ማራናታ.....MARANATHA


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደምመስላቸው ጌታ ሰለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንድደርሱ እንጅ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ሰለ እናንተ ይታገሳል።2ኛ ጴጥ 3፥9 ገና በጣም ጥቅት ጊዜ ነው፤ ሊመጣ ያለውም ይመጣል አይዘገይምም። ዕብራ 10፥37
የመወያያ ግሩፕ👇
@Marantawoch
Inbox Comment @Taddyapostolic

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


የማለዳ ትምህርት 

ቀን 9/3/217  ዓ/ም

ውድ የማራናታ ቻናል ተከታዮች እንደምን ቆያችሁ በያላችሁበት የእግዚአብሔር ሰላም ይድርስላችሁ እስከ ዛር በምህርቱ ጠብቆ ከቀን ወደ ቀን ከሳምንት ወደ ሳምንት ከ ዓመት ወደ ዓመት ያሻገር እየሱስ ክርስቶስ ለዘላለም ይመስገን እያልኩኝ ወደ ዛሬ መልእክት አለፋለው

 የመልዕክተ ርዕስ ፥አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አድርጉ


ዘፍ 5፥24፣" ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም እግዚአብሔር ወስዶታልና። "

የሰው ክፋት በበዛ አለም ላይ እንዳለን እናውቃለን ግን እግዚአብሔርን መፍራት ከክፉ መንገድ ሁሉ መመለስ ለይኛ መልካም ነው 
 ትሁት ልብ ቅን ልብ የማይቀና የማይታበይ በዎንድሙ ላይ በክፋት የማያስብ ልብ ያለው ሰው ያሰው አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደርገ ሰው ነው ።

እስት ኤራሳችን እንጠይቅ አካሄድ ከእየሱስ ጋር ነው? ወይስ ከአለም ጋር ? ? እስት እንፍትሽ ከእግዚአብሔር ምን ያህል እርቀን እየኖርን እንደሆነ ጥለን በምንሄደው ግዚያዊ በሆነ በከራይ ቤት በከንቱ አለም ስንኖር የምንዘራቸውን ዘሮችን እንምረጥ!? 

#አካሄድን ከእግዚአብሔር ጋር አድርግ
#ወዳጄ ራስህን አትሸውድ!
በወንድምህ መካከል ጠብንና ክፉ ነገርን እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ፤ ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርትን አስታውስ፤

"የሰራኸውና የምትሰራው ነገር ግዜን ይጠብቃል እንጅ የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል፤ መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ፤ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል።

 ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ፤ ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ።
ስለዚህ ጥለን በምንሄደው ግዚያዊ በሆነ በከራይ ቤት በከንቱ አለም ስንኖር የምንዘራቸውን ዘሮችን እንምረጥ!? ያልኩት ለዝነው።

✅ለሰው ክፉ አታስብ እንጂ ለአንተ ክፉ ሰው ብያስብም ችግር የለም ።
✅ዓለም በርሷ መጥፎ ናት ግን መልካም ለምያስቡት መልካም ትሆናለች መጥፎ ለምያስቡት መጥፎ ትሆናለች

🖍አንበሳ ዳንኤልን ያልበላው አንበሳው ሰውን ስለማይበላ ሳይሆን ዳንኤል ለእግዚአብሔርም ለሰው መልካም ስለሆነ አንበሳው አልበላም ።
🖍ነገር ግን የሚወረወሩትን በሩቅ ይዞ ሰባበራቸው, ዛሬ ይህች ዓለም አንበሳ ናት ለእግዚአብሔርም ለሰውም መጥፎ የሆኑትን ትውጣለች መልካም ከሆኑ ግን ጥሶ ያልፋሉ ።አለሙን ማሸነ የምንችለው እግዚአብሔርን በመፍራት ፣ልቡን ከእርሱጋር በማድርግ ነው ። ወንድሞችና እህቶች እግዚአብሔር ሁላችንም ልባም ያድርገን ልብ ከለለ የምሆነው ምንም ላይታይ ይችላል ዘመኑ መጨረሻ ዘመን ነው መጠንቀቅ አለባቹሁ።

ለዝነው ዳዊት ስፀልይ እንድ አለ ፥በሞት ጥላ እንዳልተይኛ አይኖቸን አብራ አለው ፣ የዳዊት ፀሎት ትክክለኛ ፀሎት ነው እንድ መፀለይ በዚህ ዘመን ደሞ ለእኛ በጣም አስፈላግ ነው። ውንድሞችና እህቶች ችላ አትበሉ ፀልዩ ከሰው መራቅ ምንም አይፈጠርም ከእግዚአብሔር መራቅ  መጨርሻችን ነው ።

ቀርው ዘመነ እርሱን በማገልገል እርሱን በመፍራት ለርሱብቻ በመኖር ይለቅ አሜን አሜን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏


🧎🧎በጸሎት ወጥታቹ በምዝጋና ግቡ 🤷🤷🏾‍♂️
⌚✍️ የዕለቱን ትምህርት በየማለዳ 🛌🤦

              🌻🌻መልካም ቀን🌻🌻

Any comment @Marantawoch
Inbox comment @bezanegn1

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH


የማለዳ ትምህርት
ቀን 08/03/2017 ዓ/ም

ርዕስ፦ ታማኝ ባለ አደራ......

ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሠላም በያላችሁበት ለእናንተ ይሁን። ለክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከንጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይባረክ።

ውድ ቅዱሳን! በዚህ በማራናታ ተለግራም ቻናል በኩል በየማለዳ በሰማያዊ በረከት እየባረከንና ለውሎአችን ስንቅ ሆና የሚታነጽ ት/ት እየሰጠን ለዛሬ ያደረሰን አምላክ አንዱ ኢየሱስ ይመስገን እያልኩኝ ወደ ዛሬው ትምህርታችን አልፋለሁ። ከላይ በርዕሱ ላይ እንደተገለጸው የማለዳ ት/ት ርዕስ፦ ታማኝ ባለ አደራ በሚል ርዕስ እንማራለን።

ወደ ዋናው ትምህርታችን ከመግባታችን በፊት አንድ ነገር እንደ ማሳሰቢያ ልንገራችሁ። ቤተክርስቲያናችን በየአቅጣጫው ሁሉ በትምህርት የሚታስጠነቅቀው ምክንያት ሁላችንም ወደ ኢየሱስ ስለሚንሄድ በፊቱ እፍረት እንዳይኖረን እንድያንጸን ነው እንጅ ሊያጠፋን አይደለም። ስለዚህ ሁላችንም የሚንሰማውንና የሚናነበው ነገር ተረድተን በማስተዋል እንድንጓዝ ኢየሱስ ይርዳን። አሁን ወደ ትምህርቴ አላማ ልግባ።

በቤተክርስቲያን ውስጥ እስካለን ድረስ በየተለያዬ መንገድ ታማኝ መሆን ያስፈልገናል። ምክንያቱም እግዚአብሔር ታማኝ ባለ አደራዎችን ስለሚፈልግ። በአንድ ሰው ሀላፍነትን የሚሰጠው ታማኝ ሆኖ እንድያገለግል እንጅ በተሰጠው ሀላፍነትና በአገልግሎቱ ተሰናክሎ ሊወድቅ አይደለም። ታማኝ ሆኖ በታማኝነቱ በመጨረሻም እንድሸለም ነው። ሀላፍነትን የተቀበለው ሁሉ ደግሞ ሀላፍነትን በአገባቡ መውጣት ግዴታ አለበት። የዛሬ ትምህርት ከበፊቱ ለየት የሚለው እንደ ትምህርት ብቻ ሳይሆን እንደ ስልጠና ለማቅረብ እፈልጋለሁ።

እግዚአብሔር የሰጠውን ሀላፍነት በትጋትና በታማኝነት የወጣ ሰው ታማኝ ባለ አደራ ይባላል፤ ዋጋውም ውድ ነው።

(የማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 24) 45፤ እንኪያስ ምግባቸውን በጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተ ሰዎች ላይ የሾመው ታማኝና ልባም ባሪያ ማን ነው?
46፤ ጌታው መጥቶ እንዲህ ሲያደርግ የሚያገኘው ያ ባሪያ ብፁዕ ነው፤
47፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ባለው ሁሉ ላይ ይሾመዋል።

48፤ ያ ክፉ ባሪያ ግን። ጌታዬ እስኪመጣ ይዘገያል ብሎ በልቡ ቢያስብ፥
49፤ ባልንጀሮቹን ባሮች ሊመታ ቢጀምር ከሰካሮችም ጋር ቢበላና ቢጠጣ፥
50፤ የዚያ ባሪያ ጌታ ባልጠበቃት ቀን ባላወቃትም ሰዓት ይመጣል፥
51፤ ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፥ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

                 ❖ ሀላፍነትና ተጠያቅነት
ሀላፍነት፦ እግዚአብሔርና ቤተክርስቲያን ባሰማራችው/በሰጠችው/ አደራ ላይ መታገል ነው
ተጠያቅነት፦ የተሰጠውን አደራ በአገባቡ በአለመውጣት /ባለመጠበቅ/ ምክንያት የሚመጣው ቅጣት ነው። ስለዚህ ሀላፍነትና ተጠያቅነት አንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው። ተጠያቅነት ደግሞ ከቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ዘንድም ተጠያቅ ሆኖ ቅጣት ይቀበላል።

         ❖ የሀላፍነት አይነት
✔ የገንዘብ ሀላፍነት፦ በቤተክርስቲያን ውስጥ በጣም አሰናካይና ታማኝነትን የሚያጎድል ከሚባሉት ውስጥ ገንዘብ ትልቅ ቦታ ይይዛል። ምክንያቱም በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እንደተጻፈው ገንዘብ የጥፋት ሁሉ ስር ስለሆነ ነው። ገንዘብ ለሰጭም ለተቀባይም ችግር ነው።
ገንዘብ ለሰጭው፦ ቃል መግባት ቀላል ነው፤ መፈጸም ግን ከባድ ነው።
ገንዘብ ለተቀባዩ፦ እመልሳለሁ ብሎ ያወጣው ገንዘብ አሰናካይ ይሆናል።
❖ ዛሬ በጣም ትኩረት ሰጥተን የሚንማረው ገንዘብ ለሰጭው ነው።

(ኦሪት ዘዳግም ምዕ. 23) 21፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኃጢአትም ይሆንብሃልና መክፈሉን አታዘገይ።
22፤ ባትሳል ግን ኃጢአት የለብህም።
23፤ በአፍህ የተናገርኸውን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በፈቃድህ ተስለሃልና ከከንፈርህ የወጣውን ታደርግ ዘንድ ጠብቅ።

(መጽሐፈ መክብብ ምዕ. 5) 4፤ ሰነፎች ደስ አያሰኙትምና ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ ትፈጽመው ዘንድ አትዘግይ፤ የተሳልኸውን ፈጽመው።
5፤ ተስለህ የማትፈጽም ብትሆን ባትሳል ይሻላል።

ዛሬ ስንቶቻችን ነን በእግዚአብሔር ፊት ቃል ገብተን፤ ተስለን ሳንፈጽም ባለ ዕዳ ተብለን በእግዚአብሔር መዝገብ ውስጥ ተሰፍረን የሚንገኝ? መች ሊንከፍል ይሁን? ድንገት ሳንከፍል ብንሞት ማን ይከፍልልናል? ቃል የገባነውን የማንከፍለው ለምንድነው?

