ISLAMIC SCHOOL


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


✍ ጅልከሆንክ ጅል ተከታይ ጀንትል ከሆንክ አስከታይ ትሆናለህ..!
ጅልም ጀንትልም ካልሆንክ ደግሞ አርፈህ በራስህ ዓለም ትኖራለህ..! አንባቢ እንሁን፡፡ለውጥ ከራስ ቢጀመር ...የቸገረን ጥሩ መካሪ ሳይሆን፤
የሰማነውን መተግበር ነው ያቃተን!ጅህልና በሽታ ነዉ፡፡
🎖For any comment T.me/Aisuu_bot
💠Another channal
@IslamisUniverstiy_public_group

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


>>>>>>🔰 #ድንቃ_ድንቅ_ንግግሮች🔰


🎖🎖 #የአራቱ_መዝሀብ_ባለቤቶች🎖🎖
               ✍🏼 አሚር ሰይድ


የአራቱ ዝነኞቹ መዝሀቦች ባለቤቶች የት እንደተወለዱ፣ መቼ እንደተወለዱና መቼ እንደሞቱ በቅደም ተከተል እነሆ


➊ - አል-ኢማሙ አቡ ሐኒፋ አን-ኑዕማን ቢን ሣቢት፡- በዒራቅ ውስጥ ኩፋ በምትባል ከተማ  በ8ዐኛው ዓመተ ሂጅሪያ የተወለዱና በ150 ዓመተ ሂጅሪያ ሙተዋል

➋ - አል-ኢማሙ ማሊክ ቢን አነስ (የዳሩል ሂጅራ ኢማም)፡- በመዲነቱን ነበዊያ በ93 ዓመተ ሂጅሪያ የተወለዱና በ179 ዓመተ ሂጅሪያ እዚያው ሙተዋል

➌ - አል-ኢማሙ ሙሐመድ ቢን ኢድሪስ አሽ-ሻፊዒይ፡- በ150 ዓመተ ሂጅራ በሻም ሀገር ውስጥ በጋዛ ላይ የተወለዱና በ204 ዓመተ ሂጅሪያ በግብፅ ላይ የሞቱ

➍ - አል-ኢማሙ አሕመድ ቢን ሐንበል (የአህለ ሱንና ወል ጀማዓ ኢማም) በ146 ዓመተ ሂጅሪያ በበግዳድ የተወለዱና በ241 ዓመተ ሂጅሪያ እዚያ የሞቱ ናቸዉ
አሏህ ሁሉንም ቀብራቸዉን ብርሀን ያድርግላቸው


🔰🔰🔰 #አራቱ_የመዝሀቦች_ባለቤቶች የአላህ
መልዕክተኛ ﷺ ሱንናን እንዳለ ወስደው በመከተልና አጥብቀው በመያዝ ዙሪያ እንዲህ ብለዋል፡-


☞ ኢማም አቡ ሐኒፋ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡- ሐዲሡ ትክክለኛ ከሆነ የኔ መዝሀብ እርሱ ነው፡፡ እንዲህም ብለዋል፦ እኛ ከየት እንደወሰድነው ሳያውቅ ለእንድም ሰው የእኛን ንግግር መውሰድ አይፈቀድለትም፡፡

☞ ኢማም ማሊክ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡- እኔ ስህተት የምሰራና ትክክል የምሆን የሰው ልጅ ብቻ ነኝ፤ ስለሆነም አስተያየቴን ተመልከቱ፤ በውጤቱም ከኪታብና በሱንና ጋር በገጠመ ቁጥር ያዙት፤ በኪታብና ከሱንና ጋር ባልገጠመ ቁጥር ደግሞ ተውት።

☞ኢማም አሽ-ሻፊዒይ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦ እኔ ካልኩት በተቃራኒ በነቅል (በማጣቀስ) ሰዎች ዘንድ ማንኛውም ከአላህ መልዕክተኛ ﷺ የሆነ ዘገባ ትክክለኛነት ያለበት ጉዳይ ሁሉ ካለ፣ እኔ በሕይወት ሳለሁም ሆነ ከሞትኩ በኋላ ከርሱ ተመላሽ ነኝ፡፡

☞ ኢማም አሕመድ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡- እኔን በጭፍኑ እትከተለኝ፤ ማሊክንና ሻፊዒይን በጭፍኑ እትከተላቸው፤ ይልቁንስ እነርሱ ሁላቸውም የሀይማኖቱ ኢማሞች ነበሩ፡፡ብለዋል፡፡



⚠️ ዛሬ ግን እኛ ሙስሊሞች ስለመዘሀባቸዉ የሰጡትን አስተያየት ወደ ጎን ትተን በእነሱ ዙሪያ ስንጨቃጨቅ ስንነታረክ ብዙ ዘመናት አለፍን ...መቼ ይሆን ወደ አቅላችን ተመልሰን መዝሀቦቹን ወደ ቁርአን ሀዲስ ወስደን በቁርአን መስመር መከተል የምንጀምረዉ??


◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━   
4 another channal👇
             t.me/Islam_and_Science
💐⭐️💐
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


>>>>>>>> #ይህንን_ያቃሉ?


🎖#በሰይፍ_የተስፋፋዉ_ሀይማኖት_የቱ_ነው??🎖
                      ✍ አሚር ሰይድ


     እስልምና እዉነተኛ ሀይማኖት ሆኖ የሰዎችን ልብ  ስላሸነፈ እንጂ በሀይል የተስፋፋ አይደለም፡፡

የሌላ እምነት ተከታዮች ኢስላም ሀይማኖት በሰይፍ ነዉ የተስፋፋዉ እያሉ ከእዉቀት የራቀን ሙስሊም ሲያደናግሩ እያየን እየሰማን ነዉ፡፡ ግን እዉነታዉ ኢስላም ነዉ ወይስ ሌላ እምነት ነዉ በሰይፍ የተስፋፋዉ??


እስኪ ብዙ ጊዜ የሌላ እምነት ተከታዮች በድር ዘመቻን ያነሳሉ፡፡በድር ዘመቻ ጊዜ የተፈጠረዉን እነሆ
በበድር ዘመቻ ጊዜ ሙስሊሞች ሶስመቶ አስራ ምናምን ሲሆን ሙሽሪኮች ደግሞ ወደ አንድ ሺህ አካባቢ ነበሩ፡፡
ከሙስሊሞች 14 ሲሞቱ ከሙሽሪኮች ደግሞ 70 ሟቾች ነበሩ ጠቅላላ 84 ሰዉ ከሁለቱም ወገን ሙቷል ማለት ነዉ፡፡

✨✨ በኡሁድ ዘመቻ ጊዜ የነብዩ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ተሸነፈ ባይባልም ግን ድሉ ለቁረይሾች አመዝኖ ነበር፡፡ብዙ ሰሀባዎች በአሁድ ዘመቻ ጊዜ ወደ ፈጣሪያቸዉ አሏህ ተገናኝተዋል፡፡


      ለማመዛዘን ያመቸን ዘንድ  የአላህ መልዕክተኛ የሆኑት ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ተከታዮች ከፍተኛ መስፋፋት የሳዩት ከሑደይቢያ ስምምነት በኋላ ነበር። እንደሚታወቀው በዚህ ጊዜ ውስጥ ምንም ዓይነት ጦርነት አልተካሄደም። ከሑደይቢያ ስምምነት በፊት የሙስሊሞች ቁጥር 1400 ነበር። ይህ የሰው ቁጥር ወደ እስልምና የገባው በ19 ዓመታት የደዕዋ ጊዜ ውስጥ ነው። ከሑደይቢያ ስምምነት በኋላ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ መካ በድል ሲገቡ የሙስሊሞች ቁጥር 10ሺህ ነበር። በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እስልምናን የተቀበሉት ሰዎች ቁጥር 8600 ማለት ነው። ከዚህ መረዳት የምንችለው ለኢስላም መሥፋፋት ተስማሚው አየር ከጦርነት ይልቅ የሰላም መሆኑን ነው።


🎖🎖🎖እስኪ ሙስሊሞችን ጨራሽ ጨካኝና አረመኔ  አድርገው የሚያዩትን ሕዝቦች ደግሞ ከታሪካቸው ጥቂት እንመልከት።


🟨 The dark age በሚባለው የመከካለኛው ዘመን የአውሮፓ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ የሥልጣን እርከን ላይ በነበረችበት በፖለቲካና በጦር መሳሪያ እጅግ በተደራጀችበት ወቅት ማለትም ከ1481-1808 በአውሮፓ የተለያዩ የማሠቃያ ማእከላት 340 ሺህ ሰዎች ፍርድ ተሰጥቶአቸው ተሰቃይተው እንዲገደሉ ሆኗል። ከነዚህ ውስጥ 200 ሺህ ያህሉ ከነህይወታቸው እንዲቃጠሉ የተደረጉ ናቸው። የያኔዋ ቤተክርስቲያን መሬት ክብ ናት ከሚለው ድምዳሜ ለደረሱት ሳይንቲስቶች የሰጠችው ምላሽ እጅግ ዘግናኝ ነበር። በነ ጋሊሊዮ ዘመን ከ35000  በላይሳይንቲስቶች ተገድለዋል። በዓለም ታሪክ ውስጥ በፕሮቴስታንትና በካቶሊክ ቤተ ክርስትያናት መካከል ከፍተኛ የሆነ ደም መፋሰስ ተፈፅሟል። በነኚህ ፍልሚያዎች ገለልተኛ የታሪክ ፀሀፊዎች እንደሚሉት 14 ሚሊዮን እነሱ ራሣቸው አረ አታጋንኑት˚ ብለው እንደሚመሠክሩት ደግሞ 7 ሚሊዮን ሕዝብ አልቋል።

ይህ ነው እንግዲህ የገሀዱ ዓለም እውነታ። የዚህ ዓይነት የጠቆረና የተበላሽ ታሪክ ያለው አካል ኢስላም እንዲህ ነው፣ ጨፍጫፊ ነው፤ በዳይ ነው' እያለ ለማውራት ሲሞክር አለማፈሩ እጅግ ይገርማል!

