የመካከለኛው ክፍለዘመን (Medieval century) የአርየንታል ኦርቶዶክስ ሊቃውንት እና ይህ ፍኖት አሁን ላይ ያለው መልክ ምን ይመስላል?
ይሄ ጊዜ ከአምስተኛው ክፍለዘመን በኋላ ያሉትን ጊዜያት ሲያጠቃልል አውሮጳውያን ዘመኑን ዘመነ-ጨለማ (Dark age) እያሉ ይጠሩታል።
ምንአልባት ለአውሮጳ ቢሆን እንጂ ጊዜው ሌላውን ዓለም ጨለማ የማያስብልም ሊሆን ይችላል።
በዚህ ጊዜ በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ የዓለማችን ክፍል በነገረ-መለኮት፣በፍልስፍና፣በፊዚክስ፣በሕክምና፣በፖለቲካ፣በነገረ-ከዋክብት እንዲሁም በሌሎች የትምህርት አይነቶች እና እውቀቶች ያሸበረቀበት ጊዜ ነበር!
በዚህ የዓለማችን ክፍል በሲሪያክ በአረበኛ በፐርሽያን እና መሰል ቋንቋዎች የተጻፉ መጽሐፍት ከዚህ ዘመን በኋላ ለመጡት የዘመነ-ሕዳሴ (ዘመነ-ትንሣኤ) (Renaissance) የአውሮጳ የፍልስፍና፣የሕክምና እና የሳይንስ እውቀት ላይ የድርሻቸውን አስተዋጽኦ አበርክተዋል በመካከለኛው ክፍለዘመን የነበሩ የመካከለኛው ምስራቅ ሊቃውንትም በዚያው በዘመነ-ህዳሴ በነበሩ እና ቀጥሎ በመጣው በዘመነ-አብርሆት (Enlightenment) ሙሕራን ሊቃውንት ላይ ተጽእኖ ፈጣሪነታቸው በቀላሉ የሚታለፍም አይደለም!
በዚያ ዘመን የነበሩ ክርስቲያን ሊቃውንት ውስጥ (የሶርያ ያዕቆባዊት ቤተክርስቲያን ምእመናን የኬልቄዶናውያንን ክርስቲያኖች እና የአሴሪያን ምስራቃዊት ቤተክርስቲያን (ንስጥሮሳውያን ክርስቲያኖችንን)ያጠቃልላል።
ቢሆንም እኛ የምንጠቅሳቸው ያዕቆባውያን ክርስቲያኖችን ነው።) ፍልስፍናን በአረቡ ዓለም ያስተዋወቁ እና እንዲሁም ሶርያውያን ክርስቲያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ከመካከለኛው ምስራቅ ሕዝቦች ውስጥ የአርስጣጣሊስን(Aristotle) የፍልስፍና መጽሐፍት ከግርክ ቋንቋ ወደራሳቸው ሲሪያክ ቋንቋ ተርጉመው ለሌለው ዓለም የተረፉ እንደሆኑ ይነገራል።
በተለይም ለአረቡ የእስልምና ዓለም ፍልስፍና ፈለጋቸውን አኑረዋል ለዚህም በኤዴሳ የነበረችው ትምህርት ቤት አስተዋጽኦ ሲኖራት በኋላም የእነ ዮሐንስ ተአቃቢ (John of philoponus) ቅዱስ ያዕቆብ ዘኤዴሳ፣ቅዱስ ጊዮርጊስ ዘአረቢያ እና መሰል ክርስቲያን ሊቃውት በአርስጣጣሊስ ላይ የሰሩት የትርጓሜ(Commentary) ሥራዎች አስተዋጽኦ ቀላል አልነበረም ሌሎች ክርስቲያን ፈላስፎችን ለመጥቀስ ያህልም ቅዱስ ዘካርያስ የህያ እብን አዳይ፣ቅዱስ ሙሴ ባርኬፋ፣የህያ እብን ጃሪር፣እብን ዙራ እንዲሁም ቅዱስ ጎርጎርዮስ ባር ሂብራዎስ አቡ ኣል-ፈረጅን እና ሌሎች ፍልሱፋንን መጥቀስ ይቻላል።
እኒህ ሊቃውንት ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ባለብዙ እውቀት (Polymath) መሆናቸው ነው።
ማለትም የፍልስፍና ብቻ ሳይሆን የነገረ-መለኮት፣የፊዚክስ ፣የኬሚስትሪ የነገረ-ከዋክብት፣የሕክምና እና መሰል እውቀቶች ባለቤት መሆናቸው ነው።
በዚህም ምክንያት የጻፏቸው መጽሐፍት ተተርጉመው ከኋላቸው ለመጡት እና በዘመናቸው ለነበሩት ሌሎች ሊቃውንት በተለይም ለአረቡ የእስልምና ዓለም አሻራቸውን ትተዋል።
ከእስልምናውም ዓለም ፍልሱፋን ውስጥ ደግሞ
ኣል-ኪንዲን፣ኣል-ፈራቢ፣አቡ ሲና፣እብን ረሺድ (አቬሮስ)፣ኣል-ገዛሊ እና እብን ቱፋይን የመሳሰሉ አይከን ሊቃውንትን መጥቀስ ይቻላል።
