“ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።” (ማቴ. 3፥13)
እንኳን ለከተራ በዓል አደረሳችኹ! በዚኽ አጭር ጽሑፍ የዛሬውን ዕለት የሚመለከቱ ኹለት ጥያቄዎችን በአጭሩ መልሳቸውን ከብዙ በጥቂቱ አቅርበናል።
#ከተራ ምንድን ነው?
ከተራ 'ከበበ' ከሚል የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲኾን ውኃ መከተር፥ መገደብ ማለት ነው፡፡ በጥምቀት ዋዜማ በቤተ መቅደስ ያለው ታቦት ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገደባሉ)።
ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሔድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡ በአቅራቢያ የሚገኙት አብያተ ክርስቲያናትም ተሰብስበው ከዚኹ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ፤ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማኅሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።
#ታቦታቱን እያከበርን ወደ ወንዝ (ውኃ ወዳለበት አካባቢ) መሔዳችን ለምንድን ነው?
በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሔዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፥ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
የጥምቀት አከባበር በሀገራችን ኢትዮጵያ ታቦት ተሸክሞ ወንዝ ወርዶ የክርስቶስን በዓለ ጥምቀት ማክበር የተጀመረው በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ሲኾን ይበልጥ ተጠናክሮ በሜዳና በውኃ ዳር ማክበር የተጀመረው በዐፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት (ከ530 - 544ዓ.ም) እንደ ኾነ ይነገራል።
❤️ መልካም የከተራ በዓል!
mekra_abaw✝️❤️🙏