ወደ ሌላ መረጃ እንለፍና ስለ የመስቀል ጦረኞች ጥቂት እንበል።

🟩 የሀያሏ አሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበረው ትንሸ ቡሽም በድሀዋ ሙስሊም አገር በአፍጋኒስታን ላይ ጦርነት ሲያውጅ የመስቀል ጦርነት ማወጁን ነበር የተናገረው። ኋላ ላይ የሙስሊሞች ጩኸት ሲበዛበት 'አይ አይደለም' ብሎ ቢሸፋፍንም።


🟪 ቡሽ የጅምላ ጨራሽ መሳሪያን ከለላ አድርጎ በኢራቅ ላይ በከፈተው ነዳጅን የመዝረፍ የግፍ ጦርነት ከሁለት ሚሊዮን በላይ ኢራቃውያን ተገድለዋል። 12 ሚሊዮን የተምር ዛፍ ከነሥር መሠረቱ እንዲገነደስ ሆኗል። ልብ እንበል አንድ ተምር ተተክሎ ፍሬ እስኪያፈራ የሚፈጅበት ጊዜ ከ30 - 40 ዓመታት ነው፡፡ የአንድ ጎልማሳ ሰው እድሜ።

🟧 የመስቀል ጦረኞች ቁድስ /ኢየሩሳሌም/ ሲገቡ በዚያች ትንሽ ከተማ ውስጥ ብቻ 70 ሺህ ያህል ሙስሊሞችን ገድለዋል። ከዚህም የተነሳ የደም ባህር ተፈጥሮ ወታደሮች እስከ ጉልበታቸው በደረሰ ደም ውስጥ ይዋኙ እንደነበር ይነገራል። ሰላሑዲን አል-አዩቢ ከ88 ዓመታት በኋላ ወደዚህች ከተማ ድል አድርጎ ሲገባ ሁሉንም ይቅር አለ፡፡ ሰልሀዲን አል አዩብ ምግብ ሲበላ ምርኮኞቹን ሳያበላ በፊት አይቀምስም ነበር። ከራሱ ከሚበላው ደህና ምግብም የሚሰጣቸው ሲሆን የሚበላውም እነሱ መብላታቸውን ካረጋገጠ በኋላ ብቻ ነበር። ሰልሀዲን ይህን የቁርአን አንቀፅ ተግባር ላይ ለማዋል ይመስላል ይህን የሚያደርገው፡

{ وَیُطۡعِمُونَ ٱلطَّعَامَ عَلَىٰ حُبِّهِۦ مِسۡكِینࣰا وَیَتِیمࣰا وَأَسِیرًا }
ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ለድኻ፣ ለየቲምም፣ ለምርኮኛም ለእስረኛም ያበላሉ፡፡(አል ኢንሳን 8)

   ይህን ታላቅ ሙስሊም የጦር መሪ ወዳጅ ብቻ ሳይሆን ጠላትም ጭምር ነው ስለ ስብእናውና ጀግንነቱ የመሰከረለት። ከቅርብ ዓመታት በፊት በሆሊውድ ዓለም ያደነቀው ፊልም ተሰርቶለታል። የዚህ ሰው አርአያ ሞዴልና አሠልጣኝ ታላቁ ነቢይ ናቸውና እንዲህ በመልካም ስብእና ቢቀረፅ ላይገርም ይችላል።


✏️ታጋዩ አርበኛ ሊቢያዊው ዑመር አልሙኽታር ስለ ጠላት ወገን “እነሱ ምርኮኞችህን እንደዚህ አድርገዋልና አንተም ተመሳሳዩን አድርግ' ተብሎ በተነገረው ጊዜ እነሱ አርአያችን አይደሉም' አልነበር ያለው!!። አዎን አርአያቸውን ታላቁ ነቢይ ሙሀመድ ﷺ ያደረጉ ሕዝቦች የሚኖሩት ለራሳቸው ሳይሆን ለኢስላም ነው። የሚከተሉትም ስሜታቸውን ሳይሆን አላህ ሱወ
እና የአላህን መልዕክተኛ ﷺ ፍላጎት ነው።


✏️የአሁኗ እስፔን በፊት አንደሉስ ከሙስሊሞች እጅ ወጥታ በከቶሊኮች እጅ ስትገባ በቁጥር ለመግለፅ የሚቸግር ሙስሊሞች ገለዋል፡፡
ሙስሊሞችን በህይወት እያሉ ተቃጥለዋል
◇ ከዚህም በላይ ሙታን ሙስሊሞችን ከመቃብራቸዉ አዉጥተዉ አቃጥለዋል
◇ በህይወት ያሉትን በግድ ክርስቲያን እንዲሆኑ አድርገዋል
◇ የሙስሊም አጠቃላይ ንብረታቸዉን ቀምተዋል
◇ በአንደሉስ አዛን ማድረጊያ እስኪጠፋ አዛንም እስከማይደረግ ምንም ሙስሊም እስከማይኖር ድረስ የማጥፋት ዘመቻ አድርገዋል፡፡

ኢንሻ አላህ የሆነ ጊዜ ስለ እስፔን አንደሉስ ታሪክ በአላህ ፍቃድ ይቀርባል፡፡


ታዳ ህሊና ማስተንተኛ ያለህ ወገኔ ሆይ እስልምና ነዉ ወይስ ሌላ እምነት ነዉ በሰይፍ የተስፋፋዉ❓❓❓ለባለህሊናዎች መልሱን ትተንዋል





◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━   
4 another channal👇
             t.me/Islam_and_Science
💐⭐️💐
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


(342)

[ ገንዘብ ካለህ ሴት ልጅ ጥላህ አትሄድም ]

ሀብታም ከሆንክ፣ የተደላደለ ኑሮ የምትኖር ከሆነ፣ በወጣህ በገባህ ቁጥር በስጦታ ካንበሸበሽካት፣ የምትፈልገውን ሁሉ ከገዛኽላት ... ሴት ልጅ መቼም ጥላህ አትሄድም።

ውሸት .... ውሸት .... ውሸት

ሴትን ልጅ በገንዘብ አትይዛትም።

ኤለን መስክን ታውቀዋለህ ... ያ እንደውም የቴስላ መኪና አምራች ኩባንያ ባለቤት፣ የጠፈር ምርምር ጣቢያ ባለቤት እና ቲውተር ይባል የነበረውን ማህበራዊ ሚዲያ ገዝቶ X ብሎ ስሙን የቀየረው .... አዎ እሱ። ይኼውልህ የመጀመሪያ ሚስቱን አግብቶ ስድስት ልጆች ወልዷል። አንዴ መንታ፣ አንዴ ደሞ ሶስት ልጆችን በአንድ እርግዝና ... እንዴት ቢጫወተው ነው አልክ ... ተወው እሱ ይቅር። በዚህች አለም ላይ ሁሉም ነገር ላለው እንዳሽቃበጠ ነው። ብቻ ወደ ቁምነገራችን ስንመለስ ... ይህች ሴት አብራው የቆየችው ለስምንት አመት ብቻ ነው። ምነው ስትባል ግንኙነታችን "ጤናማ" አልነበረም አለች። እህህ ... ያ ሁሉ ሀብት እና ገንዘብ እያለው ሲሏት .... ገንዘብ የትኛውንም ነገር ጤናማ አያደርግም ብላ ውልቅ።

በዚህ የተናደደው ኤለን ቆይ ምን የመሰለችውን አግብቼ ባላደብንሽ ብሎ መነሳት .... ከሁለት አመት በኋላ እንደፎከረው ምራቅ የምታስውጥ አክተር አግብቶ ለሁለት አመት ሲያጫውት ከርሞ ተለያየ። ከአንድ አመት በኋላ ያልጨረስነው ፍቅር አለን ብለው እንደገና ተጋቡ። ያላለቀው ፍቅር የቆየው ለሶስት አመታት ብቻ ነው። እቺኛዋም በቃኝ ብላ ሄደች። አሁን እሱም ገንዘቡ የትኛዋንም ሴት እንደማያቆይለት አምኖ በየሄደበት እየወለደ ሴቶቹም በጋራ ልጅ እያሳደጉ መኖርን መርጠዋል።

ይሄ ሰው የአለማችን ቁጥር አንድ ሀብታም ነው። የእሱ ገንዘብ ሴትን ካላቆየ የአንተ ሰባራ ሳንቲም በየትኛው አቅሙ ነው "በብሬ እይዛታለሁ" ብሎ ልብህን ያሳበጠው?

