ኢብኑ ተይሚያህ የሱናው አንበሳ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


"አላህ እንዳንተ አይነት መፍጠሩን ቀጥሏል ብዬ አላስብም ነበር፡፡" ኢብኑ ደቂቀል ዒድ
"ኢብኑ ተይሚያ ሸይኹል ኢስላም ካልሆነ እና ማን ሊሆን ነው?!" ኢብኑል ሐሪሪ

በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር [ሀፊዘሁሏሂ] የተጻፈ መጽሐፍ፡፡

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ታመናል በጠና!

ውጫችን ተውቦ በሱና አሸብርቆ
የሚያስደምም ሆኖ ዟሂራችን ደምቆ

ቀልብ ካልረባማ ከተቆራመደ
የድብቅን ወንጀል ከተለማመደ

ከባድ አደጋ ነው ታመናል በጠና
ፈውሱን እንፈልገው ከቁርአን ከሱና

ጀግና መስለን ውለን በቀን በጠራራ
ሌቱን ከገፋንው ከኢብሊሱ ጋራ
ምኑን ተከተልንው የነብዩን ስራ?!
ልባችን ደካክሞ ባጋንነቶች ጭፍራ!

ይብቃን አረ ይብቃ እንዲህ መዳከሩ
በድብቅ ወንጀሎች ሌት ቀን መነከሩ
መንገዱን እንጀምር በዲን በመስመሩ!!

©ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ

👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah

👉 @Twehid12


ፆምና ህመም
~
ህመምተኞች ከፆም አንፃር ለአራት ይከፈላሉ።

1ኛ አይነት፦ በህመሙ ምክንያት በቋሚነት መፆም የማይችል ሰው

ህመሙ ይድናል ተብሎ ተስፋ የማይጣልበት ቋሚ ህመም ያለበት ሰው ልክ መፆም እንደማይችል ትልክ ሽማግሌ ሲሆን በኢጅማዕ ማፍጠር ይችላል። የፆም ግዴታ የለበትም። አላህ እንዲህ ብሏል
(لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَاَ)
"አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡" [አልበቀረህ፡ 286]

ሚስኪን የማብላት ግዴታም የለበትም። ግዴታ እንደሆነ የሚያሳይ የቁርኣንም፣ የሐዲሥም፣ የኢጅማዕም አስገዳጅ ማስረጃ የለምና። ኢብኑ ሐዝምና ኢብኑ ዐብዲልበር ይህንን አበክረው ይናገራሉ።

ይሁን እንጂ ለእያንዳንዱ ቀን አንድ ሚስኪን ቢያበላ የተወደደ ነው። ምክንያቱም:-

1ኛ:- ከተለያዩ ሶሐቦች ተገኝቷልና። የብዙ ዑለማኦችም ምርጫ ነው።
2ኛ፦ ይህንን ሲፈፅም ራስን ከውዝግብም ያወጣል።

ይሄ እንግዲህ ማብላት ለሚችል ሰው ነው። ያልቻለ ምንም የለበትም።

* የምግቡ አይነት እቤቱ ከሚመገበው መካከለኛ ደረጃ ያለው ነው።

2ኛው አይነት ህመምተኛ፦ ህመም ቢኖርበትም መፆም የሚችል ነገር ግን በመፆሙ ህመሙ የሚባባስበት የሆነ ሰው ነው። ለዚህ አይነቱ ማፍጠር ግዴታ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል:-
(وَلَا تُلْقُوا بِأَيْدِيكُمْ إِلَى التَّهْلُكَةَِ)
"በእጆቻችሁም (ነፍሶቻችሁን) ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡" [አልበቀራ: 195]

★ ባይሆን ሲሻለው ቀዷእ ያወጣል (በምትኩ ይፆማል።) አላህ እንዲህ ብሏል:-
{فَمَن كَانَ مِنكُم مَّرِیضًا أَوۡ عَلَىٰ سَفَرࣲ فَعِدَّةࣱ مِّنۡ أَیَّامٍ أُخَرَۚ}
"ከእናንተም ውሰጥ ህመምተኛ ወይም በጉዞ ላይ የሆነ ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን መፆም አለበት።" [አልበቀረህ: 184]

