ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ:
፫
የዐቢይ ጾምን መግባት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ ትምህርት
(በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
የዛሬው ንግግሬ ለአንዳንዶቻችሁ አዲስና እንግዳ እንደሚኾንባችሁ ዐውቃለሁ፡፡ ነገር ግን በዓላማ (ድኅነትን ለማግኘት ብለን) እንጹም እንጂ እንዲሁ የልማድ ባርያዎች አንኹን ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ በየቀኑ ከልክ በላይ በመብላትና በሆዳምነት የምታገኙት ጥቅም ምንድን ነው? ጥቅምስ ይቅርና ጭራሽ የከፋ ጉዳትን የሚያመጣባችሁ ነው፡፡ ተመልከቱ! ከልክ በላይ በመጠጣትና በመስከር የማስተዋል ልቡና ሲታወር የጾም ጥቅምዋም ምንም ምልክትን ሳያስቀር ያጠፋዋል፡፡ እስኪ ልጠይቃችሁ፦ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ብዙ ወይንን ከሚጠጡ፣ በየመሸታ ቤቱ አድረው ፀሐይ ከምትወጣባቸው፣ ለሚያገኛቸው ሰው ኹሉ ደስ ከማያሰኙ፣ ለቤተ ሰቦቻቸው ግድ ከሌላቸው፣ ሕፃን ዐዋቂው ከሚሳለቅባቸው፣ ራሳቸውን ባለመግዛታቸውና ያለጊዜው በኾነ ደስታ ደስ በመሰኘታቸው ምክንያት ከእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን ካጡ ከእነዚህ ሰዎች በላይ ማን ጎስቋላ ሰው አለ? ቅዱስ መጽሐፍስ እንዲህ የሚል አይደለምን?፡- “ሰካሮች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም” /1ኛ ቆሮ.6፥10/፡፡ ወዮ! እንደ ጠዋት ጤዛ ለሚጠፋ፥ ያውም እጅግ ከባድ ጉዳትን የሚያመጣ እርካታን ለማግኘት ብለው፥ የዘለዓለምን መንግሥትን የሚያጡት እነዚህ ሰዎች ከሚያገኛቸው መከራ በላይ ምን መከራ አለ?
እዚህ ጉባኤ ከተሰበሰባችሁ ምእመናን መካከል አንድም ሰው እንኳን ቢኾን በዚህ ዓይነት ስንፍና መያ’ዝ የለበትም፤ እግዚአብሔር ይህን በፍጹም አይወደውም፡፡ ከዚህ ይልቅ እያንዳንዷን ቀን በትዕግሥትና ራስን በመግዛት እንዲሁም አብዝቶ መብላት ከሚያመጣው የመከራ አውሎ ነፋስ ተጠብቃችሁ ወደ ነፍሳችሁ ወደብ - ይኸውም ወደ እውነተኛ ጾም - ልትደርሱ ይገባችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነም ከእርስዋ የሚገኘውን ጥቅም በብዙ ታገኛላችሁ፡፡ በሌላ አነጋገር አብዝቶ መብላት የብዙ ውርደቶችና