ቢል ጌትስ ጋር እንምጣ። ይሄ ሰው የማይክሮሶፍት ኩባንያ ባለቤት ነው። ለ27 አመት አብራው የቆየችው ሚስቱ ጥላው ስትሄድ ምክንያት ያደረገው "በግል ጉዳይ አልተግባባንም" የሚለውን ነው። አየህ ገንዘብ ከ27 አመታት በኋላ የሚመጣ የግል ጉዳይንም አይፈታም።

የአማዞኑ ባለቤት ጄፍ ቤዞስም ለ25 አመት የኖረው ትዳሩ ባለው የገንዘብ ብዛት አልዳነም። ብር አለኝ ብሎ ውሽማ ይዞ እሽኮለሌ ሲል አንተም ብርህም ገደል ግቡ ብላው እብስ። የምትካፈለውን ብር አስባ እንዳይመስልህ .... ትንሽ ነው የወሰደችው።

እንግዲህ አስበው እነዚህ ሁሉ ሰዎች ያላቸውን ብር አንተ እድሜ ልክህን አታገኘውም ... ግን ሴቷን በብሬ እይዛለሁ ብለህ ታስባለህ።

ደ|ደ|ብ ካልሆንክ በስተቀር የየትኛዋንም ሴት ታማኝነት በገንዘብ እንደማትገዛው መረዳት አለብህ።

በፍቅር ስም አብረህ ስትጃጃል ስለከረምክ ጥላህ አትሄድም ማለት አይደለም።

ጥሩ ሰው ነህ ማለት አስደግፋህ አትሸበለልም ማለት አይደለም። አንተ መልካም ስለሆንክላት ትሳሳልሃለች ማለት አይደለም።

ብልጥ ሁን ወዳጄ

ሴትን ልጅ አስሮ የሚያስቀምጣት ገንዘብህ፣ ፍቅርህ፣ ጥሩነትህ፣ መልክህ፣ የአልጋ ላይ ነብርነትህ አይደለም .... ፍላጎቷ ብቻ ነው።

እንደውም ገንዘብህ አስሮ እንደሚያስቀምጣት በተማመንክ ቁጥር የመሄዷ ነገር እርግጥ እየሆነ ይመጣል።

ጢባርህንም .... ትቢትህንም .... እብሪትህንም በልኩ አድርገው። አለበለዚያ ታበርድልሃለች !!

~

... ብቻ ነገሩ ውስብስብ ነው !!

~

        ✨ ባሻ ዘብሔረ ጠቅላይ ግምጃ ቤት  ✨

                      ★★★ ኦሮማይ ★★★

                      🧘‍♀️🧘🧘‍♂️

                    © Abby Junior


t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


🎖 #ስላስደነገጥከዉ_ሶስት_ቁና_ጨምርለት 🎖
                  ✍ አሚር ሰይድ


       ከአይሁድ ታላላቅ መሪዎች የነበረው ዘይድ ኢብኑ ሰዕነህ ወደ ነቢያችን ﷺ ዘንድ መጣ። ይህ ሰው ከሳቸው ላይ እዳ ነበረው። ድንገትም ከኋላቸው ሆኖ ኩታቸውን ሰብስቦ አንገታቸውን በኃይል አነቃቸው። ከዚያም እናንተ የዐብዱልሙጠሊብ ልጆች የሰውን እዳ ታቆያላችሁ??በማለት በኃይለ ቃል ተናገራቸው። ዑመር ከአጠገባቸው ነበሩ ሰውየውንም ገፍትረዉ ጣሉት። በጣምም ተናገሩት።

ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ የዑመርን ድርጊት አልወደዱለትም። ፈገግ አሉና 'አይ አንተ ዑመር! እኔና ይህ ሰው እኮ ካንተ የምንፈልገው ከዚህ የተሻለውን ነገር ነበር። አሁን ያደረግከው ነገር ለኛ ምንም አይጠቅመንም። እኔን በአግባቡ ያለብኝን እዳ እንድመልስለት እሱ ደግሞ የሰጠኝን ነገር በሥርዓት እንዲጠይቀኝ ማመላከት ትችል ነበር' አሉት። .....አስከትለውም እንዲህ አሉት “ለነገሩ ከተስማማንበት የጊዜ ቀጠሮ ሶስት ቀን ቀርቶታል። ቢሆንም ግን በል ሒድና የዚህን ሰውዬ እዳ ክፈለው። አንተ ደግሞ ስላስደነገጥከው ሦስት ቁና ጨምርለት!።'አሉት

    ነቢይ ካልሆነ በስተቀር ማንም ከዚህ ዓይነቱ የሥነ-ምግባር ምጥቀት ላይ ሊደርስ አይችልም። አይገርምም! 'ስላስደነገጥከው ሶስት ቁና ጨምርለት። ሰውየው ባላሰበው መልኩ ካበደረው በላይ ጭማሪ ትርፍ አገኘ። በዚህ ባየው ክስተት አይሁዱ ሰውዬ ተገርሞ ብቻ አላበቃም።የአላህ ፈቀድም ሆነና እስልምናን ተቀበለ።


  ⚡️⚡️⚡️ይህ ሰው በሚያምንበት መፅሐፉ ተውራት ውስጥ ስለተነገሩት የነቢዩ ﷺ ባህሪዎች መረጃ ነበረው። የሰለመበትንም ምክንያት ሲናገር በዚህ ሰው ላይ ሁሉንም ነገሮች ሞከርኩኝ። ሁለት ነገሮች ብቻ ሲቀሩኝ ሁሉንም አየሁኝ። እነሱንም ዛሬ ለማረጋገጥ ቻልኩ “መቻሉ ታጋሽነቱ መሀይምነቱን ይቀድማል። ድንበር ከታለፈበትም የመቻል ሁኔታው እየጨመረ ይሄዳል ብሏል።
#ሀቢቡና_ሙሀመድ_ﷺ 😍😍




👌ሰይዲና ሙሀመድ ﷺ የእናንተ ባህሪ የሌላ ሀይማኖት አማኞችን ወደ ኢስላም ካልተጣራ ኢማናችሁ ላይ ደካማ ናችሁ ብለዋል...የእኛ ባህሪ ሌሎችን ወደ ኢስላም ይጣራል ወይ❔❔ወይስ እንኳን ሌሎችን ሊጣራ ለሙስሊም አማኙን የሚጎረብጥ እኔ ብቻ ነኝ ትክክለኛ አቂዳ የያዝኩት እያለ የሚያስቸግር ...ወይም በሚያሳየዉ ባህሪ አንተ ብሎ ሙስሊም እየተባልን ኢስላምን እያሰደብን ነዉ ወይ❓❓

ሁሉም ራሱን ይፈትሽ



┻┻             
╚▩PubLished by ▩╗
              ISLAMIC UNIVERSITY
                ◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━   
4 another channal👇
             t.me/Islam_and_Science

💐⭐️💐
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


🎖🎖 #የሀቢቡና_ሙሀመድ_ﷺ_ስሞች🎖🎖
                 ✍ አሚር ሰይድ

    
    ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ በአባታቸው በኩል የሚገርም ታሪክ አላቸው። አያታቸው ዐብዱልሙጠሊብ ጁርሁም የሚባሉ ጉሳዎች የዘምዘምን ውሀ አዳፍነው በሄዱ ጊዜ ውሀዉን ፍለጋ ቁፋሮ ጀመሩ። ቁረይሾች በዚህ ሥራ ላይ ሊተባበሯቸው አልፈቀዱም። ዐብዱል ሙጠሊብ አንድ ወንድ ልጅ ብቻ ነበራቸውና ጌታዬ ሆይ አሥር ወንድ ልዶችን ከሰጠኸኝ አንዱን በስለት መልክ ላንተ ለማረድ ዝግጁ ነኝ በማለት ተሳሉ። አላህ ሱወ አስር ወንድ ልጆች ሰጣቸው። የመጨረሻ ልጃቸው የነቢያችን ﷺ አባት የሆኑት ዐብዱላህ ናቸው።

   ዐብዱልሙጠሊብ በስለታቸው መሠረት
የነብዩ ﷺ አባት ለማረድ ወደ ካዕባ ወሰዱ። በዚህን ጊዜ ቁረይሾች ዐብዱል ሙጠሊብን በኛ መካከል ያልነበረ ባህል አታምጣብን። አንተ ዛሬ ይህንን ልጅህን ካረድክ ነገ ሌሎችም ይህን ነገር ልምድ አድርገው ይከተላሉና ይህን ሀሳብህን አንሳ በማለት አሳሰቡት። በዚሁ ጉዳይ ላይ ለማማከርም ብለው ከአንዲት ጠንቋይ ዘንድ ሄዱ። ጠንቋዩዋም የአንድ ሰው የደም ካሳ አስር ግመል ነውና ለእርድ በቀረበው ዐብዱላህና በግመሎቹ መካከል እጣ ተጥሎ የግመሎቹ እጣ በደረሠ ጊዜ ግመሎቹ በሱ ምትክ እንዲታረዱ መከረችና እጣ መጣል ተጀመረ። እጣው ከዘጠኝ ጊዜ ሙከራ በኋላ ነበር ግመሎቹ ላይ ወጣ። እጣው በግመሎቹ ላይ በመውጣቱ ዐብዱልሙጠሊብ እጅግ ተደሠቱ። መቶ ግመሎችም በዐብዱላህ ምትክ ቀርበው ታረዱና ሰደቃ ተደረጉ። የነቢያችን አባት ዐብዱላህ በዚህ መንገድ ነፃ ሊወጡ ቻሉ።

✨✨✨ ነቢዩም ﷺ ይህንኑ ክስተት ሲያስታውሱ እኔ የሁለት ለእርድ የቀረቡ ሰዎች ልጅ ነኝ ብለዋል። አንደኛው ለእርድ ቀርቦ የነበረው ሰው ቅድመ አያታቸው ነቢዩ ኢስማዒል  እንደሆኑ ይታወቃል።

   💚 የሀቢቡና ሰይዱና ሙሀመድ ﷺአባታቸው ዐብዱልሙጠሊብ ከተከበረ ቤተሰብ የሆነችው አሚናን ከእርድ ለተረፈ  ልጃቸው ለዐብደሏህ አጩ። በወቅቱ የነበረው ማህበረሰብ የጋብቻ ሥርዓቱ የተበከለ ዝሙትና አባታቸው የማይታወቁ ልጆች የበዙበት ነበር። የነቢያችን ﷺ አባት ግን በሕጋዊ ጋብቻ በክብር የሴቷ ቤተሰብ ተጠይቆ ነው የተዳሩት።

