"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ።
📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼
❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


ስለ መልአከ ምክሩ ቅዱስ ሚካኤል ጠበለ ፃድቅ ቅመሱ መጋቢ ብሉይ ቅዱስ ሚካኤል የዓመት ሰው ይበለን ከቊጥር አያጉድለን በጸሎታችሁ ወለተ ሥላሴ እያላችሁ አትርሱኝ ከርሞ በቸር ያድርሰነ።🤲🌷🌸


ነገ ¹³ፈታሄ ማህጸን ቅዱስ ሩፋኤል ነው ወቶ ከመቅረት ከድገተኛ አደጋ ከዲያብሎስ ፈተና ከመከራ ስጋ ወነፍስ ይጠብቀን አሜን!!!🙏♥


❤ቅዱስ ሩፋኤል🌹

✳ትርጉሙ እንዲህ ነው ፣ በልሳነ ዕብራይስጥ ሩፋ ማለት ጤና ፣ ፈውስ ፣ መድሃኒት ሲሆን ኤል ማለት ደሞ አምላክ ፣ እግዚአብሔር ማለትነው።
♨አምጻኤ ዓለማት እግዚአ መላዕክት እግዚአብሔር በነገደ መላዕክት አለቆች ይኾኑ ሰብዓቱን ሹሟል ። ቅዱስ ሩፋኤልን ከሊቃነ ነገደ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በመቀጠል በማዕርግ ሶስተኛ ኾኖ የተሾመው ሊቀመላዕክት ነው ፣ ዮሃንስ ወንጌላዊ ቀደም ብሎ ተናግረዋል እንዲህ ይላል ርኢኩ ሰብዓተ መላዕክተ እለ ይቀውሙ ቅድመ እግዚአብሔር ራእ 8:21 ቅዱስ ሩፋኤል የሴቶችን ማህጸን ይፈታ ዘንድ ሥልጣን ተሰጥቶታል ። መላኩ ሩፋኤል በ 23 ነገደ መላዕክት መናብርት ተብለው የሚጠሩት የተሾመው ብርሃናዊ መላክ ነው ። የነገድ ስማቸውን እንዲህ ነው ፣ አጋእዝት ፣ ሓይላት ፣ ሥልጣናት ፣ ሊቃናትና መናብርት ፣ መኳንንትና አርባብና ፣ ኪሩቤልና ሱራፌል አዕላፍም ፣ ድርገታትም ተብለው ይታወቃሉ ። አለቆቻቸውም ዓስር ናቸው ። እሊኽም ፣ ቅዱስ ሚካኤል ፣ ቅዱስ ገብርኤል ፣ ቅዱስ ሩፋኤል ፣ ቅዱስ ፋኑኤል ፣ ቅዱስ ራጉኤል ፣ ቅዱስ ኡራኤል ፣ ቅዱስ ሱርያል ፣ ቅዱስ ሰዳክያል ፣ ቅዱስ ሰላትያል ፣ ቅዱስ አናንኤል ናቸው ። እሊኽ ነገደ መላዕክትም ለዘለዓለም በሰማያት ሕያዋን ኹነው ይኖሩ ዘንድ እግዚአብሔር ወሰናቸው ። ነገር ግን እግዚአብሔር ግን በጠራቸው ግዜ ፈቃዱን ለመፈጸም እሊኽ መላዕክት እስከ ጽርሃ አርያም ይወጣሉ ። በላካችውም ግዜ የፍጥረተ ሁሉ ወሰን እስከኾነችው ጨላማይቱ የባርባሮስ ሥፍራ ድረስ ይወርዳሉ ። ተመልሰውም ብቻውን የነበረው ያለና የሚኖር በአገዛዝ ላይም ሁሉ ሥልጣን ያለው እርሱን ከማመስገን በቀር በሽታም ሞትም ቢሆን ሓዘንም ቢሆን ወደሌለባቸው ቦታቸው ይገባሉ ። እግዚአብሔር ከሊቃነ መላዕክት ሩፋኤል ሠራዊት መርጦ በመንበሩ ዙርያ አቆማቸው ፣ ከእሳት ወርቅ የተሰራ ጽናዎችምና የሚያንጸባርቅ የብርሃን አክሊል አንጓቸው ብርሃን የሆነ ዘንግንም ሰጣቸው ። መልኩ መብረቅ የሆነ የክህነት ልብስን አለበሳቸው ። ከማዕጠንታቸውም ምስጋና የተሞላ መዓዛውም ደስ የሚያሰኝ ዕጣን ይወጣል ፣ እግዚአብሔርም በማዕጠንታችሁ የቅዱሳን ሁሉ ጸሎት ወደኔ ይቀርብ ዘንድ ይደረግላችሁ አላቸው ። አዎ ወደ ፈጣሪያቸውን እግዚአብሔርም ሳያቋርጡ ዘወትር ስለሰው ልጆች ይለምናሉ ፣ በሰማያት የሚኖር የአብም ገጽ ዘወትር ያያሉ ፣ ንስሐ ስለሚገባው አንድ ሓጥእም በእግዚአብሔር መላዕክት ታላቅ ደስታ ይደረጋል ፣ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላዕክት ሁሉ ስለዚህ ነገር ፈጥራችኋል ። አዎ ከእግዚአብሔር በስተቀር የመላዕክትን ተፈጥሮ የሚያውቅ ማንም ማንም የለም ። ኩፋሌ 2:7
ቅዱስ ሩፋኤል ቅዱሳን ጻድቃን በገድላቸውም የሚረዳቸው ፣ የምያጽናናቸው ፣ የሚደግፋቸው እርሱ ነው ፣ ፈታሄ ማህጸን ፣ ዐቃቤ ሆህት ፣ ሰዳዴ አጋንንት ፣ ከሣቴ ዕውራን ፣ ፈዋሴ ዱያን ተብሎ በመሆኑ ይታወቃል ።
ሄኖክ 6:3 ዘፍ 3:24