እኛ ልንረሳ እንችላለን፤ እግዚአብሔር ግን ቃል ከገባንበት ቀን ጀምሮ ይጠብቃል። የእግዚአብሔርና የህፃናት ባህርይ አንድ ነው። ምክንያቱም ህፃናት አንድ ብር ወይንም የሆነ ነገር ከገበያ እገዛልሃለሁ ከተባለ አይናቸውን አወጥተው ይጠብቃሉ፤ ከዋሸ ግን ያ ሰው ከልባቸው አይጠፋም፣ ቅም ይይዛሉ። እግዚአብሔርም አንዴ ይህ የእግዚአብሔር ነው ከተባለ በኋላ አተኩሮ ይጠብቃል። ምናልባት ይህ ትንሽ ነው እንላለን። ለእኛ ትንሽ ለእግዚአብሔር ትልቅ ነው። እግዚአብሔር የሚፈልገው የገንዘብ መጠን ሳይሆን ስርአቱን ነው።

አንድ ጊዜ በአጥቢያችን ውስጥ የሚታገለግል እህት ነበረችና ሞተች። ይህች እህት በፊት 30 ብር ያህል የመክሊት ዕዳ ነበራትና ሳትከፍል ሞተች። በቀብር ስነ ስርዐት ቀን ሰው የአስከረን ሽኝት ለማድረግ ወጥቶ ጉድጓድ ይቆፍራል። አንድ ቦታ ስቆፈር ድንጋይ ወጥቶ ያስቸግራል፣ ሌላጋ ስቆፍር ውኃ ይወጣል...... እንዲህ እየሆነ ቀን ሙሉ ችግር ውስጥ ዋለ። ከዛም በኃላ ቤተክርስቲያን ዕዳዋን ፈለጉና 30 ብር ታዬ፤ ከዛም ተከፈለ። በዚያን ሰአት ነው ትክክለኛ ቦታ ተገኝቶ ያረፈችው። በእግዚአብሔር ስም የተደረገው ሁሉ የእግዚአብሔር ነው፤ በዚያን ቀን ጀምሮ እግዚአብሔር ይቆጣጠራል። ስለዚህ ዕዳችን ሄዶ እረፍት እንዳያሳጣን እባካችሁ መንገዳችንን እናሳምር።

✔ ገንዘብ ለተቀባዩ፦ በቦታው አስቀምጣለሁ ብሎ ያወጣው ገንዘብ ወደ ቦታው ካልተመለሰ እና ከተረሳ ሐጥአት ነው። ያ ባለ አደራ ይቀጣል፤ ባለ ዕዳ ስለሆነ። ገንዘብ ሰጭው እርሙን ከቤቱ ያወጣል፤ ተቀባዩ ግን አላማውን ሳይደርስ በመሀል የወንድሙን እርም ይበላል። በዚህ ምክንያት መሰናከል ይመጣል። በሌላ አገልግሎት ላይ በታማኝነት እያገለገልን በገንዘብ ዙርያ ሌቦች መሆን የለብንም። ምናልባት ሳናውቅ በእኛ እጅ የቀረ ሊኖር ስለሚችል ለመፈጸም እንትጋ።

2ኛ ነግ 12፥5-17 አምብቡ። ኢየሱስ ማስተዋል ይስጠንና ይህን ሁሉ ለማለት የቻልኩት እኔም ታማኝ ሆኜ ሳይሆን ለትምህርታችን ሊንጠነቀቅ ስለሚገባን ነው። ቅድም ከላድ እንዳልኳቹም ቤተክርስቲያንና እግዚአብሔር ሰዎችን በየተለያዬ መንገድና ትምህርት ለምን ያስጠነቅቃል? ብባል ይህ ሰአት ለመነጠቅ ዝግጅት ላይ ያለን ሰአት ስለሆነ ሰው በየተለያዬ ጉዳዮች ንጹህና ቅዱስ ሆኖ ለመነጠቅ ዝግጁ እንድሆንና ወደ ታች ከሚጎትቱ ነገሮች ተላቅቆ እንድዘጋጅ ነው። ስለዚህ ኢየሱስ እንድረዳን እንጸልይ።

እግዚአብሔር የልመናችን ድምጽ ይስማልን አሜን!!!

🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂🤷‍♀

      🌻የዕለቱን ትምህርት በየማለዳ🌻
       🌸የጉዞአችንን ስንቅ ከማራናታ🌸

                 🌼መልካም ቀን!!!🌼

Any Comment   @marantawoch
Inbox comment @Taddyapostolic

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH


በወልድያ
አምስቱም ሰነፎች እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ .......መክሊቱንም የቀበረ በውጭ ወዳለው ጨላማ ተጣለ!






የማለዳ ትምህርት
ቀን 07/03/2017 ዓ/ም

ርዕስ፦ በተዘጋጀ ህይወት እንመላለስ

ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሠላም በያላችሁበት ለእናንተ ይሁን። ለክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከንጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይባረክ። ውድ ቅዱሳን! በዚህ በማራናታ ተለግራም ቻናል በኩል በየማለዳ በሰማያዊ በረከት እየባረከንና ለውሎአችን ስንቅ ሆና የሚታነጽ ት/ት እየሰጠን ለዛሬ ያደረሰን አምላክ አንዱ ኢየሱስ ይመስገን እያልኩኝ ወደ ዛሬው ትምህርታችን አልፋለሁ። ከላይ በርዕሱ ላይ እንደተገለጸው የማለዳ ት/ት ርዕስ፦ በተዘጋጀ፡ህይወት እንመላለስ በሚል ርዕስ እንማራለን።

ወደ ትምህርታችን ከመግባታችን ፊት ከእግዚአብሔር ቃል ክፍል አንድ ቦታ አንብበን እንጀምር።

መዝ ዳዊት 19፥12፤ ስሕተትን ማን ያስተውላታል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ።13፤ የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ፤ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፥ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።14፤ አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።

አንድ ሰው በተዘጋጀ ህይወት መመላለስ የሚጀምረው ስህተቱን አስተውሎ ከተሰወረም ሆነ ከድፍረት ሐጥአት ነጻ ከወጣ በኃላ ነው። ከዚህ ሐጥአት ነጻ ከወጣ በኋላ በተዘጋጀ ህይወት መመላለስ ይጀምራል። ምክንያቱም መዘጋጀት ማለት ከሀጥአት ነጻ ወጥቶ መቀደስ ማለት ስለሆነ። ከላይ ከቃሉ እንደደተረዳነው በሰው ዘንድ የተሰውረም ሆነ የድፍረት ሀጥአት አይጠፋም። ነገር ግን ይህ ዘመን በሐጥአት ላይ ሐጥአትን በአመጽ ላይ አመጽን እየጨመርን የሚንሄድበት ዘመን ነው። ምክንያቱም የትምብቱ ቃል እየተፈጸመ የጌታችን መምጫ እየተቃረበ የመጣበት ዘመን ላይ ነንና። ከፍት ይልቅ መንቃት ያለብን ሰአት ላይ ደርሰናል። ሁል ጊዜም የተዘጋጀ ሰው መምሰል አለብን እንጅ የጌታ መምጫ ገና ነው ብለን የሚንቀለድበት ሰአት አይደለም። አለም ወዴት እየሄደች እንዳለም አስቡ፣ ብልህ ሰው ዘመኑን ያስተውላል።

ወደ አንድ ሀገር ለመሄድ የተዘጋጀ ሰው በወጣበት ሰአት በዚያውም ሳይመለስ ሊሄድ ይችላል። ምክንያቱም ልብሱን ታጥቧል፣ ለመንገድ የሚሆን በቂ ስንቅ አግኝቷል፣ ዝግጅቱን ጨርሷል፣ መሄድ ብቻ ስለቀረው በየትኛውም መንገድ በየትኛውም ሰአት ይሄዳል። ለምሳሌ አንድ ሰው አንድ ቀን በመንገድ ላይ በየተለያየ አደጋ ደርሶት ብሞት ተዘጋጀ አልተዘጋጀም ይሄዳል ቤቴ ደርሼ ልመለስ፣ ልጸልይ፣ ምህረት ልጠይቅ አይልም። የሁላችንም መሄጃ መንገድ አንድ ነው፤ ስለዚህ ሁሌም ንቁ ሆነን መዘጋጀት አለብን።

እኛም ለመሄድ የሚንጓጓው አንድ ሀገር ስላለን በየትኛውም ቀንና ሰአት መሄድ እንዳለብን አናውቅምና ተዘጋጅተን እንጠብቅ። በዚህ መሠረት እለት እለት ንስሐ መግባትና ልብሳችንን እንዳይቆሽሽ መጠበቅ ግዴታችን ነው። ምክንያቱም ይህ ማንነታችን ሁል ጊዜ እየተሠራ የሚሄድ ሕንጻ ነው እንጅ በአንደ ብቻ ተሠርቶ የሚያልቅ አይደለም።

9፤10፤ እግዚአብሔር። ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ፥ በምድርም በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩ ዘንድ፥ ልጆቻቸውንም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን አሰማቸዋለሁ ብሎ በተናገረኝ ጊዜ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት በኮሬብ በቆምህበት ቀን ዓይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይወድቅ ተጠንቀቅ፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አስታውቀው።" (ኦሪት ዘዳግም 4:910)

አጥብቀን እንድንጠብቅ አደራ የተሰጠን ነገር ብኖር ነፍሳችን ነው። ነፍሳችን የሚናድነውና የሚናጠፋው እኛው ነን። ካልተዘጋጀን መምጫው ከመጣ ወይንም ከጠራን ነፍሳችን በሐጥአት ምክንያት ትጠፋለች።

አንድ ጊዜ ነፍሷን አጥብቃ የጠበቀችና በተዘጋጀ ህይወት እየተመላለሰች የቆየች እናት እንዲህ አለች ይባላል።በባህር ላይ በመርከብ ወደ ቤተሰቦቿ እየተጓዘች እያለች በባህር ላይ ማዕበል ተነሳና መርከብ ልትገለብጥ ደረሰች። ሰዎች ሁሉ ኡኡኡ ብለው አንዱ ይጮኻል፤ አንዱ ይጸልያል፤ አንዱ ጠፋን ይላል፤ ርብሻ ተነሳ። እኚይ እናት ግን እየተደሰተች ትዘምራለች። ሰው ሁሉ ግን ይህች ሞኝ ምን አስደስቷት ትስቃለች ብለው ምን ሆነሻል፣ ምን ያስቅሻል? ሊንጠፋ ነው እኮ አትጸልይም/አትጮኽም እንዴ? ስሉአት እሷ ግን ኮራ ብላ እናንተ ሞኞች መጮኽና ማልቀስ መጸለይ ያለበት ዛሬ መከራ ደርሶ ሳይሆን ድሮ ደህና በሆነ ሰአት ነው፤ እኔማ በጊዜ ስለተዘጋጀሁ፦

✔ መርከብ ወደ ኋላ ብመለስ ወደ ልጆቼ እመለሳለሁ፣
✔ መርከብ ወደ ማዶ ብሻገር ወደ ቤተሰቤ እደርሳለሁ፣
✔ መርከብ ብሰበር ወደ ተዘጋጀልኝ ሀገሬ ወደ አምላኬ እሄዳለሁ አለች። አያችሁ? የተዘጋጀ ሰው በየትም ሆኖ በየትኛውም ሰአት ብጠራ አይፈራም፣ ክፍት ነው ሰማዩ፣ ችግሩ ድንጋጤ ላልተዘጋጀ ሰው ነው እንጅ።

መዝ 46፥1፤ አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።2፤ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ፥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ አንፈራም።3፤ውኆቻቸው ጮኹ ተናወጡም፥ ተራሮችም ከኃይሉ የተነሣ ተናወጡ።

የተዘጋጀ ሰው በምንም ነገር ከቶ አይፈራም
ሮሜ 13፥11፤ ከእንቅልፍ የምትነሡበት ሰዓት አሁን እንደ ደረሰ ዘመኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እኛ ቀርቦአልና።12፤ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ።13፤በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን፤14፤ ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ።
❖ እንዴት ነው ነቅተን መጠበቅ የሚንችለው?

1, በትህትና በመመላለስ፦ የዳነ ሰው በትህትና ይመላለሳል፣ አይታበይም፣ ሁሌ ምህረትን ይፈልጋል። እምባው ከአይኑ አይጠፋም አልቃሽ ነው።
" እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤"
1ኛ የጴጥ 5፥6፦
ከፍ ለማለት በመጀመሪያ ዝቅ ማለት ያስፈልጋል። አይታችሁ እንደሆነ ብዙ ፍሬ ያለበት ዛፍ ዝቅ ይላል። እኛም ዘጠኙ (9ኙ) የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ያለን ሰዎች ዝቅ ዝቅ ብለን ትህትና ብናሳይ የተዘጋጀ ሰው እየመሰለን ነን ማለት ነው።
ትዕብት ውድቀትን ትቀድማለች
ትህትና ክብረትን ትቀድማለች።

2 በፍቅር በመመላለስ፦ የተዘጋጀ ሰው በፍቅር በመመላለስ ይታወቃል። ምክንያቱም ሰማይ የፍቅር መንግስት ስለሆነ አዚሁም ፍቅርን ያሳያል።
1ኛቆሮ 16፥13፤ ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ። 14፤ በእናንተ ዘንድ ሁሉ በፍቅር ይሁን።

ኤፌ 1፥4፤ ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።
5፤ በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን።

3 በጽድቅና በቅድስና በመመላለስ፦ ያለ ቅድስና እግዚአብሔርን ማየት አይቻልምና እንቀደስ።
" እንግዲህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ። 2ኛቆሮ 7፥1፦

ብዙ ማለት ይቻላል ነገር ግን በጊዜ አንጻር በዚህ እጨርሳለሁና ኢየሱስ እንድያዘጋጀን እንጸልይ።

እግዚአብሔር የልመናችን ድምጽ ይስማልን አሜን!!!

🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂ኸኀ🤷‍♀


የማለዳ ትምህርት
     ቀን 06/03/2017 ዓ/ም

ርዕስ፦ ህይወት እና መስዋዕት

ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሠላም በያላችሁበት ለእናንተ ይሁን። ለክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከንጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይባረክ።

ውድ ቅዱሳን! በዚህ በማራናታ ተለግራም ቻናል በኩል በየማለዳ በሰማያዊ በረከት እየባረከንና ለውሎአችን ስንቅ ሆና የሚታነጽ ት/ት እየሰጠን ለዛሬ ያደረሰን አምላክ አንዱ ኢየሱስ ይመስገን እያልኩኝ ወደ ዛሬው ትምህርታችን አልፋለሁ። ከላይ በርዕሱ ላይ እንደተገለጸው የማለዳ ት/ት ርዕስ፦ ህይወት እና መስዋዕት በሚል ርዕስ እንማራለን።

ህይወት ማለት በእግዚአብሔር ዘንድ የሚታይ መልካሙም ሆነ ክፉም የሚንሠራው የሥራ ተግባራችን ነው።
መስዋዕት ማለት ግን እግዚአብሔር እንድቀበለን የሚንሰጠው ስጦታ ነው። ነገር ግን ሁለቱንም መሐያየት እጅግ ይከብዳል። ለአንድ ክርስቲያን ህይወት እና መስዋዕት ካልተስማሙ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም። በድሮ ዘመን መስዋዕት ማለት ሰው የተለያዬ ነገር በእግዚአብሔር ፊት አምጥቶ የሚያጥን ስሆን አሁን ግን በዚያ በደምና በሚቃጠል መስዋዕት ፋንታ ምስጋና፣ ዝማሬ፣ እልልታ፣ አምልኮ፣ ሽብሸባ.....ወዘተ ተተክቶ ነው መስዋዕት የሚሆነው። ስለዚህ የሚናቀርበው መስዋዕትና በእግዚአብሔር ፊት የሚታይ ህይወታችን ተስማምቷል?

እኛ ያልኖርንበት ህይወት መዘመር፣ መስበክ፣ መመስከር ነገ በአደጋ ላይ እንዳይጥለን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። የሚንዘምረው መዝሙር የሚያንጽና የሚባርክ ስሆን በዛው መዝሙር ጋር ህይወታችን ካልተስማማ ግጭት ይፈጥራል። እንደው አንዳንድ ሰዎች አሉ፦ "እኔ ይህንን መዝሙር አልዘምርም፣ ምክንያቱም ለዚህ መዝሙር የበቃሁ አይደለሁም" ይላሉ። ይህ የሚሆነው ህይወትና መስዋዕት ስለሚለይ ነው። እግዚአብሔር አገልግሎታችንንም ያያል፣ ህይወታችንንም ያያል። አንድ ቀን ዘምረን መስክረን፣ ላብ በላብ የሚንሆንበትን ብቻ አይቶ አይቀበልም። መስዋዕታችንን መቀበል ከፈለገ በመጀመሪያ ውስጣችንን ያያል። ምክንያቱም ይህ አገልግሎታችን የሚታሰብ ስለሆነ ለመታሰቢያ የሚሆን ነገር ርካሽ ነገር አይደለም።

አንድ ጓደኛ ለጓደኛው ለመታሰቢያ ብሎ ስጦታን ስሰጥ ዝም ብሎ የቆሸሸ ነገር አይሰጥም። በውድ ዋጋ ገዝቶ ውድ የሆነ ነገር ይሰጣል። ታዲያ እኛስ ለኢየሱስ የሚንሰጠው የመስዋዕታችን ስጦታ ምን አይነት ስሆን ነው የእገለ ስጦታ ነው ብሎ ለመታሰቢያ የሚይዝልን?

(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 4) 3፤ ከብዙ ቀን በኋላም ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መሥዋዕትን አቀረበ፤
4፤ አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኵራትና ከስቡ አቀረበ። እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፤
5፤ ወደ ቃየንና ወደ መሥዋዕቱ ግን አልተመለከተም። ቃየንም እጅግ ተናደደ ፊቱም ጠቆረ።

እግዚአብሔር ለክብሩ የሚመጥን አገሎግሎት ይቀበላል እንጅ መስዋዕት ነው ስለተባለ ብቻ አይቀበልም። የአንዱን ይቀበላል፣ የአንዱን ይጠላል፣ ይንቃል። የቃኤልን መስዋዕት እንዳይቀበል ያደረገው ፊቱ አይደለም፣ ነገር ግን ህይወት /ውስጡ/ ነው።

" ቆርኔሌዎስ ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸሎትህ ተሰማ ምጽዋትህም ታሰበ።" (የሐዋርያት ሥራ 10:31)

የቆርሌኔዎስ መስዋዕት ስንመለከት ንጹህና የሚታሰብ ሆኖ ተገኝቷል። ቆርሌኔዎስ በአሕዛብ ውስጥ ሆኖም በህይወቱ ንጹህ ሰው ሆኖ የሚታሰብ መስዋዕት እያቀረበ ከቆየ በኋላ አንድ ቀን ወደ ታላቁ መዳን ተጠራ። "መስዋዕትህ ታሰበ፤ ጸሎትህም ተሰማ" ተባለ።

አንዳንድ ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ የሚታይ ህይወት ተበላሽቶ በሰው ዘንድ የሚታይ መስዋዕት ያቀርባል። ይህ ግን ከውስጡ የፈለቀ ሳይሆን በሰው ዘንድ ለታይታ የሚያቀርበው ነው በእግዚአብሔር ፊት መስዋዕታችን ማቅረብ ካልቀረ በችግራችን ጊዜ የሚታሰብና ዋስትና የሚሆን መስዋዕት እናቀርብ። ታውቃላችሁ? በችግር ጊዜ መስዋዕት ይነበባል።

(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 9) 36፤ በኢዮጴም ጣቢታ የሚሉአት አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፥ ትርጓሜውም ዶርቃ ማለት ነው፤ እርስዋም መልካም ነገር የሞላባት ምጽዋትም የምታደርግ ነበረች።
37፤ በዚያም ወራት ታመመችና ሞተች፤ አጥበውም በሰገነት አኖሩአት።
38፤ ልዳም ለኢዮጴ ቅርብ ናትና ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ በዚያ እንዳለ ሰምተው፥ ወደ እነርሱ ከመምጣት እንዳይዘገይ እየለመኑ ሁለት ሰዎች ወደ እርሱ ላኩ።

39፤ ጴጥሮስም ተነሥቶ ከእነርሱ ጋር መጣ፤ በደረሰም ጊዜ በሰገነት አወጡት መበለቶችም ሁሉ እያለቀሱ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር ሳለች ያደረገቻቸውን ቀሚሶችንና ልብሶችን ሁሉ እያሳዩት በፊቱ ቆሙ።
40፤ ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፥ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ። ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች።
41፤ እጁንም ለእርስዋ ሰጥቶ አስነሣት፤ ቅዱሳንንና መበለቶችንም ጠራ ሕያውም ሆና በፊታቸው አቆማት።

ዶርቃ በጊዜ መልካም መስዋዕት ስላቀረበች በችግሯ ጊዜ ተነበበላት። በመልካም ህይወቷ መልካም መስዋዕት አቅርባለችና በችግሯ ጊዜ ስነበብ ላካ ሞት አይገባትም ተባለች። ስለዚህ ኢየሱስ ለእኛም በመልካም የሚነበብ ህይወት ይስጠን እያልን ለመታሰቢያ የሚሆን መስዋዕት እናቀርብ።

መርድክዎስም በንጉሱ በር ላይ ተቀምጦ እያለ መልካም ነገር ሠርቶ አልዋል። ህያው የሆነ መስዋዕት ስላቀረበ ዘሩን ሙሉ በህይወት አኖረ። እኛ ግን ገና ለሌላው መትረፍ ይቅርና ራሳችንንም የሚያድን ህይወት አለን? እስክ እናስብ።
ወንድሞች፣ እህቶች ለእግዚአብሔር የሚናቀርበው መስዋዕትና ህይወታችን እንድሰማማልን መጸለይ የዘወትር ልማዳችን ይሁን።

ዮሴፍ መልካም ህይወት ይዞ ነው ወደ ወይን የተጣለው።
አቤልም መልካም ህይወት ይዞ ነው የተገደለው። ስለዚህ በመልካም ህይወት ውስጥም መቸገር፣ መገደል አለ። ስለዚህ እሱን ፈርተን መልካምነታችንን አናበላሽ። ህይወታችንና መስዋዕታችን እንድሰማማልን እንጸልይ።

እግዚአብሔር የልመናችን ድምጽ ይስማልን አሜን!!!

🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂🤷‍♀

      🌻የዕለቱን ትምህርት በየማለዳ🌻
       🌸የጉዞአችንን ስንቅ ከማራናታ🌸

                 🌼መልካም ቀን!!!🌼

Any Comment   @marantawoch
Inbox comment @Taddyapostolic

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH

1.9k 0 20 11 46

የማለዳ ትምህርት
       ቀን 05/03/2017 ዓ/ም

ርዕስ፦ ጤናማ የመንፈሳዊ ሕብረት ያለበት ቤተሰብ እንሁን

ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሠላም በያላችሁበት ለእናንተ ይሁን። ለክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከንጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይባረክ።

ውድ ቅዱሳን! በዚህ በማራናታ ተለግራም ቻናል በኩል በየማለዳ በሰማያዊ በረከት እየባረከንና ለውሎአችን ስንቅ ሆና የሚታነጽ ት/ት እየሰጠን ለዛሬ ያደረሰን አምላክ አንዱ ኢየሱስ ይመስገን እያልኩኝ ወደ ዛሬው ትምህርታችን አልፋለሁ። ከላይ በርዕሱ ላይ እንደተገለጸው የማለዳ ት/ት ርዕስ፦ ጤናማ የመንፈሳዊ ሕብረት ያለበት ቤተሰብ እንሁን  በሚል ርዕስ እንማራለን።

የእምነት ነገር የሚነሳው ከቤት ነዉ። በቤት ውስጥ ጤናማ መንፈሳዊ ሕብረት ከሌለ በመንፈሳዊ ህይወት አይጠንክርም፣ ጉዳት ይመጣል። አባት፣ እናትና ልጆች በመንፈሳዊ ህይወት ካላደጉ ወይንም ከሦስቱም አንዱ ከደከሙ ክርስትና ወደ ፊት ሳይሆን ወደ ኋላ ይመልሳል በዛች ቤተሰብ ውስጥ። ስለዚህ በተቻለን መጠን ጤናማ የመንፈሳዊ ሕብረት በቤት መመሠረት አለብን።

(ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 18) 17፤ እግዚአብሔርም አለ። እኔ የማደርገውን ከአብርሃም እሰውራለሁን?
18፤ አብርሃም በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናልና፥ የምድር አሕዛብም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉና።
19፤ ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።

በዚህ ስፍራ የሚንረዳው ነገር ብኖር እግዚአብሔር የልቡን ሀሳብ ለመናገር የሚፈልግቤተሰብና ምስጥሩን ለመናገር የማይፈልግ ወይንም ሀሳቡን የሚደብቅ ቤተሰብ መኖሩን ይናገራል። ከላይ ባየነው ክፍል ውስጥ እግዚአብሔር ለአብርሃም የልቡን ሀሳብ ሙሉ በሙሉ የሚናገረው ምክንያት ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን ያስጠነቅቃል፣ ያስተምራል ፤ቤታቸው ሙሉ በመታዘዝና በመፍራት የተሞላ ነው።

" ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፥ በዚህም ዓለምን ኰነነ፥ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።"
(ወደ ዕብራውያን 11:7)

የኖኅ ቤተሰብም እግዚአብሔርን በመፍራትና በመታዘዝ የታወቁ ናቸው። ስለዚህ እስከ ዛሬ መልካምነታቸውን ይወራል። ነገር ግን በዚህ ዘመን በመልካም ቤተሰብ ምሣሌ የሚወራ ቤተሰብ የት አለ?

