🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
🔰 #የመጨረሻዉ_ክፍል
✍አሚር ሰይድ
ዚና ላይ ያለ ትዉልድ መጀመሪያ የሚያጣጥለዉ ትዳርን ነዉ...ከቤተሰብ ጉትጎታ ወይም ጫና ያገባ ከሆነ ደግሞ ለፍች ይቸኩላል፡፡ በተጨማሪ በሀራም ላይ መዘዉተር የአእምሮ እረፍት ስለሌለዉ ራሳቸዉን የሚያጠፉ ወጣቶች ተበራክተዋል፡፡ይህ ሁሉ ዚና ያመጣብን መዘዝ ነዉ፡፡
╔═══════════════════╗
🎖 #ጋብቻን_ማዘግየትና_ማጣጣል🎖
╚═══════════════════╝
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአዳጊ ሀገራት ውስጥ ወጣቶች ወደ ትዳር የሚገቡበት አማካይ ዕድሜ ከ25-30 ዓመት ነው፡፡ ነገር ግን አንድ አዳጊ ወንድ በአማካይ በ16 ዓመቱ ለወሲባዊ ጉልምስና ይደርሳል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም በዚሁ ጊዜ ወሲባዊ ኃይሉ ጣሪያ ይነካል፡፡ አንዲት ሴት ደግሞ አሁን አሁን ባለው ጥናት ከ8 ዓመት አንስቶ ለአካለ መጠን ልትደርስ ትችላለች፡፡ ታዲያ በርካታ ወጣቶች ይህንኑ ስሜታቸውን የሚያስተናግዱት የወንድ ወይም የሴት ጓደኛ በመያዝና ዝሙትን በመፈፀም ነው፡፡
#ለምሳሌ የሀይስኩል ተማሪዎችን ብናይ በአንድ ክፍል ውስጥ የወንድ ጓደኛ የማይኖራቸው ጥብቅ ሴቶች ከአስር አይበልጡም፡፡ ይህም ዝሙት ምን ያህል እንደተስፋፋ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡
✨✨ ሌላው ሴት የኮሌጅ ተማሪዎች ዘንድ የወንድ ጓደኛ መያዝን ማበረታታትና ትዳርን ማጣጣል እየተለመደ መጥቷል፡፡ ሴት ሙስሊም የመንግስት ሰራተኞች ዘንድም ይኸው ችግር እየተወራረሰ ይገኛል፡፡ ሁሉንም የሚያመሳስላቸው ነገር ደግሞ ቦይፍሬንድ መያዝን እንደ ጤናማ የህይወት ልማድ ማየታቸው ነው፡፡ በእውነቱ ይህ ትልቅ ውድቀት ነው፡፡ ለዝሙት መስፋፋትም ትልቁን አስተዋፅኦ እያበረከተ ያለው ይኸው ቦይ-ገርልፍሬንድነት ነው፡፡ ደዌው ወደ ሙስሊሞችም ተጋብቷል፡፡
╔════════════╗
🎖 #የፍቺ_መበራከት🎖
╚════════════╝
በሙስሊሙ ማህበረሰብ መካከል የፍቺ መበራከት ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረና ከባድ ቀውስን እየፈጠረ ያለ አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በቅርቡ በተገኘው አንድ መረጃ እንኳን ከ14 ትዳሮች መካከል 12ቱ ሶስት ወር ሳይሞላቸው ፈርሰዋል፡፡ ይህ በውነቱ በጣም አስደንጋጭ ነው፡፡ አንዳንዶች ሙስሊሙ ወጣት ወደ ትዳር ሲቻኮልና በከተማዋም የሙስሊም ሰርግ በዝቶ ሲያይ ይደሰት ይሆናል፡፡ ግና በዚያው ልክ የሚፈርሱትን ትዳሮች ቢያይ በእጅጉ ያዝናል፡፡ ሙስሊሙ ወዴት እየሄደ ነው? በሚል ሀሳብም ይባዝታል፡፡ ለፍቺ መበራከት ትልቁ መንስኤ ደግሞ የተጋቢዎች ከትዳር በፊት በየፊናቸው የሚፈጥሩት ፆታዊ ግንኙነትና ዝሙት ነው፡፡