🩷 ነብዩ ﷺበእርግዝናቸው ወቅት አንድ ፍጡር ወደ እናታቸው መጣና በዚህ ዑማ ታላቅ ሰው ነውና ያረገዝሽው ይህን ልጅ በምትወልጂበት ጊዜ በአንድዬ ጌታ ከምቀኛ ዓይን ሁሉ እጠብቅሀለሁ" በይ።” አላት። እናታቸው አሚና ነቢዩን ﷺ ነፍሰጡር ሆና ሳለች ሌሎች ሴቶች የሚሰማቸው የድካም እና ሌሎች ዓይነት ስሜቶች ተሰምቷት አያውቅም ነበር።

🌹🌹🌹ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ስትወልዳቸውም ከሷ የወጣ ብርሃን የሻምን ቤተ-መንግሥታት አብርቷል።

ነቢያችን ﷺ እንብርታቸው ተስተካክሎ የተቆረጠ ሆኖ፣ ዐይናቸው ተኩሎና፧ ተገርዘው ነው ወደዚህች ዓለም ተውበው የመጡት። በዉልደታቸው ቀን የፐርሺያ ነገስታት ማረፊያ የተሠነጣጠቀ ሲሆን አሥራ አራት የሚሆኑ የቤተ- መንግሥቱ ጉልላቶቹ ወድቀዋል።

🌿🌿 ለ1ሺህ ዓመታት ሳትጠፋ የኖረችው የእሳት አምላኪዎቹ ፋርሦች እሳትም በዚሁ ቀን ጠፍታለች። በሚወለዱበት ጊዜ ቤቱ በብርሃን ተሞላ።ከዋክብት ወደሳቸው ሲቀርቡ ሁለቱ አዋላጆቻቸው በግልፅ ተመልክተዋል። አላህ(ሱወ) ታላቁንና የነቢያት ሁሉ መቋጫ የሆነውን መልዕክተኛውን ሙሐመድን ﷺ
በነኝህና በመሳሰሉት ተዓምራት አጅቦ ነው ወደዚህች ዓለም ያመጣቸው።


🩵🩵   ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ በርከት ያሉ ስሞች አሏቸው። በዋናነት የሚጠቀሱት እሳቸውም የመሰከሩት አምስት ናቸው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል
➊‹‹ እኔ ሙሐመድ ነኝ።
➋ እኔ አሕመድ ነኝ።
➌ እኔ 'አል ማሒ' (አላህ በኔ አማካኝነት ክህደትን የሚያብስበት) ነኝ።
➍እኔ አል ሓሽር (ሰዎች የቂያማ ቀን ከእግሬ ሥር የሚቀሰቀሱ) ነኝ።
➍እኔ 'አል ዓቂብ (የነቢያት ሁሉ መቋጫ) ነኝ።” ብለዋል።

🌹🌹ሙሐመድ ማለት ትርጉሙ 'ምስጉኑ፣ የተመሰገነ' እንደ ማለት ነው፡፡ ይህን ስም ያወጡላቸው አያታቸው ዐብዱልሙጠሊብ ናቸው። በርግጥም የሰው ልጅ ሆኖ እንደሳቸው የተመሰገነ የለም። አሕመድ ማለት ደግሞ ትርጉሙ “አመስጋኝ ማለት ሲሆን በርግጥም ከሳቸው በላይ አላህን ያመሰገነና የተገዛ በዚህች ምድር ላይ አልተፈጠረም።

አላህ ሱወ ነቢዩን ሲያልቃቸው እሳቸው መለኮታዊውን ተልእኮ ይዘው በመጡ ጊዜ ያስዋሿቸው የመካ ሰዎች ቁረይሾች እንኳን ሲሰድቧቸው በስማቸው ጠርተው  ሰድበዋቸው አያውቁም ነበር። ሙሐመድ ከማለት ይልቅ ተቃራኒ ትርጉም  ባለው መጠሪያ ሙዘምመም እያሉ ነበር የሚጠሯቸው። ሰይዲና ሙሀመድ ﷺ አታዩም እንዴ! አላህ የቁረይሾችን ስድብ እንዴት እንደሚያርቅልኝ! እነሱ እኮ ሙዘምመም እያሉ ነው የሚሳደቡት እኔ ግን ሙሐመድ ነኝ' ይሉ ነበር፡፡


🌹🌹 ታላቁ ነቢይ ﷺ አባታቸውን ገና በእናታቸው ሆድ ሳሉ እናታቸውን ደግሞ በሕጻንነት እድሜያቸው ነው ያጡት። ወንድምና እህት አልነበራቸውም።
ነቢያችን ﷺ የቲም ሆነው በአያታቸውና በአጎታቸው ቤት ነው በቅብብሎሽ ያደጉት። ልጅ ሆነው  ሣሉም ሆነ በወጣትነታቸው ታላቅ ሰው ነበሩ። መለኮታዊው የወሕይ መልዕክት ሳይደርሳቸው ከመላካቸውም በፊት ስብእናቸው ምሉእ ነበር። ቁርኣን ስለ ታላቅነታቸውና ስለ ደረጃቸው ከመመስከሩ በፊት ታላላቅ ተአምራት በሳቸው ዙሪያ ይታዩ ነበር።

✏️✏️ ከመላካቸው በፊት ድንጋይ ሰላም ይላቸው፤ ዛፍና ሌላ ግዑዝ ነገርም የአክብሮት ስግደት ይሰግድላቸው ነበር።

በወጣትነታቸው መካ እንደሳቸው ዓይነት እውነተኛና ታማኝ ሰው አላስተናገደችም። ብዙዎች የአደራ እቃዎችን እሳቸው ዘንድ ያስቀምጡ ነበር። “ሙሐመዱ አል- አሚን" (ታማኙ ሙሐመድ) ነበር መጠሪያቸው። ጣኦታትን እና ባእድ አምልኮን እጅግ አድርገው ይጠሉ ነበር።


🩵ሀቢቡና ﷺﷺﷺ


t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የኢድ አከባበር አዲስ አበባ❤️


ኢስላም ዉበት....

t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የኢድ ጉዞ በወሎዋ እንቁ ከሚሴ🩷

t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የኢድ አከባበር በአባጅፋር ሀገር ጂማ❤️

ድከሙ ብሏቸዉ ነዉ እንጂ የኢትዮጲያ ዉበቶች ሙስሊሞች ናቸዉ፡፡

ተረቱ ሁነና የማይድግ ልጅ የእናቱን ጡት ይነክሳል ነዉ፡፡ ሀቅን መሸፈን አይቻልም ኢስላም ዉበት ነዉ




t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የኢድ አልፈጥር በአል አከባበር ሙሉዉ በድሮን ። ምንጭ:- khalid video production

t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የዛሬውን የወሎ መናገሻዋ ደሴ የኢድ አልፈጥር በአል አከባበር የድሮን ምስል። ምንጭ:- khalid video production

ካሊዶ 10Q ታሪክ አስቀምጦ አልፏል🙏



t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


🎖🎖 #ነብዩ_ﷺ_ዉዴታ_እኛና_ሱሀቦቹ🎖🎖
                 ✍ አሚር ሰይድ


     የሰው ልጅ አማኝ እስከሆነ ድረስ ከፍቅር እርከኖች ሁሉ ቁንጮ ላይ ለመድረስ የግድ ረሱል ﷺ ከምንምና ከማንም፣ ሌላው ቀርቶ ከራሱም ነፍስ እንኳን ሳይቀር አስበልጦ መወደድ ይጠበቅበታል፡፡ ይህም የሚገለፀው የእርሳቸውን ፈለግ በፅናት በመከተልና አጥብቆ በመያዝ ነዉ፡፡
    አሁን ላይ ግን ረሱልን መዉደድ ከነሺዳ ያልዘለለ ልብ ላይ ጠብ ያላለ ሁኗል...ግን ነገ አላህ ፊት ስንቀርብ የሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ የሚወዷቸዉ ጋር አብረን ስንቀሰቀስ መልሳችን ምን ይሆን??ነብዩን ስለምንወድ እሩብ ጉዳይ ሙዚቃ የመሰለ ነሺዳ እንዳምጥ ነበር ብለን ለመመለስ ተዘጋጅተናል ማለት ነዉ??ሱሀቦቹ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ዉዴታ በተግባር አሳይተዉ በህይወት እስከመጨረሻቸዉ ድረስ ዉዴታቸዉ ሳይቀንስ ወደ አኼራ ተሻግረዋል


✨✨ሱሀቦቹ ሀቢቡና ሰይዱና ሙሀመድﷺ ከራሳቸዉ በላይ ይወዷቸዉ ነበር፡፡

#በኡሁድ_ጦርነት ጊዜ የተወሰኑ ሱሀቦች  ለነብዩ ﷺ የነበረዉን ፍቅር እና ለነብዩ ሲሉ በኡሁድ ጦርነት ላይ ያሳለፉትን  ገድል እናዉሳ




🩵 ጦለሃ ኢብን ኡበይዱላህ (ረ.ዐ) እንዲህ ይላል፡-

በኡሁድ ጦርነት ከሀዲያኑ የአላህን መልእክተኛ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ለማጥቃት ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከበቧቸው፡፡ ከጠላት ጥቃት እንዴት አድርጌ ልከላከልላቸው እንደምችል አላወቅኩም፡፡ ከፊት ለፊት፣ ከኋላ፣ ከቀኝ በኩል ወይስ ከግራ እንዴት ልከላከልላቸው? ሰይፌን መዘዝኩና አንድ ጊዜ ከፊት ለፊታቸው ሌላ ጊዜ ደግሞ ከጀርባቸው እያልኩ ጠላቶቻቸውን እስኪበታተኑ ድረስ ተከላከልኩላቸው፡፡"

በዚሁ በኡሁድ ጦርነት ከከሀዲያኑ በኩል ከነበሩት ቀስት ወርዋሪዎች አንዱ የሆነው ማሊክ ኢብን ዙሃይር በአላህ መልዕክተኛ ﷺ ላይ አለመባቸው፡፡ ቀስቱን በቀጥታ ወደርሳቸው አስወንጭፈው፡፡ በዚህ ጊዜ ጦለሃ ኢብን አብይዱላህ እጁን በቀስቱ ትይዩ በማድረግ ከነብዩ ﷺ ላይ ሲከላከል ጣቶቹ ክፉኛ  ተጎዱ።(ኢብን ሰዓድ)