3ኛው አይነት ህመምተኛ፦ መፆም የሚችል ሆኖ መፆሙ የሚያስከትልበት ጉዳት ባይኖርም ነገር ግን በህመሙ ምክንያት ፆም የሚከብደው ሰው
እንዲህ አይነቱ ማፍጠር ለሱ ግዴታ ባይሆንም በላጭ ነው። ኋላ ግን ቀዷእ ያወጣል።

4ኛው አይነት ህመምተኛ:- ቀላል ህመም ያለበት ሰው ወይም መፆሙ የማይከብደው እና ህመሙን የማያባብስበት የሆነ ሰው ሊያፈጥር ማለትም ፆሙን ሊፈታ አይፈቅድለትም። ለማፍጠር በቂ ምክንያት መኖር አለበት።

ማሳሰቢያ: –
* ህመምተኛ ህመሙን ችሎ ቢፆም ፆሙ በኢጅማዕ ይቆጠርለታል።
والله أعلم
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
* "በረመዳን የተፈፀመ (ሱና የሆነ) ኸይር ስራ በሌላ ጊዜ እንደተፈፀመ ግዴታ ዒባዳ ነው።
* በረመዳን የተፈፀመ ግዴታ ዒባዳ በሌላ ጊዜ እንደተፈፀመ ሰባ ግዴታ ዒባዳ ነው።"

ይሄ ሐዲሥ ደካማ ነው። ደካማ እንደሆነ ከገለፁ ዐሊሞች ውስጥ የተወሰኑትን ልጥቀስ፦

1- ኢብኑ ሐጀር:- [አተልኺሱል ሐቢር፡ 3/1121]፣
2- አል0ይኒይ:- [ዑምደቱል ቃሪ : 10/383]፣
3- አልባኒይ:- [ተኽሪጁል ሚሽካት ፡ 1906] [ዶዒፉ ተርጊብ፡ 589]፣
4- ኢብኑ ዑሠይሚን:- [ፈታዋ ኑሪን ዐለ ደርብ: 2/ 568]