እንደሚታወቀው ከትዳር በፊት በርካታ ወጣቶች በቦይ–ገርል ፍሬንድነት (በወሲብ አጋርነት) አብረው ይቆያሉ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ አብረው የሚቆዩቱ ግን አብዛኞቹ ግንኙነታቸው በጋብቻ አይቋጭም፡፡ ከዚህም የተነሳ ሁሉም በየፊናው ሌላ የትዳር አጋር ፍለጋ ይሄዳል፡፡ ግን ከዚህ በኋላ የሚመሰርቱት ትዳር ስኬታማ የመሆን ዕድሉ በጣሙን ዝቅተኛ ነው፤ ምከንያቱም ከትዳር በፊት ያለውን የወሲብን ሕግ ያላከበረ ከትዳር በኋላም ይህንኑ ልማዱን ይደግመዋልና ነው፡፡ ከዚያም ሁለቱም በየፊናቸው ሂያጅነትን ይጀምራሉ፡፡ ሂያጅነት ወደ ትዳራቸው ሲገባ ደግሞ ትዳሩ ወዲያው መናወጥ ይጀምራል፡፡ ቤቱ መረጋጋት ይሳነዋል፡፡ በውጤቱም ፍቺ ወሃን የመጠጣት ያህል ይቀላቸዋል፡፡ ከዚያም ወጣቱ « #ኒካህሽን_እንቺ››፣ «ትሄጃለሽ ወይስ ታድሪያለሽ በሶስት ፈትቼሻለሁ ወዘተ እያለ ትዳርን መቀለጃ ያደርገዋል፡፡ይህም ችግር ስራ የሰደደና ትልቅ ማህበራዊ ቀዉስን ፈጥሯል፡፡
እኔ ብዙ ለትዳር የደረሱትን ለምን አታገቡም?ትዳር ሲመጣላችሁ ለምን ትመልሳላችሁ?ብየ ስጠይቅ የብዙዎች መልስ ከተጋባን ቡሀላ ቢፈታንስ እያሉ በጓደኞቻቸዉ የደረሰዉን የፍች ታሪክና ሳይፋቱ ደግሞ ሴቶች ባለቻቸዉ ጋር እየኖሩ እንደሆኑ በማስረጃ ነግረዉኛል፡፡የፍች ስታቲክስ በየአመቱ የሚያሳየዉ በብዙ እጥፍ እንደሆነ ነዉ፡፡ደግሞ የሚገርመዉ በፍች ብዛት የሚያሳየዉ ሙስሊም ማህበረሰብ ቀዳሚ መሆኑ ነዉ፡፡
╔══════════════════════╗
🎖 #እራስን_የማጥፋት_ወንጀሎች_መበራከት
╚══════════════════════╝
ጥናቶች እንዳመለከቱት ዝሙትና እራስን የማጥፋት ወንጀሎች የተቆራኙ ናቸው፡፡ በተጨማሪም እነዚያ በወሲብ ንቁ (አክቲቭ) የሆኑ ልጆች ከነዚያ እስከ ኒካህ ድረስ ወሲብን ከመፈፀም ከሚታቀቡት ይበልጥ ከሁለት ጊዜ እጥፍ በላይ በጭንቀት የመወረር ዕድላቸው ከፍ ይላል፡፡ ጥናቶቹ አያይዘውም እንደጠቆሙት እነዚያ በወሲብ ንቁ የሆኑ አዳጊ ወንዶች ከአስር ጊዜ እጥፍ በላይ እራሳቸውን የማጥፋት ሙከራን ያደርጋሉ፡፡