🌹❤️የቅዱስ ሩፋኤል በረከት ፣ የዕልፊ አዕላፍ ነገደ መላዕክት ረድኤት ፣ አማላጅነት ፣ የእግዚአብሄር በጎ ቸርነትና ምህረት ዛሬም ዘወትርም ከኛ ጋር ይሁን 🙏አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏

ወስብሃት ለእግዚአብሄር ።
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
💓💖❤️💙💜💚💖❤️💙

https://t.me/Orthodoxtewahdoc




📕#ተአምር_ዘአቡነ_ዘርዓ_ብሩክ🌹

📘☞•••ወር በገባ በ13 ታስበው የሚውሉ አባታችን ዘርዐ ቡሩክ ያደረገው ታአምር ይህ ነው ስሟ ፋሲካዊት በምትባል ሴትዮ ቤት እግዚአብሔር ዳግመኛ ታላላቅ ተአምራት አደረገ፡፡ ያቺም መልካም ሴት ሁል ጊዜ የዘርዐ ብሩክ መታሰቢያውን ታደረግ ነበር አሱንም ከመውደዷ የተነሳ ተገዛችለት ለቃሉም ታዙችለት፡፡

☞በአንድ ወር ለመታሰቢያው የሚሆን የማኀበሯ ተራ በደረሰ ጊዜ ትደክም ጀመር ብዙ ቀን ሰትጥር ስትግር ሰይጣን ቀንቶባት የመታሰቢያውን የወይን ጠጅ አጠፋባት፡፡

☞ይህ ሁሉ የደረሰብኝ ሰለ ኃጢአቴና ሰለ በደሌ ነው ብላ ብዙ ምሾ እያወጣቸ
ፈጽማ አለቀሰች፡፡
☞እግዚአብሔርም የለቅሶዋን ጽናትና ኅዘኗን አይቶ በሰይጣን ቅናት የጠፋባትን ያን ወይን ጠጅ የቃናን ውሃ ለውጦ የጣመ እንዳደረገው ያን ቦዶ እንስራ ወደ ወይን ለወጠው ፈጽሞም ጣፈጠ፡፡
☞በዚያ በጻድቁ አባቷ ዘርዐ ብሩክ ጸሎት ያ የወይን ጠጅ ተለውጦ እንዳ ጣፈጠ ያቺ ሴት አይታ እግዚአብሔርን አመሰገነች፡፡ እናቱ ድንግል ማርያምንም
አመሰገነች በጸሎቱና በአማላጅነቱ ተአምራትን መንክራትን ያየረገላት ቅዱስና
ብፁዕ የሚሆን አባታችን ዘርዐ ቡሩክ እጅግ ወደደችው፡፡

☞የጣፈጠው ያ የወይን ጠጅም በክቡር የሚካኤል በዓል ቀን ዳግመኛ
አለቀባት የነበሩ ብዙ ማኀበርተኞችም እጅግ አዘኑ የወይን ጠጅ ትበደራቸው
ዘንድ በየሀገሩ ዞረች የምትሰጣቸው የወይን ጠጅ ባጣች ጊዜ ከዚያ
ከሚጣፍጠው የወይን ጠጅ የቀረ(የተረፈ)አንድ ማድጋ ቅራሪ አመጣችላቸው
በቀዱት ጊዜ አተላ ሆነ፡፡

