✿𝗠𝗨𝗦𝗟𝗜𝗠 ነን﷽


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


           。➴ 。 💡 *    ✧
              。\ | /。 ★
        ೃ✧ ለኡማው ማስታወሻ 💌 ೃ✧
          ★ 。/ | \。 ✧
            。✒️ 。   。    ✫
    -;👥 .° [ @Muslim_group2 ] ୭

─────⊱◈🌟◈⊰─────
┊ ┊ ┊ ┊ ┊
┊ ┊ ✫ ˚♡ ⋆。
┊ 🔸⋆
⊹.
📬:አስተያየት ༻
@Muslim_comment_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


#ጌታህ_ይገረማል 🤍

🔖:ዑቅባ ኢብኑ ዓሚር [رضي الله عنه‌‎ ] እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለው ሲናገሩ ሰማሁ አሉ

ጌታህ፣ ተራራ ጫፍ ባለ ቋጥኝ ላይ ሆኖ የሶላት ጥሪ (አዛን) በሚያሰማና ሶላት በሚሰግድ እረኛ ይገረማል፡፡ በመሆኑም አላህ (ﷻ)፡- “ይህን የኔን ባሪያ ተመልከቱ፣ የስግደት ጥሪ (አዛን) ያሰማል፤ ሶላቱንም ይሰግዳል፤ እኔን ይፈራል፡፡ (ኃጢአቶቹን) ይቅር ብየዋለሁ፤ ጀነት እንዲገባም አድርጌዋለሁ” ይላል፡፡


- ነሳዒይ ዘግበውታል 📚

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
💡🤲


#የቤተሰብ_ቀለብ 🌱

🔖:አቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ አንህ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል➘

‹‹በአላህ መንገድ ላይ ወጪ ካደረግከው አንድ ዲናር ለአንገት (ባሪያን ከባርነቱ ነፃ ለማውጣት) ከለገስከው አንድ ዲናር፣ ለችግረኛ ከመፀወትከው አንድ ዲናር፣ ለቤተሰብህ ቀለብ ካዋልከው አንድ ዲናር፤ በአላህ ዘንድ ትልቅ ምንዳ የሚያስገኘው #ለቤተሰብህ ቀለብ ያዋልከው ነው፡፡››

- ሙስሊም ዘግበውታል
📚

💡:ለቤተሰብ ፍላጎት ለማሟላት የሚወጣ ገንዘብ ከየትኛውም ምፅዋት ዋጂብ ከሆነው #ዘካ ሲቀር በላጭ መሆኑን፡፡

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🦋


✅:አላህ ለእኛ በጣም ጥሩ የሆነውን ያዉቃል ፣ ጥሩ ነገር ለማግኘት ምርጡ ጊዜንም ቢሆን እሱ ያዉቃል! ሶብር በማድረግ እንጠብቅ፡፡

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
✈️@Muslimchannel2 💌


ዘመኑ. . .
 