ለአንድ ቤተሰብ ልጆች የሚበላሹት ዋና ምክንያት በአባትና በእናት መካከል የመተማመንና የመንፈሳዊ ጉድለት /ድርቀት/ ስኖር ነው። ይህ ማለትም በአባትና በእናት መካከል ጭቅጭቅና አለመግባባት ከተፈጠረ ልጆችም እያዩና እየሰሙ ያድጋሉ። በዚያን ሰአት ወይንም አንዴ በአባት ወይንም በእናት ጎን መቆም ይጀምራሉ። በቤት ውስጥ ክፍፍል /Partition/ ይነሳል። በመጨረሻም እግዚአብሔር አመጸኛ ቤተሰብ ይበትናል።

ደግሞም ልጆችን የሚያምጽ ዋና ትልቁ ነገር የሰንበት ትምህርት /Sunday school/ አለመማርና አለመከታተል ነው። የሰንበት ትምህርት ሳይማር በቤትና በሰፈር የአሕዛብን ትምህርት እየተማረ ያደገ ልጅ ነገም ለቤተሰብ ሸክም ከመሆኑ ውጭ ጥሩ ነገር ያመጣል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ይመስለኛል። ምክንያቱም በህፃንነቱ የቃሉ ወተት የሚቀመጥ ቦታ አለማዊ ነገር በውስጡ ተቀምጦዋል። በዚህ ዙርያ አንድ ነገር አንስቼ ብያስረዳችሁ ጥሩ ይመስለኛል።

በእስራኤል ሀገር ዛሬ ለጦርነት ቀንደኛ የሆኑት በምን ምክንያት መሰላችሁ? በፊት እስራኤል አንድ አምላክ በሚያመልኩበት ሰአት አባትና እናት ወደ church የሚሄዱበት ሰአት ልጆቻቸውን ቤት አስቀርተው ይሄዱ ነበር። አባትና እናት አምልከው ስመጡ ልጆቻቸው ቤት ተቀምጠው የተለያዩ የጦር ፊልሞች እያዩ መሣሪያ እየሠሩ በሙከራ ላይ ይውላሉ። አባትና እናት ስመጡ ቶሎ ተለቭዥን ይዘጉና ኖርማል ይሆናሉ። ያኔ የነበሩ እናትናአባት በእድሜአቸው እርጅና ወንጌልን ለልጆቻቸው ሳያስረክቡ ተራ በተራ ሞቱ። የቀሩ ልጆች ግን ወንጌልን ረሱና ጦርና ጥይት መሥራት ጀመሩ። በመጨረሻም እርስ በርስ ጦርነት ተነሳ መከፋፈል መጣ፤ እስከ ዛሬ ድረስ እየተዋጉ የሚገኙት ያኔ በተፈጠረው ስህተት ነው። ስለዚህ ዛሬም በእኛ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል ያልተማረና በቃሉ ያላደገ ሰው ነገ ምን እንደሚፈጥር አስቡ።

በተጨማርም ልጆችን የሚያበላሽ ነገር፦ ልጆችን የተለያዩ መልካም ሥነ ምግባር እንድኖራቸው አለመምከር ነው።

" ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም። " (መጽሐፈ ምሳሌ 22:6)

በሚሄዱበት መንገድ እያስተማሩ እየመከሩ እንድያሳድጉ ሀላፍነት የተሰጣቸው ለወላጆች ነው። ነገር ግን ገና ስሸመግሉ እንኳ ከልባቸው አይጠፋም። አንዳንድ ቤተሰብ ግን በራሳቸው ነው ልጆቻቸውን አመጸኛ የሚያደርጉት።
ለምሳሌ፦ በሰፈር ከልጆች ጋር ተጣልተው ስመጡ ለምን ተሸንፈህ መጣህ? አፍንጫውን አትመታውም እንደ/ በድንጋይ አትፈንክተውምን? ብለው ሽፋን ይሰጣሉ። በዚህ ሞራል ያገኙ ልጆች ነገ በተራው የእናቱና የአባቱ ራስ በድንጋይ ይፈነክታል፤ ሰፈርን ይፈነክታል። አንዳንድ ወላጆች " መታችሁ እንጅ ተመታችሁ ቤታችንን አትገቡም" ይላሉ። ከዚህ ቤተሰብ መልካም ነገርን አትጠብቁ።

ጤናማ የመንፈሳዊ ሕብረት የሌለበት ቤተሰብ

ከላይ እንዳየነው ጤናማ የመንፈሳዊ ቤተሰብ ሕብረት በሌለበት ቤተሰብ ውስጥ ሁሉም ነገር የተበታተነ እንደሆነ አይተናል። አሁንም ከአንድ ቤተሰብ በምሣሌነት ወስደን እንነሳና ለምሳሌ የኢዮብ ቤተሰብ እንመልከት

ኢዮብ በአምላኩ ፊት የታመነ የተመሰከረለት ታማኝ አገልጋይ ነበረ። በእሱ ቤተሰብ ግን እምነታቸው በሦስት የተከፋፈለ ነው።
1 የአባት /የኢዮብ/ እምነት፦ የእግዚአብሔርን ድምጽ የሚሰማ ነገርግን ለቤቱ የማያስጠነቀቅ ሰው ነበረ።
" ዖፅ በሚባል አገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ነበረ። " (መጽሐፈ ኢዮብ 1:1)

2, የእናት እምነት፦ የኢዮብ ምስት መጽናናትና ትዕግስት የሌላት ነበረች።
" ምስቱም እስከአሁን ፊጹምነትህን ይዘሀልን? እግዚአብሔርን ስደብና ሙት" አለች። (መጽሐፍ ኢዮብ 2፥7)

3 የልጆች እምነት፦ የኢዮብ ልጆች የሚጠጡና የሚሰክሩ ናቸው።
" አንድ ቀንም እንዲህ ሆነ፤ የኢዮብ ወንዶችና ሴቶች ልጆች በታላቅ ወንድማቸው ቤት ይበሉና የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር።" (መጽሐፈ ኢዮብ 1:13)

4, የጓደኛቹ እምነት፦ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያጣላ ንግግር የሚያናግሩ ናቸው።

ስለዚህ በተቻለን መጠን ጤናማ የመንፈሳዊ ሕብረት በቤተሰባችን ውስጥ እንድኖረን ሳናቋርጥ መጸለይ አለብን።

🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂🤷‍♀

      🌻የዕለቱን ትምህርት በየማለዳ🌻
       🌸የጉዞአችንን ስንቅ ከማራናታ🌸

                    🌼መልካም ቀን!!!🌼
Any Comment     @marantawoch
Inbox comment @Taddyapostolic

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH


ቀን 4/3/2017ዓ.ም

(ዩኒቨርሲቲ/ UNIVERSITY )


ውድ የማራናታ ቤተሰቦች የጌታ የኢየሱስ ጸጋና ሰላም ጤና በረከት በያለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን።

እንግዲህ ቤተሰብ የሚለው ቃል ከቃሉ እንደምንረዳው ለሁላችንም ግልጽ ነው የማይለዬን ማለት ነው ጊዜና ቦታ ሳይገድባችሁ በያላችሁበት የሚተላለፌው የሕይወት ቃል የተለያዩ መንፈሳዊ ዝማሬዎች ስብከቶች ትምህርቶች ሳያመልጣችሁ እየተካፈላችሁበት ስላላችሁ እውነትም ቤተሰባችሁ ነው እና በዚህ አገልግሎት ጊዜያቸውን ሰውተው እያገለገሉ ያሉትን ወንድሞችንና እህቶችንን ጌታ ኢየሱስ ከማያልቀው በረከት በሰማይ በረከት እየባረኬ ይባርካቸው ለማለት እወዳለሁ።

ከዚህ በመቀጠል የ2017ዓ.ም የጠቅላላ የዩኒቨርስቲ የፌሎ አስተባባሪዎችን ብቻ ይመለከታል።

ጠቅላላ የ2017E.C አዲስ የተመረጣችሁም ሆናችሁ በፊት ሲታገለግሉ የቆያችሁ የዩኒቨርስቲ አስተባባሪዎች በጠቅላላ
የሕብረቱ አስተባባሪ
የሕብረቱ ጸሐፊ
የሕብረቱ ገንዘብ ያዥ
የአጥቢያ ቸርች አላልኩኝም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ብቻ የሚመለከት ነውና።
እና በጊቢ ሕይወት ወይም ጊቢ ውስጥ ሳለን ከጊዜው ጋ ከዘሜኑ ጋር እንዴት እየሄድን እንዳለን. እነዚህ ሥራዎች እግዚአብሔርም ከሰማይ ቤተክርስቲያንም እንዲንሰራ አምና ኃላፊነት ሲትሰጠን ምን ያህል ኃላፍነት በውስጣችን አድሯል?
በጊቢ ቆይታችን በዓለም ትምህርት ዕውቀታችንን ግንብተን እንደምንወጣ ሁሉ በቤተክርስቲያን ዕውቀት ምን ያክል ወስጣችንን ገንብተናል/ ዕውቀት አለን?
እንደ ቤተክርስቲያን ልጆች በተቃራኒ ዓለም ለሚታመጣው ለተለያዩ ጥያቄዎች ምን ያክል ለመመለስ ዝግጁ ነን?
በአጭሩ ስለ ቤተክርስቲያንን ምን ያህል ዕውቀቱ አለን?
ምክንያቱም ብዙ ነገር ከእኛ ይጠበቃል
ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ...ይህንን አስብ.....
እና ስለ ጊቢ የተማሪዎች አያያዝ በሚገባ ለመወያያት እጅጉን አስፈላጊ እንደሆነ ስላሰብኩበት ነውና ስልካችሁን በውስጥ መስመር ሁላችሁም አስቀምጡ
ብዙ ነገር ስለጊቢ ሁነታዎች
በአገልግሎት ዙርያ,በአስቸባባርነቱ ዙርያ በጠቅላላ ስለምናሳልፋቸው ሕይወት መናገር ይቻላል ግን ሃሳቡን ለመግለጽ ያህል ነው
በዚሁ ዙርያ የምንወያይባቸው ነገሮች ስላሉ ነው አመሰግናለሁ።

ስለዚህ ከቀን4/3/2017ዓ.ም እስከ ቀን8/3/2017ዓ.ም
ስም....................
ስልክ..................
የጊቢው ስም..............የሶስቱ በአንድ ላይ

አሳውቁ ማንም ባይቀር የተሻለ ነው የበረከቱ ተካፋይ ሁኑ አመሰግናለሁ



👇👇👇
Comment :- @Joappo
@Joapp

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH


ግጥም

አገልጋዮች እንሁን
〰〰〰〰〰〰〰
ይድረሳችሁ ከልብ ለምንወደችሁ ውድ የማራናታ ቤተሰቦች በዚ ዘመን ላለን
የቅዱስ የእግዚአብሔር ልጆቹ ለሆንን
የኢየሱስን ስራ ድቃድቁን ላየን
ከጥፋት ላዳነን በደሙ ለገዛን

እግዚአብሔር ለስራው ሰውን ይፈልጋል
ወታደር ሊያደርገን ጌታ የሱስ ይሻል

ታዲያ ወንድሜ ሆይ አንቺም የኔ እህት
ተዘጋጅተን ይሆን ልፈፅም እቅዱን
ለእግዚአብሔር ስራ አገልጋይ ለመሆን


በሙሴ ተጠቅሞ ህዝቡን ሲያሶጣ
በልጁ በእያሱ አህዛብን ሲቀጣ
እንደልቤ ባለው ጎልያድን ሲመታ
ደግሞም በኤልያስ በአልን ሲረታ
በፈጠረው ፍጥረት ያውም በሰው ልጅ ነው
ኢየሱስ ሲሰራ ሲያደርግ እንደዚህ ነው
ለቅዱስ አላማ አገልጋይ ሚያደረገው
የእግዚአብሔርን ሃሳብ እንድንፈፅም ነው

እግዚአብሔር ሰርቷል ጥንት በነቢያት
ሥራውም ተሰርቷል በድንቅ በታምራት
ዛሬም በዚህ ዘሜን እጣው ወድቆብሃል
ምክንያትህን ትተህ አምልክ ይሻልሃል
በጠላት ራስ ላይ በድል ያቆማሃል
ኢየሱስ ከጽዮን ዘወትር ያጥንሃል
ምህረቱን ሌተቀን የሱስ ይልክሃል
የሰማዩን መንግስት የሱስ ያወርስሃል

ሐዋሪያትን መርጦ ወንጌልን ሲያሰብክ
ከዓለም ዳር እስከዳር ፍጥረትን ሲማርክ
ሰለ ኢየሱስ ገድልን ተጋድለው
ሕይወትን ሰውተው የደም ዋጋ ከፍለው
ለቅዱስ ዓላማ ጊዜያቸውን ሰውተው
አባቶችም ደግሞ ይህን ተረክበው
እዚ አድርሰዋል በአገልግሎት ጸንተው
እናም በዚ ዘመን አንተን እኔን መርጧል
እግዚአብሔር ለስራው( እኔን) ይፈልጋል
እግዚአብሔር ለስራው (አንተን) ይፈልጋል
እግዚአበሔር ለስራው (አንቺን) ይፈልጋል

ታዲያ ወንድሜ ሆይ አንቺም የኔ እህት
ተዘጋጅተን ይሆን ልንፈፅም እቅዱን
ለእግዚአብሔር ስራ አገልጋይ ለመሆን

የቱ ይጠቅመናል የቱስ ይሻለናል?