🩷 አቡ ጦለሃ (ረ.ዐ) እጅግ የታወቀ ቀስት ዓላሚ ነበር። በኡሁድ ጦርነት ጊዜ በእጁ ላይ ሁለት ወይም ሶስት ደጋኖች ተሰብረዋል። በእርሱ አጠገብ የቀስት ፍላፃ በኮሮጆ ተሸክሞ ለሚያልፍ ማንኛውም ሰው
ነብዩ ﷺ ከአቡ ጦለሃ አጠገብ የቀስት ኮረጀህን አራግፍ በማሰት ያዙት ነበር።
ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ከኋላው ከሃዲያን ሙጥተው እንዲያጠቁት ራሳቸውን ቀና አድርገው ይቃኙ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ አቡ ጦለሃ እንዲህ ይላል፡-

    የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! እናትና አባቴ መስዋዕት ይሁንልዎና ራስዎን ቀና አያድርጉ፡፡ ከሀዲያን ከሚያስወነጭፉት ቀስት አንዱ ያገኝዎታልና፡፡ ደረቴ ደረትዎን ለመጠበቅ ጋሻ ይሁንልዎ፡፡ ለእርስዎ የታለመው ፍላፃ ሁሉ እኔን ይውጋኝ፡፡” ይል ነበር (ቡኻሪ)



🧡 ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ከጠላቶቻቸው ለመከላከል ቀታዳ ኢብን ኑዕማን (ረ.ዐ) ከፊት ለፊታቸው ሆኖ ሲዋጋ ደጋኑ ተሰበረበት፡፡ በመጨረሻም በቀስት ከአይኑ ላይ ተመታ፡፡ ከዚያም የአይኑ ብሌን ከጉድጓዷ ወጥታ ከጉንጩ ላይ ተንጠለጠለች፡፡ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ
ቀታዳን በዚህ ሁኔታ ሲመለከቱት ዓይናቸው እንባ አዘለ፡፡ ከዚያም ዓይኑን በቦታዋ በመመለስ በአላህ ስም ሲያሻሽዋት ተመልሳ እንደነበረች መሆን ብቻ ሳይሆን ከዚያ በፊት ከነበራት የማየት ሀይል የተሻለች ሆነች፡፡ (ሐኪም፣ ሃይሰሚና ኢብን ሰዓድ)



🩵 በኡሁድ ጦርነት ምዕመናን የነብዩን ﷺ ሰማዕት መሆን ሰምተው በከባድ ሐዘንና ግራ መጋባት ተመቱ፡፡ በዚያ ጊዜ አነስ ኢብኑ ነድር (ረ.ዐ) እንዲህ በማለት እየጮሁ አነቃቋቸው፡-

ነብዩ ﷺ ከተገደሉ በኋላ ለእናንተ መኖር ምን ትርጉም ይኖረዋል? ኑ እንዋጋና እርሳቸውን የገጠማቸው እድል ለእኛም ይድረሰን፡ :" ይህን ካሉ በኋላ እስኪገደሉና ሰማዕት እስኪሆኑ ድረስ በፅናት ተዋጉ፡፡ ከሞቱ በኋላ በአካላቸው ላይ ከሰማኒያ በላይ ቁስል ተገኝቶባቸዋል፡፡




💙 አንድ ጊዜ ሙሐጀሮች  እና አንሷሮች መካከል የተወሰኑት ከነፍሶቻቸው በላይ በጣም የሚወዷቸውን የአላህን መልዕክተኛ ﷺ በመክበብ ለእርሳቸው ብለው ስማእት ለመሆን እንዲህ ሲሉ በነፍስ ወከፍ ማሉ፦ “ፊቴ የእርስዎን ፊት ለማዳን ጋሻ ፤ሰውነቴም ሰውነትዎን ለማትረፍ ቤዛ ይሆናል'፡ የአላህ ሰላም ሁልጊዜ ከእርስዎ ጋር ይሁን'፣ 'የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ከእርስዎ ጎን ዘወር አልልም ይህን ካሉ በኋላ እስከ መጨረሻው ድረስ ተዋጉ፡፡(ኢብን ሰዓድ)



💛 ኡሙ አማራ (ረ.ዐ) በኡሁድ ጦርነት ከነብዩ ﷺ
ጎን በመሆን ከጠላቶቻቸው ጥቃት ደጋንና ቀስቷን ይዛ በዚያ እያስወነጨፈች ስትከላከልላቸው ውላለች፡፡ ጦርነቱ እንዳበቃ ወደ መዲና ከተመለሱ በኋላ
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-

“በዚያ ጦርነት ዙሪያዬን በተመለከትኩ ቁጥር ኡሙ አማራ ስትዋጋ አስተውል ነበር፡፡”ብለዋል (ኢብን ሐጅር፣ አል ኢስባእ)





⚠️በረሱል ስም ዘፈን የመሰለ ነሺዳ የሚነሺድ ትዉልድ
ሳይሆን ለረሱል ክብር ዘብ የሚቆም ወንድ ነዉ የሚያስፈልገን፡፡


◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━   
4 another channal👇
             t.me/Islam_and_Science
💐⭐️💐
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


🎖🎖 #ለሞት_ምን_ያህል_ተዘጋጅተናል?🎖🎖
                   ✍ አሚር ሰይድ




{ كُلُّ نَفۡسࣲ ذَاۤىِٕقَةُ ٱلۡمَوۡتِۗ وَنَبۡلُوكُم بِٱلشَّرِّ وَٱلۡخَیۡرِ فِتۡنَةࣰۖ وَإِلَیۡنَا
تُرۡجَعُونَ }
ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፡፡ ወደኛም ትመለሳላችሁ፡፡(አል አንቢያእ 35)


🟢 አሊ (ረ.ዐ) እንዲህ ይሉ ነበር፡-
“ይህች ዓለም ጀርባዋን እየሰጠችንና እያለፈች ነው፡፡ መጪው ዓለም ደግሞ ከፊት ለፊታችን ሆኖ ይጠብቀናል፡፡ ሁለቱም የየራሳቸው ልጆች (ተከታዮች) አሏቸው፡፡ እናንተ የመጪው ዓለም ልጆች (ተከታዮች) እንጂ የዚህች አለም ተከታዮች አትሁኑ፡፡ ዛሬ የስራ ጊዜ ሲሆን ሒሳብ የለም፡፡ ነገ ደግሞ ሂሳብ እንጂ ለስራ የሚሆን ጊዜ የለም፡፡"ብለዋል (ቡኻሪ)


🔴 ሱፍያን አስ-ሰውሪ ገና በወጣትነት ዕድሜው ጀርባው ጐብጧል ፀጉሩም ሸብቷል፡፡ ይህ ለምን ሊሆን እንደቻለ ተጠይቆ ሲመልስ እንዲህ ብሏል፡-

“ብዙ እውቀት ያስገበየኝ አንድ መምህር (ኡስታዝ) ነበረኝ፡፡ ሊሞት በጣእር ላይ እያለ የእምነት ማረጋገጫ የሆነውን ከሊማ እንዲል ደጋግመን ብንወተውተውም ያንን ከሊማ ከአንደበቱ ሊያወጣ ሳይችል ሞተ። ይህ ክስተት ካየሁ በኋላ በሀሳብና በትካዜ ጐበጥኩ ፀጉሬም ሸበተ፡፡”ብሎ መለሰላቸዉ፡፡

🟣 የአላህ ወዳጅ የነበሩት ረቢእ ኢብን ሀይሰም (አላህ ይዘንላቸውና) ንግግርና ተግባር አንድ ሰው ለሞትና ለመጪው ዓለም ሕይወቱ ምን ያክል ማሰብና መጨነቅ እንዳለበት ያስገነዝባል፡-

“ረቢእ ኢብን ሀይሰም አንድ ጊዜ ከቤታቸው ጓሮ የመቃብር ጉድጓድ ቆፈሩ፡፡ ከዚያ በኋላ ቀልባቸው የደረቀና ከአላህ የራቁ በመሰላቸው ጊዜ ሁሉ እዚያ ጉድጓድ ውስጥ እየሄዱ በመጋደም ፍፃሜያቸውን ያስታውሱ ነበር፡፡ ይህን የሚያደርጉት አንድ ወቅት የሚገቡበት ቤታቸው ስለሚሆነዉ ቀብር እያሰቡ ስራቸውን ለማስተንተንና አካሄዳቸውን ለማሳመር ነው፡፡ እዚያ ውስጥ ገብተውም እያለቀሱ አላህን ምሕረት ይጠይቁት ነበር፡፡ የሚከተለውንም የቁርአን አንቀፅ ያነብባሉ፡-
{ حَتَّىٰۤ إِذَا جَاۤءَ أَحَدَهُمُ ٱلۡمَوۡتُ قَالَ رَبِّ ٱرۡجِعُونِ }
{ لَعَلِّیۤ أَعۡمَلُ صَـٰلِحࣰا فِیمَا تَرَكۡتُۚ كَلَّاۤۚ إِنَّهَا كَلِمَةٌ هُوَ قَاۤىِٕلُهَاۖ وَمِن وَرَاۤىِٕهِم بَرۡزَخٌ إِلَىٰ یَوۡمِ یُبۡعَثُونَ }

አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ እንዲህ ይላል «ጌታዬ ሆይ! ወደ ምድረ ዓለም መልሰኝ፡፡
በተውኩት ነገር በጎን ሥራ ልሠራ እከጅላለሁና፡፡»
(አል ሙዕሚኑን99-100)