:ወላጆች ለልጃቸው ዲን እና ባህሪ የማይጨነቁትን ያህል ስለ ልብስ እና ምግባቸው አብዝተው ይጨነቃሉ

:ጎረምሦች ቀኑን ሙሉ ሲዝናኑና ሲዘሉ ዉለው ሦስት ረከዓ መግሪብ ለመስገድ ኢማሙ አረዘመብን ይላሉ ৲


#ይገርማል . . .🖱️


:ጠዋት ላይ ሠራተኞች ወደ መንግሥት ሥራ ሲሄዱ ወደ ሞት የሚጓዙ ነው የሚመስሉት ৲

:አውቶቡስ ዉስጥ ለደከሙና በዕድሜ ለገፉ እናት አባቶች የሚነሳ ወጣት እየጠፋ ነው ৲

:በመንገድ ይሁን በመስጊድ የሃይማኖት ሰው ጊዜ ወስዶ የሚማከር አታገኝም ৲

:መንገደኞች የጉዞ ሰዓት እንዳያልፋቸው አላርም ይሞላሉ ለሱብሒ ሶላት ግን ችላ ይላሉ ৲

:ተጠቃሚዎች ለአስተናጋጅ ወፍራም ቲፕ ይሠጣሉ፣  ለነጋዴ መልሱን ይተዋሉ ፤ የተቸገረ ለማኝ ግን አይተው እንዳላየ ያልፋሉ ৲

:ዳዒዎች ለደዕዋ ሥራ አበል ይጠይቃሉ ፣ ዑለሞች የአላህን ዲን በትንሽ ጥቅም ይቸበችባሉ ৲

:ኡስታዞች ራሣቸው የማይተገብሩትን ለሌሎች ይመክራሉ ৲

:መንገደኞች አደጋ በዛ ይላሉ ፤ የጉዞን ህግ አያከብሩም ፣ የጉዞን ዱዓ አያውቁም ৲

:መስጊድ እንሂድ ሲባል ወደ ሰማይ እንውጣ የተባለ ያህል ዳገት ሆኖበት ትንፋሽ የሚያጥረው በዛ ৲

:ተው ሐራም ነው ይቅርብን ሲባል “ሁሉም እየሠራው እኛ ብቻ ለምን ይቅርብን” የሚል በረከተ ৲

:ጉቦን “የሻይ” እኮ ነው ብለው ይወስዳሉ ৲

:ወለድን “ፐርሰንት” ነው” ብለው ይበላሉ ৲

:ሙዚቃን “ነሺዳ” ነው ብለው ይጨፍራሉ ৲

:ኢኽቲላጥን ወንድም እህትማማችነት ብለው ያጠናክራል ብለው አደረጉ ৲

:ሲመክሩት ተቆጪውና ገንፋዩ በዛ ৲

:ሲያስታውሱት አትምከረኝ አውቃለሁ ባይ እንደ አሸን ፈላ ৲

:የሚያውቁ አይሰሩበትም ፤ የማያውቁ ደግሞ አናውቅም አይሉም፡፡

:አቀማመጣችን ተፋልሷል፤ ከፊት መሆን የነበረበት ከኋላ ፤ ከኋላ መሆን ያለበት ከፊት ሆኗል ৲

🔎ታዲያ ምን ይሻለናል ?

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
✈️@Muslimchannel2 💌


🤍ዳመና የውሃን ክብደት መሸከም ሲያቅተው ዝናብ ይጥላል። ልብም የውስጡን ህመም መሸከም ሲሳነው  አይን እንባ ያፈሳል።

ስሜትህ ሲጎዳ ፣ ልብህ ሲሰበርና ሲጨንቅህ እጅህን ወደላይ ከፍፍ አድርግና ጌታህን ለምነው... እርሱ የለመኑትን አያሳፍርምና!

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
✈️@Muslimchannel2 💌


እናንተ ሰዎች ሆይ !
ሰላምታን አውርዱ
😀
ምግብንም አብሉ
🍱
ዝምድናንም ቀጥሉ
🫂
ሰዎች ተኝተው ሳለ በሌሊት ስገዱ
🤲
.
.
.
ጀነትን ሰላም ሁናችሁ ትገቧታላችሁ
😀

-ነብዩ ሙሀመድ ﷺ

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
✈️@Muslimchannel2 💌


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🔝


#የእናትነት_ዋጋ

:ስራ መስራት የማይወድ አንድ ህፃን ልጅ በአንድ ምሽት ኩሽና ወዳለችው እናቱ መጣና አንድ ወረቀት ለእናቱ ሰጣት እጇን በማደራረቂያ ካደራረቀችው በኋላ አነበበችው :: ወረቀቱ ላይ የተፃፈው እንዲህ የሚል ነበር፡-

