አላህዬ
በ ሰውነት ፀጋ በ መሰጠት ሲሳይ
ከሁሉም አብልጦ ሚያረግ የበላይ
ወንጀሌን ደብቆ በ ግርማው አስውቦ
ቀኝ ና ግራዬን በ ኒእማው አካቦ
ልክነቴ ጎሎ ስሳሳት ስሳሳት
ልቤ ዘንበል ብላ አላማዬን ስስት
ዱንያ አድክማኝ ነፍስያን ሳስቀድም
በ ስተቱ መንገድ ፀጋዎችን ሳልም
መንገድህን አስፍተህ ና ባርያዬ ምትል
አንዴ ብቻ ጥራኝ ከምህረትክ መድብል
አላህዬ
መንገዴ ጭቃ ነው ትግል የበዛበት
አንዴ ለመራመድ ዝንት ምሰምጥበት
ጭቃውን አጥርተክ እሾሁንም ነቅለክ
አኑረኝ በተድላ ከማያልቀው ኒዕማክ
ምንም ለ ማልጠቅምክ
ላንተው ባርያህ ሰተክ
SELEHA--DIN