ተቀበል አዝማሪ
የሰካራም ሀሳብ ቤት ማይመታ ግጥም፣
አፍህ ላይ ባያምር ለማሲንቆህ ባይጥም።
ተቀበል ግድ የለም ልስጥህ አንዲት ቃላት፣
ግና አደራህን ሺ ጊዜ ደጋግማት።
አንቺ ማለት በላት……
አንቺ ማለት ሴት ነሽ አዳምን ያሳትሽው፣
ክብር ለመቀበል ክብሩን ያስነጠቅሽው፣
ብዬ ሴትነትሽን ልንቀው አልኩና…
ሴትነትን ክብሯ አድርጋ የኖረች፣
ለካስ ካንቺ ሌላ ሌላ ሴት ልጅ አለች።
ታድያ ባንቺ ምክንያት ፣
የሴትነት ክብርን ለምን አዘቅጣለው፣
አንቺ ብታንሽ እንኳን ሴትነት ትልቅ ነው።
ብለህ ንገርልኝ ከማሲንቆህ ጋራ፣
የሰከረው ቃሌ ባንተ ቤት ከሰራ።
አንቺ ማለት በላት……
ልክ እዳረቄዬ አፍ ላይ የምትመሪ፣
በተስፍ ምትገዪ ባሳብ ምታሰክሪ።
እንደ ሲጋራዬ ካፌ ማትጠፊ፣
በልብ የማትረጊ እንደጪስ ምጠፊ፣
ከማሲንቆህ ጋራ ይህን ደጋግምላት፣
ምን እንኳን ባይገባት ትንሽ ከተሰማት።
አንቺ ማለት በላት……
ለጆቼ መታሰር ለግሮቼ ስብራት፣
ላይኖቼ መታወር ለልቤ ውልቃት።
ለስከዛሬው በደል ለስከዛሬው ጥፋት፣
ስላንቺ ሀጥያት ነው የህይወቴ ቅጣት።
እንካ ተቀበለኝ እኔም ልበቀላት፣
አደራህን ይህን በደንብ ደጋግምላት።
የምትበሪበት ክንፍ ይርገፍ ይሰባበር፣
በረከሰው ገላሽ ሴትነትሽ ይክበር።
ልክ እንደ ቀሚስሽ አይጠር ሀሳብሽ፣
ቆንጅናሽን ወስዶ ልብ ይቀይርልሽ።
ያዝማ ተቀበል አንድ የመጨረሻ፣
ባይኔ ባላይ እንኳን ያንቺን መጨረሻ።
ምን እንኳን ባይገባት፣
ይህን ደጋግምላት።
አንቺ ብጠይኝም እኔ አልጠላሁሽም አትጠራጠሪ
ጠላትህን ውደድ ስላለኝ ፈጣሪ!!!
Join and invite your friends
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
F O L L O W M O R E . .
@TADE_KEBRARAW
የሰካራም ሀሳብ ቤት ማይመታ ግጥም፣
አፍህ ላይ ባያምር ለማሲንቆህ ባይጥም።
ተቀበል ግድ የለም ልስጥህ አንዲት ቃላት፣
ግና አደራህን ሺ ጊዜ ደጋግማት።
አንቺ ማለት በላት……
አንቺ ማለት ሴት ነሽ አዳምን ያሳትሽው፣
ክብር ለመቀበል ክብሩን ያስነጠቅሽው፣
ብዬ ሴትነትሽን ልንቀው አልኩና…
ሴትነትን ክብሯ አድርጋ የኖረች፣
ለካስ ካንቺ ሌላ ሌላ ሴት ልጅ አለች።
ታድያ ባንቺ ምክንያት ፣
የሴትነት ክብርን ለምን አዘቅጣለው፣
አንቺ ብታንሽ እንኳን ሴትነት ትልቅ ነው።
ብለህ ንገርልኝ ከማሲንቆህ ጋራ፣
የሰከረው ቃሌ ባንተ ቤት ከሰራ።
አንቺ ማለት በላት……
ልክ እዳረቄዬ አፍ ላይ የምትመሪ፣
በተስፍ ምትገዪ ባሳብ ምታሰክሪ።
እንደ ሲጋራዬ ካፌ ማትጠፊ፣
በልብ የማትረጊ እንደጪስ ምጠፊ፣
ከማሲንቆህ ጋራ ይህን ደጋግምላት፣
ምን እንኳን ባይገባት ትንሽ ከተሰማት።
አንቺ ማለት በላት……
ለጆቼ መታሰር ለግሮቼ ስብራት፣
ላይኖቼ መታወር ለልቤ ውልቃት።
ለስከዛሬው በደል ለስከዛሬው ጥፋት፣
ስላንቺ ሀጥያት ነው የህይወቴ ቅጣት።
እንካ ተቀበለኝ እኔም ልበቀላት፣
አደራህን ይህን በደንብ ደጋግምላት።
የምትበሪበት ክንፍ ይርገፍ ይሰባበር፣
በረከሰው ገላሽ ሴትነትሽ ይክበር።
ልክ እንደ ቀሚስሽ አይጠር ሀሳብሽ፣
ቆንጅናሽን ወስዶ ልብ ይቀይርልሽ።
ያዝማ ተቀበል አንድ የመጨረሻ፣
ባይኔ ባላይ እንኳን ያንቺን መጨረሻ።
ምን እንኳን ባይገባት፣
ይህን ደጋግምላት።
አንቺ ብጠይኝም እኔ አልጠላሁሽም አትጠራጠሪ
ጠላትህን ውደድ ስላለኝ ፈጣሪ!!!
Join and invite your friends
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
F O L L O W M O R E . .
@TADE_KEBRARAW