☞ያዚ ሴትም እጅግ አዘነች ማኀበርተኞችም ሁሉ እንደ አርሷ አዘኑ ዳግመኛ ቀዱት ንጹህና ጣፈጭ ሆነው አገኙት እጅግ ተደነቀች ማኀበርተኞችም እንደ እርሷ አደነቁ፡፡ ☞ይህ ሁሉ ተአምር የተደረገ በጻዱቁ አባታችን ዘርዐ ብሩክ ጸሎትና ልመና ነው፡፡

☞መታሰቢያውን ለምናደርግ ስሙን ለምንጠራ እንደ እርሷ ተአምራትን
ያድርግልን ለዘለአለሙ አሜን፡፡
☞(ገድለ ዘርዐ ቡሩክ)
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞12-7-2014




የፈፀምህ የኹሉ ፈጣሪ እግዚአብሔር አብ ሆይ ኹሉን ማድረግ የሚቻልህ ሁሉን ለአንተ የቀረበ በአንተም ዘንድ አለና በእውነተኛይቱ መንገድ መርተህ ህግን *አስተምረኝ። እግዚአብሔር አብ ሆይ በለሊትና ቀኑን ሙሉ* *ምስጋና ይገባሀል።*

እግዚአብሔር ዓብ ሆይ በክረምት እና በበጋ አውራኀ ልክ ምስጋና ይገባል ።
እግዚአብሔር አብ ሆይ በማይታየውም ኹሉ ዘንድ ምስጋና ይገባል አለም ሳይፈጠር አስቀድሞ የነበረና የአለ የሚኖርም ምስጋናህን እነሆ
ሰማይ ይናገራል አቤቱ እግዚአብሔር አብ ሆይ ከሥጋና ነፍስ መከራ እኔ
_ን ጠብቀኝ ብርሀንህንም አብራልኝ ለዘላለሙ አሜን ።

*አባታችን ሆይ* https://t.me/Orthodoxtewahdoc


🌹ወር በገባ በ13 እግዚአብሔር አብ ነው እንኳን አደረሰን🎋

♨#መልክዐ እግዚአብሔር አብ 🌹

📗•••ፀጋን የምታድል የመከራና የችግር ጊዜያትንም የምታሶግድ ፍፁም ዘላለማዊ አምላክ እግዚአብሔር አብ ሆይ ልመናውን የማታቋርጥ ነፍሴ አስቀድሞ ነብያትህ ኄኖክንና ዕዝራን ማስተዋልን እንደመላኋቸው ንጉስን ከወታደሮች ጋራ የሚያጸና ይቅርታህ ይርዳኝ ትልሀለች ።

ወዳጅህ እስራኤልን አፍህን ክፈት እኔም አመላዋለሁ ያልኽው እግዚአብሄር አብ ሆይ አንተ ርኽረኽ እና ፍፁም አምላክ ነህ ምስጋናህን አቀርብ ዘንድ አንደበቴን አዘጋጃለሁ።
በደሴተ ፍጥሞለ ለነበረ ቅዱስ ዮሐንስ ራዕይን የገለፅህ እግዚአብሔር አብሆይ ጉድለት ችልታ በሌለበት አዲስ አንደበት የመፀሐፍት ሚሥጥራትን አንብቢና ተርጉሜ ህግህን ለማስተማር የጀመርሁትን አዲስ ግብር እፈፅም ዘንድ አቤቱ ፀጋህን አድለኝ ።
ከዘመናት አስቀድሞ የነበርኽ የዘመናት ባለቤት ዘመናትንም አሳልፍኽ የምትኖር በባሕርይህ ጉድለት የሌለብህ በፈጡራን ሁሉ አንደበት የምትመሰገን እግዚአብሔር አብ ሆይ ዘመናትን በፀጥታ የምታፈራርቅ አንተ ነኽና ፈጽሞ *ለተመሰገነ ዝክረ ስምህ ሰላምታ ይገባል*
ከእግዚአብሔር ወልድ እና ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስጋርራ ዕሩይ የሆንኽ የብርሃኑ ክበብ ለሚያስደንቅ የራስ ፀጉርህና ምሳሌ የሌለው ምስጋና የሚገባህ *እግዚአብሔር አብ*
ሆይ የሦስትነት የአንድነተመቸሀለ ፀሐይ ለአለም ሁሉ ጌጥ ኾኖ ከምዕራብ። እስከ ምሥራቅ ከምድር እስከ ሰማይ ያበርራል የኹላችን መለያ ክብርህ ሰማያትን የመላ ጌትነትህም ፈጽሞ የተመሰገነ *እግዚአብሔር አብ ሆይ*
ከኹለቱ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር።መንፈስ ቅዱስ ጋራ ብርሀን በማስገኘቱ ፈፅሞ ለተመሰገነ ገፅህ ሰላምታ ይገባል ።የብርሀናት ፈጣሬ የሆነ ጨለማ ለማይስማማቸው ብሩሀት አይኖችህና ቅንድቦችህ ሰላምታ ይገባል።ኃይልና ምስጋናም ለአንተ ይገባልና አይኖቼ በምተ ኃጢት እንዳያንቀላፋ በብርሀን እረዴኤትህ ንቁሐን። አድርጋቸው
የምስጋና ምስዋዕት የምትቀበል እግዚአብሔር አብ ሆይ ሁልጊዜ ፀሎትን ለሚያዳምጡና። የሚያንፀባርቅ እሳትን ለተጎናፀፉ ጉነጮችህ ሰላምታ ይገባል ። አቤቱ ዘወትር እንደ አሽኮኮ የምጨነቅየት የጭንቅ ጨኽቴን ታሰወግድልኝ ዘንድ ኤሎሔ ኤሎሔ እያልሁኝ የምለምንህ ፀሎቴን ተቀበልኝ። በኹሉም ሁሉ ሥፈራ የነበርህና ያለህ የምትኖር ሳን ታው በተባሉ የምትመሰገን በባሕርይኅ ኀል ፈት ሸረት የሌለበረህ እግዚአብሔር አብ ሆይ የሚያስደስት መአዛን። ለተመሉ አፈንጫህዎችና ዳግመኛም የተወለደደ ።.

