የሚመሰረተው ካውንስል ወርቃማ እድል ነው- ኢዮሲያስ ኢዩኤል
=========================
አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2012 ዓም (ክርስቲያን ፖስት)
የሀገራችን ጠቅላይ ሚንስተር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ሰኔ 13፣ 2011 ዓ.ም አራት መቶ ገደማ ለሚያህሉ የወንጌላዊያን ቤተ እምነቶችና አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት መሪዎች የስብሰባ ጥሪ በማድረግ በቤተ-መግስታቸው የተገኙትን ባለድርሻ አካላት ማወያየታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ይህንንም
ውይይት ተከትሎ 15 አባላት ያሉት ቡድን ተዋቅሮ የስራ ድርሻ እንደ ተሰጠው አንዘነጋም፡፡
እንግዲህ በዚያን ወቅት እኔንም ጨምሮ ብዙዎቻችን የተለያዩ አስተያየቶችን ስንሰጥ ነበር፡፡ በወቅቱ ይሰነዘሩ ከነበሩ አስተያየቶች መካከል፡- ‹መንግስት በቤተ-ክርስቲያን ጉዳይ ጠልቃ መግባት አይችልም፡፡› ፣ ‹ቤተ ክርስቲያንን የሚመራት የመንግስት ባለስልጣን ሊሆን አይገባም፡፡ ‹የወንጌላዊያን አማኞች ጉዳይ ከኦርቶዶክስና ከእስልምና ይለያል፡፡› ‹በአስተምህሮና በልምምድ ከማይመስሉን ሰዎች ጋር ህብረትን አልያም አንድነትን እናደርግ ዘንድ ምንም አይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ የለንም፡፡› የሚሉት የማይዘነጉ አስተያየቶች ናቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል የሰው ልብ እጅግ ክፉ ነውና እነዚህን አስተያየቶች የሰነዘሩ ግለሰቦች ከምን የመነሻ ሃሳብ (Motive)
ተነስተው እነዚህን አስተያየቶች እንደ ሰጡ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም በአስተያየቶቹ የተንጸባረቁት ስጋቶች በእርግጥም ስጋቶቻችን በመሆናቸው
ጆሮዋችንን ልንነፍጋቸው አልያም ቸል ልንላቸው አይገባም ባይ ነኝ፡፡
========================
#ዝርዝር_ሃሳብ
ህንጸት የሚባል የመረጃ ምንጭ እንደ ዘገበው ከሆነ 15 አባላት ያሉት ቡድን ይፋ ያደረገው የጥናት ምክረ-ሃሳብ፡- ‹በመርህ› ዙሪያ የተሰባሰበ፣ ሁሉን አቃፊ ‹መማክርት› አልያም ‹ፌደሬሽን› መመስረት የሚል ነው፡፡ እንደ እኔ እምነት 15 አባላት ያሉት ያ ቡድን የተመሰረተለት ዓላማ ምን እንደ ነበር በወቅቱ
ለብዙዎቻችን ግልጽ ነበር ብዬ አላማንም፡፡ መረጃ በተገቢው ጊዜ ከአሻሚነት በጸዳ መልኩ ይፋ ማድረግ መቻል ብዙዎችን ከግራ መጋባት፣ ከተሳሳተ አቁዋም አልያም ከሀሰት ወሬ ለመታደግ አይነተኛ መፍትሄ ነው፡፡
የክርስቲያን አንድነት አልያም ህብረት መቆሚያ የክርስትና መሰረታዊ አስተምህሮ የመሆኑ ጉዳይ የሚያከራክር አይደለም፡፡ መሰረታዊ የክርስትና አስተምህሮ የክርስቲያናዊ አንድነትና ህብረት መሰረት ነው፡፡ አንድነት አልያም ህብረት ያለ መሰረታዊ የክርስትና አስተምህሮ አይታሰብም ሊታሰብም አይችልም፡፡ ይህ ጨርሶ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ እኔ እንደሚገባኝ 15 አባላት ያሉት ቡድን የመመስረቱ ዓብይ ዓላማ ‹የጋራ በሚደርጉ ጉዳዮች› ዙሪያ ጥናት አድረጎ የመፍትሄ ሃሳብ ማቅረብ እንጂ ሀሰተኛ አስተምህሮና ልምምድ ካላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ጋር ከላይ የገለጽኩትን አይነት ክርስቲያናዊ ህብረት አልያም አንድነት መፍጠር አይደለም፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከላይ እንደ ገለጽኩት ከመሰረታዊ የክርስትና አስተምህሮ ጋር የሚጋጭ ሀሰተኛ ትምህርትና ልምምድ ካላቸው ግለሰቦች አልያም ቡድኖች ጋር ክርስቲያናዊ ህብረት አልያም አንድነት መመስረት አይቻልምና ነው፡፡ የቡድኑ የጥናት ምክረ ሃሳብ በግልጽ እንደሚያስቀምጠው ከሆነ የጥናቱ ዓላማ ‹የጋራ በሚያደርጉ
ጉዳዮች› ዙሪያ ‹በመርህ› የተሰባሰበ ‹መማክርት አልያም ፌደሬሽን› መመስረት ነው፡፡ ይህ በጣም ወሳኝ ሃሳብ ነው፡፡ ክርስቲያን ከማያምን ግለሰብ አልያም ቡድን ጋር ክርስቲያናዊ ህብረት አልያም አንድነት ማድረግ አይችልም፡፡ ነገር ግን ክርስቲያናዊ ህብረት አልያም አንድነት ማድረግ አይችልም ማለት ግን የጋራ በሚያደርጉ ጉዳዮች ዙሪያ ከማያምኑ ግለሰቦች አልያም ቡድኖች ጋር በመርህ ደረጃ አይሰባሰብም ማለት አይደለም፡፡
