ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት
ክፍል 20 ቁረይሾች ያቀረቡት አስገራሚ ሀሳብና የአቡጣሊብ ድንቅ መልስ
ቁረይሾች ማስጠንቀቂያቸው ምንም ጥቅም እንዳላስገኘ አዩ።ነቢዩ (ﷺ) ሥራቸውን ቀጠሉበት።አቡጣሊብም ነቢዩን (ﷺ)በመርዳት ገፉበት።ይህ ማለት ደግሞ የውንድማቸውን ልጅ በመርዳት አቡጣሊብ ከነሱ ለመለየት፣ከነሱ ጋር ጠላት ለመሆንና እነሱን እነሱን ለመግጠም ዝግጁ መሆናቸውን ያሳያል። ቁረይሾች በዚህ ጉዳይ ሲያስቡበትና ሲወያዩበት ለትንሽ ጊዜ ከቆዩ በኋላ አንድ አስገራሚ በሆነ ሀሳብ ላይ ተስማሙ።ወደ አቡጣሊብ ሄዱ።አብሮዋቸው ዐምማራ ቢን አልወሊድ ነበር።ዐምማራ የወጣቶቻቸው ሹምና በቁረይሽ ውስጥ ጠንካራ ወጣት እንድሁም በጣም መልከ መልካም ነበር።አቡጣሊብ ሆይ! አሉ።ይህን ወጣት ውሰድ የሱ ጉማ (የደም ካሳ)የአንተን ነው። ይከላከልልሃል፣ትከላከልለታለህ።ልጅህ አድርገው፣እርሱ የአንተ ነው።ይህንን የአንተን ሃይማኖትና የኘባቶችህን ሃይማኖት የተፃረረ ሕዝቦችህን የከፋፈለና ያዋረዳቸውን የወንድምህን ልጅ እንድንገድለው አሳልፈህ ስጠን።ይህ ማለት አንድን ወንድ ልጅ በሌላ ወንድ ልጅ ለወጥክ ማለት ነው።አሉዋቸው።
አቡጣሊብ እንድህ አሉዋቸው ።በሱ የምትደራደሩኝ ነገር ምነኛ የከፋ ነው!ልጃችሁን ልመግብላችሁ ልትሰጡኝ ልጄን ልትገድሉት ልሰጣጣችሁ?ይህ ወላሂ በፍፁም አይሆንም።
በአላህ መልእክተኛ ( ﷺ)ላይ ድንበሮችን ማለፍ ቁረይሾች ሙከራቸው ሲከሽባቸውና ተስፋ ሲቆርጡ ማስጠንቂያውም ዛቻውም ድርድሩም ጥቅም ስላላስገኙላቸው በነቢዩ (ﷺ) አካል ላይ ድንበር ማለፍን፣ሙስሊሞቹን ማሰቃየትና መቅጣት ጀመሩ።
ነባዩ(ﷺ) የሚታገዙ፣የሚከበሩና የሚፈሩ ስለነበሩ እሳቸውን የማሰቃየቱን ሃላፊነት የወሰዱት የቁረይሾች ታላላቆችና ሹማምንትና ነበሩ። ተራዎችና የበታቾቹ ሰዎች አይደፍሯቸውም ነበር።
ነቢዩን(ﷺ)በገዛ ቤታቸው ውስጥ ድንበር የሚያልፉባቸውናየሚያስቸግሩዋቸው ሰዎች አቡለሀብ፣አል ሐከም ቢን አቢልዓስ ቢን ኡመያ፣ዑቅባ ቢን አቢ ሙአይጥ፣ዐዲይ ቢን ሐምራእ አስሰቀፊ እና እብኑል አስዳዕ አልሁዘሊይ ናቸው።እነዚህ ጎረቤቶቻቸው ነበሩ።ነቢዩ(ﷺ)ሲሰግዱ አንዳቸው የፍየል እንግዳ ልጅ ያስቀምጥባቸዋል። እንግዳ ልጁን በነቢዩ ግቢ ወይም ቤት ውስጥ በእሳት ላይ በተጣደ ድስት ውስጥም ይጥሉት ነበር። ይህ ሲጣልባቸው ነቢዩ(ﷺ)በእንጨት ይዘውት በመውጣት ደጃፋቸው ላይ ቆመው እንድህ ይላሉ፦በኒ ዐብድ መናፍ ሆይ፦ ይህ ምን አይነት ጉርብትና ነው? ከዚያም ወደ መንገድ ይጥሉታል።
ኡመያ ቢን ኸለፍ ነቢዩኝ(ﷺ)ባያቸው ጊዜ ይሰድባቸዋል፣ይዘልፋቸዋል ።ወንድሙ ኡበይ ቢን ኸለፍ ነቢዩን(ﷺ)እንድህ እያለ ያስጠነቅቃቸው ነበር፦አንተ ሙሐመድ !እኔ አንድ የፈረስ ግልገልአለኝ፣በየቀኑ የማሽላ እቅፍ እመግበዋለሁ፣በሱ ላይ ሆኜ እገድልሃለሁ። ይላል።ነቢዩ(ﷺ)ኢንሻ አላህ እኔ እገድልሃለሁ።ይሉት ነበር።ነቢዩ (ﷺ) በኡሁድ ጦርነት ላይ ገደሉት።ይህ ኡበይ ቢን ኸለፍ አንድ ቀን የበሰበሰ አጥንት ይዞ መጣና ፈርፍሮት በነቢዩ ፊት ላይ ነፋባቸው።
አንድ ቀን ዑቅባ ቢን አቢ ሙዐይጥ ከነቢዩ ጋር ተቀምጦ የሚናገሩትን ሰማቸው።ይህንን ነገር ጓደኛው አብይ ሰምቶት ወቀሰው። በነቢዩ(ﷺ)ፊት ላይ እንድተፋባቸው ጠየቀው።ተፋባቸውም።
ይቀጥላል.............
https://t.me/Menhaj_Asselefiya