✓ መኝታ ከፍሌን ላፀዳሁበት 10 ብር

✓ ቆሻሻውን ላወጣሁበት 5ብር

✓ እታከልቶቹን ውሃ ላጠጣሁበት 5ብር

✓ ወደገበያ ቦታ አብሬሽ ለሄድኩበት 10 ብር

✓ ወደ ገበያ ስትሄጂ ትንሹን ወንድሜን የጠበኩበት 10 ብር

✓ ጥሩ ውጤት ላመጣሁበት 10 ብር

ጠቅላላ ከፍያ 50ብር ይመጣል የሚል ነበር፡፡ ይህ ህፃን ልጅ ይህን ሁላ ያቀረበው ስራ መስራት ስለማይወድ እና ስልቹ ስለሆነ ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ስራው እንዲቀልለት በማሰብ ነበር፡፡ እናቱም ልጁን ለማስተማር መፃፊያ እስኪርብቶ በማንሳት ወረቀቱ ላይ ከጀርባው እንዲህ የሚል ፁሁፍ ፃፈች ፡፡

ልጄ ሆይ !

➢ ለ9ወር አንተን የተሸከምኩበት ከፍያው ስንት ነው?

➢ አንተን ስጠብቅ ያደርኩባቸው ሌሊቶች ከፍያው ስንት ነው ?

➢ ለአንተ ተጨንቄ ላፈሰስኩት እንባ ከፍያው ስንት ነው?

➢ ለመጫወቻ ፤ ለልብስ ፤ ለምግብ እና ለመሳሰሉት ያወጣሁልህ ከፍያው ስንት ነው?

➢ ያንተን ንፅህና የጠበኩበት ከፍያው ስንት ነው?

➢ ከዚህ ሁሉ በላይ ላንተ ያለኝ ፍቅር ዋጋው ስንት ነው? ብላ ወረቀቱ ላይ ፃፈችለት።

➡️ይህ ሀፃን ልጅ እናቱ የፃፈችውን አንብቦ ሲጨርስ አይኖቹ እንባ አቀረሩ ወደ እናቱ እየተመለከተ ለአንቺ ባሪያ ሆኜ ብሸጥ እንኳ, አንቺ ያደረግሺልኝን ውለታ መከፈል አልችልም ከዚያም እስከሪብቶውን አነሳውና ከእርሷ ፅሁፍ በታች በትልቁ እንዲህ የሚል ፅሁፍ ፃፈ “በሙሉ ተከፍሏል”።

📜:ዲኒያት
╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
❤️


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🔝


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ረሱላችን ﷺ ♥️


✅:ቤት የለው፣ሚስት የለው፣ልጅ የለው፣ሥልጣን የለው፣ገንዘብ የለው፣ቤተሠብ የለው......።ታዲያ ምን አለው!ካላችሁ በሶሪያ ደማስቆ ከተማ በኡመውዮች መስጊድ አጠገብ ትንሽ የአንገት ማስገቢያ ጎጆ ነበረችው። በሷ ውስጥ ተረጋግቶ የደስታ ኑሮ ይኖራል።አልፎ አልፎም መስጊድ ገብቶ ይተኛል።ወደዚህች ዓለም ለእንግድነት ብቻ የመጣ ትክክለኛ እንግዳ ነበር የሚመስለው። በቀን እንዴ ቢበላ አንድ ዳቦ ቢያገኝ ነው። ከልብስም ሁለት አለው፤አንዷን በሌላኛው ይቀይራል።

🗓:የሆነ ጊዜ የአገሬው ገዥ ሊያስረው እንደሚፈልግ ተነገረው። እሱም በቆራጥነት መንፈስ እንዲህ አለ

❝የትም ብሆን እኔ ወላሒ እንደተመቻት የሱፍ በግ ነኝ።ደስታዬን ማንም ሊነጥቀኝ አይችልም። ቢያስሩኝ እስር ቤት ለኔ ገዳሜ ነው ብቻዬን ተገልዬ አላህን እገዛበታለሁ፤ከሀገር ቢያስወጡኝ ለኔ ቱሪስትነት ነውተፈጥሮን አይቼ የአላህን ችሎታና ጥበብ በማድነቅ አስተነትናለሁ።ከዚህም አልፌ ሰዎች ወደ እስልምና እንዲገብ እጣራለሁ።ቢገድሉኝ ምን ይቀርብኛልን?!በአላህ መንገድ ሸሂድ መሆን የሁልጊዜ ምኞቴ ነውና

🔆:ይህ ሰው ማን መሰላችሁ?

