ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት
ክፍል 24 የቁረይሾች ግራ መጋባት
ሙስሊሞቹን ከሐበሻ በማስመለሱ ጉዳይ ውርደትንና ውድቀትን ሲከናነቡ ቁረይሾች ቁጣቸው በእጅጉ ጨመረ። እርር ድብን አሉ። በተለይም ነቢዩ(ﷺ) በዳዕዋው ሲገፉበት ሲያዩና በአንፃሩ ደግሞ አቡጣሊብን ቢያስጠነቅቁአቸውም፣ቢዝቱባቸውም፣ቢያስፈራሯቸውም ነቢዩን (ﷺ) ማገዛቸውንና መርዳታቸውን ስለቀጠሉ እጅግ ግራ ተጋቡ። ምን ማድረግ እንዳለባቸው አላወቁም። አንዳንዴ ጥላቻው ያሸንፋቸውና ነቢዩን (ﷺ)እና ከሳቸው ጋር የቀሩትን ወደ ማሰቃየቱ ይመለሳሉ። በሌላ ጊዜ ደግሞ የውይይትና የክርክር በር ይከፍታሉ።ሲላቸውም ማሞኛዎችንና ማታለያዎችን ያቀርቡላቸዋል።እንደዚሁም በመሓል መንገድ በሚያገናኛቸው ነገር (ለሁለቱም ወገን በሚስማማ ሃይማኖት) ለመደራደር ና ለመገናኘት ይሞክራሉ። አልፎ ተርፎም ነቢዩን(ﷺ) በመግደል ኢስላማዊውን ጥሪ ለማውደም ያስባሉ ።ከዚህ ሁሉ አንዱም የጠቀማቸውና ወደ ፈለጉት ነገር ያደርሳቸው ሙከራ የለም። የሙከራዎቻቸው ውጤት ውርደትና ኪሳራ ነበር። ከዚህ በመቀጠል ሙከራዎቻቸውን አጭር ባጭር እናቀርባለን ።
ማሰቃየትና የመግደል ሙከራ
ሙከራዎቻቸው ሲከሽብባቸው ቁረይሾች ወደ ጠላትነት መመለሳቸው የማይቀር ጉዳይ ነበር። በርግጥም የተቀሩትን ሙስሊሞች በከፋ ሁኔታ ማሰቃየት ጀመሩ። በረሱል(ﷺ)ላይም እጃቸውን በክፉ ዘረጉ። ከነዚህም ውስጥ ዑተይባ ቢን አቢለሀብ ወደ ነቢዩ (ﷺ) መጣና ቀረበ፣ ወረደም፣ የሁለት ደጋኖች ጫፍ ያህል ወይም ይበልጥ ቀረበ ። በተባለው ነገር (በጅብሪል) እክዳለሁ አለ። ከዚያም ያሰቃያቸው ጀመረ። ልብሳቸውን ቀደደ። ፊታቸውላይ ተፋ ።ምራቁ ግን ወደ ራሱ ተመለሰ። ነቢዩ (ﷺ)አላህ ሆይ ከውሻዎችህ አንዱን ውሻ ላክበት ብለው ዱዓ አደረጉበት። ዑተይባ ከነጋዴ ቅፍለት ጋር ወደሻም ሄዶ በመንገድ ላይ አንድ ቦታ ሲያርፉ አንድ አንበሳ ባሉበት ቦታ መጥቶ ሲዘዋወር አዩ ወላሂ ሊበላኝ ነው ሙሐመድ ዱዓ አድርጎብኝ ነበር። እርሱ መካ ሆኖ እኔን በሻም ምድር ገደለኝ በማለት ጮኸ። ሲተኙ መሀላቸው አደረጉት። ይሁን እንጂ አንበሳው መጣና ከግመሎችና ከሰዎች መሀል የዑትባን ጭንቅላች ይዞ ገደለው።
ሌላው ደግሞ ዑቅባ ቢን አቢ ሙአይጥ ነቢዩን (ﷺ)ሱጁድ ላይ እያሉ አይናቸው ሊወጣ እስኪቀርብ ድረስ በእግሩ አንገታቸው ላይ ቆመባቸው።
ዳዕዋውን ለመግታት ሙሽሪኮች የተለያዩ ሙከራዎቻቸው ከከሸፈባቸው በኋላ ነቢዩን(ﷺ)ለመግደል በብርቱ ማሰባቸውን ከተከሰቱት ሁኔታዎች መረዳት ይቻላል፦ ይህ ነገር ደም ወደ ማፍሰስ የሚያመራ ቢሆንም ይህንን ከሚያመለክቱ አንዱ አቡጀህል አንድ ቀን ለቁረይሾች እንድህ ማለቱነው። በርግጥ ሙሐመድ ከሚታዩት ነገር ሌላ እምቢ ብሏል። ሐይማኖታችንን ከማነወር ፣አባቶቻችንን ከመስደብ፣ እኛን ከማቅለልና አማልክቶቻችንን ከመስደብ ሌላ እምቢ ብሏል። መሸከም የምችለውን ትልቅ ድንጋይ ተሸክሜ ቁጭ ብየ ልጠባበቀውና በሶላቱ ውስጥ ሱጁድ ሲያደርግ ጭንቅላቱን ልጨፈልቀው ለአላህ ቃል እገባለሁ። ከዚያ በኋላ አሳልፋችሁ ስጡኝ ወይም ተከላከሉልኝ። ከዚያም በኋላ በኒ ዐብድ መናፍ የፈለጉትን ነገር ያድርጉ። ሲላቸው ወላሂ ለምንም ነገር አሳልፈን አንሰጥህም የምትፈልገውን ግፋበት አሉት።
ሌሊቱ ነግቶ ነቢዩ (ﷺ)ለሶላት ሲቆሙ አቡጀህል ያለውን ድንጋይ ተሸክሞ መጣ። ቁረይሾች በመሠብሠቢያ ቦታቸው ላይ በማለዳ በመገኘት አቡ ጀህል ምን እንደሚያደርግ መጠባበቅ ጀመሩ። አቡ ጀህል ድንጋዩን ይዞ ወደ ነቢዩ ቀረበ። ከዚያም ተሸንፎ ፊቱ ተለወረጦ በጣም ፈርቶ ተመለሰ። ሁለቱ እጆቹ ድንጋውን እንደያዙ ደርቀው ሸሩ። ከዚያም ድንጋዩን ወረወረው። ቁረይሾች አንተ አበል ሐኪም ምን ሆንክ? አሉት። ማታ የተናገርኩትን ነገር ለመፈፀም ስሄድ ጭንቅላቱን፣አንገቱንና ክራንቻውን በማንም ኮርማላይ አይቼ የማላውቀው የግመል ኮርማ ሊበላኝ መጣ አላቸው።
ነቢዩ(ﷺ)ያ ጅብሪል ነበር ፣ቢጠጋው ኖሮ ይይዘው ነበር አሉ።ከዚያም ከዚህ የጠነከረና የበረታ ሁኔታ ተፈጠረ።
ይቀጥላል..............
https://t.me/Menhaj_Asselefiya