የሚያጓጓ ትዳር
بسم الله الرحمن الرحيم المقدمة إن الحمد لله، نحمده ونستعينه ونستغفره، ونعوذ بالله من شرور أنفسنا وسيئات أعمالنا، من يهده الله فلا مضل له، ومن يضلل فلا هادي له، وأشهد أن لا إله إلا الله وحده لا شريك له، وأشهد أن محمداً عبده ورسوله، صلي الله عليه وعلى آله وأصحابه ومن تبعهم بإحسان إي يوم الدين وسلم تسليناً كثيراً. أما بعد:
አሰለሙአለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካትሁ
የሚያጓጓ ትዳር
ከፍል ሁለት
🎁 ጋብቻ🎀
ቁጥር 1
የሚለው የአረብኛ ቃል ሲሆን ቋንቋዊ ትርጉሙ ጥንድነት(ጥምርታነት) የሚለውን ፍች ይሰጠናል። መሰረታውይ ትርጉሙ ይህ ከሆነ አላህ ሱበሀነ ወተዓላ ይህንን የጥንድነት ህይወት በሰው ልጅ ላይ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በፈጠራቸው ላይም አድርጎታል። ለምሳሌ; እንስሳት፣እፅዋት፣ህይወት ያላቸው ነገሮች በአጠቃላይ ጥንድ ጥንድ አድርጎ መፍጠሩን በተከበረው ቁርዓን ውስጥ እንዲህ ሲል ገለፀ፣
وَمِن كُلِّ شَىْءٍ خَلَقْنَا زَوْجَيْنِ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
ትገነዘቡም ዘንድ ከነገሩ ሁሉ ሁለት (ተቃራኒ) ዓይነትን ፈጠርን፡፡ አል ዛሪያት 49
ከዚህ አንቀፅ እንድንገነዘብ ለማድረግ ከተጠቀመባቸው ነገሮች አንዱ ከሁሉም ፉጡሮች ጥንድ (ሁለት ተቃራኒ) የሆኑ ነገሮችን መፍጠሩ ነው።{ሁሉም ስንል} የሰው ልጅ እዚህ ቃል ውስጥ የሚካተት ይሆናል። የሰው ልጅ ጥንድ ሆኖ ለመፈጠሩ በተጨማሪ ቁርዓን በግልፅ እንዲህ ሲል ይነግረናል;
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَٰكُم مِّن ذَكَرٍۢ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَٰكُمْ شُعُوبًۭا وَقَبَآئِلَ لِتَعَارَفُوٓا۟ ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ ٱللَّهِ أَتْقَىٰكُمْ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌۭ
እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡
በማለት በመጀመሪያው መስመር ላይ የሰውን ልጅ ሀለት ተቃራኒ ፆታ ካላቸው አካላት ከወንድና ከሴት የፈጠረው መሆኑን በግልፅ ያሳያል። ይህ የሰው ልጅ የመፈጠሪያና የመራቢያ መንገዱ ወይም ዘዴው ግብረ ስጋ ግንኙነት ሲሆን የዚህም ህጋዊ መንገድ ጥንድነት /ጥምርታ/ በሸሪኣዊ ፍቹ #ጋብቻ በመባል የሚታወቀው የትዳር ህይወት ነው።
ለዚህም የትዳር ህይወት እስልምና የራሱ የሆነ ህግና ስርዓት አዘጋጅቶለታል። በመሰረቱ በሸሪኣ ጋብቻ ወይም ትዳር ማለት በሁለት ተቃራኒ ፆታዎች በወንድና በሴት መካከል በፍቃደኝነት የሚደረግ ህጋዊ ግንኙነት ማለት ነው።
አላህ ሱበሀነ ወተዓላ የሰውን ልጅ ግንኙነት ልክ እንደ እንስሳ ልቅና ስረዓተ ቢስ አላደረገውም። ይልቁንም ከሰው ልጅ ክብርና ማእረግ ጋር ሊሄድ የሚችል ተስማሚና ጣፋጭ ህግን በማዘጋጀት የሰው ልጅ ክብሩን እንዲጠብቅ አድርጎታል።
ይህ በእስልምና ውስጥ የተዘረጋው የጋብቻ ደንብ(ስነ ስረዓት) የሁለቱ ተጋቢዎችን ግንኙነት የተከበረና ህጋዊ ከማድረጉ የተነሳ ሰዎች ሲጓጉለት፣ሲናፍቁት፣ቦታ ሰጥተውት ልዩ ሱያደርጉት ይታያል።
ደንቦቹም ………
ሀ, መጀመሪያ የባልና የሚስት ሙሉ ፍቃደኝነት (ይህ ሲባል በሴት ልጅ በኩል እሷን ሀላፊ ሆኖ የመዳር መብት ያለው አካል ለኒካህ ሀላፊ ነው።
የዚህን ማብራሪያ ወንድም ኢብኑ ሙነወር አላህ ይጠብቀውና በሚገባ ገልፆታል
ለኒካሕ ሃላፊ (ወልይ) የሚሆኑት እነማን ናቸው?