ኃጢአቶች ምንጭ እንደ ኾነ ኹሉ ጾምም የብዙ በረከቶችና ክብር ምክንያት ነው፡፡ እንደምታስታውሱት መጀመሪያ ላይ እግዚአብሔር የሰው ልጆችን ሲፈጥር ለነፍሳቸው ድኅነት የሚኾን አንድ መፍትሔ እንደሚያስፈልጋቸው ያውቅ ነበር፡፡ በመኾኑም፥ ገና ከመነሻው አንሥቶ ለመጀመሪያው ሰው (ለአዳም) አንድ ትእዛዝ ሰጠው፤ እንዲህ በማለት፡- “በገነት ካለው ዛፍ ኹሉ ብላ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ” /ዘፍ.2፥16-17/፡፡ ይህ ስለ መብላትና ስለ አለመብላት የተገለጠው ኃይለ ቃል በምሥጢር ስለ ጾም የሚናገር ነው፡፡ ምንም እንኳን ሰው ይህቺን ትእዛዝ ይጠብቃት ዘንድ ቢታዘዝም እርሱ ግን አልጠበቃትም፡- ራሱን መግዛት አቃተው፤ ባለመታዘዝ ኃጢአት ውስጥ ወደቀ፤ በራሱ ላይም የሞት ፍርድን አመጣ፡፡ እንደምታስታውሱት ዲያብሎስ ክፉ መንፈስና የእኛ ጠላት ስለ ኾነ የመጀመሪያው ሰው አዳም በገነት ሲኖር እንዴት በነጻነት እንደሚኖርና ሥጋ ለብሶ ሳለ እንዴት የመላእክትን ኑሮ በምድር ላይ እንደሚኖር ተመለከተ፡፡ በመኾኑም፥ እንዴት እንደሚጥለው አሰበ፤ ታላቅ የኾነ ተስፋ በመስጠት ከልዕልናው አዋረደው፤ በዚህ ሽንገላዉም የነበረውን ሀብት ኹሉ ሰረቀው፡፡ በመጠን ያለመኖርና ከዓቅም በላይ የኾነን ነገር የመመኘት ክፋቱ ይኽን ያህል ነው፡፡ ጠቢቡ ሰውም ይህንን እንዲህ በማለት ግልፅ አድርጎታል፦ “በዲያብሎስ ቅንአት ምክንያት ሞት ወደ ዓለም ገባ” /ጥበ.2፥24/፡፡
ተወዳጆች ሆይ! ገና ከጥንቱ የሞት መግቢያው ራስን አለመግዛት መኾኑን ታያላችሁን? በኋላ ዘመን ላይም መጽሐፍ ቅዱስ አብዝቶ መብላትን እንዴት ደጋግሞ እንደሚነቅፈው አስተውሉ፡፡ በአንድ ስፍራ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡- “ሕዝቡም ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፤ ሊዘፍኑም ተነሡ” (ዘጸ.32፥6)፤ በሌላ ቦታም፦ “በላ፥ ጠጣም፤ ወፈረ፥ ደነደነም፤ የመድኃኒቱንም አምላክ ናቀ” ይላል /ዘዳ.32፥15/፡፡ የሰዶም ኗሪዎችም እንደዚሁ ያን የማይበርድ ቍጣ በራሳቸው ላይ ያመጡት በዚህ ኃጢአት ምክንያት ነው፡፡ ሌላውን በደላቸውን እንኳን ሳንገልጠው የነቢዩን ቃላት አድምጡ፤ እንዲህ ያለውን፡- “የሰዶም ኃጢአት ይህ ነበረ፡- እንጀራን መጥገብ” /ሕዝ.16፥49/፡፡ በአጭር አነጋገር መብል ብዙውን ጊዜ እንደ ምንጭ ውኃ ነው፤ ወይም የክፋት ኹሉ ሥር ነው፡፡
ይቀጥላል....
