደንቁ እና አገራቸው በዚህ ረገድ ኢትዮጵያን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን በማረጋገጥ የተቋሙን ሰራተኞች ስልጠና ለመስጠትና ሌሎች ቴክኒካል ድጋፎችን ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

በመጨረሻም ተቋሙ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየሰራ ያለውን ስራና ኢ ፓስፖርት
መጀመሩን አድንቀዋል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ለተቋሙ የሚሰጠው ስልጠና የባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት ወሳኝ ሚና የሚኖረው ስለሆነ ለሚደረግላቸው ድጋፍ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

--
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia

አዲስ አበባ ያመለከታችሁ ደንበኞቻችን ስም ዝርዝር የለቀቅን ስለሆነ ስምዎን እና ያመለከቱበትን ቅርንጫፍ ወይም ስምዎን እና የትራኪንግ ቁጥርዎን በቴሌግራም ቦታችን @ICSPassportBot ወይም በድረ-ገፅ አማራጭ passport.ics.gov.et ላይ በማስገባት ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን በስም መነሻ ፊደል ቀናችሁ መሰረት በመገኘት ፓስፖርታችሁን እንድትወሰዱና ወደ ተቋማችን ስትመጡ ኦንላይን ያመለከታችሁበትን ፕሪንት አውት ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

——

Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/

Показано 11 последних публикаций.