በዚህ ዘመን በርካታ የአረብ እና የሶርያ ክርስቲያን የነገረ-መለኮት ሊቃውንት ተነስተዋል አጃኢብ የሚያሰኙ ጽሑፋት ተጽፈዋል ከቅዱስ ሳዊሮስ እስከ አቡ ኣል-ፈረጅ ድረስ ብዙ አጃኢብ የሚያሰኙ ሊቃውንት ተነስተዋል በዚህ ዘመን የተነሱ የነገረ-መለኮት ሊቃውንት ባለብዙ እውቀት ስለሆነ አብዛኞቹ ፍልሱፋንም ጭምር ናቸው።
ከእነርሱም ውስጥ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ
ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ፣ቅዱስ ፈሎክሲኖስ ዘማንቡግ፣ዘካሪያስ Rhetorician፣ቅዱስ ያዕቆብ ዘኤዴሳ፣ቅዱስ ጊዮርጊስ ዘአረቢያ፣፣ቅዱስ ሀቢብ አቡ ራኢጣ ዘካርያስ የህያ እብን አዳይ፣ቅዱስ ዮሐንስ ዘዳራ
ዲዮናስዮስ ባር ሳሊቢ፣ሙሴ ባርኬፋ፣ቅዱስ ኪራኮስ ዘተክሪት፣ቅዱስ ጎርጎርዮስ ባር ሂብራዎስ አቡ ኣል-ፈረጅ ን ከሶርያ ስንጠቅስ ቅዱስ ሳዊሮስ አል አሽሙኒን፣እብን ኣል -አሳል፣
ቡሎስ(ጳውሎስ ማለት ነው በአረብኛ) ኣል-ቡሺ
እብን ከባርን ደግሞ ከግብጽ የአረቡ ክፍል መጥቀስ እንችላለን።
ከአርመን ክርስቲያኖች ደግሞ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘናሬክን እንዲሁም አርመንያዊው ፍልሱፍ ቶማስ አኩይናስ የሚባለውን ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘታቴቭን ማንሳት ይቻላል።
ይህን ሁሉ ማንሳት የፈለግኹት ምንያህል ቤተክርስቲያናችን በመካከለኛው ክፍለዘመን የነበሯትን ሊቃውንት ለማስታወስ እና ለማሳወቅም ጭምር ነው።
ባለንበት ዘመን የምስራቅ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት Neo patristic የሚባል እንቅስቃሴ ያመጡ ሲሆን በዚህም በመካከለኛው ክፍለዘመን የነበሯቸውን ሊቃውንቶቻቸውን እንዲታወቁ አድርገዋል በተይም ሊዮንጢየስ ዘበራንጥያን፣ሊዮንጥየስ ዘእየሩሳሌምን፣መክሲሞስ ናዛዜን፣ዮሐንስ ዘደማስቆን፣ስምኦን ሐዲስ ነባቤ መለኮትን፣ ፎጢየስ ዘቁስጥንጥንያን እንዲሁም ጎርጎርዮስ ፓላማስን እና መሰል ሊቃውንቶቻቸውን በመጽሐፍቶቻቸው በመጠቀም አስተምህሮዎቻቸውን Develop ያደረጉ ሲሆን ወደኛ ቤተክርስቲያን ስንመለስ ግን በዚህ ላይ ትልቅ ክፍተት እመለከታለሁ እንዳውም እነ ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያን እና መሰል ቤተኛ ሊቃውንቶቻችንን ተጠቅመን አስተምህሮዎቻችንን Develop ማድረግ ሲገባን የኛን አባቶች ገሸሽ አድርገን ወደ እነ ዮሐንስ ዘደማስቆ እና ኬልቄዶናውያን አበው መቀላወጥ ከጀመርን ሰነባበትን እኒህን አበው በስም እንኳ የማናውቅ ውለታቢስ ትውልዶች እልፍ ነን!
እዚህ ፍኖት ላይ የደረስነው Neo patristic movementን ገና እየጀመርን በመሆኑ ይመስለኛል።
በዚህ እንቅስቃሴ መዘግየት እና ፍሬ አለማፍራት የተነሳ ምስራቃውያን ሳይቀሩ የእነርሱን አስተምህሮዎች የምንወስድ እስከሚመስላቸው ድረስ ደርሰናልኮ!
ምናልባትም በዚል እንቅስቃሴ ልንጠቅስ የምንችላቸው የቤተክርስቲያናችን ዘመነኛ ሊቃውንት ትንሽ ናቸው ወደፊት ይሄ እንቅስቃሴ ባለበት ከቀጠለ እኒሁ አበው ተዳፍነው ይቀራሉ እና ይሄ እንቅስቃሴ እየጎመራ እንዲሄድ እንመኛለን!
ሌላው የቤተክርስቲያናችን ምእመናን ካላቸው ርቀትም የተነሳ ያለው ክፍተትም ነው ለዚህ ያበቃን!
@mekra_abaw