(ኦሪት ዘፍጥረት ቅጽ 1 ገጽ 23-31 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
፬
የዐቢይ ጾምን መግባት ምክንያት በማድረግ የተሰጠ ትምህርት
(በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
እንግዲህ አሁን ራስን አለመግዛት እንዴት አደገኛ እንደ ኾነ ተገነዘባችሁን? አሁን ደግሞ ጾም እንዴት ያለ በረከትን እንደሚያመጣ እንመልከት፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴ አርባ ቀን ስለ ጾመ የእግዚአብሔር ሕግ የተጻፈበትን ጽላት ሊቀበል ችሏል /ዘጸ.24፥18/፡፡ ከተራራው ሲወርድ ግን አብዝቶ የሚበላና ኃጢአተኛ የኾነ ሕዝብ የእግዚአብሔርን ሕግ ቢቀበል ምንም ትርጉም የለውም በማለት በብዙ ምልጃ የተቀበለውን ጽላት ከእጁ ጥሎ ከተራራው በታች ሰበረው /ዘጸ.32፥19/፡፡ በመኾኑም፥ ይህ ታላቅ ነቢይ በሕዝቡ ኃጢአት ምክንያት በሰበረው ጽላት ፈንታ እንደ ቀድሞ ያለ ሌላ ጽላት ለመቀበል አርባ ቀንና አርባ ሌሊት መጾም ነበረበት /ዘጸ.34፥28/፡፡ በእሳት ሠረገላ ተነጥቆ ወደ ሰማያት የተወሰደው፣ እስከ ዛሬ ድረስም ሞትን ያልቀመሰው ታላቁ ነቢይ ኤልያስም ልክ እንደ ሙሴ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾሟል /1ኛ ነገ.19፥8/፡፡ ልክ እንደዚሁ መንፈሰ ብርቱው ዳንኤልም አያሌ ቀናትን ይጾም ነበር፤ እንደ ሽልማትም እጅግ የሚያስደንቅ ራእይን ተቀብሏል፡- ቍጡዎቹን አንበሶች እንደሚያስለምዳቸው፣ ጥንተ ተፈጥሯቸው ተለውጦ ሳይኾን ከእነ ተናጣቂ ባሕርያቸው እንደ የዋህ በጎች እንደሚኾኑለት ዐየ፡፡ የነነዌ ሰዎችም እንደዚሁ በጾም መድኃኒትነት ከእግዚአብሔር ዘንድም ምሕረትን አግኝቷል፡፡ እንዲያውም በነነዌ የጾሙት ሰዎች ብቻ አልነበሩም፤ እንስሳቱም ጭምር እንጂ፡፡ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር ሊያደርገው ከተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም /ዮና.3፥10/፡፡ ከብሉያትና ከሐዲሳት እንዲህ በመጾማቸው ምክንያት የተጠቀሙ ብዙ ሰዎችን መጥቀስ እንችላለን፤ ነገር ግን የኹላችንም ጌታ ወደ አደረገው መምጣት ሲገባን አገልጋዮቹን የምናየው ለምንድን ነው? እንደምታውቁት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾሟል (ማቴ.4፥2፣ ሉቃ.4፥2)፡፡ ሲጾምም ዲያብሎስን ድል አድርጎ አሳይቶናል፡፡ ይኸውም የጾምን ትጥቅ ልንታጠቅ እንደሚገባንና ከዚህ በምናገኘው ኃይልም ብርቱ የሚኾን ጠላታችንን ድል ማድረግ እንደሚቻለን አርአያ ሲኾነን ነው፡፡
እዚህ ላይ ምናልባት ነገሮችን ጠለቅ አድርጎ የሚመረምርና ሐሳበ ልቡናዉን ንቁ ያደረገ ሰው፡- “ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልክ እንደ አገልጋዮቹ አንዲት ቀንስ እንኳን ሳይጨምር የጾመው ስለ ምንድን ነው?” ብሎ ጥያቄ ሊያነሣ ይችላል፡፡ ጌታችን ይህንን ያደረገው ያለ ምክንያት ሳይኾን ከጥበቡና ሰውን ከመውደዱ የተነሣ ነው፡፡ ይኸውም፦ “ወደዚህ ምድር የመጣው ሥጋን ሳይለብስ ነው፤ ሰውም የኾነው በምትሐት ነው” ብለው ለሚነሡ ዐብዳን ሐሳባቸውን ይገታ ዘንድ አስቦ ልክ እንደ አገልጋዮቹ አንዲት ቀንስ እንኳን ሳይጨምር ጾመ፡፡ እንግዲህ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደዚህ በገቢር ጾሞ ሳለ እንኳን እንደዚህ ያለ ምክንያት የሚያመጡ ከኾነ ከቸርነቱ የተነሣ ሊያመጡት የሚችሉትን ሰበብ አስቀድሞ ባይጥለው’ማ እንደ ምን የከፋ ነቀፋን