Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


كناشة ابن منور

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


* የሰው ሐቅ ተሸክመህ ወደ ረመዳን አትግባ። መክፈል እየቻልክ የሰው ሐቅ ይዘህ አታጉላላ። አቅቶህ ከሆነ ጊዜ እንዲሰጡህ በትህትና አስረዳቸው።
* የበደልከውን ይቅርታ ጠይቅ። የበደሉህን ይቅር በል።
* መክፈል የማይችል ሰው ላይ ሐቅ ካለህ ብትችል እለፍ ወይም ቀንስላቸው። ካልሆነ ጊዜ ስጣቸው። "የትም ገብታችሁ አምጡ" አትበል። ወንጀል ላይ ገብተው ቢሰጡህ ሐላል አይሆንልህም።
* ስትሸጥም ስትገዛም ገር እና ቅን ሁን። ገዥም ሻጭም ሆነህ ሶደቃ የምታደርግበት ሁኔታ እንዳለ አስተውል።
* ግብይትህ ላይ ከውሸት፣ መሀላ ከማብዛት፣ ከማታለል፣ ... ተጠንቀቅ። ጊዜ ካለህ ቁርኣን ቅራ። ዚክር አድርግ።
* ቤትህ ውስጥ ሰላም ሁን። ከጭቅጭቅ ራቅ። ሶብር ይኑርህ። ለሚስትህ፣ ለልጆችህ አሳቢ፣ ተቆርቋሪ ሁን። ከአላህ በታች ያላንተ ማን አላቸው? ለባልሽ ምቹ ሁኚ። አንቺ ፈተና ከሆንሽበት ውሎውን ሁሉ ሰላም ያጣል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor


ረመዳን የቁርኣን፣ የዚክር፣ የሶደቃ፣ የኸይር ወር እንጂ የፊልም፣ የመንዙማ፣ የነሺዳ ወር አይደለም። በሚጠቅመን ላይ እንጠመድ። በማይረቡ ነገሮች ራሳችንንም፣ ሌሎችንም አንፈትን።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor


⚠️🛑🛑ወንድም "ኢሳም ሐበሻ" 🛑🛑
🤲 አላህን ፍራ።

✔️ፊልም ትተህ በመምጣትህ በጣም ተደሰትናል አልሐምዱሊላህ።

🛑"ኢስላማዊ" ብለህ ግን ሰው ስታሳስት ጥፋትህ እጥፍ ድርብ ይሆናል።

"ኡስታዞች" የሚባሉት ስታጠፋ ዝም ስላሉህ ሐቅ ላይ ነህ ማለት አይደለም። እነሱ ታላቁ ወንጀል ሺርክ (በአላህ ላይ ማጋራት) ቢፈፀምም ዝም ነው የሚሉት።

ፕሮግራምህ ላይ ቶርታ ኬክ ካስቆረስካቸው ሰዎች ውስጥ በአላህ ላይ ማጋራት ያለባቸው የክህደት ጭፈራ ስብስቦች ላይ በደስታ አብሮ የሚጨፍር ሰው ይገኝበታል። እንዲህ አይነት ሰዎች ጋር አብርህ የምትሰራቸው ስራዎች ስህተትህን ይበልጥ ያገዝፉብሀል። ወደ አላህ ተመለስ።

ለነፍስህ ፍራ። "25 አመት ፊልም ኢንዱስትሪ ላይ ነበርኩ።" ትላለህ። 25 አመት የሸሪአ እውቀት መሰብሰብ ላይ እኮ አልነበርክም። እንዴት በጥፋት ዘመን ላይ የኖርክበትን ዛሬ ለመስራት ላሰብከው የጥፋት "x ኢስላማዊ ፊልም" መንደርደሪያ ታደርገዋለህ?