አለምን ወደናት አገልግሎት ትተን
ግያዝን እንሁን ምንወርስ ሀጢያትን
ወይስ ካባቶች ጎን ሳጠፋ ሳንለይ
መሆን እደ ኤልሳዕ በእጥፍ አገልጋይ

እንምረጥ መልካሙን የሂወት ጎዳና
አገልጋዮች ያርገን ያዎጣናልና።


በዚህ ቃል ክፍል ውስጥ ወደተቀደሰው ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን እንደሚወጣና በተራራው ላይ ማን እንደሚኖር በግልጽ አስቀምጦዋል። በዛው መስፈርት መሠረት ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወጥተን በዛው መኖር አማራጭ የሌለ የህይወታችን ጉዳይ ነው።

ስለዚህ አሁን እግዚአብሔር እንድረዳን እንጸልይና ቀናችንን እናስረክበው።

እግዚአብሔር የልመናችን ድምጽ ይስማልን አሜን!!!

🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂🤷‍♀

      🌻የዕለቱን ትምህርት በየማለዳ🌻
       🌸የጉዞአችንን ስንቅ ከማራናታ🌸

                 🌼መልካም ቀን!!!🌼

Any Comment @marantawoch
Ibox comment @Taddyapostolic

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH


የማለዳ ትምህርት
ቀን 04/03/2017 ዓ/ም

ርዕስ፦ ከሰይጣን ተራራ ወርደን ወደ ኢግዚአብሔር ተራራ እንውጣ

ውድ የማራናታ ቻናል ተከታዮች እንደምን ሰነበታችሁ የምህረቱ ባለጠጋ አምላክ ከፊቱ እኛን ሳያጣፋ ይህችን ቀን በምህረቱ ባርኮ የሰጠን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላዓለም ይባርክ እያልኩ ወደ ዛሬ መልእክት አልፋለሁ የዛሬ ርዕስ፦ከሰይጣን ተራራ ወርደን ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ በሚል ርዕስ እንማራለን።

በመሠረቱ ተራራ ማለት የማይታይና የተጋረደ ነገር ሁሉ ጎልቶ የሚታይ ከፍ ያለ ቦታ ነው። ስለዚህ ሁለት የከፍታ ተራሮች እንዳሉ በእግዚአብሔር ቃል እንረዳለን። ደግሞም ማንኛውም ሰው ከዚህ ከሁለቱም ተራራ ማምለጥ አይችልም። ይህ ማለትም አንድ ሰው አንዴ የሰይጣን መውጣት አለበት ወይንም ከዛ ወርዶ ወደ እግዚአብሔር ተራራ መውጣት አለበት፣ ምርጫው ግን እንደ ሰው አረዳድ ይለያል። በእሥራኤል ዘመንም የመረገም ወይም የሰይጣን ተራራና የበረከት ወይም የእግዚአብሔር ተራራ በመባል የሚታወቁ ሁለት ትላልቅ ተራሮች እንዳሉ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገረናል የእነዚህ ተራሮች ስም፦ የበረከተ ተራራ ገሪዛን ተራራ ሲሆን የመረገም ተራራ ደግሞ ጌባል ተራራ በመባል ይታወቃሉ። ከዚህ በታች በሰፈው እንመለከታለን፦

ዘዳ 11: 29፦አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ አንተን ወደምትሄድባት ምድር ባገባህ ጊዜ፥ በረከቱን በገሪዛን ተራራ መርገሙንም በጌባል ተራራ ታኖራለህ።

ሁለቱንም ተራራ እንመልከት

1, ሰይጣን የሚያወጣ ተራራ፦ የግብዝነት ተራራ /የውሽት/ የሙስና/ የአመንዝራ/የጣኦት ማምለክ ተራራ ይባላሉ። ይህ ተራራ ጊዜያዊ ስሆን በመጨረሻም የውርደት ይሆናል።
ይህንን ተራራ የወጣ ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ትዕብተኞችን ይቃወማል ለትሁታን ግን ጸጋን ይሰጣልና።

የማቴ ወ 4፥8፦....ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ።
9፦ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው።
10፦ያን ጊዜ ኢየሱስ። ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
11፦ያን ጊዜ ዲያቢሎስ ተወው፥ እነሆም፥ መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር።

2, እግዚአብሔር የሚያወጣ ተራራ፦ የትህትናና ሰማያዊ ተራራ/የፍቅር ተራራ የመንፈስ ቅዱስ ተራራ/ የመሠጠት ተራራ የባልንጀራህን የመወደድ ተራራ..ወዘተ ይባላሉ። እኒኝ ተራሮች ዘላለማዊና የክብር ተራሮች ናቸው። እግዚአብሔር ዝቅ የሚሉትን ከፍ ሊያደርግ ስለሚፈልግ በመጀመርያ በፊቱ ዝቅ የሚሉትን ይፈልጋል።

የማቴ ወ.17፥1፦....ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።
2፤ በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።
3፤ እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።
4፤ ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ።

5፤ እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
6፤ ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።
7፤ ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና። ተነሡ አትፍሩም አላቸው።
8፤ ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።

በዚህ በሁለቱም ቃል ክፍል የሚንረዳው ነገር፦
☞ ሰይጣን ተራራ አወጥቶ አለምን ያሳያል፦
☞ እግዚአብሔር ተራራ አወጥቶ አምላክነቱንና ሰማይን ያሳያል። ስለዚህ ምርጫችን ምን ይሁን የቱ ይሻለናል? ሰይጣን ዛሬ አለምን አሳይቶ ከፍ ከፍ አድርጎ ያከበረ ይመስላል፤ ከዛው ከተራራው ስጥል ውድቀትና መሰባበር ታላቅ ይሆናል። ስለዚህ ዛሬ እኛ ከሰይጣን ተራራ ወርደን ወደ እግዚአብሔርና እግዚአብሔር ወደሚያሳየን ተራራ መውጣት አለብን።

1ኛየጴጥ.መል.5፥5፦እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።
6፤ እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤

7፤ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።
8፤ በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤
9፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።

በእግዚአብሔር ፊት ራሳችንን ማዋረድ ወደ እግዚአብሔር ተራራ መውጣት ነው። በእግዚአብሔር ፊት ከፍ ከፍ ብሎ ራሱን ማሳየት ግን ወደ ሰይጣን ተራራ መውጣት ነው፤ ይህንን ልዩነት ማወቅ አለብን። በቤተክርስቲያን ውስጥ ከእኔ ውጭ ማን አለ ብሎ እራሱን Specalize ማድረግ ከጀመረ አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ተራራ ወረደ ማለት ነው። ዛሬ እኔ ስዘምር፣ እኔ ስሰብክ፣ እኔ ስያመልክ፣ እኔ እኔ እኔ..... በቃ እኔ በሌለሁበት ሰአት ለዚህ Church ማን አለ? ማለትና እራሱን ከፍ ከፍ አድርጎ በልቡ እራሱን ማድነቅ ከጀመረ የሰይጣን ተራራ ወጥቶ ከእግዚአብሔር ተራራ ወረደ ማለት ነው። ለዚህ አገልጋይ መውደቁ ታላቅ ይሆናል።

ትዕቢት ጥፋትን፥ ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።
ምሳሌ 16፥18

እግዚአብሔር ትህትና ዝቅታ ስፈልግ ሰይጣን ግን ግብዝነትን ይፈልጋል፤ ዋና መሣሪያው እሱ ነውና። ስለዚህ ከትህትና ወጥቶ እራሱን እያሳየ እየተመላለሰ ያለው ወንድም ዛሬ ከዛው ከከፍታው ወርዶ በትህትና ራሱን አዋርዶ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አለበት። ምክንያቱም እግዚአብሔር አጥብቆ የሚጠላው ነገር ብኖር ግብዝነት ነውና።

ስለዚህ ከሁለቱም ተራራ የሚበልጠውን በጊዜ መፈለግ ተገብ ነው። ነገር ግን የዚህ አለም ነገር ታይቶን የሰማዩን ጋርዶ እንዳንመለከት አድርጎን ከሆነ ቶሎ ንስሐ መግባት ያስፈልጋል።

(2ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕ. 1) 8፤ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤
9፤ እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል።
10፤ ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና።

በሰይጣን ተንኮል እንዳንሰናከል መጠራታችንና መመረጣችንን እንመልከት። ደግሞም የሰማይ ተስፋችንን እየናፈቅን መመላለስ አለብን።

(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 15) 1፤ አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል?
2፤ በቅንነት የሚሄድ፥ ጽድቅንም የሚያደርግ፥ በልቡም እውነትን የሚናገር።
3፤ በአንደበቱ የማይሸነግል፥ በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ፥ ዘመዶቹንም የማይሰድብ።
4፤ ኃጢአተኛ በፊቱ የተናቀ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም።
5፤ ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘላለም አይታወክም።


የማለዳ ትምህርት
        ቀን 03/03/ 2017 ዓ/ም

      ርዕስ፦ ጥበቃ ያለው በረከት

ውድ የማራናታ ቻናል እና የማለዳ ትምህርት ተከታዮች እንደምን አላችሁ የጌታ ፍቃድ ሆኔና የትናንትናውን በዛሬው ተክቶ የዛሬውን ቀን ባርኮ የሰጠን ኢየሱስ ይመስገን እያልኩኝ ለዛሬ ማለዳ የሚያስፈልገውን ለእኛ አስተካክሎ የቃሉን ግብዣውን የጋበዘ አምላክ ይባርክ እያልኩኝ ለዛሬ ውሎ የሚሆን የእግዚአብሔርን ቃል #ጥበቃ_ያለው_በረከት በሚል ርዕስ እንማራለን

በምድር ላይም ሆነ በሰማይ በሰማይ በረከቶች ነው ከሚባሉት ሁሉ ትልቁ በረከት መዳን ነው። ሰው መዳንን አገኘ ማለት ትልቁ ሀብት /በረከት/ አገኘ ማለት ነው። ነገር ግን መዳንን ያላገኘ ሰው ምንም አይነት ሀብት ካገኘ ጊዜያዊ በረከት አግኝቷል እንጅ ዘላለማዊ አላገኘም ማለት ነው። ይህ የመዳን በረከት ግን እጅግ በጣም ጥበቃን ይፈልጋል። ጥበቃ የሌለው በረከት ከሆነ ለትንሽ ጊዜ ብቻ ቆይቶ እንደገና ይጠፋል።

(ኦሪት ዘኍልቍ ምዕ. 6) 22፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው።
23፤ ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው። የእስራኤልን ልጆች ስትባርኩአቸው እንዲህ በሉአቸው።
24፤ #እግዚአብሔር_ይባርክህ_ይጠብቅህም፤
እግዚአብሔር ባርኮ ግን ጥበቃው ከሌለ በረከቱ በረከት ሆኖ አይቀጥልም።

(መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ ምዕ. 4) 9፤ ያቤጽም ከወንድሞቹ ይልቅ የተከበረ ነበረ፤ እናቱም። በጣር ወልጄዋለሁና ብላ ስሙን። ያቤጽ ብላ ጠራችው።
10፤ ያቤጽም። እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
ከክፉ ካልተጠበቀ መባረክ ብቻ ምን ያደርጋል? በረከት በሜዳ ላይ መቀመጥ የለበትም፥ እንክብካቤና ጥበቃ ያስፈልጋል።

" ሕዝብህን አድን፥ ርስትህንም ባርክ፤ ጠብቃቸው፥ ለዘላለሙም ከፍ ከፍ አድርጋቸው።" (መዝሙረ ዳዊት 28:9)
መቼም ብሆን ባርከን ካልን በኋላ ቀጥሎም ጠብቀን የሚል ጸሎት መቀጠል አለብን።

ራዕ 3፥8 " ትባረካለህ" ካለ በኋላ ደግሞ ከፈተናም "እጠብቅሀለሁ" አለ።

          መቼም በረከት ስመጣ ጥበቃ ይቀጥላል!!
ለምሳሌ፦ በፊት ድሀ የሆነ ሰው ትንሽ ሀብት ካገኘ በረከት ስመጣለት አሮገውን አፈርሶ አዲስ ቤት ይገነባል፤ ትንሽ ከፍ ስል መኪና ይገዛል....ከዛም በኋላ የእሾህና የቆርቆሮ አጥር አፈርሶ ግምብ ይገነባል፣ ውሻ ያሳድጋል፣ ዘበኛ ይቀጥራል...... በአጠቃላይ ለዚህ ሰውዬ ጥበቃ ያስፈልገዋል ማለት ነው። ምክንያቱም ሀብቱ በረከቱ እንዳይሰረቅ ነው እንጅ ለሌላው ልዩ የሥራ ዕድል ልፈጥርለት አይደለም። ከዛም በላይ  የኛ ሀብትና የኛ በረከትም መጠበቅ አለበት።