ከዚያ ራላቸው ከማሱት የቀብር ጉድጓዳቸው ሲወጡም እንዲህ ይሉ ነበር-

“ረቢዕ ሆይ! ተመልከት! ዛሬ ወደ ሕይወት የመመለስ እድል አግኝተሀል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ምኞትህ ፈፅሞ ተቀባይነት የማያገኝበት የምር ቀን ይመጣል፡፡ ስለዚህ ግሳፄህን ያዝ፡፡ ከዚያም መልካም ስራዎችን ለማብዛት ተጣደፍ፡፡ በአላህYy መንገድ የምታደርገውን ትግልህንና ለሞት የምታደርገውንም ዝግጅት አጧጡፍ፡፡”እያሉ ራሳቸዉን ይመክሩ ነበር፡፡


🟢 አቡ ዘር (ረ.ዐ) ለሞትና ከዚያ በሆላ የሚጠብቀን ፈተናን ሲገልፅ፡-

“በማንኛውም ንብረትህ (ሀብትህ) ይገባኛል ባዮች የሆኑ ሶስት አካላት አሉ፡፡
➊ የመጀመሪያው አንተ ራስህ ነህ፡፡
➋ሁለተኛው እድልህ ወይም እጣህ ነው፡፡ ይህም ጥሩ ይሁን መጥፎ፤ መከራ ወይም ሞት አንተን ሳያማክር ከች የሚል ነው፡፡
➌ ሶስተኛው ደግሞ ወራሽህ ሲሆን ባፍጢምህ እስክትደፋና ውርስ እስኪያገኝ ድረስ ትእግስት በማጣት የሚጠባበቅ ነው፡፡ ከሞትክለት ወዲያውኑ አንተ አላህ ፊት የምትጠየቅበትን ሀብትህን መንትፎ ዘወር ይላል፡፡ ስለሆነም አቅምህ ከቻለ በእነዚህ ሶስት ባለጋራዎችህ ላይ ክንድህ እንዳይዝል ቶሎ ቶሎ ብለህ ገንዘብህን ለመጪው ዓለም ሕይወትህ አሻግር፡፡ ብሏል


🔵 ኡመር (ረ.ዐ) በአንድ ወቅት አንዱን አገልጋያቸውን በየዕለቱ የሚከተለውን አረፍተ ነገር እንዲደግምላቸው አዘውት ነበር-
“ኡመር ሆይ! ሞትን አትርሳ!" አገልጋዩም ቀን በቀን ኡመር ሆይ ሞትን አትርሳ ይላቸዉ ነበር....ይሁን እንጂ በፂማቸው ላይ የተወሰኑ ነጫጭ ፀጉሮች መታየት ከጀመሩ በኋላ አገልጋያቸውን እንዲህ አሉት፡-

"ከእንግዲህ ማስታወሱ ይበቃሀል፡፡ እነዚህ በፂሜ ላይ የበቀሉት ነጫጭ ፀጉሮች በያንዳንዱ ቅፅበት ሞትን ያስታውሱኛልና፡፡''አሉት፡፡

እኛስ ሞትን እናስታዉሳለን ወይ??ዛሬ ላይ ወጣቱ የሚሰራዉ በስሜት ነዉ ነገ መሞትን እና አላህ ፊት መቅረብን ዘንግተናል ወገን!!!
ነገ ሞት ሳይቀድመን ዛሬ ለአላህ ቤታችን ሀብት ንብረት እናሻግር....



┻┻             
╚▩PubLished by ▩╗
              ISLAMIC UNIVERSITY
                ◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━   
4 another channal👇
             t.me/Islam_and_Science
💐_⭐️💐⭐️___💐
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


🎖🎖 #ለቁርአን_ያለን_ቦታ_እኛና_ሱሀቦቹ🎖🎖
                ✍ አሚር ሰይድ


አላህ በተከበሩ ቃሉ እንዲህ ይላል

{ وَإِذَا قُرِئَ ٱلۡقُرۡءَانُ فَٱسۡتَمِعُوا۟ لَهُۥ وَأَنصِتُوا۟ لَعَلَّكُمۡ تُرۡحَمُونَ }
ቁርአንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፡፡ ፀጥም (ዝም) በሉ ይታዘንላችኋልና፡፡(አል-አዕራፍ 204)


✨✨ በሀዲሰል ቁድስ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ💚 እንዲህ ብለዋል፡-
   በሌሊት ሁለት ረከዓ ሶላት እየሰገደ ቁርአን ከሚያነብ ሰው የበለጠ አላህ ማንንም አያዳምጥም፡፡ ባሪያው በሶላት ላይ እስካለ ድረስም የአላህ እዝነት በእርሱ ላይ ይሰፍናል፡፡ ባሪያው አላህን ከማንም በላይ ይበልጥ የሚቀርበው ቁርአንን በሚያነብበት ጊዜ ነው፡፡" (ቲርሚዚ)

✨✨ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
ቁርዓንን ተማሩ፣ ከዚያም አንብቡት! ሌሎችም እንዲያነቡትና እንዲሰሩበትም ገፋፉ፡፡ ምክንያቱም ቁርአንን የተማረ፣ ያነበበና የሰራበት ሰው በጠርሙስ ውስጥ እንደታሸገና መዓዛው ሁሉንም እንደሚያውድ ሚስክ ብጤ ነው፡፡ #ቁርአንን_ተምሮ_የማይሰራበት የታሸገበት ክዳን ላልቶ እንደተከደነ ሚስክ ማለት ነው፡፡ (ቲርሚዚ)


✏️✏️ ሀቢቡና ሰይዱና ሙሀመድ ﷺ💜 እንዲህ ብለዋል፡-
   ቁርአንን አንብቡ! ምክንያቱም በፍርዱ ቀን እርሱ በሚገባ ላነበበዉ ሰው አማላጅ ሆኖ ይመጣልና፡፡' (ሙስሊም)
📌 በሌላ ዘገባ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል
  አንድ ሰው በልቡ ውስጥ ምንም አይነት የቁርአን አንቀጽ የማይገኝ ከሆነ እንደ ወና ቤት ይቆጠራል፡፡" (ቲርሚዚ)

📌 በሌላ ሀዲስ ሰይዱና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ልብ ብረትን እንደሚያገኘው ዝገት ብጤ ይዝጋል፡፡"ሲሉ
የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ይህን ዝገት በምን ማስለቀቅ ይቻላል?" በማለት ባልደረቦቻቸው ጠየቋቸው፡፡

የአላህን ቁርአን በብዛት በማንበብና አላህንም በብዛት በማውሳት" በማለት መለሱላቸው፡፡ (አሊ አል-ሙተቂ)


⚡️⚡️ አንድ ሰዉ በነብዩ ﷺ ዘመን ቁርአን አጠናቀቀ የሚባለዉ በህይወት ሲኖረዉ ሲተገብረዉ ለሌሎችም
ሲያስተምረዉ ነዉ፡፡
ኡመር ረዐ እንዲህ አሉ፡-እኔ ሱራ አል-በቀራህን በአሥራ ሁለት አመቴ አጠናቀቅኩ፡፡ ለዚህም ምስጋና ይሆን ዘንድ አንድ ግመል አረድኩ፡፡”ብለዋል (ቁርጡቢ)

☞ በተጨማሪ አብደላህ ኢብኑ ኡመር (ረ.ዐ) ሱራ አል-በቀራህን በስምንት ዓመታት አጠናቅቀዋል፡፡ (ሙወጠእ)


✨✨ ኡመር ኢብነልኸጧብ ለቁርአን ለሚቀሩትና ለሀፊዞች እንዲህ ብለዉ መክረዋቸዋል፡-
   ቁርአን የክብራችሁ ምንጭና ከፈጣሪ የተሰጣችሁ ሽልማት እንደሆነ እወቁ፡፡ እርሱን ተከተሉ እንጂ እንዲከተላችሁ አታድርጉ፡፡ ቁርአንን ከኋላቸው ለማስከተል የሚሞክሩ ጭንቅላታቸው ተዘቅዝቆ ወደ ጀሀነም እሳት እንደሚጣሉ አትዘንጉ፡፡ ለቁርአን ታማኝ የሆነ በላእላይ ጀነት  ፊርደውስ  እንደሚሰፍር ተስፋ ያድርግ፡፡ ሁላችሁም አቅማችሁ የቻለውን ያክል የቁርአንን አማላጅነት ለማግኘት ጥረት አድርጉ እንጂ በናንተ ላይ መስካሪ አድርጋችሁ አትያዙት፡፡ ምክንያቱም ቁርአን ያማለደው ሰው ጀነት እንደሚገባና በእርሱ ላይ የመሰከረበት ደግሞ ጀሀነም እንደሚወርድ እሙን ነውና፡፡ ቁርአን ወደ ቀናው መንገድ መመራትና የእውቀት ሁሉ ምንጭ ነው፡፡ ከአዛኙ ፈጣሪ ወደ ሰብአዊው ፍጡር የተላከ የመጨረሻው መፅሐፍ ነው፡፡ እነሆ የታወሩ አይኖች፣ የተደፈኑ ጆሮዎች፣ የተዘጉ ልቦች በእርሱ ይከፈታሉ…” ብለዉ መክረዋቸዋል፡፡

✏️✏️ ኢማሙ ሻፊዒ ረ.ዐ እንዲህ ይሉ ነበር፦
ቁርዓን ያለበት ቤት ውስጥ መተኛት አይቻልም ይላሉ፤ምክንያቱም በመኝታ ሰዓት ራስን መቆጣጠር ስለ ማይቻል የሚጮህ ከሆነ ፣ህልም ላይ መናዘዝ፣ ዉዱዕ የሚያስፈታ ነገር ስለሚፈፅም
ይህ ሁሉ ጥንቃቄ ቁርዓንን ይዞ ሳይሆን ቁርዓን ቤት ውስጥ ካለ ሌላ ቤት ማደር ነው። ይላሉ።
ውዱዕ ካላደረጋችሁ ቁርዓንን እንዳትነኩ ይላሉ።