ለምሳሌ አንድ ማሳያ ላንሳ፡- በሀገራችን ኢትዮጵያ ‹የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቁዋማት ማህበር› የሚባል አለ፡፡ ይህ ማህበር ክርስቲያናዊ ህብረት አልያም አንድነት አይደለም፡፡ ነገር ግን በዚህ ማህበር ውስጥ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ-ክርስቲያናት ህብረትን ጨምሮ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ከእስልምናና ከኦርቶዶክስ የሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን የጋራ በሚያደርጉ ጉዳዮች ዙሪያ ማለትም ሰላምንና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች የጋራ ማህበር ፈጥረው መስራት ከጀመሩ ብዙ አመታት አልፈዋል፡፡
ለምሳሌ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት የእስልምናና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የምንሰብከውን ወንጌል ይክዳሉና ከእነዚህ ከሃዲያን
ጋር በአንድ ማህበር አልሰባሰብም ሲል ሰምተን አናውቅም፡፡ ይህ ምሳሌ በግልጽ የሚያስረዳን ነገር ቢኖር በመሰረታዊ የክርስትና አስተምህሮ የሚያምን ክርስቲያን ከሌሎች መሰል ክርስቲያኖች ጋር ክርስቲያናዊ ህብረትና አንድነት እያደረገ ሳለ ከማያመኑ ጋር የጋራ በሚያደርጉ ጉዳዮች ዙሪያ መሰባሰብ እንደሚችል ነው፡፡ እንደዚህ አይነት መሰል አብነቶችን ማንሳት ይቻላል፡፡
የእኔ ጥያቄ ወዲህ ነው፡- ክርስቲያናዊ ህብረት አልያም አንድነት ነው አይበሉን እንጂ ከእስልምናና ከኦርቶዶክስ መሪዎች ጋር የጋራ በሚደርጉ ጉዳዮች ዙሪያ ማህበር ፈጥረን መስራት እስከቻልን ድረስ በ15ቱ አባላት በቀረበው ምክረ ሃሳብ መሰረት የጋራ በሚያደርጉን ጉዳዮች ዙሪያ መርህን መሰረት ባደረገ አግባብ ተሰባስብን በመማክርት አልያም ፌደሬሽንመደራጀታችን ምኑ ላይ ነው ችግሩ?
ይመስረት የተባለው መማክርት አልያም ፌደሬሽን ክርስቲያናዊ ህብረት አልያም አንድነት እስካልሆነ ድረስ በመርህ ደረጃ ተሰባስብን የመደራጀታችን አጋጣሚ ኦርቶዶክስና እስልማና ያገኙትን ህጋዊ ሰውነት እንድንጎናጸፍ እድል ከመስጠቱ ባሻገር በመሰረታዊ የክርስትና አስተምህሮ ዙሪያ በመካከላችን የምንመለከተውን መለያየት በቅርበት ለመይይት የሚያስችል ወርቃማ አጋጣሚ (Golden opportunity) ነው ባይ ነኝ፡፡ የሀገራችን የወንጌላዊያን ክርስትና ትልቁ ተግዳሮት ተቀራርቦ በጋራ ማውራት ያለመቻል ይመስለኛል፡፡ መናፍቅ ስለመሆናቸው የሚያስተምሩትን ትምህርትና ልምምድ ጠቅሰንና ተንትነን በማቅረብ ለመተቸት የተካንን ብንሆንም መናፍቃዊ ትምህርት
ያስተምሀራል እንዲሁም መናፍቃዊ ልምምድ ይታይበታል ከምንለው ግለሰብ
ጋር ተቀራርብን ስንወያይና ስንዋቀስ አይታይም፡፡ በትህትና መንፈስ ቀርብን
ለመወያየት አልወደድንም እንጂ መናፍቅ ነው የምንለው ስንቱ በመንፍቅና ትምህርትና ልምምድ የመገኘቱ ምክንያት ባለማወቁ አልያም ታማኝ መጋቢ ከማጣጥ የመነጨ ሊሆን እንደሚችል መገመት ተስኖናል፡፡ ይህ ማለት ግን ሁሉም መናፍቅ ስላላወቀ አልያም ታማኝ መጋቢ ስላጣነው የመነፈቀው ማለት ግን አይደለም፡፡ የእኛ ትልቁ ደዌ ይህንንም ለመለየት ያስችለን ዘንድ በትህትና ተቀራርብን ለመወያየት አለመፍቀዳችን ይመስለኛል፡፡ በዚህ ደዌ ሁላችንም ተጠቅተናል ብል ግነት አይሆንም፡፡ የአብዛኞቻችን የእቅበተ-እምነት
አገልግሎት ትህትና ይጎድለዋል፡፡ ትህትና የአማኝ ብቻ ሳይሆን የመልካም መጋቢ ልብ መገለጫ ባህሪ ነው፡፡ ትህትና ከሌለን መጋቢያዊ ልብ አይኖረንም፡፡ መጋቢያዊ ልብ ከሌለን ደግሞ ቀርብን ያልመከርነውንና ያልሞገትነውን ከሩቅ ሆነን መናፍቅ ለማለት አይከብደንም፡፡ በዚህ ደግሞ ሁላችንም ተወቃሽ ነን፡፡ በእቅበተ-እምነት ፍል ፍላጎቶቻችን ከሰራነው መልካም ስራ ይልቅ ያፈረስነው ብዙ ነውና ልዑል አምላክ ምህረት ያድረግልን ለማለት እወዳለሁ፡፡ ለማውገዝ እንጂ ቀርቦ ለመወያየት የልብ ዝግጅት ያለን አይመስለኝም፡፡ ከውግዘት በፊት በቅርበት