Репост из: እውነት ለሁሉ ewnetlehulu.net
ሙስሊም ወገኖቻችን ብዙ ጊዜ ክርስቶስ ያስተማረው በአረማይክ ቋንቋ ስለነበረ የአረማይክ ወንጌል አምጡ ይሉናል፡፡ ለዚህ ምክንያታቸው ቁርአን መልእክተኞች ሁሉ በገዛ ቋንቋቸው እንጂ በሌሎች ቋንቋዎች አልተላኩም በማለት ስለሚናገር ነው፡-
“ከመልክተኛ ማንኛውንም፤ ለነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ በወገኖቹ ቋንቋ እንጂ በሌላ አልላክንም፤ አላህም የሚሻውን ያጠማል፤ የሚሻውንም ያቀናል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።” (ሱረቱ ኢብራሂም 14፡4)
ነገር ግን ቁርአን ለዒሳ “ኢንጂል” የተባለ መጽሐፍ እንደተሰጠው ይናገራል፡-
“በፈለጎቻቸውም (በነቢያቶቹ ፈለግ) ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን ከተውራት በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲሆን፣ አስከተልን፤ ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ገሣጭ ሲሆን ሰጠነው።” (ሱረቱ አል-ማኢዳህ 5፡46)
“ኢንጂል” የሚለው ቃል Εὐαγγέλιον “ኤዋንጌሊዮን” ከሚለው የግሪክ ቃል የተወሰደ መሆኑን ሊቃውንት ይስማማሉ፡፡ ስለዚህ መልእክተኞች ሁሉ በገዛ ሕዝባቸው ቋንቋ ብቻ ተልከው ከነበሩ ለዒሳ ተሰጠ የተባለው መጽሐፍ ቋንቋው ግሪክኛ ሊሆን እንዴት ቻለ? የቁርአን ደራሲ መልእክተኞች በገዛ ቋንቋቸው ብቻ እንደተላኩ ተናግሮ ካበቃ በኋላ በግሪክ ቋንቋ የተጻፈ መጽሐፍ ለዒሳ እንደተሰጠው መናገሩ የአይሁድን ቋንቋ ባለማወቁ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ እንዲህ ያለ የተምታታ ጽሑፍ በዘላለማዊነት በፈጣረ ዘንድ እንደነበረ ማመን መታወር ነው!