ቃል በሚስባቸው ከንፈሮችህ ሰላምታ ይገባል።
አለም ሳይፈጠር አስቀድሞ የነበርህ አዲሱ አለም ከተገለጠ ቡኋላም ለዘላለም የምትኖር ጌታየ ነህ በፍፁም ምስጋና የተሞላህ የዘላለማዊ አምላክ እግዚአብሔር አብ ሆይ በተወደደ አንደበትህና መለኮታውያን ለኾኑ ጥርሶችህ ሰላምታ ይገባል ።

በእጅ ምሀል አለምን የያዝህ እግዚአብሔር አብ ሆይ ወዶ ፈቅዶ ለሚናገር አንደበትህና እንደ ነጎድጓድ። ለሚያስተጋባ ድምፀ ቃናህ *ሰላምታ ይገባል ።*በአንተ ዘንድ ህልው የኾነ ኹሉን የማገልጥ መንፈስ ቅዱስ የእየነገዱን ቋንቋ ኹሉ ይግለጥልኝ።

ፅድቅንና ይዎሄን.የትህትናም ግብር ሁሉ የምትወድ ጠላት ሳጥናኤልን የጣለውን ትዕቢትን የምትጠላ ገናንነትህን እጅግ የሚያስደንቅ እግዚአብሔር አብ ሆይ የህውሐት እና የጤና እስትንፋስ በኾነ እስትንፋስህ የፀጥታ ደጃፍ ፤
*የሀይልመግለጫ ለሆነ ጉሮሮህ ሰላምታ ይገባል*።

እግዚአብሔር አብ ሆይ እርዝመቱ በሚያስደንቅ ዙሪያውም ክብ ለሆነ መጠኑ ለማይታወቅ *ጽህምህ ሰላምታ ይገባል*።በዝናበ እረዴኤትህ ጠልና ከፍታው እጅግ በበዛ የይቅርታህ ደመና የሕይወቴን ጽድቅ እንደ ካህኑ አሮን ፂም አርዝምልኝ።

ከመገለጥ ይልቅ የተሰወረን የበልጥ የምትሠውረ እግዚአብሔር አብ ሆይ ዕበየ።ግርማህ ለከበበው አንገትህና ዳግመኛም በአንድነት ለጸኑ *ትከሻዎችህ ሰላምታ ይገባል*።የባህርየ ልጅህ ክርስቶስ እንክርዳዱን ከስንዴኤው ለይቶ በእሳት ሲያቃጥል ብጽላሎተ ረድኤቱ ይሠውረኝ።

ጥልቅ ባህር ጥበባት እግዚአብሔር አብ ሆይ ኪሩብ ሊሸከመው ለማይችለው ጀርባህና ዳግመኛም አርባብ የተሰኙ የዋሃን ነገደ መላዕት ላይ *ከብሮ ገንኖ ለሚኖረ ቅዱስ ደረትህ ሰለምታ ይገባል* ።ኪነ ጥበቡ እጅግ የሚያስደንቅ ኃይልህ እኔ ጠቢብ ልጅህን ከስንፍና ይልቅ ጥበብን ያድለኝ።