ማሳሰቢያ:-
~
ይሄ ማለት ከላይ በተጠቀሰው ደካማ ሐዲሥ ላይ ባለው መልኩ ለመደምደም ሶሒሕ ማስረጃ ያስፈልጋል ለማለት እንጂ በተከበሩ ቦታዎች እና ጊዜዎች ውስጥ የሚፈፀሙ ተግባራት ከሌሎች ተግባራት ልዩነት የላቸውም ለማለት አይደለም። በተከበሩ ቦታዎች እና ጊዜያት ውስጥ የሚፈፀሙ ተግባራት ኸይርም ሆኑ ሸር በሌላ ቦታዎች እና ጊዜዎች ከሚፈፀሙት ተግባራት መጠናቸው ከፍ ይላል። ለምሳሌ ሐረም ውስጥ የሚሰገድ ሶላት ከሌላ ቦታ ሶላት መጠኑ በጣም ይለያል። ወንጀልም ላይ እንዲሁ። በዙልሒጃ የመጀመሪያ አስሩ ቀናት የሚፈፀም ዒባዳ በሌላ ጊዜ ከሚፈፀመው በጣም ይበልጣል። ረመዳንም የተከበረ ወር እንደመሆኑ ከሌሎች ጊዜያት ብልጫ አለው። ይሁን እንጂ ከላይ በሰፈረው ዶዒፍ ሐዲሥ ላይ በተጠቀሰው መልኩ መጠኑን ለይቶ ለመናገር ሶሒሕ ማስረጃ ያስፈልጋል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በረመዷን በብዛት የሚፈፀሙ ስህተቶች
~
① ሶላት ሳይሰግዱ መፆም፣
② ሌሊቱን በጫት ካሳለፉ በኋላ ሰሑርን አስቀድሞ በመመገብ ሱብሕ ሳይሰግዱ መተኛት፣
③ ቀኑን በእንቅልፍ፣ ሌሊቱን በተከታታይ ፊልም (ሙሰልሰላት) ማሳለፍ፣
④ ረመዷንን ጠብቆ መንዙማና ነሺዳ እየለቀቁ ሰዎችን ከቁርኣን ማዘናጋት፣
⑤ ተራዊሕን በንቃት እየሰገዱ ፈጅር ሶላትን በእንቅልፍ ማሳለፍ፣
⑥ ተራዊሕ ላይ በየአራቱ ረከዐ መሐል የቢድዐ እና የሺርክ እንጉርጉሮዎችን ማስገባት፣
⑦ የተራዊሕ ኢማሞች በጣም ረጅም የቁኑት ዱዓእ ማድረግ፣
⑧ መግሪብ ሶላት ሲጠናቀቅ ስርአት በሌለው መልኩ ለፊጥራ መጣደፍ (ሰጋጆችን የሚያቋርጥ፣ የሰው ጫማ የሚያቀያይር፣… አለ)
⑨ ሌሊት ላይ "ተሰሐሩ" እያሉ መዞር፣
(10) የሱሑር ጊዜ ሳያልቅ ለጥንቃቄ በሚል ቀድሞ አዛን ማድረግ፣
(11) ሱሑር ላይ "ነወይቱ ሰውመ ገዲን" እያሉ በቃል መነየት፣
(12) እያንቀላፉ ተራዊሕ መስገድ፣
(13) ልጆች "እንፁም" ሲሉ ማበረታታት ሲገባ መከልከል፣ "ውሃ አያስፈጥርም፣ ተደብቀህ ብላና ትፆማለህ" እያሉ መዋሸትና ውሸት ማለማመድ፣
(14) ሴቶች በተጋነነ የምግብ ዝግጅት ሰፊ ጊዜያቸውን ማቃጠል፣
(15) ሴቶች ሽቶ ተቀብተው ለተራዊሕ መውጣት፣
(16) በተራዊሕ ወቅት የሴቶችና የወንዶች በየ ጎዳናውና በየካፌው አላስፈላጊ መዝረክረክ፣
(17) ሃሜት፣
(18) ፊጥራ ላይ ከመጠን በላይ መመገብ፣
(19) ቀኑን በካርታ፣ በዳማ እና መሰል አጉል ነገሮች ማሳለፍ፣
(20) ሙዚቃ ማዳመጥ፣
(21) የሰው ስራ የሚሰሩ ተቀጣሪዎች ጧት በሰዓት አለመግባት (አማና መጠበቅ፣ ቃልን ማክበር ግድ ይላል። ግዴታ ያልሆኑ ዒባዳዎች ተፅእኖ የሚያሳድሩብን ከሆነ መተው ወይም መቀነስ ነው)፣
(22) በተለይ በስራ ቦታዎች ላይ በመንዙማና በነሺዳ ማሳለፍ (መሆን ያለበት ከተመቼ ቁርኣን መቅራት፣ ካልሆነ ዚክር ማድረግ ወይም ደዕዋ ማዳመጥ፣ ካልሆነ ዝምታ ይሻላል።)
(23) ለይለተል ቀድርን ለማየት ሰማይ ሰማይ እያንጋጠጡ ተሰብስበው እያወሩ መጠበቅ (የሚታይ ነገር የለም)፣
(24) አንዳንድ አካባቢዎች የዒሻእ ሶላትን በጣም በማዘግየት ሰው ጀማዐ ላይ እንዳይካፈል እንቅፋት መሆን፣
(25) አንዳንድ አካባቢዎች መስጂድ ውስጥ ጫት ይዞ ገብቶ መቃም፣
(26) አንዳንድ አካባቢዎች "ተርቲብ" ብለው ንፍሮ፣ ቆሎና መሰል ምግቦችን ወደ መስጂድ እንዲያቀርቡ ሰዎችን ማስገደድ፣ ወዘተ
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
አልሐምዱ ሊላህ! ሸዕባን አጠናቀናል። ቅዳሜ ረመዷን 1 ነው። ምሽቱን ተራዊሕ እንጀምራለን።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor


👆 ስለ ፆም የተሰጠ ትምህርት👆




Репост из: SadatKemal Abu Meryem
*️⃣*️⃣*️⃣ኢንሻ አላህ *️⃣*️⃣*️⃣

እሁድ ከጠዋቱ 3 ሰኣት ጀምሮ እስከ ዙሁር በሑዘይፋ መስጂድ የዳእዋ ፕሮግራም ይኖራል።

ፕሮግራም አቅራቢዎች

1️⃣🔁ኢብኑ ሙነወር፣

2️⃣🔁አቡ ኡስዋ፣

3️⃣🔁ሳዳት ከማል፣

4️⃣🔁አብዱ ሰኢድ፣

5️⃣🔁አማር በህረዲን።

ፕሮግራሙ ከሚያካትታቸው ትምህርቶች ውስጥ

1️⃣🔤ቁርኣንን በጥሞና ማዳመጥ፣

2️⃣🔤አቀራራችን ማስተካከል፣

3️⃣🔤የተመረጡ ምእራፎች የቁርአን ትርጉም፣

4️⃣🔤ዳእዋ እና ሌሎችም

ለሴቶች በቂ ቦታ አለ።
🚘🚘🚘🚘🚘🚘🚘🚘
አድራሻ ሸገር ሲቲ ከየሺ ደበሌ ከፍ ብሎ።
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem


Репост из: SadatKemal Abu Meryem
⚠️🛑🛑ወንድም "ኢሳም ሐበሻ" 🛑🛑
🤲 አላህን ፍራ።

✔️ፊልም ትተህ በመምጣትህ በጣም ተደሰትናል አልሐምዱሊላህ።

🛑"ኢስላማዊ" ብለህ ግን ሰው ስታሳስት ጥፋትህ እጥፍ ድርብ ይሆናል።

⚖ "ኡስታዞች" የሚባሉት ስታጠፋ ዝም ስላሉህ ሐቅ ላይ ነህ ማለት አይደለም። እነሱ ታላቁ ወንጀል ሺርክ (በአላህ ላይ ማጋራት) ቢፈፀምም ዝም ነው የሚሉት።

😀 ፕሮግራምህ ላይ ቶርታ ኬክ ካስቆረስካቸው ሰዎች ውስጥ በአላህ ላይ ማጋራት ያለባቸው የክህደት ጭፈራ ስብስቦች ላይ በደስታ አብሮ የሚጨፍር ሰው ይገኝበታል። እንዲህ አይነት ሰዎች ጋር አብርህ የምትሰራቸው ስራዎች ስህተትህን ይበልጥ ያገዝፉብሀል። ወደ አላህ ተመለስ።

💊 ለነፍስህ ፍራ። "25 አመት ፊልም ኢንዱስትሪ ላይ ነበርኩ።" ትላለህ። 25 አመት የሸሪአ እውቀት መሰብሰብ ላይ እኮ አልነበርክም። እንዴት በጥፋት ዘመን ላይ የኖርክበትን ዛሬ ለመስራት ላሰብከው የጥፋት "x ኢስላማዊ ፊልም" መንደርደሪያ ታደርገዋለህ?

