ተንቀሳቃሹ መስጊድ በጃፓን
በጃፓን ጎዳናዎች በከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ተንቀሳቃሽ መስጊድ ተሰርቷል።
ተንቀሳቃሹ መስጊድ የሚል መጠሪያ ያለው ይህ መስጊድ 48 ስኩዌር ሜትር ስፋት ሲኖረው፥ ከመኪናው የኋላ ክፍል የሚከፈት የተሟላ የፀሎት ክፍል አለው።
የዚህ ተንቀሳቀሽ መስጊድ ዓላማ በ2020 በሚካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ ለሙስሊም ተሳታፊዎች ንፁህና ደህንነቱ የተጠበቀ የፀሎት ስፍራ ማቅረብ ነው።
ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ለሁሉም ሀይማኖት ተከታዮች በተለያዩ የውድድር ስፍራዎች አስፈላጊ መገልገያዎችን ለማዘጋጀት ጥረት እየተደረገ መሆኑም ተጠቁሟል።
በጃፓን 105 መስጊዶች እንደሚገኙ የሀገሪቱ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አስታውቀዋል።
ሆኖም እነዚህ መስጊዶች ትንሽ እና ከቶኪዮ ውጭ የሚገኙ በመሆናቸው በቀን አምስት ጊዜ ፀሎት ማድረግ ለሚፈልጉ ሙስሊሞች ላይመቹ ይችላሉ ተብሏል።
ምንጭ፡- ቪ ኦ ኤና ሬውተርስ
@Loveyuolema