በዚህ በእኛ ቤት መጠበቅ ያለበት ሀብት፣ ገንዘብ፣ ንብረት፣ ብር፣ ወርቅ ሳይሆን #መዳን ነው። ምክንያቱም በኪሳችን ውስጥ ያለው ትልቁ ሀብታችን መዳናችን ስለሆነ ነው። በኪሱ ውስጥ ብዙ ብር የያዘ ሰው እንደፈለገ መንቀሳቀስ አይችልም። በፈለገ ቦታ አይገኝም፤ ምክንያቱም ሊጠፋበት ስለሚችል ነው።

የሳምሶም በረከት ስትመለከቱ አያስገርምም? ከዱር 300 ቀበሮዎች አምጥቶ ሁለት ሁለት ቀበሮ ይዞ ጥንድ አድርጎ ችቦን እስክሎክስ ድረስ ተረኞቹ ቁጭ ብለው ታዝዘው ተራቸውን ይጠብቃሉ። ምን አይነት በረከትና ጸጋ ነው እግዚአብሔር በጸጉሩ ላይ ያስቀመጠው? የዚያን ሰአት ለሳምሶም ያስፈለገው ተጨማሪ በረከት ሳይሆን ጥበቃ ነው። ሳምሶም ግን ይህንን ጸጋ ይህንን በረከት ይዞ ከደሊላ ጋር ይጫወታል፣ ይተኛል። በኪሱ ውስጥ ያለው በረከት አቃለለ። አያያዝና ጥበቃ ስለሌለው ጸጋውን አጠፋ፣ ተራ ሰው ሆነ።

    ወንድሞችና እህቶች እግዚአብሔር ይጠብቀን!!
ጀግናው ናቡቴ ግን የአባቶቼ የወይን ቦታ የሚመስል ሌላ የለምና እጠብቃለሁ ብሎ የአባቶቹን በረከት ጠብቆ ሞቴ።
1ኛ ነግ 20፥1
እኛም ዛሬ ብንሞት እንኳ የአባቶቻችን እምነት /ጸጋ/ መዳን/ ጠብቀን ብንሞት ምን አለበት? ወንድሞች እህቶች እየተቸገረንም፣ እየተራበንም በሞት ላይ ብንሆንም ስንኳ መዳናችንን ጠብቀን እንሙት፤ ዛሬ ብደላንም ነገ መሞታችን አይቀርምና። ናቡቴ፦ ግደሉኝ እንጅ በርስቴ ላይ ሆኜ እሞታለሁ እያለ በሜዳ ላይ ተወግሮ ሞቷል።

አንድ ጊዜ ዳዊት ሳኦልን በአንድ ዋሻ ስያሳድድ ብቻውን ተኝቶ አገኘ። የዳዊት ሰራዊት እግዚአብሔር ለአንተ አሳልፎ የሚሰጥበት ቀን ዛሬ ነውና ግደለው" አሉት። ዳዊት ግን ነገ ንጉስ መሆኑን ስለተረዳው መዳኑን /ንግስናውን/ ጠበቀውና አለፈ።

" እነሆ፥ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።"
(የዮሐንስ ራእይ 16:15)
ለምሳሌ እንበልና፦ አንድ ሰው በ1000 ብር አንድ ሸምዝ ከገዛ ምን ያህል ጥንቃቄ ይሰጣል? ቆሻሻ እንዳይነካው፣ እንዳይቆሸሽ እንዴት እንደሚጠነቀቅ ታውቃላችሁ። ነገር ግን እኛ ምንም ሳንከፍል የመዳን ልብስ #ኢየሱስን በጥምቀት ብቻ ለብሰን ስንወጣ አይገርምም? ይህን የለበስነው መዳን መጠበቅ በረከት ነው። ግን እንዴት አይነት ልብስ ነው የሚናቆሽሸው? ኤሳውንም ስትመለከቱ በኩር ልጅ ነበረ። በዚያን ዘመን ብኩርና እንደ መዳን ይቆጠራልና ብኩርና አግኝቶ ነበረ። ነገር ግን የጎደለበት ነገር ዋና ጥበቃ ነው። አንድ ቀን መታገስ አቃተውና መዳኑን የሚያስጥል ነገር መጣ፣ መዳኑን እንድሸጥ አደረገ። በነገራችን ላይ መዳናችንን የሚፈትን ነገርበጎደለን በኩል ይገባል። ኤሳው ከአደን ስመጣ የወጥ ሽታና የተራበ አፍ ተገናኘ፥ ብኩርናዬ የምኔ ናት አለ።

ስለዚህ ለማጠቃለል ያህል የኛ መዳን ጥበቃ የሚፈልግ በረከት ስለሆነ ብንቸገርም፣ ብንራብም፣ ብንጠገብም መዳናችንን እንጠብቅ። ምናልባት ዛሬም ከዚህ ወጥቶ በሚውልበት በውሎ ምክንያት መዳኑን አቃልሎ የሚመልስ ሊኖር ይችላልና እግዚአብሔር ጥበቃውን እንዳይለየን መጸለይ አለብን።

እግዚአብሔር የልመናችን ድምጽ ይስማልን አሜን!!!

🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂🤷‍♀

      🌻የዕለቱን ትምህርት በየማለዳ🌻
       🌸የጉዞአችንን ስንቅ ከማራናታ🌸

                    🌼መልካም ቀን!!!🌼
Any Comment @marantawoch
Ibox commet    @Taddyapostolic

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH

2.8k 0 20 12 45

የማለዳ ትምህርት
          ቀን 02/03/2017 ዓ/ም

ርዕስ፦ የእግዚአብሔርን ቃል ለማደግና ለመዳን ስማ

ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሠላም በያላችሁበት ለእናንተ ይሁን። ለክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከንጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይባረክ።

ውድ ቅዱሳን! በዚህ በማራናታ ተለግራም ቻናል በኩል በየማለዳ በሰማያዊ በረከት እየባረከንና ለውሎአችን ስንቅ ሆና የሚታነጽ ት/ት እየሰጠን ለዛሬ ያደረሰን አምላክ አንዱ ኢየሱስ ይመስገን እያልኩኝ ወደ ዛሬው ትምህርታችን አልፋለሁ። ከላይ በርዕሱ ላይ እንደተገለጸው የማለዳ ት/ት ርዕስ፦ የእግዚአብሔርን ቃል ለማደግና ለመዳን ስማ በሚል ርዕስ እንማራለን።

የእግዚአብሔር ቃል ከአንድ ህይወት ወደ ሌላ ህይወት ወይንም ወደ ሌላ ማንነት የሚቀየርና የሚለወጥ ነው። ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ የማይለወጥና የማያድግ ሰው ቃሉ እንደሚለው በድንጋይ ላይ እንደፈሰሰ ውሀ ነው። ይህ ማለትም የፈለገ ውሀም ሆነ ዝናብ በድንጋይ ላይ ስፈስ ውጤቱ ዜሮ ነው፤ አይለማም። ነገር ግን በመልካም መሬት ላይ ትንሽ ጠብታም ብፈስ ለውጡ ቀን በቀን ይታያል። በእኛ ህይወት ላይ በየቀኑ የእግዚአብሔር ቃል ይፈሳል፤ ይወርዳል። ነገር ግን በዚያን ሰአት ተባርከን፤ ከታንጸን በኋላ ግን ወደ ቦታችን የሚንመልሰው ለምንድ ነው?

(ወደ ዕብራውያን ምዕ. 6) 7፤ ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ መሬት፥ ለሚያርሱአትም ደግሞ የምትጠቅምን አትክልት የምታበቅል፥ ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለችና፤
8፤ እሾህና ኵርንችትን ግን ብታወጣ፥ የተጣለች ናት ለመረገምም ትቀርባለች፥ መጨረሻዋም መቃጠል ነው። 9፤ ስለ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ምንም እንኳ እንዲሁ ብንናገር፥ አብልጦ የሚሻለውና ለመዳን የሚሆነው እንዲሆንላችሁ ተረድተናል።

የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተን ካደግን በኋላ ወደ መዳን እንደርሳለን። ቃሉ ያሳድጋል፤ ያድናልም። መስማት ወደ ማደግ ያሻግራል፤ ማደግ ደግሞ ወደ መዳን ያደርሳል። ለራሱ ሰምቶ ያደገ ሰው ለሌላውም ይተርፋል። ነገር ግን ለትምህርቱ ያልተጠነቀቀ ሰው እራሱንም የሚሰማውንም አያድንም።
"ለራሱ ሳይበቃ ለሌላው ጠበቃ" እንደሚባለው ተናጋሪው ለራሱም ጠመነቀቅ ያስፈልጋል።

(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ምዕ. 4፥ 15፤ ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ይህን አስብ፥ ይህንም አዘውትር። 16፤ ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፥ በእነዚህም ጽና፤ ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና።

ሰው አያስተውልም እንጅ በየትኛውም ጊዜ በየትኛውም ቃለል እግዚአብሔር ይናገራል። ስናገር ደግሞ በሁለት መንገድ ይናገራል።

1ኛ ልቦናን ከፍቶ ይናገራል
2ኛ ልቦናን ዘግቶ ይናገራል
እግዚአብሔር ለፈርዖን ስናገር ልቦናውን ዘግቶ ስለተናገረው ጠፋ። አሥሩንም መቅሰፍት ስያመጣለት ፈርኦን ደንድኖዋል፤ እግዚአብሔር ልቡን አደነደነው። ቃኤልም እንደዛው እግዚአብሔር ወንድሙን ስጠይቀው ንስሐ መግባት አቅቶት መከራከርና ማታለለል ጀመረ፤ የወንድሜ ጠባቂ እኔ አይደለውም አለ። ዛሬመም ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር እየተናገራቸውም የማይመለሱ፣ ንሰስሐ የማይገቡ አሉ። ልባቸው የተከፈታቸው ሰዎች ግነን ቶሎ ንሰስሐ ይገባሉ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ይታረቃሉ። የተለያየ ኮንፈራንሶችም ሆነ በየአጥቢያችን እገግዚአብሔር ስናገረን ከፍቶን ነው ወይስ ዘግቶን ነው?

እግዚአብሔር ልቦናቸችንን ከፍቶ ይናገረን አሜን!

የሰይጣን አጉል ልንገራችሁ፦ ሰይጣን በፊት ሰው ወደ መዳን እንዳይመጣ የመዳን ወንጌል እንዳይሰማ እንዳይቀበል ይከልክል ነበረ። አሁን በዚህ ዘመን ግን አባቶቻችን በብዙ ጸሎትና ትግለል አስለቀቁትና አሁን ግን መጥቶ የተጠመቀ ሰው በወንጌል ሰምቶ እነንዳያድግ፣ የሰማውን እንዳይተገብርና እነንድባከን እያደረገ የድንዛዜ መንፈስ እየለቀቀ፤ ውስጡን ባዶ እያደረገ ይገኛል። እኛ ክርስትያኖች ይህንን የሰይጣንን ሴራ አውቀን መንቃት ግድ ይለናል። ይህንን ሴራ ጥሰን ወደ መዳን ማለፍ አለብን።

(የያዕቆብ መልእክት ምዕ. 1) 22፤ ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ። 23፤ ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤ 24፤ ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል።

አንዳንድ ሰው ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል ለአባልነት ይሰማል፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን ለአባልነት ሳይሆን ለመዳን የሚሰማ ነው። ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የማያደርጉት ለምንድነው ብባል ቃሉ መዶሻ ስለሆነ ለመዶሻ ሁለት ባህርይ ስላለው ነው።
   1ኛ ያገነባል
   2ኛ ያፈርሳል....... የመዶሻ ባህርይ ነው።
አንዳንድ ሰዎች ወደ መዳን ቀርበው ቤተክርስቲያን ገብተው እንደገና የሚወጡበት ምክንያት የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው በእርሱ ማደግ ስለከበዳቸው ፤ሰምተውም ስለማያድጉ የቃሉ መዶሻ እንደገና ያፈርሳቸዋል።

ይህ ወንጌል ደግሞ "እሽ" ለሚል ሰው በረከትን ይሰጣል /ይከፍላል/ እምብ ለሚል ግን ሰይፍን ይሰጣል። ይህ ወንጌል ደግሞ እሺ ለሚል ሰው ይከፍልለታል፤ እምብ የሚለውን ያስከፍላል።

በረከቱ፦ ለአንተ የሚከፈል ነው
ሰይፉ፦ አንተ የሚትከፍለው ዋጋ ነው
ይህ ማለት የእግዚአብሔር ቃል በአንተ ላይ ወርዶ ፍሬ ሳያፈራ በአየር ላይ ከተበተነ ዋጋ ያስከፍላል፤ ሰሚው ይከፍላል። ስለዚህ እግዚአብሔር ነገ #የተጠራቀመ_ክፍያ እንዳያስከፍለን ማረን እያልን መጸለይና ለቃሉ መታዘዝ ግድ ይለናል።

🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂🤷‍♀

      🌻የዕለቱን ትምህርት በየማለዳ🌻
        🌸የጉዞአችንን ስንቅ ከማራናታ🌸

                    🌼መልካም ቀን!!!🌼
Any Comment @maranathawoch
Inbox comment @Taddyapostolic

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH

3k 0 19 6 34

የማለዳ ትህምርት
ቀን 01/03/2017 ዓ.ም

አርዕስት፦ከመሥዋዕት በፊት የሚትታይ ራስን አዘጋጅ!!!