🔑 ይልቁንም ለነፍስህ እዘንላት ሀይማኖትህን ተማር እና ወሎ፣ ሰሜኑ ኢትዮጵያ፣ መላው ኢትዮጵያ ላይ አላህ ንሰሃ ሳይገባ ለሞተ ሰው የማይምረው ወንጀል ሺርክ (በአላህ ላይ ማጋራት) ይሰራል። ሰውን በአላህ ፍቃድ ከዚህ ክህደት እንዲወጣ ተምረህ አስተምር ይህም የነብያት መንገድ ነው።

ወሎ ላይ
📱📱📱📱📱📱📱
1) የቦረናው ደግዬ እርዱኝ አባብዬ ይባላል። ይሄ ክህደት ነው።
2) ሙወከል እየተባለ ለሰይጣን ለነ ሰይፉ ጨንገሬ ይታረዳል። ይሄም ከኢስላም ያስወጣል።

📱📱📱📱📱📱📱

ታድያ ይሁ ሁሉ ክህደት እና በአላህ ላይ ማጋራት ያለበትን የኢትዮጵያ ህዝብ ጭራሽ ፊልማቸው ኦርቶጉል ውስጥ ኩፍር የጨመሩትን ቱርኮች አንት ልትሰራ ላሰብከው "ፊልም" ጭራሽ እርዳታ መጠየቅህ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አይሆንምን?

🛑ወንድሜ መልካም ነገር ማለት አንተ መልካም ያልከው ሳይሆን ኢስላም መልካም ያለው ነው።

🎧 ኢስላምን ለማገዝ ከቁርአን ከሐዲስ ኡለማዎች ከሄዱበት መንገድ ውጭ ያለው ሁሉ የጥፋት መንገድ ነው።

😀 ገንዘብ እና ጊዜህን በጥፋት መንገድ ላይ አታባክን።

⚖ አላህ ፊት ብቻችንን ራቁታችንን የምንቆምበት ቀን አለ።

😀 ለአላህ ብለህ ተወው። አላህ በተሻለ እሱ በሚወደው፣ ወደሱ ለሚያቃርብህ አምልኮ አንተንም እኛንም ይለግሰን።
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem


Репост из: ስለ ቀልባችን
🎉መልካም ዜና!
~
ለ ሶስት ቀናት ብቻ የሚቆይ ልዩ የቴሌግራም ኮርስ አዘጋጅተናል!

🗓 ቀናት፦ ከእሮብ - ጁምዐ
⏰ ሰዓት፦ከምሽቱ 3:45 ጀምሮ
👤 አስተማሪ፦ አብዱ ረዛቅ ባጂ

📚 የኪታብ ስም፦ሚፍታሁ ጠሪቂል አዉሊያ
(مفتاح طريق الأولياء)

🖋 የ ኪታቡ አዘጋጁ፦ አል-ኢማም ዒማዱ' ዲን አልዋሲጢይ رحمه الله

🔗የኪታበን pdf ለማግኘት

https://t.me/fewaidabdurazaq/1935



ኮርሱ የሚሰጥበት ቻናል፦👇
https://t.me/Sle_qelbachn1
https://t.me/Sle_qelbachn1


አል ኢማም ኢብኑ ረጀብ አልሐምበሊ እና ኢኽላስ

ከኢርሻድ ደርስ የረቆረጠ

https://t.me/Muhammedsirage


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ስብስብ:
~

1 - ባለ ኒቃቧ ዶ/ር ዛኪራ ተባረክ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።

ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ በሜዲስን 3.87 አምጥታ በዛሬው እለት የተመረቀችው እህታችን በሶስት ዘርፍ ተሸላሚ ሆናለች።
* ከሁሉም የህክምና ተማሪዎች አንደኛ ወጥታ ተሸልማለች።
* ከሁሉም ሴቶች አንደኛ ወጥታ ተሸልማለች።
* ከሁሉም ተማሪዎች አንደኛ ወጥታ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልማለች።

2 - ሌላኛዋ እህታችን ዶ/ር ረሕማ አንሷር ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሜዲስን የተመረቀች ሲሆን ከአጠቃላይ ተማሪዎች 3ኛ ከሴቶች ሁለተኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆናለች።

3 - ሌላኛዋ እህታችን ኸውለት ከOther health (radiology) ከሴቶች 3ኛ በመውጣት ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡት አንዷ ናት!

