አ ን ድ ጓ ደ ኛ አ ለ ኝ
አንድ ጓደኛ አለኝ በጣም የሚወደኝ፣
እኔ ብርቀውም እሱ የማይርቀኝ፣
ወዳጄ ሲሸሸኝ ያመንኩት ሲከዳኝ፣
ዛሬ ጥሎኝ ሲሄድ ትናንት የወደደኝ፣
ዙሪያዬ ጨልሞ መድረሻ ሲጠፋኝ፣
ሀዘንና ድብርት ዱካክ ሲጫጫነኝ፣
አይዞህ እያለ ውስጤን ሚያክመኝ፣
በጣም የሚወደኝ አንድ ወዳጅ አለኝ፣
እሱም አምላኬ ነው ለዚህ ያደረሰኝ፣
#ራዚ✍
አንድ ጓደኛ አለኝ በጣም የሚወደኝ፣
እኔ ብርቀውም እሱ የማይርቀኝ፣
ወዳጄ ሲሸሸኝ ያመንኩት ሲከዳኝ፣
ዛሬ ጥሎኝ ሲሄድ ትናንት የወደደኝ፣
ዙሪያዬ ጨልሞ መድረሻ ሲጠፋኝ፣
ሀዘንና ድብርት ዱካክ ሲጫጫነኝ፣
አይዞህ እያለ ውስጤን ሚያክመኝ፣
በጣም የሚወደኝ አንድ ወዳጅ አለኝ፣
እሱም አምላኬ ነው ለዚህ ያደረሰኝ፣
#ራዚ✍