የክብርህን ነገር ለመናገር የሚያስደንቅ በማስተዋል ለመንግሥትም ፍፃሜ የሌለህ እግዚአብሔር አብ ሆይ የፀጋ ብርሀናትን ለሚያፈልቅ ሕፅንህና ዳግመኛም ለመመገብ *ለተዘረጉ የምህረት እጆችህ ሰላምታ ይገባል*።

ድዊይ የምትፈውስ እግዚአብሔር አብ ሆይ ለአሸናፊ ድል ለሚያንጎናፅፍ ክንዶችህ እና ከአካልህ ጋር ለተስማሙ ክርኖችህ ሰላምታ ይገባል።የሀጥያቴን ደዌ አውሬ ዲያብለስን በወጋህበት በጦር ወግተህ በአዳኝ ሀይል አድነኝ .።

ከእግዚአብሔር አብ ወልድና ከእግዚአብሔር መንፍ ቅዱስ ጋራ በእሳታዊጨ ዙፋንህ ከብረህ ገንነህ የምትኖ አለም ሳይፈጠ አስቀድም በሥልጣነ የባህሪህ የሆቸ እግዚአብሔር አብ ሆይ ለሚያስፈራ አምላካዊ ክንድህ ይህን ። ይህነ ስፊ አለም ለያዘ መሐል *ሰላምታ ይገባል*

የፍቅርና የቸርነት መገኛ ሰማያት በምድር በየብስና በባህር ያሉትን ፍጥረታትን ኹሉ የምትመግብ። እግዚአብሔር አብ ሆይ ይህን አለም ለፈጠሩ ጣቶችህና ድንቅ ሥራዎችህን *ለሚያፈጥኑ ጠረፍሮችህ ሰላምታ ይገባል*
ከንፎቻቸው ስድስት የኾኑ ኪሩቤልና ሱራፌል አንተን የዘወትር ከባህርይ። ልጅህ እግዚአብሔር ወልድና ከባህርይ ሕይወትህ ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋራ የሚያመሰግኑህ እግዚአብሔር አብ ሆይ ልብሱ መብረቀ ስብሐት ለኾነ ጎንህና የመኖሪያ ሥፍራ *ለማይወስነው ሆድህ ሰላምታ ይገባል*።
ይቅርታህን ርኀራኄህ ብዙ ነውና በፍጡራን አንደበት ኹሉ የምትመሰገን እግዚአብሔር አብ ሆይ ቅንና የዋህ ልብህና የዘመናትን ፍፃሜ አስቀድሞ ለሚያውቅ ሕሊናህ ሰላምታ ይገባል ክንድህም ለይቅርታ ዘወትር የተዘረጋ ነው ።

።በለይም በታችም ለዘመለአለም ነግሠህ የነበርህና ያለህ የምትኖር ንጉሥ ነገሥት እግዚአብሔር አብ ሀሰይ መልኩ ለሚያስደንቅ ኀንብርትህና ዳግመኛም *ለትጥቁ ደግ ለሚያምር ሀቊህ ሰላምታ ይገባል* አቤቱ ለይልህ አሸናፊ ነው እናአዐፄም አውሬ ዳቢሎስን አሸንፍ ዘንድ የትዕግስትን ትጠረቅ አልብሰኝ

የእግዚአብሔር ወልድ የባህርየ አባት እግዚአብሔር አብ ሆይ ክቡድና መለኮታዊ ለኾኑ ጭኖችህ ዳግመኛም *ለጉልበቶችህ ሰላምታ ይገባል*
ጠላት ዳቢሎስ ከሰጠህው ስልጣነ ከተባረረ ቡሀላ ትጉሀን
ሰማይ ከሆነ ነገደ መላእክት በአንድነት አመሰገኑህ

አለምሠ ሳይፈጠር አስቀድሞ የነበርህ ምድርንም የዘረጋህ ሥራህንም በድንቅ በማስተዋል ከመሥራትህ አሰቀድሞ የምትኖር እግዚአብሔር አብ ሆይ ምድር ለሚያንቀጠቅጡ እግሮችህና ከእግርህ *መረገጨም ጋራ ለተረከዝህ ሰላምት ይገባል*።
የአባታችን አዳም የህይወቱ መሰረት እግዚአብሔር አብ ሆይ *ጋራ ባይለዩ ለሚኖር አስሩ ጥፍሮችህና ጣቶችህም ሰላምታ ይገባል*ልቤ ለመዳን ይሻልና ለዘለአለሚዊነትህ ከከንቱ ሞት ኀጢአት ያድነኝ ዘንድ እማፀንህ አለውለመንግሥትህ ፍፃሜ የሌለው ቃልህና አካልህ በመልክዕና በቁመት እጅግ የከበረ የምትደነቅ የብርሃናት መገኛ እግዚአብሔር አብ ሆይ ከአቅም በላይ በኾነና ለመይወሰን አካለ አቅም ህና ዳግመኛም ግርማ *ራእዩ ለሚያስደንቅ መልክዕህ ሰላምታ ይገባል* አንተ እውነተኛ አምላክ ሥትሆን ኹሉን በፈቃድህ