ሁላችሁንም እንኳን ደስ አላችሁ! አላህ ከራሳችሁ አልፋችሁ ለቤተሰባችሁም፣ ለወገናችሁም የምትጠቅሙ ያድርጋችሁም።

ምንጭ፦ https://t.me/Arbaminchuniversitymuslimstudent
=
በየአካባቢው፣ በየ ተቋማቱ ያላችሁ ሌሎችም ተማሪዎች ትምህርቱ ላይ እስካላችሁ ድረስ ከልብ አድምታችሁ ተማሩ፣ በቂ ጥረት አድርጉ። የናንተ ውጤት ከናንተ አልፎ ለሌላውም ኩራት ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ🌹
ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም

#ሀዋሳ_ቢላል_መስጅድ
በአላህ ፍቃድ የፊታችን እሁድ በቀን 16/ 06/ 2017 በሀዋሳ ከተማ ቢላል መስጅድ ከጧዋቱ 3፡00 (ሶስት ሰዓት) ጀምሮ እስከ 6፡00 (ስድስት ሰዓት) የሚካሄድ በአይነቱ ልዩ የሆነ ከተማ አቀፍ የዳዕዋ ፕሮግራም የተዘጋጀ ስለሆነ እርሶም ሌሎችን በማነሳሳት እና የፕሮግራሙ ታዳሚ በመሆን የከይር ስራው ተቋዳሽ እንድሆኑ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

ተጋባዥ ኡስታዞች

1.ኡስታዝ አብዱሰላም ሸይኽ ሀሰን
2.ኡስታዝ ኢስሃቅ (አቡ አብዱልሀቅ)
3.ኡስታዝ ሙስጠፉ ሰኢድ
3. ኡስታዝ አብዱፈታሀ ሀሚዴላ

ርዕሱ፡- ረመዳንን እንዴት እንቀበል ይሆናል።

#የቢላል_መስጅድ_ወጣቶች_ጀመዓ


Репост из: 🇸🇦يونس ابن حسن🇸🇦
♥️السلام عليكم ورحمة الله وبركاته♥️

🌙ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም🌙

♥️የፊታችን እሁድ ሸዕባን 24 [የካቲት 16] በአሏህ ፈቃድ በዘህራ መስጂድ ውስጥ ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም ይቀርባል።

💡ተጋባዥ ኡስታዞች፡

♥️ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
♥️ኡስታዝ አቡል ዐባስና ሌሎችም።

⏰️ፕሮግራሙ ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት እስከ ዙሁር ድረስ የሚቀርብ ሲሆን ለሴቶች በቂ ቦታ ተዘጋጅቷል።

📍አድራሻ፡- ሸገር ሲቲ አሸዋ ሜዳ፡ ሻቃ ሞል ጀርባ አሸዋ ሜዳ ኮንዶሚኒየም አካባቢ።

✔️በአካል መገኘት ለማይችሉ ዝግጅቱ በ https://t.me/abufurat ቻናል በቀጥታ ይተላለፋል።

✔️በተውሂድ በሱናና በሰለፎች መንገድ የታነፀ ማህበረሰብን እንፍጠር⚡️

ዘህራ መስጂድና መድረሳ

📚መልዕክቱን ሼር በማድረግ እንተባበር፡ ባረከሏሁ ፊኩም።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ዳዒያው ሆይ! አስመሳይ እንዳትሆን ተጠንቀቅ!
~
ታላቁ ኢትዮጵያዊ ዓሊም ሙሐመድ አማን አልጃሚ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
“ከሁሉም ሰው ዘንድ ተወዳጅ መሆን የሚፈልግ፤ በተለያዩ ደረጃዎች፣ ዝንባሌዎችና ቡድኖች ላይ ሆነው ሳለ ሁሉም የሚወዱት ዳዒያህ አስመሳይ ነው!! ሁሉንም ሰው ሊያስደስት፣ ማንም እንዳይቆጣበት የሚጥር፣ ሁሉም “እከሌ ሚዛናዊ ነው፣ ረባሽ አይደለም” የሚለው ዳዒያህ፣ ሁሉም ቡድኖች፣ ሁሉም አንጃዎች፣ ሁሉም ጭፍራዎች፣ የተለያየ የአስተሳሰብ አቅጣጫዎች ላይ ያሉ ሁሉም ሰዎች የሚወዱለት ሰው ይህ አስመሳይ ሙ^ና^ፊ^ቅ ነው፡፡ በዚህ ላይ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ምክንያቱም ይሄ የማይሆን ነውና፡፡ ሻፊዒይ ረሒመሁላህ እንዳሉት 'ሁሉን ሰው ማስደሰት የማይደረስበት ግብ ነው።'