ውድ የማራናታ ቻናል ተከታዮች እንደምን ሰነበታችሁ የምህረቱ ባለጠጋ አምላክ ከፊቱ እኛን ሳያጣፋ ይህችን ቀን በምህረቱ ባርኮ የሰጠን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላዓለም ይባርክ እያልኩ ወደ ዛሬ መልእክት አልፋለሁ #ከመሥዋዕት በፊት የሚትታይ ራስን አዘጋጅ በሚል ርዕስ እንማራለን።

እውነት ነው በዚህ ጊዜ በተለምዶ ከእኔም ጭምር በመሥዋዕቱ ላይ ብቻ ነው ትኩርት የምናደርገው? እንጂ መሥዋዕት አቅራቢው ላይ ትኩርት ስሰጥ አይታይም እንደ ምክንያት የሚታየው ውስጡ ለሚፈልገው እግዚአብሔር ውስጡ ሳንሰጥ በውጭ ገጽታ ላይ ትኩርት በሚያደርጉ ሰዎችን ለማሳየት በውጫዊ ገጽታ ላይ ብቻ ነው የሚንሸንቀረቀርው።

እግዚአብሔር ሰው የሚያበት አካሉን አያይም እግዚአብሔር የልብ አምላክ ነው። በዚህ ዘመን ደግሞ ውስጡ ወይም የልብ ንጽሕና ለሚያይ አምላክ የሚናሳየው የውጫዊ እንቅስቃሴ ነው። የለበሰነው ያማረ ልብስን፣የፀጉራችን አሰተካከልን እንድሁም የፊታችን ገጽታ ማማሩን ለማሳየት እንሞክራለን።

ቄሱ የሚያዬ እውነት ነው ውጫዊ ገጽታ ነው አንቺ ቤተክርስቲያን በሳምንት ሦስት ጊዜ የምትመጪውን፣ በኳይር አግልግሎት ማይክ የምትይዠውን፣ ዜማ ያማረውን፣....ወዘተ። ወንድሜም ቢሆን በዚህ ተግባሮች ላይ ስሳተፍ ያየ ቄሱ አቤት፣ አቤት ወንድም እጌለ አግልግሎት በጎነ ሆኖ እንዴት እየረደኝ እንደሆነ? እንዴት እያገለገልች እንደሆነች ብሎ ያወራ ይሆናል! ነገር ግን ልቡን በሚያይ በእግዚአብሔር ፊት ያንተ እንቅስቃሴ እንዴት ነው? ለመሥዋዕትስ? ምን ያህል ዝግጁ ነህ/ሽ?

እኔ በአይነ የማየውንና የሚሰማውን በእርግጥ በዚህ መናገር ባይጠበቅብኝ እውነት ነው የምለው ትናንት አልጋ ቤት አድሮ በነጋታው ቅዱሱን የእግዚአብሔርን ኤፉድ የለበሱ ሰዎችን እውነት አውቃለሁ። ማረኝ።

1ኛ ሳሙኤል 16፥6፦እንዲህም ሆነ፤ በመጡ ጊዜ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ፦ በእውነት እግዚአብሔር የሚቀባው በፊቱ ነው አለ።
7፦እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፦ ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ፤ ሰው እንዲያይ እግዚአብሔር አያይምና ናቅሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል አለው።

ትኩርት እንድትሰጡ የሚፈልገው በዚህ ክፍል በቁጥር 7ላይ ያለው ነው። ፊቱን የቁመቱንም ዘለግታ አትይ ካለ በኋ ሰው እንደያይ እግዚአበሔር አያይምና ይላል። ታዲያ በመሠዊያው ድምጽ ዜማ፣ ያልኖረከውንና ያለተረዳውን የእግዚአብሔርን በማስተማር ይሁን? በየሳምንቱ ሳናታክት ወደ ቤተክርስቲያን መሄዳችን ይሁን ወይ? መሥዋዕታችንና እኛን የሚቀበለን እግዚአብሔር? አይደለም።

ለዚህ ቀለል ያለ መልስ በመንፈሳዊ ሕይወት ላይ ምን አይነት ሰው መሆን ነው የምትፈልገው? ያ የምትሆነው ሰውን ደግሞ ለምን መሆን ፈለከው? በግልጽ ማወቅ አሁን በመንፈሳዊ ሕይወት ላይ በመጥፎ ደረጃ ላይ ያለህ ከሆነ በቤተክርስቲያን የምትሆነውን አንተን በውጪው ሕይወት ላይ ለማሰቀጠል የምትፈልግ ከሆንህ? አሁን ያለህበትን የመንፈሳዊ ሕይወትን እወቀው ከዛ ወደየት መሄድ እንዳለብህ ወስን ከዛ በጉዙ ላይ የሚደረጉ የጉዙ ሂደቶቹን አጥና....በቃ። በተግባር ወይም በአክሽን ላይ ስትቆይ ውጤት እያደገ እያሳዬ ይሄዳል።

እባካችሁ ውድ ቅዱሳን ወንድሞች እና እህቶች የእግዚአብሔር እይታ እኔና እናንተ ማየት ከሚንችለው ባሻገር ነው። ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሉን እየበላችሁ ለራሳችሁም ለእግዚአብሔር ታማኝ አገልጋይ ሁን!!

ዕብራውያን 4፥11፦እንግዲህ እንደዚያ እንደ አለመታዘዝ ምሳሌ ማንም እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንትጋ።
12፦የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤
13፦እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።
14፦እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ።

እግዚአብሔር የልመናችን ድምጽ ይስማልን አሜን!!!

🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂ኸኀ🤷‍♀

      🌻የዕለቱን ትምህርት በየማለዳ🌻
        🌸የጉዞአችንን ስንቅ ከማራናታ🌸

                    🌼መልካም ቀን!!!🌼
Any Comment @maranathawoch

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH


የማለዳ ትህምርት
ቀን 30/02/2017 ዓ.ም

አርዕስት፦ ለእግዚአብሔር ክብር ተፈጠረክ

ውድ የማራናታ ቻናል ተከታዮች እንደምን ሰነበታችሁ የምህረቱ ባለጠጋ አምላክ ከፊቱ እኛን ሳያጣፋ ይህችን ቀን በምህረቱ ባርኮ የሰጠን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላዓለም ይባርክ እያልኩ ወደ ዛሬ መልእክት አልፋለሁ የዛሬ ርዕስ፦ለእግዚአብሔር ክብር ተፈጠረክ በሚል ርዕስ እንማራለን።

ኤር 1: 5፦በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።

ወደ ኤርምያስ ይህ ቃል ስመጣ በጣም ሕፃን በነበረበት ጊዜ ላይ ነው። ሰው ልጁን እግዚአብሔር ከምን አይነት መልክ ጋር ይፍጠር አጭር ረጅም ቢሆንም ጥቁር ነጭ ቢሆንም በቃ እንዴትም አድረጎ ይፍጠር የእግዚአበሔር አለማ ሰው ልጁን ለክብሩ ብሎ ነው የፈጠረው። ሰዎች የተፈጠሩት ለዚህ ሆኖ ሳለ የራሳቸውን ክብር በመፈለግ የእግዚአብሔርን ክብር በማሣነስ እየኖሩ ነው።አንተ ወንድም አንቺ እህቴ አሁን ያለው የኑሮ ደረጃ ምንም ይሁን ምን ከዘመናት በፊት ይህ ሕይወት ላንተ አቅደዋል።

አንተ/ቺ የምትኖረው ሕይወትን አትወደውም ወይም ትወዳው ይሆናል ዛሬ አንተ የምትኖረው ሕይወት አንተን ልደንቅ ወይም ልከፋ ይችል ይሆናል እግዚአብሔርን ግን አለደነቀውም እንድሁም አሳዳግን ሁላ አጥተህ ልትኖር ትችል ይሆናል... እግዚአብሔር ግን ያውቃል።

አንተን ለክብሩ ስሰራ እነዚህን አካሎችን የማጣመር ተግባር የእግዚአብሔር ነበር። ያለ እርሱ አንዳች ነገር በዚህ ምድር አይሆንም። እሱ ሁን ብሎ ያልፈቀደው ነገር በሙሉ...አይከናወንም።

መዝ 139: 15፦እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ፥ አካሌም በምድር ታች በተሠራ ጊዜ፥ አጥንቶቼ ከአንተ አልተሰወሩም።

እዚህ ዘማሪው ምን ይላል እኔ በስውር በተሠራሁ ጊዜ በዛ በጨለማ ላይ እንዴት አድረጎ አጥንቶቹን እንደገጣጠመ ማንም የሚያወቅ የለም። በጣም እኔን ከሚያሳዝነኝ ነገሮች አንዱ ምንድ ነው? የሆነ በጣም ጉልበት ኃይል ያለን ሰዎች መሠለን ራሳችን ማቆለላችንኮ ነው የሚገርመኝ። አንድን ዕቃ የፈጠረ/ያፈበረክ ሰው ስለዕቃ ጥቅሙን አግልግሎቱን የሚገልጽ ነገር ከዕቃው ጋር ያሰቀምጣል። ይህንን ያየ ግለሰቡ ዕቃውን እንዴት መጠቀም እንዳለበት ስላየ በአግባቡ ይጠቀማል። ካለሆነ የዕቃውን አግልግሎቱን ለማወቅ ሠሪውን መጠየቅ ጥሩ አማራጭ ነው ልክ እንደዛ...አንተን የፈጠረ አካሌ አለ እሱን አካል በደንብ ማወቅ ለክብሩ መፍጠርን በግልጽ ይናገራል።

በትንሹ ለማንም ሰው ልጅ መነሻ አለው መደረሻ አለው በመሀከል ያለውን ጉዙ ደግሞ ለምን እንደሆነ ሳንረዳ በተለያዬ ነገሮች ላይ እናሳልፋለን። ስለዚህ ከመደራሸው በፊት የነበረውን ሕይወት አሁን የፈጠረህን በማክበር አሳልፍ። ሁላችንም ኢየሱስ ይረዳን አሜን።

እግዚአብሔር የልመናችን ድምጽ ይስማልን አሜን!!!

🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂ኸኀ🤷‍♀

      🌻የዕለቱን ትምህርት በየማለዳ🌻
        🌸የጉዞአችንን ስንቅ ከማራናታ🌸

                    🌼መልካም ቀን!!!🌼
Any Comment @maranathawoch

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH




የማለዳ ትህምርት
ቀን 29/02/2017 ዓ.ም

አርዕስት፦ በፊቴ ተመላለስ

ውድ የማራናታ ቻናል ተከታዮች እንደምን ሰነበታችሁ የምህረቱ ባለጠጋ አምላክ ከፊቱ እኛን ሳያጣፋ ይህችን ቀን በምህረቱ ባርኮ የሰጠን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላዓለም ይባርክ እያልኩ ወደ ዛሬ መልእክት አልፋለሁ የዛሬ ርዕስ፦ በፊቴ ተመላለስ በሚል አርዕስት እናገራለሁ።

በፊቴ ተመላለስ ማለት ውድ ቅዱሳን ወንድሞች ምን ማለት ይሁን? ማን ያውቃል ያማረ፣ያጌጠ ውድ ዋጋ የሚወስድ ልብስ ለብሰን በየሳምንቱ ወደ ቤተክርስቲያን መምጣት ይሁን? ምን ይሁን? እስቲ ከቃሉ እንመለከት

መጽሐፍ ቅዱስ ዘፍ 17፥1፦ ጀምርን ስናነብ አብራምም የዘጠና ዘጠኝ አመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና እኔ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመላለስ ፍጹምም ሁን ቃልኪዳንን ካንተ ጋር አደረጋለሁ አለው።

ከሁሉ በማሳቀደም እዚህ ክፍል ላይ እግዚአብሔር ትኩርት የሰጠባቸው አንኩር ነጥቦች አንዱ በፊቴ ተመላለስ የሚል ነው። ይህን መልእክት እግዚአብሔር ወደ ልቤ ስያመጣ አንድ ወር አከባቢ ሆኖኛል። ለምንድ ነው አብራምን እግዚአብሔር በፊቴ ተመላለስ ያለው? ይህን ቃል እግዚአብሔር ከአፉ እሰከሚያወጣበት ደቂቃ ድርስ የአብራም ጉዙ ምን ይመስል ነበር? እንድስ እንድል እግዚአብሔርን ያነሳሰው ምክንያት ምን ይሁን? መቺስ ለአንድ ነገር መነሻን ከመፈለግ ውጭ ማግኘት ይቻላል ወይ?