#አቡነ ዮሐንስ ዘደብረ ቢዘን ማለት⁉

♨☞ወር በገባ በ13 የአቡነ ዮሐንስ (ዘደብረ ቢዘን)ወርሐዊ መታሰቢያ በዓል ነው እኚህ ጻድቅ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ በጥቅምት 14 ቀን ተወለዱ ሀገራቸው ትግራይ አድዋ አውራጃ አህሳአ ልዩ ቀበሌ እንዳ መንደር ይባላል።

☞አቡነ ዮሐንስ የአቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ቢዘን ደቀመዝሙር ሲሆኑ፣አቡነ ፊልጶስ
ሲያርፉ በሳቸው ተተክው ደብረ ቢዘን ገዳምን በአበምኔትነት አስተዳድረዋል።
☞እንደ ነቢየ እግዚአብሔር ደመናን ዝናም እንዳይሰጥ የለጎሙ የከለከሉ
ስለሆኑ "ለጓሜ ደመና" በመባል ይታወቃሉ።
ነቢዩ ኤልሳዕ በመንፈስ ቅዱስ ሁሉን እንደሚያውቅ ሁሉ አቡነ ዮሐንስም
ሰው በልቡ የሚያስበውን ያውቁ ነበር።
☞አቡነ ዮሐንስ በተወለዱበት ሀገር ትግራይ በአህሳአ በስማቸው የተገደመ
''እንዳ አቡነ ዮሐንስ ገዳም" ፣ዛሬ ደብር ነው።
አቡነ ዮሐንስ በመነኮሱበትና ባገለገሉበት በደብረ ቢዘን ገዳም በኅዳር 13
ቀን አርፈው ተቀብረዋል።
☞""አቡነ ዮሐንስ ዘአስገዶም"" በመባልም ይጠራሉ።
☞በስማቸው የተሰሩ 5 አብያ ተክርስቲያናት አሉ
አምላካችን እግዚአብሔር ስለ ጻድቁ ስለ አቡነ
ዮሐንስ ዘደብረ ቢዘን
ብሎ ከዘመኑ መቅሰፍትና ጥፋት ይሠውረን፡፡
☞(ገድለ አበው ቅዱሳን ዘደብረ ቢዘን)

https://t.me/Orthodoxtewahdoc




+ቅዱሱ ግን በትእግስት ሁሉን ቻለ:: በዚህ መካከል ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ነጻ ወጣ:: ያን ጊዜም ሕዝቡን ሰብስቦ ጸሎትን አደረገ:: "ጌታ ሆይ! ይህንን መኮንን እባክህ ማርልኝ? ያደረገው ነገር ሁሉ ባለ ማወቅ ነውና::"
+ይህንን ጸሎት በወሬ ነጋሪ የሰማው ያ መኮንን በጣም ተገርሞ በቅዱሱ ፊት ሔዶ በግንባሩ ተደፋ:: "ስጠላህ የወደድከኝ አባት ሆይ! ማረኝ?" አለው:: ቅዱስ ጢሞቴዎስም አስተምሮ አጠመቀው:: 2ቱም አብረውሲጋደሉ ኑረው ዐርፈዋል::

=>አምላከ ቅዱሳን በረድኤተ መላእክት ጠብቆ በወዳጆቹ ምልጃ ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ኅዳር 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አእላፍ (99ኙ) ነገደ መላእክት
2.ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ
3."13ቱ" ግኁሳን አበው (ሽፍቶች የነበሩ)
4.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘእንጽና
5.አባ ዘካርያስ ሊቀ ዻዻሳት

=>ወርኀዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
3.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
4.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

=>+"+ ስለ መላእክትም:-
"መላእክቱን መናፍስት: አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ" ይላል . . .
ነገር ግን ከመላእክት:-
"ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ" ከቶ ለማን ተብሏል?
ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ: የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን? +"+ (ዕብ. 1:7-14)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††


የዲ/ዮርዳኖስ አበበ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት:
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን! †††

††† እንኩዋን "ለ99ኙ ነገደ መላእክት": "ቅዱስ አስከናፍር" እና "ቅዱስ ጢሞቴዎስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

††† አእላፍ መላእክት †††

=>እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100): በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጉዋቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በ3 ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጉዋል::

+መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር: ራማና ኢዮር" ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-