ስለዚህ ሁሉንም ሰው አስደስታለሁ ብለህ መጣርህ የማይደረስበት ህልም ነው፡፡ ይልቅ የሚደረስበትና የሚፈለግ ግብ አለ፡፡ የሰውን ሁሉ ውዴታ ማግኘት የማይደረስበት እና የማይፈለግ ግብ ነው፡፡ የጠራውን ጌታ ውዴታ ማግኘት ግን አላህ ላደለውና ውዴታው ላጋጠመው የሚገኝ ግብ ነው፡፡ እናም ውዴታው የሚገኝና የሚፈለግ ግብ ነው፡፡ ስለዚህ ዳዒያህ የሆነ ሰው ወደ ደዕዋ አደባባይ ሲወርድ ሀሳቡ ይሄ ነው መሆን ያለበት፡፡ ይህን ማድረግ ያልቻለ ከቤቱ ይቀመጥ!!”
[ሸርሑ ሹሩጢ ላኢላሀኢለላህ፡ 102-103]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ረመዷንን በማስመልከት

ዛሬ ሐሙስ ምሽት ታላቅ የሙሓደራ ፕሮግራም አዘጋጅተን እየጠበቅናችሁ እንገኛለን ።
.
ተጋባዥ እንግዶቻችን

1️⃣ ኡስታዝ አቡ ዑሰይሚን አብዱረሕማን ዝናቤ (حفظة الله)

ርዕስ የረመዷን አቀባበል

2️⃣ ኡስታዝ አሚር ሙሀመድ (حفظة الله)

ርዕስ ረመዷን ኸይር የበዛበት ወር

3️⃣ ኡስታዝ ሙሀመድ ሲራጅ (حفظة الله)

ርዕስ ረመዷንን እንደት እናሳልፍ

4️⃣ ኡስታዝ አቡ ረይስ ሙሐመድ ኢማም (حفظة الله)

ርዕስ በስአቱ ይነገራል

መድረኩ በኡስታዝ አቡ ፋሩቅ ኑረዲን አል-ዐረብ የሚመራ ይሆናል በዛውም "ረመዷን እና ህዝባችን" በሚል ርዕስ ያስታውሰናል

ፕሮግራሙ የሚተላለፍበት ቻናል

ሊንኩን ሼር በማረግ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ


Репост из: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
መቆሚያ ያጣው የመርከዙ የቁልቁለት ጉዞ!
~
የሸሪዐ ቀዳሚ ግብ ጉዳትን ማስወገድ፣ ካልሆነ መቀነስ እንዲሁም ጥቅምን ማስገኘት ነው። አንዳንዴ የከፋውን ሸር ለማለፍ ወይም ለመቀነስ ሲባል ያነሰውን ሸር እንፈፅም ዘንድ ጫና ሊገጥመን ይችላል። በዚህ የተነሳ ለአጠቃላዩ የደዕዋ መስለሐ ሲባል ውስጣችን የማያምንበት ጉዳይ ላይ ልንነካካ እንችላለን። ይሄ ብስለት አልፎም ድፍረት የሚፈልግ ጉዳይ ነው።