🔑 ይልቁንም ለነፍስህ እዘንላት ሀይማኖትህን ተማር እና ወሎ፣ ሰሜኑ ኢትዮጵያ፣ መላው ኢትዮጵያ ላይ አላህ ንሰሃ ሳይገባ ለሞተ ሰው የማይምረው ወንጀል ሺርክ (በአላህ ላይ ማጋራት) ይሰራል። ሰውን በአላህ ፍቃድ ከዚህ ክህደት እንዲወጣ ተምረህ አስተምር ይህም የነብያት መንገድ ነው።

ወሎ ላይ
📱📱📱📱📱📱📱
1) የቦረናው ደግዬ እርዱኝ አባብዬ ይባላል። ይሄ ክህደት ነው።
2) ሙወከል እየተባለ ለሰይጣን ለነ ሰይፉ ጨንገሬ ይታረዳል። ይሄም ከኢስላም ያስወጣል።

📱📱📱📱📱📱📱

ታድያ ይሁ ሁሉ ክህደት እና በአላህ ላይ ማጋራት ያለበትን የኢትዮጵያ ህዝብ ጭራሽ ፊልማቸው ኦርቶጉል ውስጥ ኩፍር የጨመሩትን ቱርኮች አንት ልትሰራ ላሰብከው "ፊልም" ጭራሽ እርዳታ መጠየቅህ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አይሆንምን?

🛑ወንድሜ መልካም ነገር ማለት አንተ መልካም ያልከው ሳይሆን ኢስላም መልካም ያለው ነው።

🎧 ኢስላምን ለማገዝ ከቁርአን ከሐዲስ ኡለማዎች ከሄዱበት መንገድ ውጭ ያለው ሁሉ የጥፋት መንገድ ነው።

ገንዘብ እና ጊዜህን በጥፋት መንገድ ላይ አታባክን።

አላህ ፊት ብቻችንን ራቁታችንን የምንቆምበት ቀን አለ።

ለአላህ ብለህ ተወው። አላህ በተሻለ እሱ በሚወደው፣ ወደሱ ለሚያቃርብህ አምልኮ አንተንም እኛንም ይለግሰን።
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem


ሙሓደራ 222

አተቅዋ ወሲየቱላህ

↪️ በ ቡታጅራ ከተማ የተደረገ ሙሓደራ

🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሓቲም)

=
t.me/UstazKedirAhmed/8378


በያካባቢያችሁ ያሉ አቅመ ደካማ መሻይኾችን፣ ዱዓቶችን፣ የቁርኣን አስተማሪዎችን፣ የመስጂድ ኢማሞችን፣ ሙአዚኖችን፣ በዒልም ፍለጋ ላይ የተሰማሩ ደረሶችን፣ ... ብትችሉ አስተባብራችሁ፣ እሱ ባይሆን የአቅማችሁን በራሳችሁ ማገዝን አትርሱ። "እንዴት እየኖሩ ይሆን?" ብላችሁ አስቡ። ኑሯቸውን ደጉሙ። ኪታብ ግዙላቸው። ከጎናቸው ቁሙ። እነዚህን ማገዝ ዲንን ማገዝ ነው።

በተለይ በተለይ የመስጂድ ኮሚቴዎች በዚህ ረገድ ሃላፊነታችሁን ተወጡ። ነጋዴዎች ጓደኞቻችሁን አስተባብሩ። ሌሎችም እንዲሁ አላህ የገራላችሁን ያህል ሳትሰስቱ በየ ሰፈሩ ላሉ አቅመ ደካሞች አድርጉ። ነብዩ ﷺ “ከሰው ሁሉ በላጩ ለሰዎች ይበልጥ ጠቃሚ የሆነው ነው” ይላሉ። [አሶሒሐህ፡ 426] በደዕዋ ላይ የተሰማሩ አካላትን ማገዝ ሲሆን ደግሞ ዋጋው ይለያል።

"ሼር" አድርጉ፣ ባረከላሁ ፊኩም። ምናልባት ለሆነ አካል መታገዝ ሰበብ ትሆኑ ይሆናል።
الدَّالُّ عَلَى الْخَيْرِ كَفَاعِلِه
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor


ደግሞም ልንገርህ! አካደሚ እውቀት ቀርቶ ሌሎች የሸሪዐ ዘርፎች እንኳ ዋጋ ይኖራቸው ዘንድ ተውሒድ ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው። ሸምሰዲን አሰፋሪኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ “ሌሎች የእውቀት ዘርፎች ለተውሒድ እውቀት ቅርንጫፎች ናቸው። ምክንያቱም እሱ ከአምልኮቶች ሁሉ የላቀው፣ ከትእዛዛት ሁሉ በላጩ እንዲሁም እያንዳንዱ አምልኮትና ትእዛዝ፣ ጤናማ ይሆን ዘንድ ብሎም ዋጋ ይኖረው ዘንድ መስፈርቱ ነውና። የክብርና የልቅና ባለቤት የሆነው (ጌታ ምንነት) የሚታወቅበትም ነውና።” [ለዋሚዑል አንዋሪል በሂያ፡ 1/57]
ስለዚህ በቅድሚያ ለራስህ ሁን! ለራስህ ሳትሆን ለህዝብ አትሆንም። ያለበለዚያ አስር ገንብተህ ሺ ታፈርሳለህ። ምንም ላይ ሳትሆን ትልቅ ነገር ላይ ያለህ ይመስልሃል። በተውሒድ የምትሳለቅ፣ ለቀብር አምልኮ የምትወግን ከሆንክ የታሪክም ሆነ የፖለቲካ አስተዋፆህ የዜሮ ብዜት ነው የሚሆነው። አልዓስ ብኑ ዋኢል በጃሂሊያ መቶ ግመል ሊያርድ ስለት ተስሎ ነበር። ስለቱን ሳይፈፅም ስለሞተ ልጁ ሂሻም ሃምሳ ግመል አረደለት። ሌላኛው ልጅ ዓምር ግን የድርሻውን ከማረዱ በፊት የአላህ መልእክተኛን ﷺ ስለ ጉዳዩ ቢጠይቅ {አባትህማ ተውሒድን ቢቀበል ኖሮ ብትፆምለት ብትሰድቅለት ይጠቅመው ነበር} ነው ያሉት። [አሶሒሐህ፡ 1/180] ሰላም!

(ኢብኑ ሙነወር፣ የካቲት 19/2014)
=
https://t.me/IbnuMunewor


መኖርህ እዳ አይሁን!
ላንተ ነው! “ቀለም ለገባህ”!
~
1. አንተ ልዩ አይደለህም!

ሙስሊሙ፤ እንደ ማህበረሰብ ሰቅዘው የያዙት ብዙ አይይነት ችግሮች እንዳሉበት ግልፅ ነው። በኛ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አለማት ኢኮኖሚው የደቀቀ፣ ማህበራዊ ህይወቱ የተናጋ፣ ፖለቲካዊ ስርኣቱና ሚናው የወረደ፣... ብዙ ሙስሊም ማህበረሰብ አለ። ችግሩን ‘ፍሬም’ በማድረግና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ላይ ሃሳቦች ሊለያዩ ቢችሉም ይህን እውነታ በመረዳት አንተ ብቸኛ አይደለህም። እራስህን ከማህበረሰቡ አንዱ እንጂ ልዩ አድርገህ አትሳል። ሙስሊሙ ኡማ ውስጥ የተማረው የቀለለ ከመሆኑ ጋር የተማርከውን የተማሩ፣ የምትረዳውን የሚረዱ ብዙ እንዳሉ አትዘንጋ። ይህንን እውነት ለነፍስህ ሹክ በላት። “ብርቅየ አይደለሽም” በላት። ያኔ እብጠቷ ይተነፍሳል። መንጠራራቷ ይቀንሳል።

2. የደዕዋው ዘርፍ የመፍትሄዎቻችን ሁሉ እናት ነው!

