❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
ታኅሣሥ ፳፬ (24) ቀን
አቡነ ተክለሃይማኖት
እንኳን ለቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።
🕊
† ሰዳዴ ጽልመት አባታችን ቅዱስ ተክለሐይማኖት †
"...ከበዐቱ ሳይወጣ ሌሊትና ቀን ቆመ። አልተቀመጠም ወደ ግራና ወደ ቀኝም አልተንቀሳቀሰም። ውኃም ቅጠልም ቢሆን ከቅዳሜና ከእሑድ በቀር በዚያ ወራት ምንም ምን አልቀመሰም። እህል ግን ከመነኰሰ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ አልቀመሰም። ፀሓይንም ጨረቃንም ከዋክብትን በጋና ክረምትንም ቡቃያና አበባንም ፍሬውንም አላየም። ዓይኖች ሳሉት እንደ ዕውር ጆሮዎች ሳሉት እንደ ደንቆሮ የሚናገር የተከናወነ አንደበት እያለው እንደ ዲዳ ሆነ። ከምስጋና በቀር ምንም ምን አይናገርም።
ሌሊትና ቀንም እግዚአብሔርን አመሰገነ። ዓለምንም እንደ ትቢያና እንደ ጉድፍ ቆጠረው ከክርስቶስ ጋር እንደተሰቀለ ሆነ ልቡናውም ዘወትር ወደ ዓየር የተመሰጠ ነበር።
እንዲህ ባለም ገድል ብዙ ዘመን [፳፪ [22] ዓመታት] ኖረ። ቁመትንም ካበዛ ወዲህ አንዲቱ የእግሩ አገዳ ተሰበረች ደቀ መዛሙርቱ አንሥተው አክብረው በሰበን ጠቅልለው ከመንበሩ እግር በታች ቀበሯት። ከዚህም ባንዲት እግሩ ሰባት ዓመት ቆመ። ከነዚህም አራቱን ዓመት ውሃው አልጠጣም"።
[ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ]
[ የኢቲሳ አንበሳ ፥ የኢትዮጵያ ብርሃን ፥ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐራሴ ወንጌል ፥ የጣኦታት ጠላት ፥ ጣኦታትን የሰባበሩ ፥ የአምላካቸውን ስም ያስከበሩ ፥ ሐዲስ ሐዋርያ በረከታቸው ይደርብን ምልጃ ጸሎታቸው አይለየን፡፡ ]