በሌላ በኩል ደግሞ ከእለት ወደ እለት መንሸራተቱን በ "መስለሐ" ወረቀት እየጠቀለለ የሚያቀርብ ብኩን አለ። ማዶ ላይ ያለን "መስለሐ" ሲያስብ ዙሪያውን ስላለው ተጨባጭ አያስብም። "የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች" እንደሚባለው ማለት ነው።

የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ አካሄድ እዚህ ላይ ነው ያለው። መሪዎቻቸው በዑጅበ ነፍስ የተወጠሩ፣ ቀድራቸውን የማያውቁ፣ "ከኛ ወዲያ መስለሐ እና መፍሰዳ የሚለይ ላሳር" ውስጥ የገቡ ናቸው። ይሄ አዲስ የመጣ ሳይሆን ነባር አመላቸው ነው። "አገር ለመምራት እድሉ ቢስሰጣቸው መምራት የሚያስችል ብቃት አላቸው" የሚል፣ ቢያጥፉት የሚታጠፍ፣ ቢዘረጉት የሚዘረጋ እንዳሻቸው የሚሰሩት ስብስብ ለራሳቸው የተሳሳተ ግምት እንዲይዙ አድርጓቸዋል። የፈለገ ቢወርዱ "ኧረ አሁንስ በዛ!" የሚል ድፍረት ያለው ከኖረ ከስንት አንድ ነው። እሱውም ከተገኘ። ሰው በዚህ መጠን በጋራ ጭፍን ተከታይ ይሆናል? የሚገርም ነው!

ወላሂ! መርከዙን የምታድኑት ኢኽላስን መሰረት ባደረገ እውነተኛ አካሄድ እንጂ በጭፍን ውግንና አይደለም። ሰዎቹንም ሲያጠፉ እጃቸውን በመያዝ እንጂ በጭፍን ብትከላከሉ እነሱንም ላትጠቅሙ ራሳሁንም ትጎዳላችሁ። ይልቁንም ከዚህ "እናንተን የማይታያችሁ ይታየናል" ከሚል አጉል ግብዝነት እንዲወጡ ብታግዟቸው ነው የሚሻለው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Репост из: MuhammedSirage M.Nur.
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ፆማችንን ከሀሜትና ከመሳሰሉ ወንጀሎች እንጠብቅ !!

በርካታ የባከኑ ረመዳኖች አልፈዋልና መጪው ላይ እንበርታ !!!


https://t.me/Muhammedsirage


Репост из: ፈዋኢድ
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
الله الله


Репост из: የቡታጅራ አህለሱና ቂራኣትና ዳዕዋ ቻናል
ታላቅ የዳዕዋና ኮርስ ፕሮግራም      
           በቡታጅራ ከተማ!

=
እነሆ የፊታችን ሐሙስ ቀን 06/06/2017 ከመግሪብ ሰላት በኋላ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ቀን 08/06/2017 ድረስ የሚቆይ የዳዕዋና ኮርስ ፕሮግራም በቡታጅራ ተሰናድቶ ይጠብቅዎታል።

በዕለተ እሁድ ደግሞ ሰፋ ባለ መልኩ በኢንሴኖ ከተማ ደማቅ ፕሮግራም የሚካሄድ ይሆናል። በዚህ ፕሮግራም የተለያዩ ጊዜውን ያማከሉ አርእስቶችና ረሳኢል በኮርስና ዳዕዋ መልክ ይሰጣሉ።

እርሶም የዚህ ታላቅ ፕሮግራም ተሳታፊ ይሆኑ ዘንድ ጥሪ ስናቀርብልዎ በታላቅ ደስታ ነው።

☞ ተጋባዥ እንግዶች፦
     * ሸይኽ አወል አሕመድ አልከሚሴ
     * ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አልከሚሴ እና ሌሎችም ኡስታዞችና ዱዓት ይገኛሉ።

«እውቀትን ፍለጋ መንገድን የጀመረ አላህ የጀነትን መንገድ ያገራለታል።» ረሱልﷺ

https://t.me/butajira_Qirat_daewa_group

Показано 20 последних публикаций.