============================
: ያለ ሃላፊ (ወሊይ) ኒካሕ ዋጋ አለው?
~~~~~~~~~~~~~~~~
በመጀመሪያ ወሊይ ለኒካሕ ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ ነው። ያለ ወሊይ እውቅና የተፈፀመ ጥምረት ፈፅሞ ከጋብቻ አይቆጠርም። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–
(لا نكاح إلا بولي )
"በወሊይ ካልሆነ በስተቀር ኒካሕ የለም!!" [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል።]
•
* ስለዚህ ፈትም ሆነች ልጃገረድ አንዲት ሴት ያለ ወሊይ ፈፅሞ ልታገባ አይፈቅድላትም። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–
أَيُّمَا امْرَأَةٍ نُكِحَتْ بِغَيْرِ إِذْنِ وَلِيِّهَا فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ، فَنِكَاحُهَا بَاطِلٌ
"ያለ ወሊዩዋ ይሁንታ የተገባች የትኛዋም ሴት ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው! ጋብቻዋ ውድቅ ነው!" [አቡ ዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።]
•
ክፍል ሁለት:– ወሊይ የሚሆኑት እነማን ናቸው?
~~~~~~~~~
ወሊይ የሚሆኑት በቅደም ተከተል የሚከተሉት ናቸው:–
1ኛ:– አባት፣
2ኛ:– የአባት አባት፣
3ኛ:– ወንዶች ልጆች፣
4ኛ:– ወንድም፣
5ኛ:– የወንድም ልጆች፣
8ኛ:– አጎቶች (የአባት ወንድም) …እያለ ይቀጥላል።
•
ማሳሰቢያ: –
•
* ወሊይ የሚሆነው በአባት በኩል ያለ ሃላፊ ብቻ ነው። በእናት በኩል ያሉትን አያካትትም። ሌላው ቀርቶ በእናት ብቻ የሚገናኙት ወንድም እንኳ ወሊይ መሆን አይችልም።
* በአባትም በእናትም የሚገናኝ ወሊይ በአባት ብቻ ከሚገናኘው ይቀደማል። ለምሳሌ በአባትም በእናትም የሚገናኙት ወንድም በአባት ብቻ ከሚገናኙት ይቀድማል።
* ተቀዳሚ የሆነው ወሊይ በቀላሉ የማይገኝ ከሆነ ተራውን ጠብቆ ሌሎች ወሊዮች ኃላፊነቱን ይወስዳሉ።
•
* አንድ ሰው ወሊይ ለመሆን
~~~~~~~~~~~~~~~~~
• ሙስሊም መሆን አለበት። ካፊር ወሊይ ሆኖ ሊድር አይችልም።
• አእምሮው ጤነኛ መሆን አለበት።
• ለአቅመ ኣደም የደረሰ መሆን አለበት።
• ወንድ መሆን አለበት።
•
* ወሊይ ከነ ጭራሹ ከሌለ ወይም ለአቅመ ኣደም የደረሱ ካልሆኑ ቃዲ ወሊይ ይሆናል።
َ (فالسلطان ولي من لا ولي له )
"አስተዳዳሪ ወሊይ ለሌለው ወሊይ ነው።" [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል]
•
* ወሊይ (ሃላፊ) በቅርብ ከሌለ ሌላ ሰው መወከል ይችላል። ውክልናው እንዲሁ "ይበጃል ላልከው ዳርልኝ" አይነት ክፍት ሊሆን ይችላል። ወይም "ለእከሌ ዳርልኝ" የሚል የተገደበ ሊሆን ይችላል።
* የሸሪዐ ቃዲዎች በሌሉበት ሃገር የኢስላማዊ መርከዝ ሃላፊ ወይም የመስጂድ ኢማም ወሊይ ሆኖ መዳር ይችላል።
* ወሊዩ ሺርክ ላይ የተዘፈቀ ወይም ሶላት የማይሰግድ ከሆነ ተራው ተጠብቆ ወደተሻሉት ኃላፊነቱ ይሻገራል።
* ወሊዩ #ያለ_ተጨባጭ_ምክንያት ለመዳር ፈቃደኛ ካልሆነ ተራው ተጠብቆ ወደተሻሉት ኃላፊነቱ ይሻገራል። ሌሎችም ፈቃደኞች ካልሆኑ ወደ ቃዲ ይሻገራል።
======================
🖼
ኢንሻአላህ ቁጥር 2 ይቀጥላል
🖊ወንድማችሁ አቡተቅይ ቃዒድ
አደራ ለአላህ ስትሉ ሼር አድርጉት
በአሁኑ ሰአት ድንበር የሚታለፍበት ተግባር ሆኖል።
ከልብ ነው ከታች ጠቁሙኝ
ሼር ካደረጋችሁ 📢
ሼር ካላደረጋችሁት 🔇
http://t.me/LoveOfMarriage