ስለዚህ ለአብራም ኢየሱስ ይህን ከመናገሩ በፊት የአብራም ጉዙ ፍጹም ያልነበር፣እግዚአብሔር ለቃልኪዳኑ ብቻ የተሸከመው ሰው ነው። አንዴ ግብጽ ይወረዳል በሄደበት በዛ ሀገር ላይ ደግሞ ሚስቱውን እህቴ ነች እያሌ የሚስቱን ምክር በመስማት የማይሆን ድርጊት እየፀጸመ የነበረ ነው።

ግን እግዚአብሔር መጣና መተላለፎችን አብዝታሃል በፊቴ ተመላለስ ፍጹምም ሁን አለው።በዚህ ሰዓት ነው የእውነት አብራም ልብ የገዘው።

ለምን እኛን እግዚአብሔር በፊቱ እንድመላለስ ይፈልግናል? ስንፈጥር ለእርሱ ክብር የተፈጠረን ስለሆነን ነው። ብዙ ጊዜ ጌጠኛ ልብስ ለብሰን ቤተክርስቲያን መምጣታችን ይህኔ በእግዚአብሔር ፊት የተመላለሰን ልያመስለን ይችላል ግን እሱ በፍጹም እንዳያደርገን እናውቃለን ግን በፊቱ የመመላለስ ኃይል አንሞላም።

በጸድቅ መንገድ በፊቱ እንድንመላለስ ይፈልግናል በአግልግሎቱ ዘረፍ በፊቱ ልንመላለስ ይፈልግናል ሁል ጊዜ ለእርሱ ክብር እየሰጠን ለእርሱ ክብር እየሰጠን እንድንኖር ይፈልግናል ግን እንሰጣለን ወይ ?አንሰጥም። ለምን በፊቱ መመላለስ በጣም ከባድ ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ ስለሆነ!!

ከዘመናት በፊትም የእግዚአብሔር ጩኸት አንድ ነው አሁንም ያው ነው እሱም የሰው ልጅ በፊቴ ተመላለስ የሚል ነው በእርሱ ፊት በመመላለስ የምናገኘቸው በርከቶች አያሌ ናቸው ነገር ግን አዕምሩችን በጊዜያዊና በአለማዊ ነገር ማለትም ቶሎ በምከናወኑ ነገር ላይ ግን የዘለቀታ ጉዙ በሌሉ ነገር ላይ አይናችን እንጥላለን በዚህም ምክንያት ብዙ የሕይወታችን በረከቶችን ርቆብናል።

ስለዚህ እንመለስ ወደ እግዚአብሔር ፊት እሱ ነው የሚሻለን በስቆቃ ኤር 5፥20 ላይ በተጻፈው ቃል መሠረት ወደ ራሱ ይመልሰን።

በዚህች አጭር ክፍል ላይ በቀረበው መልእክት ልባችሁን አንጽታችሁ ወደ እግዚአብሔር በፍጹም ልብ እንደምትመለሱ እርግጠኛ ነኝ ቀር ዘመናችን ኢየሱስ ይባርክ መልካም የበርከት ቀን ይሁንላችሁ!!

እግዚአብሔር የልመናችን ድምጽ ይስማልን አሜን!!!

🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂ኸኀ🤷‍♀

      🌻የዕለቱን ትምህርት በየማለዳ🌻
        🌸የጉዞአችንን ስንቅ ከማራናታ🌸

                    🌼መልካም ቀን!!!🌼
Any Comment @maranathawoch

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH


መከባበር

መከባበር ማለት ለሌላው ሰው ያለን ልባዊ የሆነ አክብሮትና መታዘዝ ፣የፍቅር ፍርሃት፣ የምናሳየው ከፍ ያለ ዋጋ ነው።

መከባበር የፍቅር ሌላኛው ገጽታው ነው።


► እርስበርስ መከባበር

   " በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤"
                                      ሮሜ 12 : 10

► እናትና አባትን ማክበር

    " መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ ናት።"
               ኤፌ 6 : 2-3

►  ታላላቅ ሰዎችን ማክበር

   🫵" በሽበታሙ ፊት ተነሣ፥ሽማግሌው ንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። "
               ዘሌዋ 19 : 32

► ባለስልጣናትን ማክበር

 🫵 " ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብ ሔር የተሾሙ ናቸው።"
                    ሮሜ 13 : 1

► አገልጋዮችን ማክበር

    🫵" በመልካም የሚያስተዳድሩ ሽማግሌዎች፥ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚደክሙት፥ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል።"
                               1ጢሞ 5 : 17

► አሰሪዎቻችንን ማክበር

 🫵 " ባሪያዎች ሆይ፥ ለክርስቶስ እንደምትታዘዙ በፍርሃትና በመንቀጥ ቀጥ በልባችሁ ቅንነት በሥጋ ጌቶቻ ችሁ ለሆኑ ታዘዙ፤"
                              ኤፌሶን6 : 5
  🫵"የእግዚአብሔር ስምና ትምህርቱ አንዳይሰደብ፥ ከቀንበር በታች ያሉቱ ባሪያዎች ሁሉ ለገዙአቸው ጌቶች ክብር ሁሉ እንደ ተገባቸው ይቍጠሩአቸው።       
                            1ጢሞ6:1

► የትዳር አጋርን ማክበር

 🫵 "ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ ክርስቶስ ደግሞ የቤተክርስቲ ያን ራስ እንደ ሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደ ሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና። ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምት ገዛ እንዲሁ ሚስቶችደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ።ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተክርስቲያ ንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደ ዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ "
                  ኤፌ5 :22-26

🔘 መከባበር መንፈሳዊ ፣ ሞራላዊ እና ማህበራዊ  እሴት ነው።

🔘 መከባበር የሰላም፣የአንድነትና የመስተጋብር ሁሉ መሰረት ነው።

🔘 መከባበር ከላይ የተሰጠ ትእዛዝም ነው።

🔘 መከባበር ታላቅ ዋጋ አለው።

🔘 መከባበር የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም ነው።

@MARANATHAWOCH


የማለዳ ትህምርት
ቀን 28/02/2017 ዓ.ም

አርዕስት፦ባሰቀመጠበት ስፍራ ላይ እሱን መጠበቅ!!

ውድ የማራናታ ቻናል እና የማለዳ ትምህርት ተከታዮች እንደምን አላችሁ የጌታ ፍቃድ ሆኔና የትናንትናውን በዛሬው ተክቶ የዛሬውን ቀን ባርኮ የሰጠን ኢየሱስ ይመስገን እያልኩኝ ለዛሬ ማለዳ የሚያስፈልገውን ለእኛ አስተካክሎ የቃሉን ግብዣውን የጋበዘ አምላክ ይባርክ እያልኩኝ ለዛሬ ውሎ የሚሆን የእግዚአብሔርን ቃል#ባሰቀመጠበት ስፍራ ላይ እሱን መጠበቅ በሚል ርዕስ እንማራለን

መዝሙር 40፥1፦ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ።
2፦ከጥፋት ጕድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና።

ዕንባቆም 2: 1፦በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፤ የሚናገረኝንም፥ ስለ ክርክሬም የምመልሰውን አውቅ ዘንድ እመለከታለሁ።

ውድ ወንድሞች እህቶቼ በተለያዬ አጋጣሚ ፀሎታችን ለእግዚአብሔር እናደርሳለን ነገር ግን ያ ፀሎት ባሰበነው ወይም በጠበቀነው ልክ ተመልሶልን አናገኝም። አንዳንዴ ብትጠብቅ ብትጠብቅ ብትጠብቅ የለም ምን ሆንኩ እንዴት ነው ፀሎቴ መልስ ያለገኘው ብለን ከራሳችን ጋር እንጋጫለን ደግማ ደግሞ ፀሎት እናደርጋለን በተለያዬ ኮንፈራንሶች ላይ በመንሰበሰብበት ቦታ ላይ የምልጃ ፀሎት ይሁን የምስጋና ፀሎት የመሠዋት ፀሎትንም እንድሁም የስዕለት ፀሎትን እናቀርባለን ግን ከብዙ ጠያቂ ሰዎች መካከል ጥቅቶች መልስ ያገኛሉ ቀረችዎስ ?

ከላይ በኩል ሁለት የእግዚአብሔር ቃል አስቀምጫለሁ አንዴ በትኩርት ብታዩ መልካም ነው የሚመሰለኝ ሁሉቱም የቃሉ ክፍል በመጠበቂያ መቆየት እንዳለበት ይናገራል። ወደ እግዚአብሔር የላከነው ፀሎት ቶሎ መልስ የማንገኘባቸው ምክንያቶች አንዱና ዋነኛው በመጠበቂያ ሆኖ እግዚአበሔርን መጠበቅ ነው። ፀሎት እንደደረገነው በኋላ በዛው ፀሎት መንፈስ ሆነን ለአንድ ሰዓት መቆየት አንችልም።

አንድ ጻፊ ይህንን የእግዚአብሔርን ቃል የደገፈ እና በሕይወቱ ያየውን እንዲህ ብሎ ተናገረ ሰዎች በአንድ ሀሳብ ላይ ለ15ስኳንድ መቆየት የምችል ከሆነ ያንን ጥያቄ ከእግዚአብሔር ሳይቀበለ አይቀረም በሏዋል።ይህ እውነት ነው ዘማሪው ዳዊትም ቆይቼ የእግዚአበሔር ደጄ ጠናሁት እርሱም ዘንበል አለልኝ ያለው በዚህ መንገድ እንደሆነ በግልጽ መረዳት እንችላለን።

መጀመሪያ ፀሎትን ባደረሰክበት ቦታ ላይ ቆይተህ አለመቀበል የአጽናፊ ገዥ የሆነው የእግዚአብሔርን ኃይል እንዳናምን ልያደረገን ይችላል። ምንም እንኳን በለስ ባያፈራ ይላል ወንድማችን ዕንባቆም እኔ በመጠበቂያዬ ላይ አንተን እጠብቃለሁ ብሉዋል። ይህ ለጠየቀነው ጥያቄ ባለንበት ጉዙ ላይ የቆየ ቢመሰልም ግን በቦታ ሆነን ስንጠበቅው እንድሁም በለስ ያላፈራ ቢመሠልም፣ከወይን ሀረገ ፍሬ ባይገኝም....ወዘተ። እንዲህ ያለ የደረቀ ሕይወት አሰመሠሎ የሚይሳየው የሰይጣን ንግግር ስለሆነ ሳንሰማ ወደፊት መቀጠል መቻል ነው።

የፀሎታችን መልስ ቶሎ እንዳይመልስ ከሚያደረግባቸው ምክንያቶች፦
1ኛ፦በቦታ አለመጠበቅ
2ኛ፦ትዕግስት ማጣት
3ኛ፦የጠየቀነው ነገር የእውነት አሰፈላጊ እንደሆነ አለማመኑ
4ኛ፦የሚያሰከፈለው ዋጋ በመከፈል ወይም በፅናት አለመቀጠል።

እግዚአብሔር የልመናችን ድምጽ ይስማልን አሜን!!!

🤷‍♂🤷‍♀በጸሎት ወጥታችሁ በምስጋና ግቡ🤷‍♂ኸኀ🤷‍♀

      🌻የዕለቱን ትምህርት በየማለዳ🌻
        🌸የጉዞአችንን ስንቅ ከማራናታ🌸

                    🌼መልካም ቀን!!!🌼
Any Comment @maranathawoch

@MARANATHAWOCH
@MARANATHAWOCH

Показано 20 последних публикаций.