............................ረመዷን 1/1446 ዓ᎐ሂ
•°•°•°•°• ★ ፆምና ጥበባቱ ★•°•°•°•°•°
ኢስላም አንድን ነገር ለጥበብ ቢሆን እንጂ አይደነግግም፡፡ አንዳንዱ ቢረዳውና ሌላው ባይረዳውም፡፡ አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ የድንጋጌው ጥበባት ድንቅ ነው፡፡
በአፈጣጠሩም በትእዛዛቱም ጥበበኛ ነው፡፡ ምንም ነገር ለከንቱ አልፈጠረም፤ ምንም ነገር ለቀልድ አላዘዘም፡፡
#አላህ_ሱብሃነሁ_ወተዓላ_ከዓለማት_የተብቃቃ_ነው_ፍጡራኑና_ባሪያዎቹ_ግን_ወደርሱ_ከጃዮች_ናቸው
ባሪያዎች የሚፈፅሙት ወንጀል እንደማይጎዳው ሁሉ ትእዛዛቱ ስለተፈፀሙለትም ጥቅምን አያገኝም፡፡
ምክንያቱም
#የአላህን_ትእዛዛት_የመፈፀም_ጥቅም_ወደታዛዦች_ተመላሽ_ነውና፡፡
💎የሀይማኖቱ ድንጋጌ ሰነዶች ባመለከቱት መሰረት ፆም ብዙ ጥበባትና ጥቅሞች አሉት፡፡ ከነሱም ውስጥ፡-
🔵 የአላህን ትእዛዛት በመፈፀም ራስን ማጥራት፤ ከእቀባዎቹ ራስን በመግታት ሙሉ ታዛዥነት ላይ ነፍስን ማለማመድ፤ ነፍስን ከስሜቷ በማገት ዙሪያዋን ከተበተቧት ማነቆዎች ነፃ ማውጣት ነው፡፡
ሰውዬው የአላህን ውዴታ ከጃይ ባይሆንማ (በረመዳን ቀን ክፍለ ጊዜ) ከፈለገ ይበላል ፣ ይጠጣል ከባለቤቱም ጋር ግንኙነት የፈፅማል፡፡ ይህን ሁሉ ቢያደርግ ከአላህ በስተቀር ማንም አያውቅበትም፡፡
ይህን አስመልክቶ አቡሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፦
“ነፍሴ በጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ የፆመኛ ሰው የአፍ ጠረን አላህ ዘነድ ከሚስክ ሽቶ በላይ ጣፋጭ ነው። ምግብ መጠጥና ስሜቱን ለእኔ ብሎ ነው የተወው። የአደም ልጅ ስራ በሙሉ ለራሱ ነው። ፆም ሲቀር እርሱ ለእኔ ነው። እርሱን እኔ ነኝ የምመነዳው።”
(ቡኻሪና ሙስሊም)
🔵 ዶክተሮችና የጤና ባለሙያዎች እንዳረጋገጡት ፆም የሰውነትን ጤና ለመጠበቅ ይጠቅማል፡፡
ከዚህም ባሻገር የሰው ልጅን መንፈሳዊ ማንነቱ በቁሳዊ ክጃሎቱ ላይ ድልን ይጎናጸፍ ዘንድ ያግዘዋል።
የሰው ልጅ ወደ ጥሩም ወደ መጥፎም የማዘንበል ተፈጥሯዊ አቅም ተሰጥቶታል።
ብሎም የአፈጣጠሩ መዋቅር የተቦካ ጭቃ እንዲሁም ከአላህ የሆነ መለኮታዊ እስትንፋስ (ሩህ) ውህድ ነው፡፡
አንዱ ለውርደቱ ምክንያት ሲሆን
ሌላኛው ደግሞ ማዕረጉን ይጨምርለታል።
ጭቃዊ አፈጣጠሩ በማንነቱ ላይ የበላይ ከሆነ ውርደትን ከመላበስ በተጨማሪ ወደ እንስሳ ደረጃ ያዘቅጠዋል፤ አልያም መንገዱን የሳተ ያደርገዋል።
#ግና_መንፈሳዊ_ማንነቱ_የበላይ_ከሆነ_ወደ_መላእክት_አድማስ_ከፍ_ይላል_ልዕልናንም_ይጎናፀፋል፡፡
ስለዚህ በፆም ወቅት መንፈሳዊ ማንነት ቁስን፤ ህሊና ስሜትን ያሸንፋሉ፡፡
ጿሚ የሆነ ሰው በየቀኑ እስኪያፈጥር ድረስ የሚያጣጥመው ደስታ ሚስጥሩ ይህ ነው። በሃዲስ እንዲህ ተብሏል፦
“ለፆመኛ ሁለት ደስታዎች አሉት፡፡
① ሲያፈጥር በማፍጠሩ ይደሰታል።
② ከጌታው ጋር ሲገናኝም በጾሙ ይደሰታል፡፡”
(ቡኻሪና ሙስሊም)
🔵 ፆም ፍላጎትን የመግሪያ፣ ነፍስን (ከመጥፎ ጎዳና) ታግሎ የመጣያ፣ ብሎም ትዕግስትን መለማመጃ የሆነ ታላቅ የንቅናቄ አውድማ ነው።
የሰው ልጅ በፍላጎት የተከበበ አይደለምን?
መልካም ነገርስ በፍላጎት እንጂ ይገኛልን?
(ዲን) እምነትስ ታዛዥ በመሆን ላይ መጽናትና ከወንጀል መራቅ ላይ ብርቱ መሆን አይደለምን? በዚም ጾም በራሱ ሁለት የትዕግስት ምህዳሮችን ያመላክተናል።
☆አንደኛ: የአላህ መልእክተኛ ሰለለሁ ዓለይሂ ወሰለም የረመዳንን ወር የትዕግስት ወር ብለው ሲጠሩት እንዲሁ አልነበረም።
በሀዲስ ከኢብን ዐባስ እና አሊይ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንደተጠቀሰው
“የትዕግስት ወር (የሆነውን ረመዳን) መጾም፤ እንዲሁም ከእያንዳንዱ ወር ሶስት ቀን መጾም የደረትን ዝገት ያስወግዳሉ።”
በዚህ ሀዲስ የደረት ዝገት ሲባል የነፍስን ውስወሳና አባይነት ነው
እንዲሁም ተንኮልንና ንዴት(ብስጭት) ነውም ተብሏል
☆ሁለትኛ: የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንደገለጹት “ጾም ጋሻ ነው”።
ይህንንም በተለያዩ ዘገባዎች ብዛት ባላቸው ሰሃቦች ተነግረው በሀዲስ እናገኛቸዋለን።
ለአብነት ያህል ከአቡ ሁረይራ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና የተዘገበው ሀዲስ “ጾም በዚህች ዓለም ከወንጀል መጠበቂያ፤ በመጨረሻይቱ ቀንም ከእሳት መዳኛ ነው።”
በሌላም ሀዲስ
“አንዳቹ በጦርነት እንደሚከላከልበት ጋሻ ጾምም ከእሳት መከላከያ (ጋሻ) ነው።”
(አህመድና ነሳኢ) እንዲሁም አቢ ኡማማ በጠቀሱት ሌላ ሀዲስ ደግሞ
“ጾም ጋሻ ነው። እሱም ከሙእሚን ምሽጎች ውስጥ አንዱ ነው።” (ጦበራኒ)
•°•°•°•°•°•°•° ★__★ •°•°•°•°•°•°•°
https://t.me/MuslimNegnEneSul