𖥉 ሸይኽ አል ኢስላም ሙሐመድ ኢብን ሱለይማን አት-ተይሚይ (ኢብን ተይሚያህ)
𖤿

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌


:ኢማሙ ሻጢቢይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«የወንጀሉን ትንሽነት አትመልከት፣ ነገር ግን የምታምፀውን አካል ትልቅነት ተመልከት።»

📚سـيـر أعـلام النبـلاء

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🦋


#የስራ_ክቡርነት 📈

:የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) በመስጊድ ውስጥ ቁርኣን ለሚቀሩ ነገር ግን ለማይሠሩ ሰዎች እናንተ "ቁራኦች ሆይ! ተነሱና ርዝቅ ፈልጉ ፤ በሰው ላይ ሸክም አትሁኑ" ብለዋል። (ኢማም በይሀቂ እንደዘገቡት)

:"ቂያማ አሁን ልትቆም ነው ቢባል እንኳን በእጅህ ያለችውን ችግኝ ከመትከል ወደኋላ አትበል" ብለዋል፡፡ (ኢማም አህመድ እና ሌሎች በዘገቡት መሰረት)

:ዑመር (ረዲየሏሁ አንህ) በመስጊዱ ውስጥ ለተሰበሰቡ ወጣቶች ውጡና ርዝቅ ፈልጉ /ሥሩ/ ሰማይ ወርቅ አሊያም ብር አታዘንብም፡፡' ይሉ ነበር።

:ሁሉም ነቢያት ሠርተው ያለፉት ሥራ ፍየል ወይም በግ ማገድ ነው።

:ነቢዩ ዘከሪያ (ዓለይሂ ሰላም) አናፂ ነበሩ። ነቢዩ ዳውድ (ዓለይሂ ሰላም) የላባቸውን ውጤት የሚበሉ ጎበዝ አንጥረኛ ነበሩ።

:ነቢያችን (ﷺ) በልጅነታቸው በግ ያገዱ ሲሆን በወጣትነታቸው ደግሞ ለንግድ ወደ ሻም ሀገር ይመላለሱ ነበር

:በእጁ ሠርቶ ከሚያገኘው ወዛደር የሚወጣው የላብ ሽታ ፤ ከሥራ ፈት ሽቶ በላይ ያውዳል።

:የቀን ሠራተኛ አንደበት የሚወጣው የሥራ እንጉርጉሮ ከሰነፍ መዝሙር በላይ ይማርካል።

:"የሰውን እጅ ከማየት በመርፌ🪡 መሬት ቆፍሬ ብዘራ ፤ ሁለት ባሮችን ከጥቁር ወደ ነጭ ለማንፃት በማጠብ ሥራ ብሰማራ ይሻለኛል።"( አንድ ሷሊህ ሰው)

📖:አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል➘

🔹:هُوَ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ ذَلُولًا فَامْشُوا فِي مَنَاكِبِهَا وَكُلُوا مِن رِّزْقِهِ ۖ وَإِلَيْهِ النُّشُورُ

🔸:እርሱ ያ ምድርን ለእናንተ የተገራች ያደረገላችሁ ነው፡፡ በጋራዎችዋና በመንገዶችዋም ኺዱ፡፡፡ ከሲሳዩም ብሉ፡፡ (ኋላ) መመለሻውም ወደእርሱ ብቻ ነው፡፡(ሙልክ : 15)


╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌


#ግብረሰዶም (LGBTQ+)

:አላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-

«በዑመቴ ላይ በጣም የምፈራው የሉጥ ህዝቦችን ተግባር ነው።»[ቲርሚዚ]