ቀዳዳዎቻችን ብዙ ናቸው። በዚያው መጠን ዘርፈ ብዙ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ያስፈልጉናል። በሆነች ዘርፍ ላይ ትንሽ አስተዋፅኦ ስለኖረችህ ለሌሎች በተለይም ለደዕዋው ዘርፍ ያለህ እይታ አይንሸዋረር። ለደዕዋው ዘርፍ ያለህ አክብሮት ለኢስላምህ ያለህ አክብሮት ነው። የደዕዋውን ዘርፍ ሳታከብር ለኢስላም አክብሮት ሊኖርህ አይቻልም። ኢስላም ያለ ደዕዋ ምንም ነው። አዎ በደዕዋው ዘርፍ ላይ ብዙ ችግሮች አሉ። ግና “ችግሩ የሚፈታው በማነው?” ብለህ እራስህን ጠይቅ። አንተ ለዚህ ብቃቱ አለህ? የተማርከው ትምህርት ለዚህ የሚያበቃህ ነው? የእውነት አካደሚ ስለተማርክ ብቻ ያለውን መሰረታዊ ችግር የምታውቀው ይመስልሃል? እንዴት ሆኖ?!

3. አንጃዎችን መኮነን ከአንጃ ውጭ አያደርግህም!

ብዙ የተማሩ ወንድሞች አንጃዎችን ስላወገዙ ብቻ ገለልተኛ የሚሆኑ ይመስላቸዋል። ነገሮችን በዚህ መጠን መረዳት ሲበዛ ግልብነት ነው። በቅድሚያ ገለልተኝነትህ ከሐቅም ሊሆን ስለሚችል ጉዳዩን ከልብ መርምር። ጉዳዩን ቀርበው ሳይመረምሩ ሁሉንም በጭፍንና በጅምላ ማውገዝ በስንፍና ውስጥ ማድፈጥ እንጂ ልዩነትን መፀየፍ አይደለም። ይህንን ለማድረግ አቅምና ፍላጎቱ ከሌለህ ዝምታን ማን ያዘብህ? ምላስህንም ብእርህንም ከንዲህ አይነቱ ጉዳይ ሰብስበህ በምትችለው ሙያ ወገንህን አገልግል። በአደብህ ተከበር። የማትችለውን ገብቼ አቦካለሁ ስትል፣ በምትችለው ዘርፍ ልታበረክተው የምትችለውን አስተዋፅኦ ታመነምነዋለህ።
ልንገርህ ወዳጄ! የሆኑ የሚፋጩ አካላትን ስላየህ፣ የሚወረወሯቸውን ቃላት ስለሰማህ ብቻ ስለጉዳዩ ያለህን መረዳት በዚያ መጠን አቅልለህ አትመልከት። እንዲህ አይነቱ ጥራዝ ነጠቅ ድምዳሜ ነው አንዳንዶችን በመሰረታዊ የኢስላም ክፍል ላይ እንዲሳለቁ እየገፋቸው ያለው። ሳይረዱ እንደተረዱ ማሰብ።
እንዲያውም የአንዳንዶቹ ገለልተኝነት ከማስመሰል የዘለለ አይደለም። ክስተቶችን እየጠበቁ ለይተው ሲያጠቁ፣ ለይተው ደግሞ ሲያደንቁ ታገኛቸዋለህ። “የአይነላህ ተቆርቋሪዎች” እያለ በነብዩ ﷺ ሐዲሥ ላይ የሚያሾፍ ሰው፣ “ተው” እና “ሂድ” እያለ በተውሒድ ላይ የሚሳለቅ ሰው በየትኛው ሞራሉ ነው ስለ ገለልተኝነት የሚያደነቁረን? ለኡማው መትረፉ ቀርቶ እራሱን ባዳነ!

4. ይልቅ ለኡማው ሸክም አትሁን!

እራስህን ብቻ ሁን! ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ ላይ አይወጣም። ማኔጅመንት ወይም ፖለቲካ ተምረህ የደዕዋ ስልጠና ካልሰጠሁ አትበል። በዱዓት ላይ መዘባነንህን አቁም። ፖለቲካ ብትደሰኩርም፣ ታሪክ ብትተርክም፣ መድረክ ብታደምቅም ዋጋ የሚኖረው ለተውሒድ በሚኖርህ ክብር ነው። አክብሮቱ ቀርቶ ሸክም የምትሆን ከሆነ የትኛውም ያንተ አበርክቶ ገለባ ነው። ተውሒድና ሺርክን የማትለይ፣ በተውሒድ ላይ እየተሳለቅክ ለቀብር አምልኮ የምትወግን ከሆነ፣ ወይም ደግሞ በገለልተኝነት ስም ተውሒድንም ሺርክንም እኩል የምታወግዝ ከሆነ እውነቴን ነው የምልህ ከመኖርህ አለመኖርህ የሚሻል ለመባል እንኳን አትመጥንም። እንዲያውም ለሙስሊሙ ኡማ ከጠላት የከፋ እዳ ነህ።

5. ከ“ንቃትህ” ንቃ!