🌙🌙 የአቡበከር (ረ.ዐ) ልጅ የሆነችው አስማ (ረ.ዐ) አንድ ጊዜ በልጇ ልጅ በአብደላህ የሚከተለው ጥያቄ ቀርቦላት ነበር-

“አያቴ! የነቢዩ ባልደረቦች ቁርዓንን ሲያዳምጡ ምን ያደርጉ ነበር?''
.....አስማ እንዲህ አለች፡- #ከዓይኖቻቸው_እንባ ይፈሳል፡፡ እንዲሁም በቁርዓን እንደተገለፀው መላ አካላቸው ይንዘፈዘፋል፡፡ ኃያሉ አላህ ቁርዓንን በጥልቅ ተመስጦ የሚያነቡ ባሮቹ ምን ሁኔታ እንደሚታይባቸው እንዲህ በማለት ገልጿል፡-
{ وَیَخِرُّونَ لِلۡأَذۡقَانِ یَبۡكُونَ وَیَزِیدُهُمۡ خُشُوعࣰا ۩ }
እያለቀሱም በግንባራቸዉ መሬት ላይ በስግደት  ይወድቃሉ  አላህን መፍራትንም ይጨምራላቸዋል፡፡
(አል-ኢስራእ 109)

{ ٱللَّهُ نَزَّلَ أَحۡسَنَ ٱلۡحَدِیثِ كِتَـٰبࣰا مُّتَشَـٰبِهࣰا مَّثَانِیَ تَقۡشَعِرُّ مِنۡهُ جُلُودُ ٱلَّذِینَ یَخۡشَوۡنَ رَبَّهُمۡ ثُمَّ تَلِینُ جُلُودُهُمۡ وَقُلُوبُهُمۡ إِلَىٰ ذِكۡرِ ٱللَّهِۚ ذَ ٰ⁠لِكَ هُدَى ٱللَّهِ یَهۡدِی بِهِۦ مَن یَشَاۤءُۚ وَمَن یُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنۡ هَادٍ }

አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን፣ ተመሳሳይ፣ ተደጋጋሚ የኾነን መጽሐፍ አወረደ፡፡ ከእርሱ (ግሣጼ) የእነዚያ ጌታቸውን የሚፈሩት ሰዎች ቆዳዎች ይኮማተራሉ፡፡ ከዚያም ቆዳዎቻቸውና ልቦቻቸው ወደ አላህ (ተስፋ) ማስታወስ ይለዝባሉ፡፡ ይህ የአላህ መምሪያ ነው፡፡ በእርሱ የሚሻውን ሰው ይመራበታል፡፡ አላህም የሚያጠመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡
(አዝ ዘሙር 23)


ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከማሳለፍ ቁርአን ያለን ቦታ ያለንን ቁርኝት እንፈትሽ...ከቁርአን ከራቅን ገነ ጀነት የመግቢያ ካርዳችን እንደራቀን ልናቅ ይገባል፡፡
እናም ከዛሬ 6-10 አመት በፊት የነበረን ለቁርአን ቦታ እና አሁን ያለንበት ከቁርአን የራቅንበትን ራሳችንን እንፈትሽ ⚠️



┻┻             
╚▩PubLished by ▩╗
              ISLAMIC UNIVERSITY
                ◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━   
4 another channal👇
             t.me/Islam_and_Science
💐_⭐️💐⭐️___💐
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


🎖🎖#ሶላት_አሰጋገድ_እኛና_ሱሀቦቹ🎖🎖
                 ✍አሚር ሰይድ

   
     የሀቢቡና ሰይዱና ሙሀመድ ﷺ💚 ባልደረባዎች በሶላት ላይ ለአላህ የነበራቸውን ፍራቻና መተናነስ የሚደንቅና የሚገርም ነዉ እስኪ የአሊ ረዐ የገጠመዉን ታሪክ እነሆ

  ⚡️⚡️⚡️ በአንድ ጦርነት ላይ በዓሊ (ረ.ዐ) እግር የቀስት አረር ተሰካባቸው፡፡ ከዚያም ሰዎች ሊያወጡት ሲሞክሩ ከባድ ህመም ስላስከተለባቸው ዓሊ (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡-

“ሶላት ስሰግድ ያን ጊዜ ታወጡልኛላችሁ፡፡" ሰዎቹም እንደተባሉት ዓሊ (ረ.ዐ) ሶላት ላይ በቆሙ ጊዜ ያለምንም ችግር መዝዘው አወጡላቸው፡፡ በዚያን ጊዜ ምንም ህመም ያልተሰማቸውና ሶላታቸውን ተረጋግተው
የጨረሱት ዓሊ (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡-
.....“ምንድን ነው ያደረጋችሁት?'
.........“የቀስቱን አረር መዘን አወጣንልዎ፡፡" አሏቸዉ፡፡ ይሄን ያህል ሶላት ላይ ሲሆኑ ቀጥታ ጌታቸዉ ጋር በኹሹዕ ይሰግዱ ነበር...የእኛስ ሶላት አሰጋገድ አስተዉለንዋልን???

⚡️⚡️⚡️  ዓሊ(ረ.ዐ)እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዉ ነበር ፡-የምእመናን አዛዥ ሆይ! የሶላት ሰአት ሲቃረብ የፊትዎ ቀለም የሚቀያየረዉና የሚንቀጠቀጡት ለምንድን ነዉ ??
ዓሊ (ረ.ዐ) እንዲህ በማለት መልስ ሰጡ """ይህ ሰአት ሰማያትና ምድር እንዲሁም ተራሮች ሊሸከሙት እንዳልቻሉ በመግለፅ ያልተቀበሉትን አደራ ወደ ባለቤቱ የመመለሻ ሰአት በመሆኑ ነዉ ፡፡እኔ በትክክል መቻሌን አለመቻሌን አላዉቅም ለዛ ነዉ አሏቸዉ

✏️✏️ የሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ💚 የልጅ ልጅ የሆነዉ ሀሰን(ረ.ዐ) ምን ጊዜም ዉዱዕ ባደረገ ቁጥር ፊቱ ይገረጣ ነበር
አንድ ዕለት አንድ ሰዉ ሀሰን ሆይ!!! ዉዱዕ ባደረግክ ቁጥር ፊትህ የሚገረጣዉና ወደ ቢጫነት የሚቀየረዉ ለምንድን ነዉ ?? በማለት ጠየቀዉ
ሀሰን (ረ.ዐ) የሚከተለዉን መልስ ሰጠ፡- ብቸኛዉ የሀይል ባለቤት ታላቅና ባለግርማ ከሆነዉ አላህ ፊት የመቅረቢያ ሰአት  በመሆኑ ነዉ ""
ሀሰን(ረ.ዐ) ወደ መስጊድ ሲገባ የሚከተለዉን ዱአ ያደርግ ነበር፡-
#ጠባቂየ_ሆይ!!!! ባሪያህ በቤትህ ደጃፍ ላይ ደርሷል፡፡ምህረት ሁሉ በእጅህ የሆነዉ ሆይ!!! ሀጢያተኛዉ ባሪያህ ወደ አንተ መጥቷል ፡፡ ቅን ባሪያዎችህ ሌሎች ሰዎች የሰሩባቸዉን መጥፎ ነገር ይቅር እንዲሉ አዘሀል፡፡ ምክንያቱም አንተ ይቅር ባይና ቸር ነህ፡፡ አላህ ሆይ በተለመደዉ ይቅር ባይነትህና ምህረትህ በደሌን ይቅር በል እዘንልኝም፡፡ ይል ነበር
ለሶላት ክብር ፍራቻ ነበራቸዉ እኛስ ??ብዙዎቻችን የመስጊድ ሙአዚን አዛን ሲል ሳንጠላዉ እንቀራለን ብላችሁ ነዉ?? ከኔ ጀምር ማን ነዉ አላህን ፈርቶ ሶላትን የሚሰግደዉ??? መልሱን ሁሉም በየቤቱ


✏️✏️  #ዘይኑል_አቢዲን ሁልጊዜም ዉዱዕ ሊያደርጉ ሲዘጋጁ ፊታቸው ይገረጣል፤ እንዲሁም ሶላት ሲጀምሩ እግሮቻቸው ይንቀጠቀጣሉ፡ ይህ ሁኔታ የሚታይባቸው ለምን እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ እንዲህ አሉ፡-ከማን ፊት ለመቆም እየተዘጋጀሁ እንዳለሁ አትገነዘቡምን?”ብለዉ መለሱላቸዉ

     በአንድ ወቅት ዘይኑል አቢዲን ከቤታቸው ውስጥ ሆነው እያሉ ቤታቸው ተቃጠለ🔥🔥🔥፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ሁኔታ እርሳቸው አላወቁም ነበር፣ ሶላታቸውን እንደጨረሱ ስለተፈጠረው ሁኔታ ከነገሯቸው በኋላ ሰዎች የሚከተለውን ጥያቄ አቀረቡላቸው።

ቤትዎ በእሳት መያያዙን እንዳይገነዘቡ ያደረገዎት ነገር ምንድን ነው?”

