✨#ሰሐቦቹ_ለምን_ቀደሙ_እኛስ_ለምን_ዘገየን?!
✍ አሚር ሰይድ
በወርሀ ረጀብ በ13ኛው ዓመተ ሒጅራ ስፍራው በሻም ምድር በዛሬዋ ሶሪያ የርሙክ ወንዝ ስር ሁለት በመጠንና በአደረጃጀት ፍፁም የተለያዩ ሀይሎች ለወሳኝ ፍልሚያ ተፋጠዋል። አርባ ሺህ ሙስሊም ወታደሮች ሁለት መቶ ሺህ የሮም ሠራዊትን ሊገጥሙ በተጠንቀቅ ቁመዋል።
ኻለድ አብኑል ወለድ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ሱረቱል አንፋል አንዲቀራ አዘዘ። አቡ ሁረይራ ተነስቶ ዳዕዋ አደረገ አቡ ሡፍያንም ቀጠለ። የሱሀቦች የውጊያ ወኔ ተቀሰቀሰ። በቁጥር አናሳዎቹ ግዙፉን የሮም ጦር አንበርክከው በሙስሊሞች ድል አድራጊነት ጦርነቱ ተደመደመ።
የሮሞች መሪ ሂረቅል ወደ አንጣኪያ አቅጣጫ አመለጠ። ያ ሁሉ ሰራዊት በአናሳ ጦር እንደዚህ መበታተኑ ንድድ አድርጎታል። አንጣኪያ ከተማ ላይ ሆኖ ከውጊያ ግንባር ሸሽተው የመጡትን ወታደሮች አነጋገረ :-
“አነዚያ የሚጋደሏችሁ እንደናንተው ሰዎች አይደሉምን? " ሲል ጠየቃቸው።
" አዎ ናቸው" አሉት።
"በሁሉም ግንባር ከእነሱ በእጥፍ ትበዛላችሁ ታዲያ ለምን ትሸነፋላችሁ?" አለ በብስጭት።
ከጦር አለቆቹ መሐል የተሰየመ አዛውንት ተነሳና : -
“እነሱ” አለ ንግገሩን ሲጀምር።
.... “እነሱ ለሊቱን ለጌታቸው ቆመውና ሱጁድ ተደፍተው ያነጋሉ። ቀኑን በሐሩር ይፆማሉ። ቃላቸውን ሁሌም ይሞላሉ። በመልካም የሚያዙ ከመጥፎም የሚከለከሉ ትውልዶች ናቸው። እርስ በርስ የሚተዛዘኑ የሚተባበሩ የሚረዳዱ ናቸዉ....
አኛ ግን በተቃራኒው አስካሪ መጠጥ አየጠጣን ሰዎችን የምንበድል.... ቃላችንን የምናፈርስ ነን። ሙስሊሞች እንደኛ በእኩይ ተግባር ካልተሳተፉና ከጌታቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ካልሻከረ እርስ በርሳቸው ያላቸው ውዴታና መተናነስ ተንዶ ወደ ጥላቻ ካልተለወጠ በፍፁም እነሱን ማሸነፍ አንችልም" አለ።
ሂረቅል የጦር አለቃዉን ንግግር ሰምቶ ሲያበቃ “አንተ እውነቱን ነገርከኝ" ሲል ተደመጠ።
‼️ ይሄዉ ዛሬ ዘመን ላይ የጦር አለቃዉ እንዳለዉ ሀራም ላይ ሙስሊሙ እየተሳተፈ..ሰዎችን እየበደልን የሰዉ ሀቅ
መፍራት ትተን በእኩይ ነገር በማንኛዉም ሶሻል ሚዲያ ላይ ሀያዕ አጥተን እየታየን ....ከጌታችን ጋር ያለን ግንኙነት ከአንገት በላይ ስለሆነ ...በትንሹም በትልቁም እርስ በራሳችን ቁርአንና ሀዲስ እያለ ለስሜታችን የሚመቸን እንዲሆን ክርክር የኔ ትክክል ነዉ የአንተ ጥመት ነዉ እያልን ጊዜያችንን እንጨርሳለን የሌሎች ሀይማኖት ተከታዮች እንደፈለጉ ያሸከረክሩን ይዘዋል...በሂጃብ ጉዳይ የተናቅነዉ አንድ ተራ ሰዉ ተነስቶ ሂጃብን ከልክሎ ተማሪዎችን የሚያሰቃየዉ የኛን ልብ አይቶ እንደሆነ ሁላችንም ልናቅ ይገባል፡፡
-----------------------------
ታላቁ ዓለም አብኑ ቁተይባ ዑዩኑል አክባር በተባለ ከታባቸው ላይ ቀጣዩን ታሪክ አስፍረዋል።
✅✅ ዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይርና ዐብዱልመሊክ ኢብኑ መርዋን እርስ በርስ መዋጋት በጀመሩበት ሰዓት የሮማዋያን መኳንንቶችና የጦር አበጋዞች ተሰባስበው ንጉሳቸው ዘንድ አመሩ። “ንጉሥ ሆይ! አሁን ሙስሊሞች እርስ በርስ መጣላት ጀምረዋል። ይህ ዕድል ሳያመልጠን እንፋለማቸው" አሉት።
.... ንጉሡ ግን "በፍፁም እንዳታደርጉት!" በማለት ግርምትን የሚያጭር መልስ ሰጣቸው።
መኳንንቶቹ በመልሱ በመደነቅ ምክኒያቱን ጠየቁ። ንጉሡም ሁለት ውሻዎችን አስመጣና እንዳያናክሳቸው አስደረገ። ውሻዎቹ እርስ በርስ እየተናከሱ ጠባቸው ሲፋፋም ንጉሡ ቀበሮ አስመጣና ወደ ውሾቹ ላከ። በዚህ ጊዜ ውሻዎቹ ጠባቸውን ትተው በመተባበር ቀበሮውን አሳደው ገደሉት። በዚህ ጊዜ ንጉሱ
“የኛና የሙስሊሞች ምሳሌ ይህ ነው! ካጠቃናቸው አንድ ሆነው ይጨርሱናል ከተውናቸው ግን እርስ በርስ ይጨራረሳሉ" አላቸው።...ይኸው ነው ምሳሴያችን ዛሬ ዘመን ላይ በሚዲያዉ በየመስጊዱ እርስ በራሳችን በቃላት እንነካከሳለን....እነ ፉላን ግን ሂጃብ የለበሱ ሙስሊም እህቶቻንን ትምህርት አትማሩም አትፈተኑም ምን ታመጣላችሁ.... ዩኒቨርስቲ አትገቡም ተብለዉም እዉጭ ያሳድሯቸዋል የዚህ የኛ በቃላት የመነካከስ ዉጤት ነዉ፡፡
ወንድሜ! እህቴ ! ታሪኩ እርስ በርስ መናከሳችን ትርፉ
ለጠላት መሆኑን ነው የሚነግረን!
ግን መቼ ይሆን ከተኛንበት የምንነቃዉ !!!???🤔
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group