መንቃት ማለት እንግሊዝኛ እየቀላቀሉ ማውራት አይደለም። መንቃት ማለት በግምት የታጨቀ የሴራ ፖለቲካ መፈትፈት አይደለም። መንቃት ማለት የራስን እያናናቁ በፈረንጅ ፍልስፍና ላይ መራቀቅ አይደለም። መንቃት እራስን ማወቅ ነው። መንቃት የማህበረሰብን መሰረታዊ ችግር መለየት ነው። ተውሒድና ሺርክን የማትለይ፣ የወገንህ የሙታን አምልኮ ላይ መነከር የማይቆጠቁጥህ ከሆነ እንኳን ለሰው ልትተርፍ ለራስህ አንቂ ያስፈልግሃል።
ደግሞም እወቅ! ይሄ ሌሎችን ማናናቅና እራስን መቆለል የጀርባ መንሴው ለዘመናዊ ትምህርት ያለህን የተንሸዋረረ እይታ ነው የሚያጋልጠው። ትምህርቱ አስፈላጊ እንደሆነ የሚያከራክር አይደለም። ህዝበ ሙስሊሙ ባለመማሩ የደረሰብት ውስብስብ ችግር እንዳለ የሚዘነጋ አይደለም። ቢሆንም በልክ አድርገው። የቀለም ትምህርት ከዲን ትምህርት፣ እንግሊዝኛ ከዐረብኛ፣ የነ ዑመር፣ የነ ሙዓዊያ ታሪክ፣ ከነ ሶቅራጠስ ሊነፃፀር አይችልም። በቅድሚያ እራስህን ከአስተሳሰብ ተፅእኖ ነፃ አውጣ! እነ ፍሮይድና ማስሎውን እያደነቅክ ዑለማዎችን የምትንቅ ከሆነ ብሽቅነትህን ብቻ ነው የምታሳየው። “የፋርስና የሮማ ፈላስፎች ጥበብ ላይ የሚያተኩር ለኢስላማዊ ጥበብና ስርኣት ልቡ ውስጥ ቦታ አይኖርም” ይላሉ ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ። [አልኢቅቲዷእ፡ 217]

6. ሚናህን ለይ!

ዱዓት መሃል ብዙ ችግሮች እንዳሉ የሚታወቅ ነው። የምታየው ቢያምህ ሰውኛ ስሜት ነው። ሃሳብ ካለህ ዲኑ ያንተም ነውና እርምትና ሃሳብ መስጠት ያባት ነው። ችግር የሚመጣው ያልገባህን እያወራህ የእብድ ገላጋይ ስትሆን ነው። ወይ ዲንህን ተማር! ወይ ሃሳብህ የተመጠነ ይሁን። ባቅምህ ልክ ብቻ አውራ። ቀይ መስመር አትለፍ። ማኔጅመንት ተምረህ ቀዶ ጥገና ህክምና ካላደረግኩ ትላለህ እንዴ? ሳይኮሎጂ ላይ እድሜህን ፈጅተህ ተፍሲር ካላስተማርኩ ይባላል ወይ? ልክ ሃያ ሰላሳ አመት እድሜህን የቀለም ትምህርት ላይ ስለፈጀህ ብቻ ይሄ ነው የሚባል ትኩረት ባልሰጠኸው እምነት ላይ ፈራጅ ቀዳጅ ካልሆንኩ አይባልም። በቃ አቅምህንና ተሰጥኦህን ለይ! የግድ ስለ ሁሉም ማውራት አይጠበቅብህም።