📌 #ሴቶችን_በተመለከተ ደግሞ እነዚያ ከጋብቻ በፊት ወሲብ የሚፈፅሙ አዳጊና ወጣቶች ሴቶች ከነዚያ ከማይፈፅሙቱ ሶስት እጥፍ እራሳቸውን ለማጥፋት ሙከራ ያደርጋሉ፡፡ እንግዲህ የዝሙት ዋጋ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ተመልከቱ፡፡ የዝሙት ፈጣን ዋጋው ሴሰኝነት ነው፡፡ ሴሰኝነትን ተከትሎ ደግሞ ከበሽታ ባሻገር ጭንቀት ብቅ ይላል፡፡ ጭንቀት ደግሞ ራስን ለማጥፋት ትልቅ መንስኤ ነው፡፡ ታዲያ ከዚህ በኋላ ምንድነው ይሆናል ብለህ የምትጠብቀው? አዎን! ጭንቀት እራስን ለማጥፋት ትልቁ መንስኤ ነው፡፡
✏️✏️ #ራስን_ማጥፋትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ውስጥ ከሁለት ዓመታት በፊት በእስጢፋኖስ አበራ የተዘጋጀና በጥልቅ የዳሰሰ ጥናት የተደገፈው መጽሐፍ ላይ እንድ አስደንጋጭ እውነታን ቀርቧል፡-
ለምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ነገር ግን የነገሮች ግጥምጥሞሽ ሁሌም ያስደነግጠኛል፡፡ የነገሮች ግጥምጥሞሽ ሁሌም ያስጨንቀኛል፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ ተመሳሳይ ነገሮች በአንድ ጊዜ ሲከሰቱ ሳይ በጣም እረበሻለሁ፡፡ ለምን እንዲህ ሆነን ብዬም እራሴን ደጋግሜ እጠይቃለሁ፡፡ መልስ ፍለጋም እራሴን ብዙ ጊዜ አስጨንቃለሁ፡፡ መልስ እስከማገኝ ድረስም ስለተፈጠረው ጉዳይ ጊዜ ሰጥቼ ማሰብ እና ማሰላሰል እጀምራለሁ፡፡»የሚል አካቷል
በተጨማሪ የመፅሀፉ ርዕስ «ውስጠ አዋቂ - ከአዲስ አበባ ጓዳ እስከ አደባባይ.. የተሰኘ ሲሆን እራስን ማጥፋት ሌላኛው የአዲስ አበባ ፋሽን፡ በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር በአዲስ አበባ እራስን የማጥፋት ወንጀል በወጣቶች ዘንድ እጅጉን መጨመሩን ይገልፃል፡፡
✏️✏️ #ወደ_ሙስሊሞች_ስንመጣ ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ከኮልፌ መስጂድ ኢማም በመስጊድ ሲናገሩ እንደተሰማው እራስን የማጥፋት ወንጀል ተበራከቷል፡፡ እንደሚታወቀው በተለምዶ ኮልፌ አዲሱ መስጂድ ጀናዛ ሶላት በብዛት ይሰገዳል፡፡ በዚህም መነሻነት ለኢማሙ የሰዎችን አሟሟት አስመልከቶ በርካታ መረጃዎች ይደርሷቸዋል፡፡ የሟቾችን ሁኔታ ሲጠይቁ እራሳቸው ያጠፉ ወጣቶች እንደሚገኙባቸው ይነገራቸዋል፡
የወንጀል መጨረሻዉ ይሄ ነዉ መፍትሄዉ ከዝሙት መራቅ በዝሙት መስመርም ያለ እንደ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት ቶብቶ አልቅሶ ከወንጀል ፀድቶ አዛኝ ረሂም ለሆነዉ ጀሊሉ እጅ መስጠት ነዉ፡፡ በዝሙት ላይ እገፋለሁ ያለ ምርጫዉ በእጁ ነዉ በዱንያ ደስታ ማጣት የእርዚቅ መገፋት እና አሏህ እንዳለን ለወንጀለኞች ብርቱ የሆነ ቅጣት ይጠብቃቸዋል እንዳለዉ የአሏህን ቅጣት እወጠዋለሁ ጀሀነም ይሻለኛል ያለ ምርጫዉ በእጁ ነዉ፡፡👇👇👇