:እንደሚታወቀው ሶዶምነት ወይም በሁለት ወንዶች መካከል የሚደረግ የግብረ - ሥጋ ግንኙነት ሶዶምና ገሞራ የተባሉ የነቢዩ ሉጥ(ዓለይሂ ሰላም) ሕዝቦች የጀመሩት #ወንጀል ነው፡፡

📍:አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ) እንዲህ ይላል፦

🔹:وَلُوطًا إِذْ قَالَ لِقَوْمِهِ إِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الْفَاحِشَةَ مَا سَبَقَكُم بِهَا مِنْ أَحَدٍ مِّنَ الْعَالَمِينَ

🔸:ሉጥንም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ) «እናንተ ጠያፍን ስራ ትሠራላችሁን በእርሷ ከዓለማት አንድም አልቀደማችሁም፡፡

🔹:أَئِنَّكُمْ لَتَأْتُونَ الرِّجَالَ وَتَقْطَعُونَ السَّبِيلَ وَتَأْتُونَ فِي نَادِيكُمُ الْمُنكَرَ ۖ فَمَا كَانَ جَوَابَ قَوْمِهِ إِلَّا أَن قَالُوا ائْتِنَا بِعَذَابِ اللَّهِ إِن كُنتَ مِنَ الصَّادِقِينَ

🔸:«እናንተ በእርግጥ ወንዶችን ትመጣላችሁን መንገድንም ትቆርጣላችሁን በሸንጓችሁም የሚነወርን ነገር ትሠራላችሁን» (አላቸው)፡፡ የሕዝቦቹም መልስ «ከእውነተኞቹ እንደ ሆንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡[29:28-29]

👍:ከወንጀሉ አስቀያምነትና ክብደት የተነሳ አላህ(ሱብሃነሁ ወተዐላ) እነዚያን የነቢዩ ሉጥ(ዓለይሂ ሰላም) ሕዝቦች ያጠፋቸው በአራት ዓይነት ታላላቅ ቅጣቶች ነበር። ከዚህም በተጨማሪ የዚህ ዓይነት የከበደና የተደራረበ ቅጣት በሌላ ሕዝብ ላይ ደርሶ #አያውቅም። እነዚህ ቅጣቶችም፦

¹
🔹:የነቢዩ ሉጥ(ዓለይሂ ሰላም) ሕዝቦች ዓይናቸው ታውሮ ነበር፣

²
🔹:ተጠብሰው የተደረደሩ የድንጋይና የሸክላ ጠጠሮች ከወደ ሰማይ በነርሱ ላይ ዘንበው ነበር፣

³
🔹:ነጓድጓዳማ ጩኸት በድንገት ደርሶባቸው ነበር፣

🔹:ከተማቸው ከላይ ወደታች ተገልብጣ ነበር።

╭┈─────── ೄ
🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🥹


✅:የአንተ ሀጢያት የሚያልቅ ነው፡፡ የአላህ #እዝነት ግን ማለቂያ የለውም፡፡ ወንጀልህ የፈለገውን ያህል የከበደና የገዘፈ ቢሆንም አንዳች ደረጃ ላይ ሲደርስ ያበቃል፡፡የሀያሉ አላህ እዝነትና ርህራሄ ግን ሰፊ የሆነና ማለቂያ የሌለው ነው፡፡ አላህም እንዲህ ይላል ፦

╔╦══• • •❀
🌼 ❀• • •══╦╗
... ችሮታዬም ነገሩን ሁሉ ሰፋች ፤...
      / | አል አዕራፍ ፡ 156 | \
╚╩══• • •❀
🌼 ❀• • •══╩╝

🔎:የሀያሉ አላህ እዝነት የፈለገውን ያህል የገዘፈ ቢሆን እንኳ ሀጢአቶችን ይደመስሳል⚡️

-ማለቂያ የለሽ የሆነን ነገር አላቂ ነገር ሊበግረው አይችልምና
!

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤
@Muslimchannel2 💌

Показано 20 последних публикаций.