7. ስለ ዲንህ ተማር

በቀለም ትምህርት ላይ መራቀቅ እንደምትሻው ሁሉ ለዲናዊ ትምህርትም ጊዜ ስጥ። ከምንም በላይ የዚያኛውን አለም ስንቅ ታዘጋጅበታለህ። በመተጓዳኝ የራስህን ጨምሮ የወገንህን ችግርና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ትለይበታለህ። በርግጠኝነት ነገሮችን የምትመለከትበት መነፅርም ይቀየራል።
በተለይም ደግሞ መሰረታዊ የእምነትህን ክፍል ተውሒድን ተማር። አካደሚ ስለተማክ ብቻ ከሺርክ የምትርቅ ከመሰለህ ሞኝ ነህ ወላህ! በአለም ላይ ቁራጥራጭ እንጨቶችን፣ ያሸበረቁ ስዕሎችን፣ ላሞችን፣ አይጦችን፣ በሰው ልጅ ብልት አምሳል የተቀረፁ ሀውልቶችን የሚያመልኩ ህልቆ መሳፍርት ዶክተሮች፣ ፕሮፌሰሮች አሉ። የተማሩት ትምህርት፣ የሚቀናጡበት ቴክኖሎጂ፣ የተቆናጠጡት ስልጣን፣ የሚያጋብሱት ሀብት ግኡዛንና እንስሳትን ከማምለክ አላወጣቸውም። ብልህ በሌሎች ይማራል። ሞኝ በራሱ ላይ በሚደርሰው ይማራል። አንተ ከሁለቱም ተራ ወጥተህ ሳይማሩ የተማሩ ከሚመስላቸው አትሁን።




‏[الفرق بين الفجر الصادق و الفجر الكاذب ]

ليس الفجرُ الأبيضَ المستطيلَ في الأفُقِ، ولكنَّهُ الأحمرُ المعترِضُ
الألباني (١٤٢٠ هـ)، صحيح الجامع ٥٣٧٨ • صحيح


"አላህ ከዐርሽ በላይ ነው"

ሸዕባን 25/1446 (የካቲት 17/2017)
በዳሩ ተውሒድ የኢሞ ግሩፕ ላይ የቀረበ
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor




ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
٤٥١٠ - «كل امرء في ظل صدقته حتى يقضى بين الناس»
“በሰዎች መካከል ፍርድ እስከሚስሰጥ ድረስ ሁሉም ሰው በሶደቃው ጥላ ስር ነው የሚሆነው።” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 4510]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor


የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
(إذا أكل أحدكم فليأكل بيمينه ، وإذا شرب فليشرب بيمينه ، فإن الشيطان يأكل بشماله ويشرب بشماله)
"አንዳችሁ ሲመገብ በቀኙ ይመገብ። ሲጠጣም እንዲሁ በቀኙ ይጠጣ። ምክንያቱም ሸይጧን ነውና በግራው የሚበላውና በግራው የሚጠጣው።"
[ሙስሊም፡ 2020]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor


አንዳንድ እህቶች ኒካሕ ሲቃረብ አባቶቻቸው ሺርክ ላይ እንደሆኑ በመጥቀስ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ይጠይቃሉ።
1- በመጀመሪያ የእውነት ሺርክ መኖሩን በተጨባጭ ማረጋገጥ ይገባል። ኹራፋት፣ ቢድዐዎች፣ ተወሱላት ጥፋት ከመሆናቸው ጋር ብቻቸውን ሺርክ ላይ ላይደርሱ ይችላሉ። ችግሩ እዚያ የሚደርስ መሆን አለመሆኑን በትክክል መለየት ይገባል።
2- በተጨባጭ አባት ሺርክ ላይ መሆኑ ከተረጋገጠ ተስፋ ሳይቆርጡ የሚችሉትን ሁሉ ጥረት በማድረግ ለመመለስ መጣር ይገባል። ይሄ የኒካሕ ሰሞን ሳይሆን ቀድሞ ነው ሊሰራበት የሚገባው። ከኒካሑ የበለጠ የሚያሳስበው ይሄ ነው። "ክፉ ደግ አይቶ፣ ለፍቶ ያሳደገኝ አባቴ ኒካሕ አታስርም ሲባል በጣም አዘንኩኝ፣ ከፋኝ፣ ..." የሚል የዓጢፋ (ስሜት) ንግግር ዋጋ የለውም። ሺርክ ከኢስላም የሚያስወጣ፣ ዘላለማዊ ክስረትን የሚያስከትል፣ እስከወዲያኛው ከሚወዱት የሚለያይ ከባድ ጥፋት ነው። ከኒካሑ በፊት ሺርክ ውስጥ ሲኖሩ ያልተሰማን ስሜት "ወሊይ አይሆኑም" ሲባሉ ከተሰማን ችግሩ ከራሳችን ነው። ገና ያልጠራ ነገር አለ ማለት ነው። እናጥራ።
3- በተረፈ ከኢስላም የሚያስወጣው ትልቁ ሺርክ መኖሩ በተጨባጭ ተረጋግጦ፣ ተመክረው ተዘክረው ከተቀበሉ ወሊይ ሆነው ኒካሑን ያስራሉ። ከኢስላም የሚያስወጣው ትልቁ ሺርክ መኖሩ በተጨባጭ ተረጋግጦ፣ ተመክረው ተዘክረው ለመቀበል አሻፈረኝ ካሉ ግን ወሊይ ሆነው ኒካሕ ሊያስሩ አይፈቀድም። ከዚህ ዝቅ ባለ ጉዳይ ሶላት የማይሰግዱ ሆነው እንዲሰግዱ ቢመከሩም ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ለኒካሕ አይሆኑም። የሶላት ጉዳይ በንፅፅር ከተውሒድ ያነሰ ከመሆኑ ጋር ማለት ነው።
4- እንዲህ አይነት ሁኔታ ከገጠመ ወሊይነቱ ወደሌላ ቅርብ ቤተሰብ ይሻገራል። ኒካሑ በነሱ በኩል ይታሰራል። ለኒካሕ የሚሆን ቤተሰብ ከሌለ በቃዲ ይታሰራል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor


የሁለቱ "ስደቶች" ወግ!
~
"ስደት ላይ ነን" የሚለው የነ ሐሰን ታጁ እየየ አላማ አንዳንድ ደጋፊ ባለ ስልጣናትን በመጠቀም የመጅሊስ ሰዎችን በማስደንገጥ ዳግም ቦታውን ያለ ተቀናቃኝ መቆናጠጥ ነው። ሰሞኑን ላይ ታች እያለ የሚዶልተውም ለዚሁ ነው። ከዚያ እግሩን በተከለ ማግስት ወደ ህልሙ ይመለሳል። "ድመት መንኩሳ አመሏን አትሳ!" ከነ አባይ ፀሐዬ ጋር አሲረውት የነበረውን የማሳደድ ስራ አጠናክሮ መቀጠል ነው ህልማቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
"ሂጅራ ላይ ነን" እያሉ ነው አሕ ^ ባሾች። በመንግስት እገዛ መስጂድ ሲነጥቁ ፣ ህዝብ ሲያሳድዱ፣ በጉልበት ሲያጠምቁ የነበሩት የሱ ቡድን ሰዎች ናቸው። ሙስሊሞችን ለማስመታት እነ አባይ ፀሐዬን ሲቀሰቅሱ የነበሩት እነሱ ናቸው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
"እራስ ሳይጠና ጉተና መነቃቀሱ ፈተና!"
~
አሁን ይሄ ሳይሞቅ ፈላ "ው ር - ጋ ጥ" ቢባል የሚከፋችሁ ትኖራላችሁ። ይሁና! ግን እንዴት ነው የሚሰራው?! እንዴት ነው የሚያደርገው? ራሱን ምን አድርጎ ነው የሚያስበው? እንዴት ነው የሚበጣጠስብን? ምስኪን! ወላሂ እንዲህ አይነቱን የጥጃ ቀን ~ ዳ ም መድረክ የሚሰጡ ሰዎች ናቸው በጠዋቱ ያመከኑት። ተው ለማይሆኑ ሰዎች መድረክ እየሰጣችሁ ሞኝ አንጋሽ አትሁኑ። እነዚህ አጥፍቶ ጠፊ ናቸው። ﻍሩር በጣም መጥፎ ነገር ነው። አስክሮ ሲያበቃ ገደል እየከተታቸው ነው።
የኹጥባ አካሄዶች ላይ ካሉ ክፍተቶች በላይ በነዚህ ወጠ ~ ጤዎች የሚደርሰው ጥፋት የከፋ ነው። ሺርክና ቢድዐ አይጎረብጣቸውም። በየደረሱበት ደዕዋ ገምጋሚ ናቸው። ለራሳቸው ሳይማሩ የደዕዋ ስልጠና መስጠት ይፈልጋሉ። በራሳቸው የቃላት ኳኳታ ተደፍነዋል። ኃላፊነት የጎደላቸው የሚዲያ ሰዎች መድረክ ይሰጧቸዋል። በቲቪ መስኮት ላይ ያየውን ሁሉ የሚሰቅል እ^ብ *ድ አንጋሽ መንጋ ያጨበጭብላቸዋል። ተያይዞ መዝቀጥ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


