👆👆👆
በተለይ ሰለፊይ የሆነ ሰዉ ከእንደዚህ አይነት ባህሪ ሊርቅ ይገባል።ሀሜትና ወሬ ማመላለስ በአሁን ሰዓት በሰለፊዮች መካከል ሰርፆ የሚገኝ አደገኛ በሽታ ነው።
አብዛኛዉ በማካከላቸዉ የሚመጣዉ ኺላፉ ከእነዚህ ሁለት በሽታዎች ነዉ።
ለአኼራዉ የሚጨነቅ ሰዉ ማንኛዉንም ወሬ ሳያጣራና ከባለቤቱ ሳያረጋግጥ ማውራት ዬለበትም።
አብዛኛዉ ሰዉ እያደረገ ያለዉ ግን በተቃራኒዉ ነዉ፣ የሆነ ሰዉ የሆነ ወሬ ይሰጠዋል እሱ ከባለቤቱ ሳያረጋግጥ ቶሎ ብሎ እርምጃ ይወስዳል።
አገሌ እንዲህ ብሏል ወይም አገሌ እንዲህ አድርጓል ስትባል የነገሩን ምንጭ በደንብ ማጥናት ይኖርብሃል። ይህን ያለዉ ሰዉ ለምንና ከምን አንፃር እንደተናገረዉ ሳታውቅ ወደ አቋም መያዝ አትሂድ።
እንደዉም አብዛኛዉ ሰዉ የመንሃጅና የዱንያን ልዩነት ለይቶ አያውቅም። አንድ ወንድምህ በሆነ ነገር ሲሳሳት ያ የተሳሳተበት ነገር ዱንያዊ ጉዳይ ነው ወይስ መንሃጃዊ ብለህ መለየት ግድ ነው።
ወደድንም ጠላንም ከአንድ ወንድማችን በሆነ ነገር ባንስማማና ያ ነገር መንሃጃዊ እስካልሆነ ድረስ ከሶስት ቀን በላይ መኮራረፍ አይቻልም።
ታዲያ ከማሀላችን ስንቱ ነዉ መንሃጃዊ ባልሆነ ነገር ከሶስት ቀን በላይ የሚኮራራፈዉ?። ከዚህም አልፎ መንሃጃዊ ባልሆነ ነገር ደእዋዉን ለመጉዳት የሚንቀሳቀስ ስንት ኣለ!?።
ከሆኑ ሰዎች ጋር በሆነ ነገር ስላልተስማማህ ብቻ ደዕዋን ለመጉዳት መንቀሳቀስ ወይም ደዕዋዉን ለመጉዳት ማሰብ አላዋቂነት ነዉ።
እንደዚህ የሚያረጉ ሰዎች እንደዉም ደዕዋ ሰለፊያ ካለማወቅ ይመስለኛል። ሰለፊያን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰዉ እያንዳንዱ ንግግሩ፣ እያንዳንዱ አካሄዱ በጥንቃቄ የተሞላ ነዉ።
አንድን ንግግር መቼና ዬት ለምን እንዴት መናገር ወይም መተግበር እንዳለበት ያውቃል።
በአጠቃላይ ሰለፊያን በትክክል የሚያውቅ ሰዉ ስሜቱን ከሰለፊያ ደዕዋ አያስቀድምም።
እያንዳንዱ እንቅስቃሴዉ ወይም ንግግሩ ከሰለፊያ ጥቅምና ጉዳት ጋር ያመዛዝናል። ለግለሰቦች ጥቅም ሳይሆን ለደዕዋዉ ጥቅም ይንቀሳቀሳል።
ምክሩ ለራሴም ጭምር ነው።
t.me/ibnawolllllt.me/ibnawolllllt.me/ibnawolllll