😔ይድረስ ለነንትና😔
✍ራዚ...😉
እኔ ስወዳችሁ፣ይበልጥ ስቀርባችሁ፣
እናንተ ጠልታቹኝ፣እጥፍ የራቃችሁ፣
ለደስታችሁ ብዬ ደስታዬን በተውኩኝ፣
እንደ ሞኝ ቂላቂል ፋራ ያያችሁኝ፣
ትልቁን ንብረቴን ልቤን ብሰጣችሁ፣
ለሌላ 'ን 'ኳ እንዳይሆን ሰብራችሁ ሄዳችሁ፣
ህመሜን ሸሽጌ ራሴን አክሜ፣
ያለፈ ስህተቴን ላልሰራ ደግሜ፣
ከሄድኩኝ ቡሃላ ሁሉን ነገር ትቼ፣
ደሞ ምን ቀርቷችሁ ወደ ኔ መጣችሁ፣
የልቤ መሰበር ክፉኛ ጎድቷችሁ?
ወይስ ስላልሞትኩኝ እቅድ ከሽፎባችሁ?
#እኔ_ግን
እናንተን አልሻም በራሴ ቆሚያለሁ፣
በፈጣሪ ፈቃድ አቅሜን አውቂያለሁ፣
ከአስመሳይ ሰዎች መራቅ ወስኛለሁ፣
የራሴ የምለው ጓደኛ አግኝቻለሁ፣
ከሰዎች ተገልሎ መኖር መርጫለሁ፣
እናንተም ላትመጡ እኔም ርቄያለሁ
ገጣሚ:ዑስማን|ራዚ...😉|
✍ራዚ...😉
እኔ ስወዳችሁ፣ይበልጥ ስቀርባችሁ፣
እናንተ ጠልታቹኝ፣እጥፍ የራቃችሁ፣
ለደስታችሁ ብዬ ደስታዬን በተውኩኝ፣
እንደ ሞኝ ቂላቂል ፋራ ያያችሁኝ፣
ትልቁን ንብረቴን ልቤን ብሰጣችሁ፣
ለሌላ 'ን 'ኳ እንዳይሆን ሰብራችሁ ሄዳችሁ፣
ህመሜን ሸሽጌ ራሴን አክሜ፣
ያለፈ ስህተቴን ላልሰራ ደግሜ፣
ከሄድኩኝ ቡሃላ ሁሉን ነገር ትቼ፣
ደሞ ምን ቀርቷችሁ ወደ ኔ መጣችሁ፣
የልቤ መሰበር ክፉኛ ጎድቷችሁ?
ወይስ ስላልሞትኩኝ እቅድ ከሽፎባችሁ?
#እኔ_ግን
እናንተን አልሻም በራሴ ቆሚያለሁ፣
በፈጣሪ ፈቃድ አቅሜን አውቂያለሁ፣
ከአስመሳይ ሰዎች መራቅ ወስኛለሁ፣
የራሴ የምለው ጓደኛ አግኝቻለሁ፣
ከሰዎች ተገልሎ መኖር መርጫለሁ፣
እናንተም ላትመጡ እኔም ርቄያለሁ
ገጣሚ:ዑስማን|ራዚ...😉|