መስገጃ ስንገዛ ትኩረት የማይስብ፣ ዲዛይኑ ወጥ የሆነ፣ ልሙጥ ቀለም ያለው ቢሆን የተሻለ ነው። የተለያዩ ጥልፎችና መስመሮች ያሉበት ሲሆን በሶላት ውስጥ ተሁኖ ትኩረት ሊከተለው ይችላል። ነብያችን ﷺ እንዲህ አይነቱን መስገጃ መልሰው አንድ ቀለም ብቻ በሆነው ቀይረዋል። [አልቡኻሪይ፡ 252] [ሙስሊም፡ 556]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


📣🖱 የሙሓደራ ፕሮግራም 🖱📣

🛜 ለኢሞ ተጠቃሚዎች በሙሉ! እነሆ የፊታችን [ ሰኞ ] ደማቅና በአይነቱ ለየት ያለ የሙሐደራ ድግስ ተዘጋጅቶ እየጠበቃቹህ ይገኛል።

▫️ተጋባዥ እንግዶቻችን፦

1⃣ ኢብኑ ሙነወር
     〰〰〰〰〰〰〰
☑️ ርዕስ : አሏህ ከዐርሽ በላይ ነው
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

2⃣🎙 ኡስታዝ አቡል ዓባስ
     〰〰〰〰〰〰
☑️ ርዕስ : ጭፍን ተከታይነት ያለው አደጋ
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

👁‍🗨 ፕሮግራሙ በአቡ ረያን እና በአቡ ሐኒፋ የሚመራ ይሆናል።

💳 ሌሎችም የሱና ወንድሞች እና ኡስታዞች ይገኙበታል።

🕰 የፕሮግራሙ ሰዓት:-
🌌 ምሽት ፦ 02:30 በኢትዮ

🔎 አድራሻ ⤵️⤵️⤵️
(ዳሩ_ተውሒድ )🇸🇦 ኮድ (2⃣) የኢሞ ግሩፕ#⃣
🛜🚁. انقر على الرابط للانضمام إليها! https://s.imoim.net/eOvNnM?from=copy_link

📟 ምናልባት ሊንኩ ቴሌግራም እያላቹህ አላስገባቹህ ካለ ሊንኩን ኮፒ አድርጉና ኢሞ ላይ ለሌላ አካል ሸር በማድረግ ከዚያም ያንኑ በመጫን ሞክሩት ያስገባል ኢንሻ አሏህ።
🔗🔗🔗⤵️⤵️⤵️
https://s.imoim.net/eOvNnM?from=copy_link


ዛሬ እሁድ ሸዕባን 25/1446 (የካቲት 16/2017)
አሸዋ ሜዳ ዘህራእ መስጂድ የቀረበ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

Показано 20 последних публикаций.