🍀ሸይኽ ሰይድ ኢብራሒም ጫሌ ረሂመሁሏህ
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂
→ክፍል ሁለት
ሐበሻ የርሳቸው አይነት በጣት የሚቆጠሩ እንጂ አልተቸረችም ቢባል ማጋነን አይሆንም። እስኪ ስለሳቸው አንድ ወንድም የከተበውን ላካፍላችሁ:
የሼህ ጫሌ አዋቂና ሊቅነት ፤ በአማርኛ የመራቀቅ አቅም ፤ ገጣሚነት ፤
በግጥሞች ላይ የሚታየዉ ሀሳብና አተያይን የመሻትና የማክበር ፤ የበሰሉ መልዕክቶችና
ያልተደዘደዙ ቃላቶች ተሰባጥረዉ ያለበሷቸዉ የገጣሚነት ግርማ ሞገስ እንዲሁም ለዚች
አለም የነበራቸዉ ግድ-የለሽነትና ሁለ ነገራቸዉ ተደማምረዉ ቀልባችንን በናፍቆት እንጥልጥል ያደርጓል ፡፡
ሼህ ጫሌ ነፍስን ጥግ ድረስ የማላጋት ሀይል ደራርበዉ ለብሰዋል ። ተአምር ባጀበዉ
ብዕራቸዉ ብዙ ትዝታዎችን ቀስቃሽ ፤ ለነፍስያችን ምግብ እየፈተፈቱ አጉራሽ ፤ ካለፉትም
ከኛም ላይ ሙቶና ደንዞ የነበረዉን የሐቢቢን ፍቅር ከተቀበረበት ምሰዉ ህያዉ ማድረጋቸዉ
በተከሰተልን ጊዜ ፤ የጨለመዉ አስተሳሰባችን ላይ እንደ ተወርዋሪ ኮከብ ተፈትልኮ ወገገን ይዘሩብናል፡፡
የነተበዉ አጥንታችን እንደ ዉሃ ዳር ቄጤማ ይለመልማል ፡፡ተስፋችን
ተንሰራርቶ ይፍረመረማል ፡፡ ድብርታችንን ፀዳላማዉ ስራቸዉ አሙለጭልጮ ፍግምግም
ያደርግልናል ፡፡
.
የሁልጊዜም ንግግራቸዉ ከገዛ እዉነታችን የተቀዳ ነዉና ኪታባቸዉን ባየን ጊዜ ፤ ራሳችንን
ህዝብና ሃገራችንን እየታዘብን እንቆጫኘለን ፤ እንደመማለን እንደገና አስበንም እንተክዛለን ፡፡
በዚህ መሃል ተስፋችን ሊመነምን ሲባጅ ፤ ዳግም የነርሱን ስራ አስተዉሎ ይቆዝማል ፡፡
እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ተደራርበዉ ነዉ ፤ ሞተዉ ትዝ የሚሉ ብቻ ሳይሆን ፤ የሚናፈቁም
ያረጋቸው !
━━━━━━━━━━