Репост из: Wolkite University yeselefiyah channel
👉 ሺዓዎችና ዓሹራእ
ዓሹራእ ሲታወስ በዋነኝነት የሚታወሰው የሑሰይን ኢብኑ ዐልይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ ከርበላእ ላይ መገደል ነው ። ሑሰይን ከርበላእ ላይ የተገደለው ሙሐረም 10/61ኛው አመተ ሂጅሪያ ላይ ነበር ።
የሑሴይን መገደል መንስኤ የነበረው ለየዚድ ኢብኑ ሙዓዊያ ኢብኑ አቡ ሱፍያን ሙባየዓ አላደርግም ማለቱ ነበር ። በኢስላም ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው የሐሰን ኢብኑ ዐልይ ለሙዓዊያ የመሪነቱን ቦታ መልቀቁ ( ተናዙል ) ማድረጉ ነው ። ዑስማን ኢብኑ ዐፋን በዐብዱላሂ ኢብኑ ሰበእ አል የሁዲይ የተንኮል መረብ ከተገደለ በኋላ ዐልይ የኸሊፋነቱን ቦታ በሶሓቦች ግፊትና ውትወታ ተረክቦ ሁኔታዎችን ለማረጋጋት እየሰራ ባለበት ወቅት ሙዓዊያ የሻም ዋሊ ( አስተዳደር ) ነበርና ለዐልይ የዑስማን ገዳዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጥያቄ ያቀርባል ። ዐልይም መጀመሪያ ሙባየዓ ማድረግ እንዳለበትና ሁኔታዎች ከተረጋጉና ገዳዮቹ በህዝብ ውስጥ ተደብቀው ስላሉ መለየት በሚቻልበት ወቅት ለፍርድ እንደሚቀርቡ ይገልፅለታል ። ሙዓዊያም ምናልባት መዲና ያለው ሁኔታ ካልተረጋጋና አቅም ከሌለው ሀላፊነቱን ለሱ እንዲሰጠውና እሱ ገዳዮቹን ለፍርድ ሊያቀርብ በሚችልበት አቅምና አቋም ላይ መሆኑን በመግለፅ ይህ ሳይሆን ሙባየዓ እንደማያደርግ ለዐልይ ያሳውቃል ። ይህ አለመግባባት ሳይፈታ ዐልይ ኢብኑ አቢጧሊብ ዐብዱራሕማን ኢብኑ ሙልጂም በሚባል ኻሪጂ ይገደላል ። በቦታው ሐሰን ኢብኑ ዐልይ ሙባየዓ ተደረገለት ኸሊፋም ሆነ ። ነገር ግን ከሙዓዊያ ጋር የነበረው አለመግባባት በቀላሉ የሚፈታ አልነበረምና ሐሰን ለሙዓዊያ መሪነቱን አስረከበ ።
ይህ የሐሰን ተግባር ለሑሰይን አላስደሰተውም ። ነገር ግን ታላቁ ነውና ምንም ማድረግ አልቻለም ለሙዓዊያ ሙባየዓ አደረግ ። በዚህም ሀገር ሰላም ሆነ ሙስሊሞች ኡፈይ አሉ ። በዚህ ሁኔታ ነገሮች እየሄዱ እያሉ ሙዓዊያ መሪነቱን ለልጁ የዚድ አሳልፎ ሰጠ ። የዊላያት መሪዎችና የጦር አዛዦች እንዲሁም ታዋቂ ሶሓባዎች ለልጁ ሙባየዓ እንዲያደርጉ ጠየቀ ። ሑሰይን ኢብኑ ዐልይ ለየዚድ ሙባየዓ እንደማያደርግ ግልፅ አደረገ ። በዚህን ጊዜ የዚድ ለመዲናው አስተዳዳሪ ከሑሰይን ሙባየዓ እንዲቀበልለት ትእዛዝ አስተላለፈ ። ሑሰይንም ሁኔታው ስላላማረው መዲናን ትቶ ወደ መካ ተሰደደ ። የዚህን ጊዜ ኢራቅ ያሉ የሙዓዊያ ተቋዋሚ ፋርሳዊያን ( ሺዓዎች ) ሑሰይንን ወደ እነርሱ እንዲመጣና መሪያቸው እንዲሆን መወትወት ጀመሩ ። ሑሰይንም ለመውጣት አሰበ የኩፋ ሰዎች በየቀኑ ወደ ሑሰይን ይልካሉ ። ይህ ሁኔታ ያላማረው የዚድ የሑሰይንን እንቅስቃሴ መከታተል ጀመረ ።
ሑሰይንም የአጎቱን ልጅ ሙስሊም ኢብኑ ዓቂልን ወደ ኩፋ ሄዶ ነገሮችን እንዲያጣራ ላከው ። ሙስሊም ኩፋ እንደደረሰ በጣም ጥሩ አቀባበል ተደረገለት ለሑሰይን ሙባየዓ አደረጉ ። የዚህን ጊዜ ለሑሰይን መምጣት እንዳለበትና ሙባየዓ እንደተደረገለት ገልፆ ላከለት ።
የዚድ የሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ኩፋ መግባትና ሰዎች ( ሺዓዎች ) ለሑሰይን ሙባየዓ እያደረጉ መሆኑን በሰማ ጊዜ ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድን የበስራና የኩፋ መሪ አድርጎ በመሾም ወደ ኩፋ እንዲሄድና የሆነውን ነገር አጣርቶ እርምጃ እንዲወስድ ላከው ። ወደ መዲናና መካ የሚገኙ ትላልቅ ሶሓቦችም ሑሰይንን ወደ ኩፋ እንዳይወጣ እንዲመክሩትና ሙባየዓ እንዲያደርግ እንዲነግሩት መልእክት ላከ ።
ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ ወደ ኩፋ እንደመጣ ለወታደሮች በጣም ከፍተኛ ስጦታ ሰጠ ። ታዋቂ ሰዎችን አስጠርቶ ከሱ ጋር እንዲሆኑ የፈለጉት ነገር እንደሚያደርግላቸው ካልሆነ ግን አይቀጡ ቅጣት እንደሚቀጣቸው ገለፀላቸው ። ማንኛውም ሰው አዲስ ሰው እንዳያስጠጋ አስጠግቶ የተገኘ እርምጃ እንደሚወስድበት ተናገረ ። ቀጥሎ በስራና ኩፋ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ አዘዘ ። ማንኛውም አዲስ ሰው ከተገኘ ወደርሱ እንዲቀርብ ትእዛዝ ሰጠ ። ቀጥሎ አሉ የተባሉ ታዋቂ ሰዎችን በተለያየ ጥቅማጥቅም በመያዝ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ያለበት እንዲያደርሱትና ከሱ ጎን የቆሙ ሰዎችን እንዲለዩለት አደረገ ።
ወዲያውኑ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ያለበት ቦታ ጦቀሙት ። ወደ ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል ጉዞ ቀጠለ ደረሰበትም ። ሙስሊም ኢብኑ ዐቂል የተከሰተው ነገር ሲያይ ማመን አቃተው እነዚያ ቃል የገቡና ሑሰይንን እንዲያስመጣ ያዘዙት ሺዓዎች ክደውታል ። ዑበይዱላህ እጅ እንዲሰጥ ጠየቀው አላደረገውም ተገደለ ። የሚቀጥለው ስራ የሑሰይንን መምጣት መጠበቅ ነው ። በተለያዩ መንገዶች ጠባቂ አደረገ ። ስለሙስሊም መገደል እንዳይደርሰው አደረገ ።
ሑሰይን ከመካ ወደ ኩፋ እንቅስቃሴ ጀመረ ። ትላልቅ ሶሓቦች እንዳይሄድ ከለከሉት ። ከእነዚህ ውስጥ : –
– ዐብዱላሂ ኢብኑ ዐባስ
– ዐብዱላሂ ኢብኑ ዑመር
– ጃቢር ኢብኑ ዐብዱላሂ
– ዐብዱላሂ ኢብኑ ዙበይር
– አቡ ሰዒድ አል ኹድርይ
እና ሌሎችም ግን አልተሳካም ።
የሑሰይን መንቀሳቀስ ተሰማ ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ 1000 ፈረሰኛ እሱን ለመጠባበቅ ላከ ። ሌላ ጦር ደግሞ ዑመር ኢብኑ ሰዕድን መሪ አድርጎ ላከ ። ለዚህ ጦር እጅ ከሰጠ ይዘው እንዲያቀርቡት ካልሆነ እንዲገሉት ትእዛዝ ሰጠ ። ሑሰይን ወደ ኩፋ በቀረበ ጊዜ የአጎቱ ልጅ መገደል ፣ የኩፋ ሰዎች ከዑበይዱላህ ኢብኑ የዚድ ጎን መቆማቸውንና የአጎቱን ልጅና እሱንም እንደካዱዋቸው የሙስሊም ኢብኑ ዑቅባ ደጋፊዎች ሀኒእ ኢብኑ ዑርዋን ጨምሮ ሁሉም መገደላቸውን ሰማ ። ብዙም ሳይቆይ ከዑመር ኢብኑ ሰዕድ ጦር ጋር ተገናኘ ። እነዚያ ወትውተው ከመካ ያስወጡት ሺዓዎች አዘጋጅተው ለጅብ ሰጥተውታል ።
የዚህን ጊዜ ከሱ ጋር ያሉትን ማስጨረስ አልፈለገም ሙሉ በሙሉ ሀሳቡን ቀይሮ ሶስት አማራጭ ለዑመር ኢብኑ ሰዕድ አቀረበለት ። አማራጮቹ የሚከተሉት ነበሩ : –
– እንዲተውትና ወደ መካ እንዲመለስ
– ወደ ድንበር ሄዶ እንደማንኛውም ሙስሊም ድንበር እንዲጠብቅ ( ሀገር ጠባቂ ወታደር እንዲሆን )
– ወደ ሻም ሄዶ ከየዚድ ጋር ተነጋግሮ እንዲግባባ የሚል ነበር ።
ዑመር ይህን ሲሰማ በጣም ደስ ብሎት ለዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ ላከለት ። ይሁን እንጂ በሙስሊሞች ደም የሚታጠበው ዑበይዱላህ ኢብኑ ዚያድ እጅ ካልሰጠ እንዲገድለው አዘዘ ። ዑመር ለሑሰይን እጅ እንዲሰጥ ጠየቀው ሑሰይንም አይደረግም አለ ። በሙሐረም 10 ኛ ቀን በ61ኛው አመተ ሂጅሪያ ሺዓዎች ከመካ መሪያችን ሁን ብለው አውጥተው ከርበላእ ላይ እንዲገደል አደረጉት ።
ይህን ቀን ነው ሺዓዎች ከርበላእ ላይ ራቁታቸውን ሆነው ራሳቸው እየገረፉ ለሑሰይን ሞት ሐዘን እያሉ ያ ሑሰይን ብለው የሚጮኹት ።
https://t.me/bahruteka