😔የተረታ ልሳን😔
ቃላትን ሰብስቤ ላሰፍር ስሜቴን፣
አስቤ ነበር ለመግለፅ ድካሜን፣
ግን ምን ያደርጋል ቃላቶቼም ሸሹኝ፣
አነሱም እንደሰው ሲቸግረኝ ከዱኝ፣
ልሳኔም ተረታ ማስረዳት አቃተው፣
ልቤም ተሰባብሮ አጣ ሚጠግነው፣
ሀዘኔን ሚጋራ ሰው ባጣ ግዜና፣
በብዕሬ ልፅፍ ላወራው ሻትኩና፣
ወረቀት ዘርግቼ ቀለም አነሳሁኝ ፣
የብሶቴን መድብል በእምባ ጀመርኩኝ፣
ከቀለሜ ቀድሞ እምባዬ ተዘራ፣
ነጩ ወረቀቴም ዥንጉርጉሩን ሰራ፣
በዕንባና ብዕር የተፃፈው ስሜት፣
ክብደቱ ግን ያው ነው አልቀነሰም ጥቂት፣
ብዕሬም ነጠፈ እምባዬም ደረቀ፣
በውሸት ፈገግታ ፊቴ እየደመቀ፣
ህይወቴ ቀጥሏል ወዳጄ እየራቀ፣
#ራዚ✍
🔺መታሰቢያነቱ🔺
"እንደኔ የህይወት ትርጉም ጠፍቶባችሁ ልባችሁ ተሰብሮ በውሸት ፈገግታ ችግራቹን ደብቃችሁ ለምትኖሩ ይሁንልኝ"
ቃላትን ሰብስቤ ላሰፍር ስሜቴን፣
አስቤ ነበር ለመግለፅ ድካሜን፣
ግን ምን ያደርጋል ቃላቶቼም ሸሹኝ፣
አነሱም እንደሰው ሲቸግረኝ ከዱኝ፣
ልሳኔም ተረታ ማስረዳት አቃተው፣
ልቤም ተሰባብሮ አጣ ሚጠግነው፣
ሀዘኔን ሚጋራ ሰው ባጣ ግዜና፣
በብዕሬ ልፅፍ ላወራው ሻትኩና፣
ወረቀት ዘርግቼ ቀለም አነሳሁኝ ፣
የብሶቴን መድብል በእምባ ጀመርኩኝ፣
ከቀለሜ ቀድሞ እምባዬ ተዘራ፣
ነጩ ወረቀቴም ዥንጉርጉሩን ሰራ፣
በዕንባና ብዕር የተፃፈው ስሜት፣
ክብደቱ ግን ያው ነው አልቀነሰም ጥቂት፣
ብዕሬም ነጠፈ እምባዬም ደረቀ፣
በውሸት ፈገግታ ፊቴ እየደመቀ፣
ህይወቴ ቀጥሏል ወዳጄ እየራቀ፣
#ራዚ✍
🔺መታሰቢያነቱ🔺
"እንደኔ የህይወት ትርጉም ጠፍቶባችሁ ልባችሁ ተሰብሮ በውሸት ፈገግታ ችግራቹን ደብቃችሁ ለምትኖሩ ይሁንልኝ"