ዘይኑል አቢዲን እንዲህ አሉ፡- "በመጪው ዓለም የሰውን ልጅ የሚጠብቀውና የተደገሰለትን የጀሀነም እሳት🔥🔥🔥 ሳስብ የዚህችን ዓለም እሳት እንድዘነጋው አደረገኝ፡፡"
ብለዉ መለሱላቸዉ

🌟🌟 የሙስሊም ቢን ያሲር ሶላትም ተመሳሳይ ሁኔታ ይንፀባረቅበት ነበር። አንድ ጊዜ በበስራ መስጊድ ውስጥ ይሰግድ ነበር፡ በቅፅበት መስጊዱ ተደርምሶ መሬት ላይ ወደቀ፡፡ ይሁን እንጂ ሙስሊም ቢን ያሲር ይህን ክስተት ሳይገነዘብ በሶላቱ ላይ እንደተመሰጠ ቀጥሏል፡፡ ሶላቱን እንደጨረሰም ሰዎች ጠየቁት፡-
መስጊድ በላይህ ላይ እየተደረመሰ አንተ ግን አንድ ኢንች እንኳን አልተንቀሳቀስክም ይህ ሁኔታ ምንድን ነዉ?
ብለዉ ጠየቁት
....ሙስሊም ቢን ያሲር በመደነቅ የሚከተለዉን ጥያቄ
ለጠያቂዎች መልሶ አቀረበላቸዉ
...እንዴ! መስጊድ ተደርምሷል ነው የምትሉኝ?''
ጠያቂዎቹ በሙስሊም ቢን ያሲር መልስ ተአጀቡ::

✏️✏️ አንድ የአላህ ወዳጅ እንዲህ ይላል፡- “እኔ የዙህርን ሶላት ከዘኑን መስሪ ኋላ ቆሜ በመስገድ ላይ ነበርኩ፡፡ ያ ብሩክ ሰው 'አላሁ አክበር' ሲል #አላህ የሚለው ቃል በእርሱ ላይ የሚፈጥረውን ተፅእኖ ሳስተውል በአካሉ ውስጥ ነፍስ ያለው እስከማይመስል ድረስ ድርቅ ብሎ ነበር የሚቆመው፡፡ #አክበር የሚለውንም ከአፉ ሲያወጣው ከቃሉ ከባድነት ባለግርማ መሆን የተነሳ ልቤ ፍርስ ልትል ምንም አይቀራትም ነበር::

✏️✏️ አምር ኢብን አብዱሏህ ሶላት ላይ በሚቆምበት ጊዜ ከውጨኛው ዓለም ጋር የሚያስተሳስረው ነገር ሁሉ ይቆረጥና ከአላህ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያውክ አንዳችም ነገር አይፈጠርበትም ነበር፡፡''

ይህንን ሁኔታ ራሱ በአንደበቱ ሲገልፅ እንዲህ ይል ነበር፡-

“እኔ ሶላት ላይ እያለሁ የሰዎችን ድርጊትና ድምፅ ከምከታተል በቀስት ፍላፃ ሰውነቴን ብወጋ ይሻለኛል፡፡"ይል ነበር...




⚠️⚠️⚠️የእኛስ ሶላት ፈትሸነዉ እናዉቃለን??አሁን ላይ ሰዉ በስራ ቦታ እቤት ሲሰግድ ገና አሰጋጁን ኢና አእጦይናን ለሁለት አድርግ...እየተባለ ከአንገት በላይ እየሰገድን ነዉ ያለነዉ...አንተ አንቺስ ሁላችንም ሶላታችንን ፈትሸንዋልንን???



┻┻             
╚▩PubLished by ▩╗
              ISLAMIC UNIVERSITY

                ◈━━━━━━━━◈━━━━━━━━   
4 another channal👇
             t.me/Islam_and_Science
💐_⭐️💐⭐️___
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


>>>>


>>>>>>🎖🎖#የጀመአ_ሶላት🎖🎖


=============== #ሶላት==============
                   ✍አሚር ሰይድ

     ሀቢቡና ሰይዱና ሙሀመድ ﷺ💚 ስለሶላት አንገብጋቢነት እንዲህ ብለዋል፡-

   አንድ ሰው ሩኩኡንና ሱጁዱን አሳምሮ ሶላቱን የሚሰግድ ከሆነ ሶላቱ ሰውየውን እንዲህ ይለዋል፡-

አሳምረህ እንደሰገድከኝ አላህ አንተንም ያሳምርህ!' ይህን ካለ  በኋላ ወደ ሰማይ ይወጣል፡፡

ሰውየው ሶላቱን ሳያስተካክልና ሩኩእና ሱጁዱንም በግብር ይውጣ ከሰገደ ሶላቱ እንዲህ ይለዋል፡-

"እንዳበላሸኸኝ አንተንም አላህ ያበላሽህ፡፡'' ከዚያም እንደ አሮጌ ቁራጭጨርቅ ወርዶ ከፊቱ ላይ ይለጠፋል:: ብለዋል፡፡

>>>በቅዱስ ቁርአን እንዲህ የሚል አንቀፅ ተፅፎ እንገኛለን፡-ወዮላቸዉ ሰጋጆች፡ለእነዚያ እነርሱ ከስግደታቸዉ ዘንጊዎች ለኾኑት(አል-ማዑን 4-5)



🌙🌙 ሚስወር ቢን መሕረማ (ረ.ዐ) እንዲህ ብሏል፡-

ኡመር ቢን አል ኸጧብ (ረ.ዐ) በጩቤ በተወጉ ጊዜ ህሊናቸውን ስተው መሬት ላይ ተዘረሩ፡፡ ልጠይቃቸው ከተኙበት ክፍል ገባሁ ሰውነታቸውን ሸፍነዋቸው እንደተንጋለሉ ነበር፡፡ ዙሪያቸውን ያሉትን ሰዎች ጠየቅኩ-

"አሁን እንዴት ናቸው?''
.....እንደምታየው ህሊናቸውን ስተዋል" በማለት መለሱልኝ።

“ለሶላት ጥሪ አደረጋችሁላቸውን? በህይወት ካሉ ከሶላት በስተቀር ሊያነቃቸው የሚችል አንድም ነገር የለም፡፡" በዚህ ጊዜ ሰዎቹ እንዲህ

የምእመናን አዛዥ ሆይ! ሶላት፣ ሶላት እየተሰገደ ነው፡፡” ይህን የሰሙት ኡመር (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡-

እንደዚያ ነው? ወላሂ ሶላትን የተወ፣ ከኢስላም አንዳች ነገር የለውም" ይህን ካሉ በኋላ ከሰውነታቸው ደም እየፈሰሰ ተነስተው ሶላታቸውን ስገዱ።" (ሃይሰሚ፣ ኢብን ሰዓድ፣ መውጦእ) ዘግበዉታል፡፡

🌙🌙 እጅግ በጣም ጠንካራና በአምልኮ ላይ ፅኑ በመሆኑ ታላቅ ምሳሌ ሆኖ ሊጠቀስ የሚችለው የካውካሱ ሙጃሂድ ሸይኽ ሻሚል ሲሆን በብዙ ቦታዎች ላይ በሳንጃ፣ በሰይፍና በጥይት ተመትቶ ቆስሏል፡፡ እኤአ በ1829 በተደረገው የጊርሚ መከላከል ጦርነት በሰይፍ በመወጋቱ በደረቱ በኩል የገባው ሰይፍ ሳንባውን፣ የጎን አጥንቱንና ከአንገቱ አካባቢ ክፉኛ ጐድቶት ነበር፡፡ ለስድስት ወራት ያክል ከታከመ በኋላ ነበር ለማገገም የበቃው፡፡

ይህ ወጣት ሙጃሂድ ከቆስለ በኋላ ለ25 ቀናት ያክል ህሊናውን ስቶ ነበር የቆየው፡፡ በ25ኛው ቀን መጨረሻ ላይ አይኑን ሲገልጥ ከአጠገቡ እናቱን እንዳያት ከአንደበቱ መጀመሪያ ያወጣቸው ቃላት እንዲህ የሚሉ ነበሩ፡-

#የምወድሽ_እናቴ! የሶላት ወቅት አልፎኝ ይሆን?''ነበር ያለዉ .....

🟢 ከፈርድ ሶላት ዉጭ በሱና ሶላት ላይ መጠንከር እንዳለብን  የአላህ መልዕክተኛ የሆኑት ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል-

በፍርዱ ቀን አንድ ባሪያ መጀመሪያ የሚጠየቀው ሶላቱን የተመለከተ ጥያቄ ነው፡፡ ግዴታ የተደረጉበት ሶላቶች የተስተካከሉ ከሆነ የእርሱ ጉዳይ ቀላል ስለሚሆን ሌላ ችግር ሳይገጥመው ፈተናውን ያልፋል፡፡ ሶላቱ ያልተስተካከለ ከሆነ ፈተናውን ስለሚወድቅ ከባድ ችግር ይገጥመዋል፡፡ የሰውዬው ፈርድ ሶላቶች ችግር ካለባቸው ኃያሉና የላቀ የሆነው አላህ እንዲህ ይላል፡-

“ባሪያዬ አንዳች ዓይነት የሱና ሶላት እንዳለው ፈልጉለት፡፡'' ሱና ሶላቶች በፈርድ ሶላት ላይ የተከሰተውን ጉድለት ያካክሳሉ፡፡ በዚህ ዓይነት በሌሎች ጉዳዮቹም ላይ ምርመራው ይቀጥላል፡፡” (ቲርሚዚ)

🔶 በፈርድ እና በሱና ሶላት ላይ ያለንን ቁርኝት እናስተካክል...እራሳችንን እንፈትሽ ሶላት ስንሰግድ የጠፋ እቃ መፈለጊያ አርገንዋል ወይስ በተመስጦት በሁሹዕ እየሰገድነዉ ነዉ ወይ??

🔶የእኛ ሶላት ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዳሉት ሶላቱ አሳምረህ እንደሰገድከኝ አላህ ያሳምርህ ከሚለን ዉስጥ ነን ወይስ አበላሽተህ እንደሰገድከኝ አላህ አንተንም ያበላሽህ?? ከሚለዉ ወይስጥ ነን ወይ??



join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
  t.me/IslamisUniverstiy_public_group


>>>>>>>>>>>>>> #ዉዱዕ

Показано 20 последних публикаций.