1.አጋእዝት (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አህን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው)
2.ኪሩቤል (አለቃቸው ኪሩብ)
3.ሱራፌል (አለቃቸው ሱራፊ)
4.ኃይላት (አለቃቸው ሚካኤል)
5.አርባብ (አለቃቸው ገብርኤል)

6.መናብርት (አለቃቸው ሩፋኤል)
7.ስልጣናት (አለቃቸው ሱርያል)
8.መኩዋንንት (አለቃቸው ሰዳካኤል)
9.ሊቃናት (አለቃቸው ሰላታኤል)
10.መላእክት (አለቃቸው አናንኤል) ናቸው::

+ከእነዚህም *አጋእዝት: *ኪሩቤል *ሱራፌልና *ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው:: *አርባብ: *መናብርትና *ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው:: *መኩዋንንት: *ሊቃናትና *መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው::

+መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::

+ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::

+ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት (አራቱ ወቅቶች) እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::

*ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ (ዘካ. 1:12)
*ምሥጢርን ይገልጣሉ (ዳን. 9:21)
*ይረዳሉ (ኢያ. 5:13)
*እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ (መዝ. 90:11)
*ያድናሉ (መዝ. 33:7)
*ስግደት ይገባቸዋል (መሳ. 13:20, ኢያ. 5:13, ራዕ. 22:8)
*በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ (ማቴ. 25:31)
*በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::

+"+ አእላፍ +"+

=>ይህ ዕለት በሊቃውንት አንደበት "አእላፍ" እየተባለ ይጠራል:: በሃይማኖት: በተልእኮትና በምስጋና የሚኖሩ 99ኙ ነገደ መላእክት በአንድ ላይ የሚከበሩበት ቀን ነው:: ምንም እንኩዋን የጐንደሩን ፊት ሚካኤልን ጨምሮ በአንዳንድ አድባራት ታቦቱ ቢኖርም ሲያነግሡ ተመልክቼ አላውቅም::

+ሊቃውንቱ በማሕሌት: ካህናቱም በቅዳሴ እንደሚያከብሯቸው ግን ይታወቃል:: ሕዳር 13 ቀን ዓመታዊ በዓላቸው ነው ማለት በየወሩ በ13 ወርሃዊ በዓላቸው መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልናስባቸው ይገባል::

+ቅዱስ መጽሐፍ ቅዱሳን መላእክትን በስምና በማዕረግ እንደሚነግረን ሁሉ በማሕበር (በትዕይንት) አገልግሎታቸውም ይነግረናል:: ለምሳሌ:-

*ያዕቆብ= በረዥም መሰላል ሲወጡና ሲወርዱ ተመልክቷል:: (ዘፍ. 28:12)
*ኤልሳዕ ለግያዝ አሳይቶታል:: (2ነገ. 6:17)
*ዳንኤል ተመልክቷል:: (ዳን. 7:10)
*በልደት ጊዜ በዝማሬ መገለጣቸውን ቅዱስ ሉቃስ ጽፏል:: (ሉቃ. 2:13)
*ዮሐንስ በራዕዩ አይቷቸዋል:: (ራዕይ. 5:11)

+ከዚህም በላይ በብዙ የመጻሕፍት ክፍል ተጠቅሰዋል:: ቅዱሳን መላእክተ ብርሃን: መንፈሳውያን: ሰባሕያን: መዘምራን: መተንብላን (አማላጆች) ተብለውም ይጠራሉና ያስቡን ዘንድ ልናስባቸው ይገባል::

+"+ ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ +"+

=>የዚህ ቅዱስ ሰው ሕይወት ታሪክ ደስ የሚያሰኝና የሚያስተምር ነው:: ቅዱሱ የገዳም ሰው አይደለም:: በሮም ከተማ እጅግ ሃብታም: ባለ ትዳር: የአንድ ልጅ አባትና የከተማዋ መስፍን ነው:: ይህ ሰው በጣም ደግና አብርሃማዊ ነው::

+ከጧት እስከ ማታ ነዳያንን ሲቀበልና ሲጋብዝ ነበር የሚውለው:: ነገር ግን አንድና ብቸኛ ልጁ መጻጉዕ (ድውይ) ሆነበት:: ለ35 ዓመታትም ከአልጋ ላይ ተጣብቆ ይኖር ነበር:: ቅዱስ አስከናፍር ግን ፈጣሪውን ያማርር: ደግነቱን ይቀንስ ዘንድ አልሞከረም:: አሁንም ነዳያኑን ማጥገቡን: እንግዳ መቀበሉን ቀጠለ እንጂ::

+በዚያ ወራት ደግሞ በሮም ግዛት ቁዋንጃ የሚቆርጡ: ሰው እየገደሉ የሚዘርፉ 13 ሽፍቶች ነበሩ:: ስለ ቅዱስ አስከናፍር ደግነት ሰምተው ገድለው ይዘርፉት ዘንድ ተማከሩ:: የሠራዊት አለቃ በመሆኑ በማታለል ሔዱ::

+መነኮሳትን ይወዳልና 13ቱም ልብሰ መነኮሳትን ለብሰው: ሰይፎቻቸውን ደብቀው: ከበሩ ደርሰው: "የእግዚአብሔር እንግዶች ነን: አሳድረን" አሉት:: ቅዱስ አስከናፍር ድምጻቸውን ሲሰማ ደነገጠ::

+ብቅ ብሎ አያቸውና "ጌታየ! ምንም ኃጢአተኛ ብሆን አንድ ቀን ወደ ባሪያህ እንደምትመጣ አምን ነበር" ሲል በደስታ ተናገረ:: እንዲህ ያለው ሽፍቶቹ 13 በመሆናቸው ጌታ 12ቱን ሐዋርያት አስከትሎ የመጣ መስሎት ነው::

+ወዲያውም ወደ ቤቱ አስገብቶ እግራቸውን አጠባቸው:: የእግራቸውን እጣቢ ወስዶም በልጁ ላይ አፈሰሰበት:: ድንገትም ለ35 ዓመታት አልጋ ላይ ተጣብቆ የኖረው ልጅ አፈፍ ብሎ ከአልጋው ላይ ተነሳ::

በዚህ ጊዜ ቅዱስ አስከናፍር ለ13ቱ ሽፍቶች በግንባሩ ሰገደ:: ሽፍቶቹ ግን ነገሩ ግራ ቢገባቸው ደነገጡ::

+ጌታ 12ቱን ሐዋርያት አስከትሎ መምጣቱን የሰሙ የሃገሩ ሰዎችም እየመጡ ይሰግዱላቸው ገቡ:: በዚህ ጊዜ ሽፍቶቹ ልብሳቸውን አውልቀው እውነቱን ተናገሩ:: "እኛ ሽፍቶች ነን:: የመጣነውም ልንገልህ ነው:: አምላክ ግን ባንተ ደግነት ይህንን ሁሉ ሠራ:: አሁንም እባክህ ትገድለን ዘንድ ሰይፋችንን ውሰድ" አሉት::

+እርሱ ግን "ንስሃ ግቡ እንጂ መሞት የለባችሁም" ብሎ: ስንቅ ሰጥቶ አሰናበታቸው:: 13ቱ ሽፍቶችም ጥቂት ምሥሮችን ይዘው ወደ ተራራ ወጡ:: ምስሩን በመሬት ላይ በትነው ማታ ብቻ እየቀመሱ በጾምና በጸሎት ተጋደሉ:: በዚህች ቀንም 13ቱም በሰማዕትነት የክብር አክሊልን ተቀዳጁ:: ቅዱስ አስከናፍርም በተቀደሰ ሕይወቱ ተግቶ ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል::

+"+ ቅዱስ ጢሞቴዎስ +"+

=>ይህ ቅዱስ አባት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በዘመነ ሰማዕታት የነበረ የእንጽና (ግብጽ) ክርስቲያን ነው:: በጐ ሕይወቱን የወደዱ አበው በወቅቱ የከተማዋ ዻዻስ: የሕዝቡም እረኛ እንዲሆን መርጠው ሾሙት::

+ጊዜው የመከራ በመሆኑ ከትንሽ ጊዜ በሁዋላ የከተማው መኮንን ክርስቲያኖችን ይገድል ገባ:: ቅዱስ ጢሞቴዎስንም "ክርስትናህን ካልካድክ" በሚል አሠረው:: ጧት ጧት እያወጣም ደሙ እስኪፈስ ድረስ ይገርፈው ነበር:: ደቀ መዛሙርቱንም አንድ አንድ እያለ ፈጀበት::










ትርጉም:- ከፍ ከፍ ያለነው መቀመጫውም
 ከፍ ከፍ ያለ ነው ሚካኤል መቀመጫው።

🌷እንኳን አደረሳችሁ🤲🌸


ትርጉም:- የሰላም መልአክ ኃይልን የሚያደርግ መልአከ ሚካኤል መንበሩ ልዑል ነው። ለእኛ ይለምንልን። ለኢትዮጲያም ይለምንላት። በመከራ ጊዜም ረዳት ይሁናት።


✝እንኳን አደረሰነ!

☞ደመና የጋረደ፥ መና ያወረደ፤ ውሃን ያፈለቀ፥ ባሕርን ያደረቀ፤ ድንጋይ ያዘነመ፥ ለአበው የቆመ . . . ቅዱስ ሚካኤል በረድኤት አይለየነ!

Показано 20 последних публикаций.